But one thing is needful sat at Lord feet, and hear his word.
የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ነው ከጌታ እግር አጠገብ ተቀምጦ ቃሉን መስማት
የሉቃስ ወንጌል 10Luke 1038 ሲሄዱም እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው።38 Now it came to pass, as they went, that he entered into a certain village: and a certain woman named Martha received him into her house.
39 ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች።39 And she had a sister called Mary, which also sat at Jesus’ feet, and heard his word.40 ማርታ ግን አገልግሎት ስለ በዛባት ባከነች፤ ቀርባም። ጌታ ሆይ፥ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አይገድህምን? እንኪያስ እንድታግዘኝ ንገራት አለችው።
40 But Martha was cumbered about much serving, and came to him, and said, Lord, dost thou not care that my sister hath left me to serve alone? bid her therefore that she help me.41 ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥
41 And Jesus answered and said unto her, Martha, Martha, thou art careful and troubled about many things:42የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።42 But one thing is needful: and Mary hath chosen that good part, which shall not be taken away from her.
ከጌታ ቃል እንደ ምናስተውለው የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ነው ሲል ከጌታ እግር አጠገብ ተቀምጦ ቃሉን መስማትን አጉልቶ ያስረዳናል።
ከጌታ እግር አጠገብ ተቀምጦ የሚለው ሃሳብ እራስን ረጋ አድርጎ በትህትና ዝቅ ማለትን የሚያጠቃልልና ለመንፈሳዊ ህይወት እድገት ቃሉን ለመመገብ አስፈላጊና አይነተኛ ነገር መሆኑን እናስተውላለን ። የበላ ያድጋልና። ደግሞም “ልጆችሽ ሁሉ ከእ/ር ዘንድ የተማሩ ይሆናሉ ሰላማቸውም የበዛ ይሆናል ” እንደተባለ ከውጤታማው አስተማሪ ከእ/ር መማር ማለት የሚበዛ ሰላም ውስጥ መኖር ማለት ነው። ሰው እንካንስ ከእዚያብሄር እግር ስር ተቀምጦ ተምሮና ከጥሩ የሰው አስተማሪ እግርስር ተቀምጦ ቁም ነገር ይሆናል ከመጽሐፍ ለዚህ ምሳሌ የሚሆነን ሐዋሪያው ጳውሎስ ነው።
በኛ ዘመን ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ የትምህርት ተቅዋም እንደሆነ ሁሉ በታሪክ መዛግብት ስታስተውሉ በዚያ ዘመንም ገማሊያ ከተባለ በአይሁድ የተከበረ የህግ ትምህርት ቤት አንዱ ወስጥ ተምረዋል:: በመጽሐፍ ቅዱስም ስለዚህ ት/ቤት መስራች ሰው ወጤማታማ የህግ መምህር ዕንደ ነበረ ፍንጭን ይሰጠናል::
“በሐዋ5:32 ነገር ግን በህዝቡ ሁሉ ዘንድ የከበረ የህግ መምህር ገማልያል የሚሉት “ ሲለው እራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ ከዚህ ሰው እግር ስር የአባቶችን ህግ ማለትም የሙሴ ህግን እንደ ተማረ ይናገራል:: “ሐዋ22:3 በገማልያል እግር አጠገብ ያደግኩ: የአባቶችንም ህግ ጠንቅቄ የተመርሁ::” ነኝ ይላል::
የሚማር ልብ ይዘን ከጌታ እግር አጠገብ መቀመጥ ፈቃዱን እንድናውቅ ብቻ ሳይሆን የሚጠቅመን ይህን በማድረጋችን ብቻ ጠላትም እድል ፈንታ እዳይኖረው ያደርጋል።
“የያዕቆብ መልእክት 4፡7 እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤
Jas 4፡7 Submit yourselves therefore to God. Resist the devil, and he will flee from you.” ቀመሩ ፎርሙላው ቀላል ነው ዲያብሎስን እንዴት ነው የምንቃወመው? አዎን እራሳችንን ለእ/ር ስናስገዛ አውቶማቲካሊ ጠላትን ተቃውምነው በአንድ መንገድ ቢመጣም በሰባት መንገድ ከእኛ ይሸሻል።
እንዳስተዋልነው በዚህ ቃል ላይ ቅደም ሁኔታው ግልጽ ነው። “እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ Submit yourselves therefore to God”. የግሪኩ ቃል ተገዙ፤ Submit የሚለው “hupotasso’ሁፖታሶ” ሲሆን ትርጉሙም “to set in array under” ይህውላቹሁ እንግዲህ ከጌታ እግር አጠገብ ወደ መቀመጥ መልሶ ሲያመጣን እንግዲህ ለእግዚአብሔር መገዛት ማለት ያነው። አሁን ያለው ሂደቱ እና አላማው ይሄ አይደለምን? እየአንዳዱ የፍቃዳችን ክፍል ለፈቃዱ እንዲበረከክ? ከዛም በነገር ሁሉ ዲያቢሎስን ተቃቅመን ከኛ ይፈረጥጣል።
መቼም እምናወራ ያለነው መንፈሳዊ ነገር እንደሆነ ለሁሉ ግልጽ ነው። ከጌታ እጅውስጥ መሆናችን ለሌሎች ሃይላት የማይነኩያደርገናል።
“ የዮሐንስ ወንጌል 10፡29 የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።
John 10፡29 My Father, which gave them me, is greater than all; and no man is able to pluck them out of my Father’s hand.”
ተገዙ፤ Submit የሚለው “hupotasso’ሁፖታሶ” ሲሆን ትርጉሙም “to set in array under” ዝም ብሎ አይመጣም የጌታ የማያቃርጥ ክትትል መከባከብ ተግሳጽ ጭምር ከሌሎች መንፈሳዊ አሰራሩ ታክሎበት የሚመጣ ነው።
“ወደ ዕብራውያን 12፡9 ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
Heb 12፡9 Furthermore we have had fathers of our flesh which corrected us, and we gave them reverence: shall we not much rather be in subjection unto the Father of spirits, and live?”
ለአማኞች ሁሉ የማያቃርጥ ተግዳሮት ቢኖርብን ተገዙ፤ Submit የሚለው “hupotasso’ሁፖታሶ” ሲሆን ትርጉሙም “to set in array under” ዝም ብሎ አይመጣም የጌታ የማያቃርጥ ክትትል መከባከብ ተግሳጽ ጭምር ከሌሎች መንፈሳዊ አሰራሩ ታክሎበት የሚመጣ ነው።
እ/ር ለምን ተቃራኒ ሃይላትን ፈጠረ? ከሚለው ትምህርታችን ብንጠቅስ ጡሩ ነው።
“የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው? ከሚገልጥልን በቀር ማስተዋል አይቻልም መንፈሳዊው ነገር ከሰው ማስተዋል በላይ ግዙፉ ነውና።
ቢሞከርም ከውቂያኖስ ይልቅ ጠሊቅ ከሆነው ምክሩ በማንኪያ ጨልፈን እደመረዳት ያህል ነው። ስለ ተቃራኒ ሃይላት ስናስብ መገንዘብ ያለብን ከሚቋቋመን ተቃራኒ ነገር የምንማረው ነገር አለ። ለዚያም ነው እ/ር ተቃራኒ ሃይላትን የፈጠረው። በትንቢተ ኢሳይያስ 45፡7 ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ እነነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።
አዎን ሁሉን መፍጠሩን እ/ር ሃላፊነቱን ወስደዋል:: እራስ በራሳቸው የሚቃረኑትም ጭምር ማለት ነው። ለማሰብ ያህል መራራና ጣፋጭ፤ ሃዘንና ደስታ፤ ድሃና ባለጠጋ፤ ጨለማና ብርሃን፤ መልካምና ክፉ፤ ህግና ጸጋ፤ ተፈጥራዊ ነገሮች ና መንፈሳዊ ነገሮች፤ ሞትና ህይወት፤ እስራትና ነጻነት፤ ለምን ብሎ እ/ር እንደዚህ በጥብቅ የሚቃረኑ ሃይላትን ፈጠረ?
አዎን ማየት ያለብን እ/ር መንገዱን ሊያስተምረን ተቃራኒ ሃይሎችን መፍጠር ነበረበት። መልካምን እንዴት እንረዳው ነበረ ክፉ ባይኖር ኖሮ? የእ/ርን ረቂቅ ጥበቡን በመጠኑም ቢሆን ልንገነዘበው ይገባል።
ፉጡራኑን ወደ ብስለት ለማምጣት በምን እደሚያሳልፈን ስናስተውል ይደንቃል:: ተፈጥሮውና ባህርዩ በሰው ውስጥ ይገለጥ ዘንድ የሚጠቀመው ተቃራኒ ሃይላትን ነው:: “መዝሙረ ዳዊት 119፡71 ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።” መጽሐፈ ኢዮብ 36፡15 …. በመከራም ጆሮአቸውን ይገልጣል። Job 36፡15 He… openeth their ears in oppression.
አንድ ሰው በእብራዊን ቋንቋ የጌታን ድምጽ ሰማሁ ካለ ፈጽሞ ሰምቶ ፈጽሞ መታዘዙን የሚያሳይ ነው። ሰምቶ ካልታዘዘም ፈጽሞ አልሰማም። በመገለጥ እንዲሰማም በሌላ ሂደት ያልፋል። “በመከራ ጆራቸውን ይከፍታል። እዮብ36፡15 በእብራይስጥ መከራ የሚለው ውጥረት ይለዋል። አንዳንድ ጊዜ ለምን ይሄ ሁሉ ውጥረት በመንገዳችን እንደ ሚያልፍ እንደነቃለን።
እንደ ዛም ሆኖ ነገር ሁሉ ተያይዘው ለበጎ እንዲደረግ እንረዳለን። በብዙ መከራ ማለፋችንም ለብዙ አላማ እንደሆነ እናውቃለን። ከዛ ውስጥ አንዱ ጆራችን እዲከፈት ነው። ጳውሎስ የደቀ መዛምርቱን ልብ በማበረታታትና በእምነታቸወ ጸንተው እንዲሩ በመምከር “ወደ እ/ር መንግስት ለመግባት በብዙመከራ (ግሪክ፦ pressure, እደአገባቡ ቃሉ ሲተረጎም ውጥረት ግፊት መገፋፋት ተጽኧኖ የሚያመጣ ውጥረት )ማለፍ አለብን “” ሐዋ14፡22 ይህም ውጥረት ከአሮጌው አውጥቶ ወደ አዲሱ ተጭኖ ያስገባናል። እ/ር አምላክ ጥበበኛ ነው። አንዱን ውጥረት ከአንድ ነገር ለማውጣትና በተመሳሳይ ሰአትም የስጋን ፈቃድ ሰብሮ የመንፈስን ድምጽ ወደ መስማት ግዛት ያመጣናል።
አብዛኛውን ጊዜ እ/ር በሂወታችን አንድ ነገር እዲያደረግ እንፀልያለን ስራውን ይጀምራል ከዛም እርሱን በቃወም እንዋጋዋለን እርሱ ግን ለጸሎታችን መልስ እየሰራ ነው ለምን ግን? አዎን ይህን የምናደርገው መንገዱን ስለ ማንረዳ ነው:: እኛን ለማስተማር የሚጠቀምባቸውን ተቃራኒ ሃይላት አናስተውለውም አይገቡንንም።
እ/ር የፍቅር ሰው እድትሆኑ ከጠየቃችሁት ለጥላቻ ያጋልጣችሃል። ይህን የሚያደርገውም ጥላቻንና ፍቅርን አይታችሁ ምን እደሆኑ እንድታውቁና ምንን እንደሚያዘጋጁ እድትረዱ ነው። ይህንንም ወይ በሂወታቹሁ ወይ በሌላ ሰው ህይወት ሊሆን ይችላል። ይሄ ለምሳሌ ያህል ነው እንጂ ይህን የሚረጋግጡ ብዙ ነጥቦችም አሉ። እናተም የምትገነዘቡትም ብዙ ይኖራል።
በእግዚአብሄር አሰራር ውስጥ የሚጠቀምባችውን ተቃራኒ ሃይላት ካላስተዋልን ለመማር እንቸገራለን። እራሳችንን በፊቱ ዝቅ አድርገን ለመንገዶቹ የነቃ ህሊና ይኑረን። ወደ መለኩና አምሳሉ ሊያመጣን ሊሞርደን ተቃራኒ ሃይላት እደሚጠቀም መገንዘባችን ውስጥ ሃይል አለው።
ምን አይነት ታላቅና በጥበብ ሁሉ የተሞላ አምላክና አባት ነው ያለን? ጌታ በማርቆስ ወንጌል 9፡49 ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፥ ሲል እውነቱን ነገሮናል እውነት የሆነውን አስቡ ተብለናልና እውነት የሆነውን እናስብ። ወደ ዕብራውያን 5፡8 ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ እኛ ከሱ አንበልጥምና መታዘዝን እንማር ዘንድ በሚያሳልፈን መንገድ ሁሉ ፈቃድህ ይሁን እንጂ ፈቃዳችን አይሁን ማለት እንችል ዘንድ የእ/ር ጸጋ ይርዳን። አሜን!” የተጠቀሰው ተፈጸመ።
ለእድገታችን እና ለድል ህይወት ወሰኝ የሆነው ዋናው ለውጥ የሚካሄደው በአስተሳሰባችን ግዛት ነው። እርግጠኛ ለመሆንም እ/ር ሲሰራ የኖረውና እየሰራ ያለው ከአስተሳሰባችን ጋር ነው።
በአይምራችን መታደስ መለወጥ አለብናንና we shall be “transformed by the renewing of our mind” አይምሮ ለዘመናት የፍልሚያ ሜዳ ሆኖ ሰንብተዋል። የክፉ ሃይላትም አይምሮን በክፉው ሃሳብ ለሞምላት ፍልሚያ ያደርጋሉና። እውነትን በአይምራችን ሲሞላ ፤ሲተካ ግን አንዱ እውነት ብዙ ሺ የክፉን ውሸት ሲያፈርስ እና ነጻ ሲያረግ ለድል ህይወት ሲያበቃ አስተውለናል።
አሁንም የሚማር ልብ ይዘን ከጌታ እግር አጠገብ መቀመጥ ፈቃዱን እንድናውቅ ብቻ ሳይሆን የሚጠቅመን ይህን በማድረጋችን ብቻ ጠላትም እድል ፈንታ እዳይኖረው ያደርጋል።
“የያዕቆብ መልእክት 4፡7 እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤
Jas 4፡7 Submit yourselves therefore to God. Resist the devil, and he will flee from you.” ለእ/ር በመገዛት በትህትና ከአጠገቡ ከእግሩስር ለመስማት ለመማር በመቀመጥ ተገዙ፤ (Submit የሚለው “hupotasso’ሁፖታሶ” ሲሆን ትርጉሙም “to set in array under) ዲያብሎስን እንቃወመዋለን እርሱም ይሸሻል። አሜን።
Posted on February 08, 2012 by Brother Binyam T. Alemayehu