የዘላለም ስቃይ ፍርድ ሲኦል፤ገሃነም፤ በእሳት ባህር ለዘላለም መቀቀል የሚሰብኩ የክፉው ሰራተኞች ናቸው።


Binyam TA

February 15, 2019 ·

የዘላለም ስቃይ ፍርድ ሲኦል፤ገሃነም፤ በእሳት ባህር ለዘላለም መቀቀል የሚሰብኩ የክፉው ሰራተኞች ናቸው። ክፍል 1፡ “እ/ር መንፈስ ነው። ዮሃ 4/24” መንፈሳዊው ነገር ለቁሳዊው አለም ለማስረዳት በአካላዊ ቋንቋ መስሎ ያስረዳናል። የብዙ አማኞች ችግር ይሄ ነው። ለዚህም ነው በመንፈስ መገለጥ እንድንረዳቸው በተምሳሌነት የተጠቀመባቸው ምልክቶች፣ SYMBOLS ቀጥታ ከመተርጎም የመጡ ብዙ ችግሮች የተከሰቱት። መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ መጽሐፍ ነው። አስተውሉት እስቲ “የእሳት ባህር” የሚለውን ቃል እንየው “ባህር ምንድነው?” ስፋትና ጥልቀት ያለው በውሃ የተሞላ ቦታ ነው። ይሄኛው ልዩነቱ በእሳት መሞላቱ ነው። በምልክት ወይም በገላጭ ቋንቋ ጌታ ተጥቅሞ ተናገረው። እስራኤል ቀይ ባህር በጌታ ለሁለት ተከፍሎ መንገድ አድርጎላቸው በውስጡ ባለፉ ግዜ ሐዋርያው በጥምቀት አልመሰለውምን ? 1ኛ ቆሮ 10/2 እነዚህም በመለኮታዊ ማጣርያ በእሳት ባህር የሚያልፉትም እንደዚሁ ነው። ለእ/ር እንዲ ሰለጥኑለት በልምድ ውስጥ ያሳልፋቸዋል።
በዚህ ቦታ ላይ ሁለተኛው ሞት ማለት የመጀመርያው ሞት እና ሲኦል በእሳት ባህር ውስጥ ሲደመሰሱ ማለት ነው። “በራእይ 20/4 ሞትና ሲኦልም የእሳት ባህር ውስጥ ተጣሉ። ይህም “የእሳት ባህር” [ይህ ሃሳብ ሲተረጎም ለሁለተኛ ጊዜ የተጨመረ ነው።] ሁለተኛው ሞት ነው።” “death and hell were cast into the lake of fire. THIS IS THE SCOND DATH.”k.j.v. ትክክለኛው ትርጉም ለአንባቢያን እንዲገባ መሆን የነበረበት “ሞትና ሲኦልም በእሳት ባህር ውስጥ ተጣሉ። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።” እንደ ምናስተውለው ሞትና ሲኦል ወደ እሳት ባህር ሲጣሉ ሁለተኛው ሞት ይባላል። ይሄ መንፈስ ቅዱስ እራሱ ሲያጽፈው ሁለተኛው ሞት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሰጠው ፍቺ ነው።
አስተውሉ ሁለተኛው ሞት ማለት ሰዎች በማይጠፋው እሳት ለዘልአለም ሲቀቀሉና ሲሰቃዩ ማለት አይደለም። አሊያም እንደ ሚባለው ክርስቶስን ያልተቀበሉ ከሞት ቡሃላ የሚጠብቃቸው ኑሮ አፈ ታሪኩ የዘልአለም ሞትና ስቃይ አይደለም። አሁን አይናችን ተከፍቶ ማየት ችለናል ሁለተኛው ሞት ማለት የአንደኛው ሞትና የሲኦል የሞት ግዛት ሁሉ በእሳት ባህር ውስጥ ተጥለው ሲደመሰሱና ሲጠፉ ማለት ነው ። በህይወት መጽሐፍ ያልተገኘ ሁሉ የመተላለፍና የሃጥያትና የሲኦል ተፈጥሮ ማንነቱ የተናወጣቸው አመል ሁሉ የአመፃ ሚስጥር ሁሉ ወደ የመለኮት የማጣርያ የእሳት ባህር ይጣላሉ።
ክፍል 2፡ የሉቃስ ወንጌል 12፡5 እኔ ግን የምትፈሩትን አሳያችኋለሁ፤ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም[የእዮርሳሌም የቆሻሻ ገንዳ በትል የተሞላ ይህን ግማት ለመከላከል 24 ሰአት ቆሻሻውን ለማቃጠል እሳት ያነዱ ነበር] ለመጣል ሥልጣን ያለውን ፍሩ። አዎን እላችኋለሁ፥ እርሱን ፍሩ። የStrongን የዕብራይስጥና የግሪክ ቁጥሮች አስተውል፤ 1067 geena gheh’-en-nah of Hebrew origin (1516 and 2011); valley of (the son of) Hinnom; ge-henna (or Ge-Hinnom), a valley of Jerusalem, used (figuratively) as a name for the place (or state) of everlasting punishment:–hell. see HEBREW for 1516 see HEBREW for 2011
በእብራይስጥ ትክክለኛው ገሃነም Gehenna [የሄኖም ሸለቆ Ge-Hinnom “valley of Hinnom”]የአሮጌው ኪዳኑ “hell” ወይም ገሃነመ እሳት ስያሜ ምንጭ የመጣበት በእዮርሳሌም፡ በስተደቡብ ይገኝ ከነበረ “የሄኖም ሸለቆ” ከተባለው ነው። በእንግሊዝኛው “Hell” በአማርኛ “ገሃነም” “ሲኦል” ተብሎ የተተረጎመው ነው። ክፉ አፀያፊ ባእድ አምልኮ ይለማመዱ የነበሩ ነገስታት በነበሩት በአክአዝና በምናሴ ዘመነ መንግስት ሞሎክ ለተባለ ለአሞናውያን ጣኦት ሰዎች በጭካኔ ወንድ ልጁን እና ሴት ልጁን መስዋእት አድርገው በዚህ ሸለቆ ያቀርቡበት ነበር። ይደረግ የነበረው ክፉ አፀያፊ ባእድ አምልኮም የተነሳ ኢዮስያስ ይህን ሸለቆ ርኩስ ሆኖ እንዲቆጠር አደረገ። ይህም ስፍራ ለዘመናት የከተማው ቆሻሻ መጣያ ና ማቃጠያ ቦታ ሆነ ቡሃላም የፍርድ ቅጣት ተምሳሌት ሆኖ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ተጠቅሞበታል። ከዚህ ሸለቆ አጠገብም ከፍ ባለው አቀበት ወይም ከፍታ ላይ ነበር እዮርሳሌም የተገነባችው።
መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 23/10 ማንም ሰው ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት እንዳያሳልፍ በሄኖም ልጆች ሸለቆ የነበረውን ቶፌትን ርኩስ አደረገው።[የቀድሞው ትርጉም]
‘በሄኖም ሸለቆ የነበረውን ቶፌት የተባለውን ማምለኪያ አረከሰ፤ ይኸውም ማንም ሰው ወንድ ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ እንዳያቀርብበት ነው። ‘2 ነገሥት 23:10[መደበኛው ትርጉም]
2Kgs 23/10 And he defiled Topheth, which is in the valley of the children of Hinnom, that no man might make his son or his daughter to pass through the fire to Molech.[KJV]
ኤርምያስ 7:30-32/ የይሁዳ ልጆች በፊቴ ክፉን ነገር ሠርተዋል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ያረክሱትም ዘንድ ስሜ በተጠራበት ቤት ርኵሰታቸውን አኑረዋል። 31 እኔም ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ያለችውን የቶፌትን መስገጃዎች ሠርተዋል።32 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ስፍራ ከማጣት የተነሣ በቶፌት ይቀበራሉና የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።[የቀድሞው ትርጉም]
‘እኔ ያላዘዝኋቸውን፣ ከቶም ያላሰብሁትን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት አቃጥለው ለመሠዋት በሄኖም ልጅ ሸለቆ የቶፌትን መስገጃ ኰረብቶች ሠሩ። ስለዚህ አስተውሉ፤ ይላል እግዚአብሔር ፤ ስፍራ እስከማይገኝ ድረስ ሙታንን በቶፌት ስለሚቀ ብሩ፣ የዕርድ ሸለቆ እንጂ ከእንግዲህ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል። ‘ ኤርምያስ 7:31-32 [መደበኛው ትርጉም]
30 For the children of Judah have done evil in my sight, saith the Lord: they have set their abominations in the house which is called by my name, to pollute it.
Jer 7/31 And they have built the high places of Tophet, which is in the valley of the son of Hinnom, to burn their sons and their daughters in the fire; which I commanded them not, neither came it into my heart. 32 Therefore, behold, the days come, saith the Lord, that it shall no more be called Tophet, nor the valley of the son of Hinnom, but the valley of slaughter: for they shall bury in Tophet, till there be no place.[KJV] ….. ክፍል 3 በወንድም ቢኒ፤

ክፍል 3 በወንድም ቢኒ፤ እግዚአብሔር በነብይ ኤርምያስ የእ/ርን ቁጣ በትንቢት ተናገረ ፍርድ በእዮርሳሌም ሲመጣ “የዕርድ ሸለቆ” ተብሎ እንደ ሚጠራ ተነበየ። ትንቢተ ኤርምያስ 19/6 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡[የቀድሞው ትርጉም]
Jer 19/6 Therefore, behold, the days come, saith the Lord, that this place shall no more be called Tophet, nor The valley of the son of Hinnom, but The valley of slaughter.
እ/ር በትንቢት ሲናገር ፍርድ በእዮርሳሌም ሲመጣ “የሸክላ ገምቦውንም ከአንተ ጋር በሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ፤ ይህን ሕዝብና ይህቺን ከተማ እንዲሁ እሰብራለሁ፤” ብለዋል ብለህ ንገራቸው አለው።
‘“ገምቦውንም ከአንተ ጋር በሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ፤ እንዲህም ትላቸዋለህ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የሸክላ ሠሪው ገንቦ እንደ ተሰበረና ሊጠገን እንደማይቻል፣ ይህን ሕዝብና ይህቺን ከተማ እንዲሁ እሰብራለሁ፤ የቀብር ቦታ ከመታጣቱ የተነሣ ሙታናቸውን በቶፌት ይቀብራሉ። ‘ኤርምያስ 19:10-11
ከዛም እዮርሳሌም ትንሽ ቆይታ በባቢሎናውያን ሰራዊት ጠፋች። ከአንድ ክፍለ ዘመን ቡሃላ በነህምያ ዘመን ድጋሚ ተሰራች። ላለፉት 2000 ሺ አመታት በተደጋጋሚ ጠፍታ ነበር። የደገመች ተሰራች። ከተማዋም አሁን ቆማለች። የኤርምያስ ትንቢት የመጀመርያው የፍርድ ገጽታ ነው የተፈፀመው። የዚህ ትንቢት ሙሉ ጥፋት የሚያካትተው ቅሪት አለው።
ጌታ እየሱስም ከገሃነም ጋር ተያይዞ የተነገረውን ትንቢት በእዮርሳሌም ላይ የተነገረውን ጭምርና በተምሳሌነትም ደጋግሞ ተናገረው። በገሃነም ምሳሌም 11 ግዜ ተጠቅሞበታል። ( በማቴ 5:22 , 29 , 30 ; 10:28 ; 18: 9 , 23:15 , 33 ; ማርቆስ 9 43 , 45 , 47 ; ሉቃስ 12 5 ያንብቡ ።)
‘ “እናንተ እባቦች፤ የእፉኝት ልጆች! ከገሃነም ፍርድ እንዴት ልታመልጡ ትችላላችሁ? ስለዚህ ነቢያትን፣ ጠቢባንንና መምህራንን እልክላችኋለሁ፤ ከነዚህም አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፤ አንዳንዶቹን ትሰቅላላችሁ፤ ሌሎቹንም በምኵራቦቻችሁ ትገርፏቸዋላችሁ፤ ከከተማ ወደ ከተማ ታሳድዷቸዋላችሁ። ስለዚህ፣ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ ለፈሰሰው ንጹሕ ደም ሁሉ እናንተ ተጠያቂዎች ናችሁ። እውነት እላችኋለሁ፤ ላለፈው ነገር ሁሉ ይህ ትውልድ ይጠየቅበታል። ‘ማቴዎስ 23:33-36

ቡሃላ ወረድ ብሎ በእዮርሳሌም ላይ የፍርድ ቃሉን ሲናገር እናያለን።
‘ “አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ፣ ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ አንቺ ኢየሩሳሌም! ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ፣ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ! እናንተ ግን ፈቃደኛ አልሆናችሁም፤ እነሆ፤ ቤታችሁ ወና ሆኖ ይቀርላችኋል! እላችኋለሁና፤ ‘በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው’ እስከምትሉ ድረስ ዳግመኛ አታዩኝም።”’ማቴዎስ 23:37-39
ኤርሚያስ የእዮርሳሌምን ጥፋት ከገሃነም ሸለቆ ላይ እንደተሰበረው የሸክላ ገንቦ እንደምትሰባበር ከፍርድ ጋር ካያያዘው ቡሃል ገሃነም የእ/ር ቃል የሚቃወሙት ላይ የመለኮት ፍርድ ተምሳሌት ሆነ ። ጌታም እዮርሳሌም እንደምትጠፋ ደግሞ ተነበየ።
ስለዚህ፣ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ ለፈሰሰው ንጹሕ ደም ሁሉ እናንተ ተጠያቂዎች ናችሁ። እውነት እላችኋለሁ፤ ላለፈው ነገር ሁሉ ይህ ትውልድ[genea, “ዘር race, ዝርያ offspring”] ይጠየቅበታል። ‘ማቴዎስ 23:34-36
ጌታ እየሱስ አማኞች እየሩሳሌም በውጭ ጦር ስትከበብ ከከተማዋ ፈትለክ ብለው እንዲያመልጡ አስጠነቀቃቸው። እነሱም ከ 66-67A.D. ገደማ ተበተኑ። በ70AD ላይ ታይተስ የተባለ የሮማ ጀነራል እዮርሳሌምን አጠፋት። አሁንም የትንቢቱ ሙልአት ገና በመሆኑ አማኞች የእየሱስን ቃል ሊያስቡበት ይገባል። አማኞች እየሩሳሌም በውጭ ጦር ስትከበብ ከከተማዋ ፈትለክ ብለው ሊያመልጡ ይገባል እ/ር ያድነናል ብለው መቀመጥ የለባቸውም ይህ ትንቢት ከላይዋ ነው እና። የነብዩ ኤርሚያስ ትንቢት ግልጽ ነው ዳግም ልትስራ እስከማትችል በገሃነም ሸለቆ ላይ እንደሰበረው የሸክላ ገንቦ እንደምትሰባበር ተናግረዋልና አማኞች የወረራ ምልክት ካዩ ሊዘናጉ አይገባም። ምናልባትም ከተማይቱ መርገሙየሚሰበርላት “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው” ብላ ክርስቶስን ከተቀበለች ብቻ ነው።
ስለዚህ ጌታ ጋሃነም የሚለውን የእብራይስጥ ቃል ተጠቅሞ ለግሪኮችና ለሮማዊያን ዝምድና የሌለው ቃል ቢሆንም ለ11 ግዜ በእርሱ ቃል የማይታመኑትን እነሱም እያስጠነቀቀ ካላመኑ የኤርሚያስ ትንቢት እንደ ሚፈፀምባቸው እየነገራቸው ነበረ። እነሱም በግላቸው በጅምላ ፍርዱ ላይ ተካተው ሊገኙ እንደሚችሉ ኤርሚያስ እንደ ተነበየው “የእርድ ሸለቆ” እንደ ሚሆን አስጠነቀቃቸው።….. ክፍል 4 በወንድም ቢኒ፤

ክፍል 4 በወንድም ቢኒ፤ ሌላው ጌታ ከተናገራቸው የገሃናም ተምሳሌት ፍርድ መካከል ሊታዩ የሚገባቸው አንዱ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤” የሚለው ቃል ነው።
‘ዐይንህ ብታሰናክልህ ጐልጒለህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል፤ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤ ‘ማርቆስ 9:47-48
ጌታ የጠቀሰውና የተነተነው የነብዩ ኢሳያስን ትንቢት ነበር። ‘“ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትም፤ እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።”’ኢሳይያስ 66:24
ኢሳያስ እየተናገረ የነበረው ስለ አሮጌዋ እዮርሳሌምና ስለ አዲስትዋ እዮርሳሌም ነበር።
‘“ወዳጆቿ የሆናችሁ ሁሉ፣ ከኢየሩሳሌም ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ስለ እርሷም ሐሤት አድርጉ፤ ለእርሷ ያለቀሳችሁ ሁሉ፣ ከእርሷ ጋር እጅግ ደስ ይበላችሁ። ‘ኢሳይያስ 66:10
‘“እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ የእናንተና የዘራችሁ ስም እንደዚሁ ጸንቶ ይኖራል” ይላል እግዚአብሔር ፤ ‘ኢሳይያስ 66:22

ስለዚህም ነበር ጌታ ገሃናምን የተጠቀመው ይደረግ የነበረው ክፉ አፀያፊ ባእድ አምልኮም ርኩሰት በዛ ዘመን ቆሞ ነበርና በዚያ ዘመንም ይህም ስፍራ ለዘመናት የከተማው ቆሻሻ መጣያ ና ማቃጠያ ቦታ ሆነ ቡሃላም ብዙ የሞቱ እንስሶች እና የሰዎች አካል ሳይቀር ይጣልበት ነበርና የበሰበሰም የበዛበት ያለማቋረጥ በትላትሎችም የተሞላ ነበረ። ጠረኑን ለመቋቋም ሲባል ቆሻሻውንም ለማቃጠል ሁልጌዜ የማይጠፋ ፍምና እሳት ይታይበት ነበረ። በዚህም የፍርድ ቅጣት ስፍራ ምሳሌ ሆኖ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና” የሚለውን ተጠቅሞበታል።
‘ዐይንህ ብታሰናክልህ ጐልጒለህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል፤ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤ ‘ማርቆስ 9:47-48
ሌላው ሲኦል የሚለው ቃል በመጀመርያ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ የሚገኘው ፔንታቱክ [ባለ አምስት ቅጽ መጽሓፍት(ማለት ነው)] ተብለው በሚታወቁት አምስቱ የሙሴ ጹሁፎች መካከል በኦሪት ዘኍልቍ 16/30 ሲሆን ከዛ ቡሃላ በብዙ ቦታ ላይ ተጽፈዋል። ይህም አንድ የእብራይስጥ ቃል እናም ሰዎስት የግሪክ ቃል በእንግሊዝኛው “Hell” በአማርኛ “ሲኦል” በማለት የተተረጎመው ነው። በአብዛኛው በብሉይ ወይም በአሮጌው ኪዳን በሁሉም የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ሁሉ “SHEOL” የሚለው ቃል ተጠቅመውበታል ትርጉሙም ድርብ ሳይሆን ነጠላ የሆነ “የሙታን ቦታ” “the place of the dead.” ማለት ነው። ሌላው ትርጉሙ የሙታን መቃብር grave, ጉድጋድ pit የሙታን ግዛት the realm of the dead።
ኦሪት ዘኍልቍ 16/30 እግዚአብሔር ግን አዲስ ነገር ቢፈጥር፥ ምድርም አፍዋን ከፍታ እነርሱን ለእነርሱም ያለውን ሁሉ ብትውጣቸው፥ በሕይወታቸውም ወደ ሲኦል ቢወርዱ፥ ያን ጊዜ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን እንደ ናቁ ታውቃላችሁ። Num 16/30 But if the Lord make a new thing, and the earth open her mouth, and swallow them up, with all that appertain unto them, and they go down quick into the pit[ sh’owl sheh-ole’] then ye shall understand that these men have provoked the Lord.
ሌሎች ተዛማች ሊጠኑ ሊታዩ የሚገባቸው ሃሳቦች ቢኖሩም እነዚህ ምንም ይሁኑ ምንም የሲኦል እና የገሃነም ፍፃሜው በጥቂቱ ካለፈው ፁሁፍ “እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሁለተኛው ሞትና የእሳት ባህር ፍቺ” ከሚለው ላይ ፍፃሚያቸውን እናያለን። ……ክፍል 5 በወንድም ቢኒ፤
ክፍል 5 በወንድም ቢኒ፤ “ስለዚህ ሃሳብ በብዙ ሰዎች ብዙ ተጽፎ አንብቢያለሁ ሚዛን የሚደፋና፡ብሎም የማይደፋም ቀልሎ የተገኘም አጋጥሞኛል። በእ/ር ቃል ሲመዘን ማለቴ ነው። በዚህ ሃሳብ ላይ በብዙ ሰዎች ዘንድ ሰፊ የሆነ ግራ የተጋባ አመለካከት እንዳለ ግልጽ ነው። ለብዙወገኖች ይጠቅማል በማለት ይህን የመረዳት ብርሃን አብረን እንድናየው እወዳለሁ መልካም ነገር አለውና። ከቀድሞው አባቶች ሲኦል ዘልአለማዊ ነውን? (is hell eternal or will GOD’S plan fail?) በRev-Charles pridgeon ከነቮበር ወ 1920 እትም መጽሐፋቸው። የእሳት ባህርን በተመለከተ ከገለጡት እጅግ ከሚያስደንቀው የመረዳት ብርሃን የተሞላበት የሊቅ ወይም
የእስኮላር ስራቸው ለተሻለ ግንዛቤ ለብዙ አስተዋዮች እንደ ታገዙበት ሁሉ እኔም ከታገዝኩበትና ከተረዳሁበት መካከል ለወገኖች ጥቅም ልጠቅስ እወዳለሁ። “የእሳት ባህርና ዲኑ (BRIMSTONE) የሚያመለክቱት እሳቱ ከዲኑ ጋር ሲነድ ነው። ዲን፡brimstone ወይም ድኝ፡ sulphur የሚለው የእሳቱ ባህርይ ነው።
የግሪኩ ቃል THEION ሲተረጎም ዲን፡brimstone ተብሎ የተተረጎመ ሲሆን ያው የግሪኩ ቃል እራሱ THEION መለኮት ማለት ነው። በጥንታውያን ግሪኮች መካከል ድኝ ፡sulphur የተቀደሰ ነበረ። እናም ለማጠን፤ ለማንፃት፤ ለማጥራት ለአምላካቸው ያውሉት ነበር። ለዚህም አላማ ያጥኑ ነበር። homer’s lliad[16:228] አንድ ሰው በእሳትና በዲን ዋንጫውን እያፀዳ እንደሆነ ሊናገር ይችላል። THEION ከሚለው ቃል የተሳበው ግስ {ግስ፡ ማለት የቌንቋ አረባብ የዘርና ነባር መሰረት ቃል ነው። } THEIOO ሲሆን ማለትም ማወደስ፤ መለኮትን መስራት፤ ለአምላክነት መለየት ማለት ነው። [liddel and scott Greek English Lexicon, 1897 Edition] ተመልከት/ቺ።
ለማንኛውም ግሪካዊ ወይም በግሪክ ቋንቋ ለሰለጠነ ሰው “የእሳት ባህርና ዲን” ሆኖ መረዳት የነበረበት “የመሎከት የማጣርያ ብህር፣a lake of divine purifcation” ነበር። ፍርድ የሚለው ሃሳብ መከልከል የለበትም። እ/ር መንገዱ ሁሉ እውነትና ፍርድ ነውና። በጥንታዊ ግሪክ ቋንቋ መለኮታዊ ማጣርያና ለመለኮት ማዋል የሚል ነው ፍቺው። በተራው አገላለጽ ይህ የቃሉ ትርጉም ገንጥለው አውጥተውታል። አመፀኛ ሃፍረት የለውም ተብሎ እንደ ተፃፈ ምንም ነገር ሳያስቀሩ ግን የዘልአለም ስቃይ ጋር አዛምደውታል።” የተጠቀሰው ተፈፀመ።
በነገራችን ላይ THEION የሚለው ቃል የተሳበው theo ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን እግዚአብሔር (መለኮት) GOD እየተባለ በአብዛኛው የተተረጎመው ቃል ነው። ቲዮሎጂ {Theologi or Theology is the study of GOD} የስነ መለኮት ጥናት ወይም ስለ ስነ መለኮት ማጥናት ከዚህ ሃሳብ የተገኘ ነው።
የእ/ርን አሰራርና አደራረጉን ለማወቅ አንድ ሰው ቃሉን እያጠና መንፈስም መረዳትን እያበዛለት ሲመጣ የቃሉን መንፈሳዊ አመልካች በትክክል ማስተዋል ሲጀምር በመጽሐፉ ፀሐፊ በእ/ር የዘልአለም አጀንዳ በቅዱሱ ልእለ ተፈጥሮ ውበትና እንዲሁም በታላቅ ጥበቡ፤ በፍቅሩ ብልጽግና ይነደፋሉ። እ/ርንም ውድድድ ያደርገዋል። በእ/ር ዘንድ ያለው ፍርድ ለማቅናት እንደሆነ ማስተዋል ይጀምራልና።
ሰዎች ለመከራ ይቀጣሉ። እ/ር ግን በፍርዱ ያቀናል ያፀዳል።በግሪኩ ቃል የጠራ ወይም የነፃ pur በዚህ ዘመን እንግሊዝኛ ማጽዳት ወይም ማጥራት ፡ ንፁህ ማድረግ PURGE and PURIFY ለሚሉት ቃላት ስር ወይም ምንጭ ነው። የእ/ር እሳትም የሚያደርገው ይህንኑ ነው። የእ/ር ባህርይና ተፈጥሮ ያሳያል። በዛሬው ጥናታችን በጥቂቱ የእሳቱን ባህሪ በመፅሐፍ ቅዱስ የእውነት ቃል እናጠናለን። ይህን እሳት እየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ለኩሶታል። በእሳት የሚያጠምቅ ሆኖም መጥተዋል። ለሚከተሉት ሁሉ እንደ እሳት መምጣቱን ቀጥለዋል። ገናም ለፉጡራኑ ሁሉ ይመጣል። አሜን ጌታ ሆይ ማራናታ አብዝተህ ቶሎ ቶሎ ምጣ። አሜን።
እንደ መፅሐፍ ቅዱስ ቃል ሰው ሊድንበት የሚችለው በሰማይ ይሁን በምድር እየሱስ ብቻ እደሆነ ይነግረናል ሐዋ4/12 በዚህ መንፈሳዊ በር ካልሆነ ማንም ወደ አባት ሊገባ እንዳይችል የታወቀ ነው። ዮሀ 14/6 ታድያ ጌታን ሳይቀበሉ ሳያውቁ የሞቱ ፍጥረታቱን ሁሉ ምን ይሆን ፍፃሚያቸው? እንደ ምናውቀው እ/ር ፍጥረቱን ሁሉ በልጁ ወደ ራሱ የማስታረቁ ጉዳይ የሚደግፉ የመፅሐፍ ቅዱስ ቃል በብዛት አሉ በዛው ልክ የዘልአለም ስቃይ አማኞችም ከመፅሐፍ ቅዱስ የሚጠቀሱት ቃላት በብዛት አሉ። (ዳን12/2፣ ማቴ12/32፡ 18/8፡ 25/41፡46 ማር3/29፡ 2ተሰ1/9 ዕብ6/2፡ 2ጴጥ2/17 ይሁዳ7፡ ራእ14/11፡ 19/3፡20/10 እውነት መቸም ሁለ ጊዜ በውሸት ሊሰቃይ አይችልም ሁለቱም ትክክል ሊሆኑ አይችሉም። አንድ እውነት ካወቅን አንድ ሺ ወሸቶችን ከህሊናችን ያባርራል። እ/ር ግራ የመጋባት አምላክ አይደለም እግዚአብሄር ሰላም ነው!“1Cor 14/33 For God is not the author of confusion, but of peace, as in all churches of the saints.” ይህ መጽሐፍ በሱ መንፈስ ተነድተው እስካጸፋቸው ድረስ እርሱ መልስ አለው።
ከአሮጌው ኪዳን እንጀምር በቀድሞው ኪዳን ዘልአለም ሲል በሂብሩ “Olam”(Strong #5769) በመፅሐፍ ቅዱስ ተጠንቅቀን ብናስተውል በትክክል ዘልአለም የሚል ተግባር ይዞ አናየውም። ነብዩ ዮናስ በታላቁ አሳ ሆድ ውስጥ ሆኖ ”ትንቢተ ዮናስ 2/7 ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፤ በምድርና በመወርወሪያዎችዋ ለዘላለም “olam” ተዘጋሁ፤ አንተ ግን፥ አቤቱ አምላኬ፥ ሕይወቴን ከጕድጓዱ አወጣህ።“ ለዘልአለም ተዘጋሁ ቢልም በአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ የቆየው ለ3 ቀናት ብቻ ነው እንጂ ለዘልአለም አልነበረም። ዮና1/17። የዕብራውያን ባርያ ጌታውን ሲወድና ጆሮውን ይበሳና ለዘልአለም“Olam” ያገልግለው ዘጽ21/6 እደ ሚታወቀው ይህ ማለት በህይወት ዘመኑ ብቻ ነው እንጂ ከዛ በላይ አያገለግለውም ይሞታልና።….. ክፍል 6 በወንድም ቢኒ፤
ክፍል 6 በወንድም ቢኒ፤ መቸም ምስክርነት በሁለትና በሰዎስት ይጸናልና እንጨምር እ/ር ስለ ሰለሞን መቅደስ ሲናገር ስሙን ለዘልአለም“Olam” በዚያ አስቀምጣለሁ አለ 1ነገስት9/3 የሰለሞን መቅደስ ግን ከ400 አመት ቡሃላ እስከ መሬት ድረስ ድዋ ብሎ ተቃጠለ። ለዘልአለምም አልኖረም። ትንቢተ ኢሳ32/14 አንዳንድ ቦታዎች ለዘልአለም“Olam” የተተው ይሆናሉ ይላል እዛው ቀጥሎ ሲፈታው ይህ የሚሆነው መንፈሱን ከላይ እስኪያፈስ እና በረሃው ፍሪያማ እስኪሆን ድረስ እደሆነ ይናገራል። የአሮን ክህነት ለዘልአለም“Olam” እደሚሆን ጌታ እ/ር ተናግሮ ነበር ዘፀ40/15 ቃሉ ሲነግረን ግን የመልከ ጸዲቅ ክህነት የበላይ እደ ሆነበት ያሳየናል። ዕብ7/11-8 ስለዚህ “ትንቢተ ዳንኤል 12/2 በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም“Olam” ጕስቍልና” ይሄ ፍፃሜ የሌለው የዘልአለም ቅጣትን ለማሳየት የተነገረ አልነበረም እ/ር የሚቀጣው ሰዎች እስኪታረሙና ንስሃን እስኪ ሰጣቸው ድረስ ነው። “Olam” ተብሎ መተርጎም የነበረበት “indefinitely ላልታወቀ ጊዜ” ወይም “age-lasting እድሜ ልክ.” ነበር። በጥንቃቄ በዚህ መልክ ቢተረጎም ኖሮ ብዙ አወዛጋቢ ሃሳቦችን ባጠራ ነበር።

የዘልአለም ፍርድ፡ Eternal Judgment ወይም ፍፃሜ አልባ ቅጣት Endless punishment ብሎ ነገር መፅሐፍ ቅዱስ አያስተምርም። የፍርድን ተፈጥሮ ከማስተዋላችን በፊት ዘመን እና ዘልአለም የሚሉትን ሁለት ቁልፍ ቃላቶች ልዩነታቸውንና ተናጋሪው መንፈስ የሆነው እ/ር ከተናገራቸው አካያ ማየቱ እጅግ ጠቃሚ ነው። “የዘልአለም ፍርድ“ ቅጣት እውነት እንደሆነ ለማረጋገጥ ከሚጠቀሱት ቃላቶች ዋንኛው “ዘልአለም” የሚለው ቃል የእንግሊዝኛውም የአመርኛውም ላይ ከተፈጠረው የትርጉም ስተት የተገኘ ጽንሰ ሃሳብ ነው። ”መጽሐፍትን እና የእግዚአብሄርን ሐይል ካወቅን አንስትም“ በሚለው ፁሁፍ ላይ እንደገለጽኩት የትርጉም ስራዎችን እንደ ፍጽም ስራ እንዳንደገፍባቸው ታሪካዊ አመጣጣቸውን በማስተዋል መቃኘታችን ለዚህና ለሌሎ ች ሃሳቦች እንደ መንደርደርያ እንዲጠቅመን፡ነው። BROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU WRITINGS,…..። ክፍል 7 በወንድም ቢኒ፤
ክፍል 7 በወንድም ቢኒ፤ በአዲስ ኪዳን ”ዘልአለም Eteernal, Everlasting” የሚለው ቃል ከዋናው የግሪኩ ቅጂ ላይ “aionions” ከሚለው ቃል የተረጎመ ነው የቃሉ ስር ወይም፡ ንብረትነቱ “EION” ነው። ትርጉሙም “ዘመን age” ማለት ነው። ሁለቱ የተለያየ ትርጉም ያላቸው ናቸው ማለት አይደለም ። aion(the noun form) ሰዋሶው ወይም ነባር ስም ሲሆን aionions (the adjective form ቅጽል ነው። ሁለቱ ቃላት ሰዋሶው እና ቅፅል ናቸው። ለምሳሌ ሳምንት ሰዋሰው ሲሆን ሳምንታዊ ደግሞ ተቀፅላው ነው። ልክ እለት፦ እለታዊ, አመት ፦አመታዊ እንደሚባለው መለት ነው። Greek word “aion” (Strongs #165) or its adjective form “aionios” (#166).
በመረዳት ብርሃን ማስተዋል ያለብን ዘመን ማለት ዘልአለም ማለት አይደለም። ብዙ ጊዜና ብዙ ወቅቶች አሉ። ነገር ግን አንድ ዘልአለም ብቻ አለ። ዘልአለም ጅማሬ የለው ፍፃሜም ቢሆን የለውም። ነገር ግን ጊዜ ዘመን ወቅቶች ሁሉም ጅማሬ አላቸው ፍፃሜም አላቸው። ጊዜ ሲያበቃ ዘልአለም ይጀምራል የሚለው አባባል ፈጽሞ ስህተት ነው። ምክንያቱም ዘልአለም ጅማሬ የለውም የሚያበቃም አይደለም። ዘልአለም ጊዜ ሲመጣ የሚጀምር አይደለም። ዘመናት በዘልአለም ውስጥ የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው። ልክ ሴኮንድ በደቂቃ ውስጥ ቦታ እንዳለው ደቂቃም በሰአት ውስጥ የራሱ ቦታ እንዳለው ሰአትም በአመታት ውስጥ የራሱ ቦታ እንዳለው። አመታት እና ዘመናት ያልቃሉ በዘልአለም ውስጥም የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ጊዜ እናስተውል ዘንድ በነዚህ ቃላቶች መካከል ያለው ልዩ ነት ግልጽ እይታ ሊኖረን ወሳኝ ነው። ዘመን የሚመደበው በጊዜ ውስጥ ሲሆን ዘልአለም ግን ጊዜ አልባ ነው። በመጽሐፍ ስለ ዘመን የተናገሩትንና ሰለ ዘልአለም የተናገሩትን ለይተን ማስተዋሉ የእ/ርን ጠቅላላ ምክር እናስተውል ዘንድ እጅግ ይጠቅመናል።
በጣም የሚያሳዝነው አብዛኛዎቹ የእንግሊዝኛም ሆነ የአመርኛ ትርጉሞች ብዙ የሚመሰገኑበት ቢኖርም ዘመንን በተመለከተ ሲተረጉሙ ግድ የለሽ ሆነው ዘልአለም እያሉ በመተርጎማቸው በእ/ር ህዝብ ላይ ለዘመናት ትልቅ ግራ መጋባትን አስከትለዋል። ይህም ብዙ ትውልዶችን ለአያሌ ዘመናት የተዛባ መረዳት ውስጥ ቆልፎ አስቀምጠዋቸዋል። ለመጥቀስ ያህል የእንግሊዝኛም ሆነ የአመርኛ ትርጉሞች KJV ላይ እዲሁም በዚህ መጽሐፍ ተጽኖ ስር የተተረጎሙ ሁሉ ላይ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ስለሚሳደብ ሰው የተናገረውን ቃል እንዲህ ያስቀምጡታል። እግዚያብሄር ያሳያችሁ አንዱ ቃል ወደ ስንት ተበታትኖ እንደ ተተረጎመ age {2 ጊዜ beginning of the World {2} ጊዜ, for ever and ever,(8) course{1}ጊዜ World {32} ጊዜ eternal {42}ጊዜ, world began{1}ጊዜ forever{27}, for evermore{2}, እነዚህ ሁሉ ዘመን ወይም እንደ አገባቡ ከዘመን ዘመን፤ ለዘመናት፤ ለዘመኑ፤ ወዛተ ተብሎ በቀላሉ በዚህ መልክ መተርጎም ነበረበት። ….. ክፍል 7 በወንድም ቢኒ፤
ክፍል 7 በወንድም ቢኒ፤ “ማርቆ3/29 መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ግን “የዘልአለም” ሃጥያት ይሆንበታል እንጂ አይሰረይለትም” ከዚህ የተሳሳተ ትርጉም የተነሳ የተሳሳተ ጽንሰ ሃሳብ ተወልደዋል። ለዘልአለም ይቅር የማይባል ሃጥያት አለ ብለን እንድናስብ አድርጎን ነበር። ነገር ግን የቃሉ ፍቺ በትክክል እንዲያቀብል አድርገው ከተረጎሙት ከጥቂት የእንግሊዝኛም ትርጉሞች መካከል Emp hatic Diaglott የተባለው ትርጉም ትክክለኛውን ትርጉምi እዲህ ያስቀምጠዋል። “Whoever may blasphemy the Holy Spirit no forgiveness to the age but is exposed to anian lasting judgment mar3/29” “መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ “ለዘመኑ” ይቅር አይባልም። ነገር ግን ”ለዘመኑ“ ፍርድ ይጋለጣል።“ እንደ ምናስተውለው ይቅር የማይባለው ለፍርድ የሚጋለጠው ለዘመኑ ፍርድ እንጂ ለዘልአለም ፍርድ አይደለም። በማትዮስ 12/32 ያለው ደግሞ እንዲህ ተብሎ ተተርጉመዋል ”በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ ”አለም“ ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም። አለም የሚለው ቃል ከግሪኩaion ማለትም ዘመን age ተብሎ መተርጎም ከነበረበት ቃል የመጣ ነው። ቃሉ መተርጎም የነበረበት “መንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ “ዘመን” ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም” ነው። ጌታ እየሱስ የተወለደው በህግ ዘመን ስለ ነበር በዚህ ዘመንም ቢሆን ማለቱ የህግን ዘመን ለማሳየት ሲሆን በሚመጣው ዘመን ቢሆን ሲል ደግሞ አሁን እኛ ያለንበትን የፀጋውን ዘመን ማለቱ ነው። ይህን ካስተዋልን ስለ ዘመንና ስለ ዘልአለም ያለውን ብዥታ ያጠራልናል። በግሪክ aion(ሰዋሰው noun) በግልጽ “ዘመን ወይም ያልተወሰነ ክፍለ ጊዜ ነው an age or an indefinite period of time, Young’s Concordance” BROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU WRITINGS, 9/12/2018 RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND.

.[16:228]5Demis Nida, Mulugeta Shiferaw and 3 others3 Comments2 SharesLikeCommentShare

Comments
  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal