
የትውልድ እርግማን[ Generational Curses] ስትል ምን ማለትክ ነው? ይህ ትምህርት የክርስቲያን የፈጠራ ወሬ[ኦሮሚኛ፤ ዱቢ ሶባ፣ ዋን ኦፉማ ኡመን፡ ትግሪኛ፤ ናይ ፈጠራ ወረ] ነው። የትውልዶች እርግማን ብሎ ነገር የለም። ምንም ኩነኔ[ condemnation] የለም፤ ወደ ክርስቶስ ዘወር ስትሉ ተገፈዋል። የዮሐንስ ወንጌል 8:36 እንግዲህ ልጁ አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ። የዮሐንስ ወንጌል 8:32 እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡1 እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።
ይህ ቃል ምን ይላል? በትውልዶች እርግማን ስር ናችሁ ይላልን? ወይስ ነጻ ናችሁ አርነት ወጥታችሃል ይላል? ነጻ ነን!!
ትርፍራፊ የትውልድ እርግማን አለ ይላልን? ምን ይህል የእርግማን ቅሪት አለ ይላል? ምንም የእርግማን ቅሪት አልተወም! ሁሉንም እርግማን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመስሦታል፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታልና፤
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡14 በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤። ኩኔና እርክማን ሞተዋል በልጁ በእውነት አርነት ወጥተናል። ወንድም ቢኒ።
Mulugeta Shiferaw እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ አለምን ወደደ…..የእግዚአብሔር ፍቅር ማጠቃለያ የለውም ። በሞቱ የሞት ስልጣንን ሲሽር በመስቀሉ የሕማም የመርገም ና የኃጢአት ሙሉ ዋጋ ተከፈለ።
በሰው በጎ ፍቃድና ፍላጎት ሳይሆን እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ሰላምን አደረገ ።
በሰማይ በምድር ከምድር በታች ያሉ ለጌታ ክብር ሊንበረከኩ ምላስ ሁሉ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ተመሠከረ ደግሞ ይመሰከራል ።
ስለዚህም ፍቅርን ተከታተሉ ፣ የወንድማማች ፍቅር ይኑር…በማለት ተነገረ ።ፍቅር በምድር በክርስቶስ ቅዱስ መስዋዕትነት ስለተገለጸ ።ፍቅርም የመርገምን ኃይል ሽሮ አለምን ከእግዚአብሔር ጋር ስላስታረቀ ….በጌታችን የማስታረቅ መስዋዕትነት ከእግዚአብሔር ጋር ሰላምን ስላደረገልን ….. የመርገም ኃይል ተሽሯል። ክርስቶስ ስለከበረ መርገም በማንም ላይ ኃይል የለውም።
Genaration curse የሚባል የኀይማኖት ፍልስፍናና አዲስ ትምህርተ ኀይማኖት ነው።
ዉንጌልን የሚያጨልም ጥቂት ግለሰቦችን ገናና መርገም ሰባሪ የተቀባ ለመባል የመድረክ ላይ ጩኸት ነው ።
ደግሜ ማለት የምፈልገው : ኃጢአት በሽታዎች ሁሉ መርገም በሙሉ ዋጋቸውን በመስቀሉ ላይ ተቀብለው የእግዚአብሔር የማዳን ብርሃን ፈንጥቋል።
ሐዋርያው : Pulling down strong holds and casting out imaginations በ፪ ኛ ቆሮንቶስ ፲ : ፩ – ፭
ትልቅን ምክርን ይመክራል ። ከኢማጂኔሽን የወጣውን ቢሰብኩና መርገምን በጸሎት ሊሰብሩ ቢጮሁ እነዚህ የበአል ነቢያት ያሰኛቸዋል። የመስቀሉን ምስጢር ክደዋልና
የወንጌል አገልጋይ የቤተክርስትያን መልክተኞች አይደሉም ።ልዩ ወንጌልን ይዘዋልና።