ከውይይት የተጠቀሰ፤ Temesgen Atanaw እውነት ያስቆጣል እንዴ? ያስቆጣህ የእ/ር ምህረት በፍጥረቱ ላይ ማስተዋል በመጀመርክ ነው ነብዩ ዮናስን መሰልከው እንደሰበኩት ነነዌን ለምን አላጠፋካትም ብሎ እንደበገነ አትሁን። እኛ የዳነው “በእምነታችን በኩል በጸጋ ነው” (ኤፌ 2 8), ነገር ግን ከእግዚአብሄር እስካልተሰጠን ድረስ እምነት የእኛ አይደለም. ሮሜ. 12: 4, “እግዚአብሔር ለእያንዳንዱም የእምነትን መጠና አካፈለው ለገሰው” እግዚአብሔር ለእኛ እምነት ከሰጠን በኋላ የእኛ ይሆናል! በጣም ቆንጆና ቀላል ሆኖ ልንረዳው ከምንችለው በላይ ባለመፃፉ ደስ ይላል።‘ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ መጀመሪያ በኵራት የሆነው ክርስቶስ፣ ከዚያም በኋላ እርሱ ሲመጣ የክርስቶስ የሆኑት። ‘ 1 ቆሮንቶስ 15:22-23አዳም ሁሉን ወደ ሃጥያት ይዞ ለመውደቅ አቅም እንደ ነበረው ሁሉ ክርስቶስ ይበልጡኑ ሁሉን ወደ ጽድቅ ይዞ ሊነሳ የበለጠ ሃይል አለው። ‘እኔ ግን ከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሰውን ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ[ እጎትታለሁ: በጡንቻ በሃይል to drag , muscular ።” ዮሐንስ12:32 ጥያቄ/ሁሉም ድነትን ተቀብሎ ከሆነ ምስክር መሆንና ወንጌልን መስበክ ለምን አስፈለገ? እ/ር ሁሉን የሚያድን ከሆነና ሲኦልም ሞትም በእሳት ባህር የሚደመስሰው ከሆነ ለምን እናመልከዋለን እንደልባችን አንሆንም? የሚሉም አሉ። ይህ የሚያሳየው እ/ርን የሚከተሉት ፍርድና ሲኦልን ፈርተው እንጂ ለእ/ር ፍቅር ስላላቸው እንዳልሆነ ከልባቸው የተገለጠው ሰልፍ ያሳያል።እያንዳንዱ በራሱ ተራ ስለሚድን ማለትም ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ተራውን ስለማናውቅ ወንጌልን እንሰብካለን።ለሁሉም ሰዎች የእግዚአብሔር ፍቅር ይሰበካል ይታወጃል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፤ የእውነትን ቃል በቅንነት ማስተዋልና መለየት፤ እውነትን በፍቅር ማስተማር፤ በክርስቶስ ተቀባይነትን፤ እና ይቅርታን ለማድረስ እንጥራለን!የእግዚአብሄር ትግስት ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ እንደሆነ እናውቃለንና። ‘አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ማንም እንዳይጠፋ ፈልጎ፣ ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ ስለ እናንተ ይታገሣል።’2 ጴጥሮስ 3:9 ሞት በአንድ ሰው በኩል እንደ መጣ፣ የሙታንም ትንሣኤ በአንድ ሰው በኩል #ሆኖአልና። ሰዋች #ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች #ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤ አዳም ሁሉን ወደ ሃጥያት ይዞ ለመውደቅ አቅም እንደ ነበረው ሁሉ ክርስቶስ ይበልጡኑ ሁሉን ወደ ጽድቅ ህይወት ይዞ ሊነሳ የበለጠ ሃይል አለው። 21 ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል #ሆኖአልና።22 ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ #ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። 23 ነገር ግን #እያንዳንዱ#በራሱ#ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው1 ቆሮንቶስ 15:21-22እንዲሁ ደግሞ፦ ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15/45በዚህ ጉዳይ ላይ እ/ር የሚያውቀው ሁለት የሰዎችን ዘር አዳሞችን ብቻ ነው። ሁለቱም የዘር መጀመሪያ ና መጨረሻ ናቸው። የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው፤ ሁለተኛው ሰው ከሰማይ የሆነ ጌታ ነው።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15/47 The first man is of the earth, earthy: the second man is the Lord from heaven. የመጀመሪያው የሰው ልጆችን ወደ #ሞት ይዞ ወረደ ሁለተኛው ወደ #ህይወት ይዞ አወጣ። አዳም ሁሉን ወደ ሃጥያት ይዞ ለመውደቅ አቅም እንደ ነበረው ሁሉ ክርስቶስ ይበልጡኑ ሁሉን ወደ ጽድቅ ህይወት ይዞ ሊነሳ የበለጠ ሃይል አለው። ‘እኔ ግን ከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ #ሰውን#ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ[እጎትታለሁ፤- በሃይልና በጡንቻ drag, forcefully it is muscular ።” ዮሐንስ12:32 ኅይል የእ/ር ነው!ሁሉን ወደኔ እስባለሁ ! ፤ እያንዳዱም በራሱ ተራ ይሆናል !በሮሜ5/18 “በአንዱ በደል ምክንያት ፍርድ ለኩነኔ ወደ ሰው ሁሉ መጥተዋል። ”ይላል። ማወቅ ያለብን ግን ከውድቀቱ ጋር መነሳቱም እኩል መሆኑን ነው። እንዲሁም በአንዱ ፅድቅ ምክንያት ስጦታው ህይወትን ለማፅደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ። አስተዋላችሁን የመጨረሻው {እየሱስ ክርስቶስ)በፅድቁ ሁሉን ማዳን አይችልም ብሎ መወሰን በመጀመርያው {በአዳም] ውድቀት ምክንያት ወደ ሰው ሁሉ ኩነኔ አልመጣም እንደ ማለት ነው ። ደህንነት ከውድቀት ጋር እኩል ሀይል አለውና። የመጀመርያው አዳም ሁሉን ይዞ ለመውደቅ ሀይል እንደ ነበረው ሁሉ ሁለተኛው አዳም ክርስቶስም ሁሉንወደ ራሱ ለመሳብ ሀይሉ አለው። የፈለገ ቢሆን የአዳም ሁሉን የመጣል ሀይል ከእየሱስ ሁሉን ከማዳን ሀይል አይበልጠውም። ነገር ግን “ጠላቶችህ ባንተ ላይ ዋሹብህ” ተብሎ እንደተፃፈ ነው። “ዮሀ12/32 እኔም ከምድር ከፍ ያልኩ እንደ ሆነ ሁሉን ወደኔ እስባለሁ” ለመሆቃሉ ቢያንስ ያመኑልኝን ብቻ የተወሰኑትን ወደኔ እስባለሁ ይላልን? አይልም! ሁሉን ወደኔ እስባለሁ ይላል እንጂ። ሀሌሉያ! በአንዱ ምክንያት ሁሉ ወደቁ በአንዱ ምክንያት ደግሞ ሁሉ ዳኑ ።ሁሉ በአዳም እንደሞቱ ሁሉ በክርስቶስ ህያዋን ይሆናሉ።ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል። 1ኛቆሮ.15/22” ከላይ እንደተፃፈው አሁን ተራቸው ደርሶ ያልዳኑት እያንዳንዱ በተራቸው መዳናቸው አይቀርም። ማወቅ ያለብን “የሁሉ ነገር መታደስ ዘመን አለ።ሀዋ3/21”“ያም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በእየሱስ ስም በሚበረከኩ ጊዜ ምላስም ሁሉለእ/ር አብ ክብር እየሱስ ጌታ እንደሆነ የሚመሰክርበት ጊዜ ነው። ፊል2/10” ታድያ እኮ ሁሉን ነገርእ/ር በሚያድስበት ዘመን “እ/ር ሁሉን በሁሉ ይሆናል ተብሎ እንደተፃፈ አሁን የእ/ርን የዘላለም አጀንዳ እና አሰራሩን ላልተረዳ ሰው በሰማይ በምድር ከምድር በታች ያሉት ሁሉበዝያን ጊዜ እየሱስጌታ ነው! ብለው የሚመሰክሩት ተገደው ይመስለዋል እንጂ በእ/ር መንፈስ ሆነው አይመስለውም። ምክንያቱም የሚምበረከኩት ስቃይ ቅጣት በዝቶባቸው ተሸንፈው በፍርሀት እየተማፀኑ ይመስለዋል እንጂ ከአባት ከአብ} ፍጥረቱን ከሚያርመው ፍርዱና ከምህረቱ ባለጥግነት የተነሳ ክብር ለመስጠት አይመስለውም። በደልን ንቆ የሚተው ይከበራልና። “መዝ130/4 ነገር ግን በአንተ እ/ር ዘንድ ይቅርታአለ ስለዚህም ልትፈራ {ልትከበር)ይገባሀል።“ther is forgivness withthee{GOD},in order that you may be respected”ማወቅ ያለብን “1ኛ ቆሮ,12/3 በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር እየሱስ ጌታ ነው! ሊል አንድ እንካ እንዳይችል አስታውቃችሀለሁ።” አስተውሉ እንግዲህ በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር አንድስ እንካ እየሱስ ጌታ እደሆነ ክብርን መስጠት የማይችል ከሆነ አሁን ጠላቶቹ የሆኑት ሁሉ በዝያን ጊዜ ሲታደሱእየሱስ ጌታ ነው! የሚሉት በመንፈስ ቅዱስ ሆነው ነው። ሀሌሉያ! ባለ ራእዩ ዮሀንስ አረ በአውነት ግዛት አንድ የሰማሁት ነገር አለ። ይላል እሱምራእ5/13 በሰማይና በምድርም ከምድርምበታችም በባህርም ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ያለው ፍጥረት ሁሉ፥ በረከትና ክብር ምስጋናም ሀይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለበጉ ይሁን ሲሉ ሰማሁ።“አስተዋላችሁንሞት ዘላለማዊ አይደለም ሞት ሲደመሰስ ፍጥረት ሁሉ፥ በመንፈስ ቅዱስ ሆኖ ለአብ ክብር እየሱስ ጌታ ነው! ይላል ። ሀሌሉያ! እየሱስ ክርስቶስ ትላንት ዛሬም ነገም ጌታ ነው! አሜን! ተፈፀመ! በወንድም ቢንያም