
ከውይይት የተወሰደ። ፍጥረት ከእርሱ ወጥተዋል በእርሱ ሕያው ሆኖ ይንቀሳቀሳል ይኖርማል። ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና። በእርሱ ስልጣን ስር ሁሉ ታድሶ ፤ተጠቅልሎ በእርሱ ያበቃል። ሰባተኛው መልእክት ሲነገርና ሲነፋም በሱ ህይወት consummate ሆኖ በዚህ መልኩ የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል የዮሐንስ ራእይ 10/7 ይህን ቃል አስተውሉ። (Rom 11:36 [AMP])
For from Him and through Him and to Him are all things. [For #all things #originate with #Him and #come #from Him; #all things #live #through Him, and #all things center in and tend to consummate and to #end #in #Him.] To Him be glory forever! Amen (so be it). ወንድም ቢኒ።
ከውይይት የተወሰደ። ወደ እሳቱ ፍቺ እንመለስና አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነው። የእ/ር እሳት የለውጥ ሃይል ነው። ሁሉም እሳቶች አንድ አይነት አይደሉም። ጌታ ለሙሴ በሚነደው ቁጥቃጦ ሲገለጥ ቁጥቃጦው አላሰቃየውም አላጠፋውም አሁን በዚህ ዘመን ሽሮና ዶሮ ወጥ ተከሽኖ ከሚንከተከትበት እሳት ጋርም አንድ አይነት አልነበረም። የእ/ር እሳት የተለየ ነው እንደ እ/ር የፈቃዱ ምክር አላማው ስራውም ይለያያል።
በአረጀው ሰማይ መረዳት እንደ ተነገረን አይደለም እርሱ ማንንም በዘልአለም እሳት አያሠቃይም። ይህ ሁሉ ማለት ግን ስጋዊ አስተሳሰብህን/ሽን ና ሃይማኖታዊ ከፋፋይ ሃሳቦችን ደግሞም የ/ርን ቃል በልጆቹ እንዳይሰራ ከንቱ የሚያስቀሩትን ወግና ባህል ከፍ ያለውን የሰው እውቀትን ሁሉ ወደጎን ካላሽቀንጠርክ/ሽ እሳቱን በተለየ ባህርዩ ትለማመደዋለህ/ሽ። ያም በዘላለም ስቃይ ቅጣት መልክ ማለት ሳይሆን ፍርዱ ከሆነ የሚያርም ፍርድ ነው እሳቱም ከሆነ የሚያነፃ የሚያነጥር ነው። የእ/ር እሳት በተፈጥሮህ ውስጥ ከእርሱ ያልሆነውን ተፈጥሮ ሁሉ ይበላዋል ማለት ነው። ጌታ እየሱስ ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማል ብሎናልና።
‘ ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና። “ጨው መልካም ነው፤ ነገር ግን ጨው ጨውነቱን ቢያጣ እንዴት መልሳችሁ ጣዕም እንዲኖረው ታደርጉታላችሁ? ጨው በውስጣችሁ ይኑራችሁ፤ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።”’ ማርቆስ 9:49-50
ጌታ ሁለት ትምህርት ቤቶች ለልጆቹ አሉት፡ የመጀመርያው በመንፈሱ ለሚመሩና ለፍቅሩ በጎህሊና ምላሽን ለሚሰጡና ለሚታዛዙ ከልጅነት የሚጠበቀውን ባህሪ ለማሳየት ለሚተጉ ልጆቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የልጅነት ክብር ፍሬዎችን ይለማመዳሉ። ፍቅሩን፡ ምህረቱን፡ ቸርነቱን፡ ፀጋውን፡ ሰላሙን፡ በጎነቱን፡ ጥበቡን፡ ምክሩን፡ ትህትናውን፡ከውቂያኖስ ይልቅ ማስተዋሉን፡ሃይሉን፡ምሪቱን፡ወዘተ… ሁለተኛው ትምህርት ቤት ደግሞ ፍቅሩን እባቡ አፈራቸውን[ስጋቸውን]እየላሰ እንዲነቃ ለሚወዱ በእባቡ ባህሪም ሆነው ፍቅሩን ለሚያሰቃዩ ልጆቹ በመገለጥ ካልተማሩ መንፈስ ቅዱስ ወደ ተግባር ትቤት ያስገባቸዋል። ያስጨነከኝ ለመልካም ሆነልኝ እስኪሉ ድረስ እሳቱ መጠኑን ጨምሮ ይታረማሉ ዘንድ ይለማመዱታል። አንድ ተክእሎ ያለው ወርቅ አንጣሪ እሳት ከወርቅ ላይ አፈሩንና ዚንኩን ማለትም መራራውን ንጥረ ነገር ከወርቁ ፈጽሞ እንደሚያራግፍ እንደሚለየው የእ/ር ባህርይ የሚመስለው ወርቁ እስኪቀር ድረስ በእሳቱ ያሳልፋቸዋል። አንድ ተክእሎ ያለው ወርቅ አንጣሪ አንዴ የሚፈለገው ነገር አለ። ወርቁ በእሳት ሲከተው በኧላማ ነው እንጂ ወርቅ የማሰቃየት አባዜ የለበትም። ባለተክእሎ ወርቅ አንጣሪ ለዘልአለምም በእሳት ወርቁን የሚተውበት ምክንያት የለውም በቅድምያ ወርቁ የእሳት ልጅ ወይም ውጤት ስለሆነ የሚፀዳውም በእሳት ብቻ እንደሆነ ያውቃልና።
እሳቱውጥ ሲከተው ባለወርቁ ወርቁለሚፈልገወ ክብር መድረሱን የሚያቀው በእሳቱ ወደሚቀልጠው ወርቅ ፊት ለፊት አጎንብሶ ያያል ወርቁ ላይ የነበረው አፈርና ዚንክ በእሳቱ ገለል ብሎ ፊቱን መልኩን አንፀባርቆ ካሳየው በቃ አሁን መልኬን በሱውስጥ ካታየበት ዘንዳ የክብር እቃ ሆነዋል ብሎ ከእሳቱለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ያወጣዋል፡አባትም እንዲሁነው የሚፈልገውን መልኩን በእኛ ካየ ቡሃላ እሳቱ አላማውን ጨርሰዋል ብሎ ከዛ ያወጣናል። መጽሓፍ የማይጣፋ እሳት ሲል የማይጠፋው የፈለገ ብትንከባለል መሎከትን በአንተ ሳይሰራ አይጠፋም ለማለት እደሆነ የታወቀ ይሁን።
የእኛ ሰብዓዊ ሕይወት ውስጥ ገኖ ያለው የሐሰት ስሜት ከእግዚአብሔር ተለይቶ የሚኖር ሰው ነህ የሚልህን/ሽን የእረኛው ሳይሆን የሌላውን ድምጽ ነውና ይህን ከለየነውና ከካድነው ከከለከልነው በክርስቶስ ውስጥ ያለን እውነተኛ ሕይወት እውስጣችን እናገኘዋለን። ይህ ከውስጣችን ያለው የእ/ር ህይወት መንገዱ ጠባብ ቢሆንም የሚያገኝዋትም ጥቂቶች ቢሆኑም የእ/ር ምህረትና ፀጋ ድጋፍ ከዚህ የህይወት ወሃ በደስታና በማስተዋል ልንቀዳና ልንጠጣ ለፍጥረትም ልናካፍል እንችላለን። አንዱን ቅዱስ የእ/ር መንፈስ ጠጥተማልና በዚህ መንፈስ ከመመራት ውጪ ደግሞ ሌላ ልጅነት የለምና። ‘እግዚአብሔር ግን ይህን በመንፈሱ አማካይነት ለእኛ ገልጦልናል። መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራል። በውስጡ ካለው ከራሱ መንፈስ በስተቀር ከሰው መካከል የአንድን ሰው ሐሳብ የሚያውቅ ማን አለ? እንደዚሁም ከእግዚአብሔር መንፈስ በስተቀር፣ የእግዚአብሔርን ሐሳብ የሚያውቅ ማንም የለም። ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ፣ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንምና፤ ይህም እግዚአብሔር በነጻ የሰጠንን እናውቅ ዘንድ ነው። ‘1 ቆሮንቶስ 2:10-12 የእኛን ሰብዓዊ ሕይወት የሐሰት ስሜት ከከለከልን ዘንዳ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ነን ከእግዚአብሔር የተለየን አይደለንም። እኛ የእውነተኛው ግንድ ቅርንጫፍ ነን። ይህን ካወቅን ማንነታችን አወቅን ማለት ነው። ከኛ ተሙዋጦ መጥፋት ያለበት የስጋዊ አስተሳሰባችን ሁሉ ነው። ለመንፈሳዊው ሰው ሁሉ ነገር መንፈሳዊ ነውና። የሁሉ ፍቺ ደጎሞ ሁሉ ነው። ስጋዊ አእምሮ ማለት ሞት ነውና። እኛ በመንፈስ ምስክርነት ላይ እንቆማለን የጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንፈሳዊ አእምሮ መንፈስ ቅዱስን ያደምጥ እንደነበረ እኛም እጣ ክፍላችን እሱ ነው። ውንድም ቢኒ።