
Binyam TA
ሞት የሚገባው ኃጢአት ሲል ምን ለማለት ነው? ፡ ይህ ሃሳብ ከወንድማችን በሌ Bele Melaku ጋር በተነሳ ውይይት ተመርኩዞ ቢዘጋጅም በሰፊው ስለጻፍኩት በሌ ቅር እንደማይለው ስለሚገባኝ ለወገኖች ጥቅም ለጥፌዋለሁ። በውንድም ቢኒያም 1/21/2020 ፤ በጥቅሉ ስንፀልይ ፣ ዮሐንስ እንደሚያስረዳን “እግዚአብሔርን እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ” ጸሎታችንን በእርግጥ ይሰማል ብሏል ፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ዋስትና የማይሰጣቸው ብዙ የሰዎች ምኞቶች እንዳሉ ግልፅ ነው ፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው እንደዚህ ካሉ ሃሳቦች ምሳሌዎች እንዲሆነን አንዱን ልብ በሉ ይለናል ፡፡ 1 ዮሐ 5፡16 ማንም ሰው ወንድሙ ለሞት የማያበቃ ኀጢአት[“sinning sin”] ሲያደርግ ቢያየው ይጸልይ፤ እግዚአብሔርም ለሞት የማያበቃ ኀጢአት ላደረጉት ሕይወትን ይሰጣል። ለሞት የሚያበቃም ኀጢአት አለ፤ ስለዚህኛው ግን ይጸልይ አልልም። 17ዐመፅ ሁሉ ኀጢአት ነው፤ ለሞት የማያበቃም ኀጢአት አለ።
የሃንስ መእራፍ አምስት ላይ ይህንን ሃሳብ ከማስተማሩ በፊት በመራፍ 3 ላይ ኃጢአት ህግን መተላለፍ ማለት ነው ሲል ፍቺውን አስረድቶ ነበር። Sin IS the transgression or breaking of the law, We must always come back to Scripture, facts, definitions, and principles. “Sin IS the transgression or breaking of the law” (I John 3:41 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3/4 ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን[ ህግን መተላለፍ፤የህግን ኢላማ መሳት ነው] ደግሞ ያደርጋል፥ ኃጢአትም ዓመፅ[ ህግን መተላለፍ፤ የህግን ኢላማ መሳት ነው] sin is the transgression of the law] ነው። 1John 3/4 Whosoever committeth sin transgresseth also the law: for sin is the transgression of the law.
በዚሁ መንፈሳዊ ገጽታው እንየውና በክርስቶስ ውስጥ እስከተፈጠርን ድረስ መልእክት የሚያነብ ልብ በሚያነበብበት ጊዜ በእያንዳንዱ ገጽ ፊቱን ያያል በእያንዳንዳቸው መስመር ከክርስቶስ ጋር በምሳሌ እራሱን ጨምሮ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ካላየን የሚታያየው ሁሉ ከንቱ ነው። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደዚህ መጽሐፍ በመቅረብ በክርስቶስ የክብር ባህር መዋኘት እንችላለን። የእግዚአብሄር ክብር የክርስቶስ መልክ ነው። “ሁሉ ሃጥያትን ሰረተዋል የእ/ር ክብር ጎድላቸዋል” በሃጥያት ምንያት የጎደለብን ብር አልነበረም የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ነው። ሃጥያት የሚለው መንፈሳዊ ገጽታውን ጳውሎስ ያስረዳበት ምሳሌ ጽንሰ ሃሳብ ልንረዳው ይገባል በግሪኩ HARMATIA ሲሆን ይህ እስፖርታዊ ቋንቋ ነው፤ ትርጉሙም ምልክቱን መሳት ነው። MISSING THE MARK በአንድ ቀስተኛ ቀስቶ የቀስቱን ፍላጻውን ካሽቀነጠረ ኢላማውን ወይም አላማውን ከሳተ ውድዱርን የሚያየው ህዝብ ሃማሪቲያ HARMATIA ብሎ በታላቅ ድምጽ ይጮካል። እኛም ኢላማችን የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ስለሳትን ሃማሪቲያ HARMATIA ሆነብን አሁን ግን እ/ር ይመስገን በሃማሪቲያ HARMATIA ያጣነው የጎደለብን የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ተመለስን። የእ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን ክ-ብ-ር ኢ-የ-ሱ-ስ ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ነው። የሐዋርያት ሥራ 7/55 መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን ክ-ብ-ር ኢ-የ-ሱ-ስ-ን-ም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፦
በጥሬ ትርጉሙ ኃጢአት ህግን መተላለፍ ከሆነ። የመጀመርያው ለሰው ልጅ የተሰጠው የእ/ር ህግ የቱ ነው? “ኦሪት ዘፍጥረት 2/17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።” በዚህም የመጀመርያውን ኃጢአት ህግን መተላለፍ አዳም ሰራ ። ያልተገባው የእውቀት ምንጭ መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ ዘንድ ተጠቀመ።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ይህንኑ ነው ያስተማረው በማቴዎስ ምዕራፍ 7 /22 ውስጥ በዚያች ዘመን ብዙዎች እንዲህ ይላሉ ” በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን ? በስምህስ ብዙ ድንቅ ነገሮች አላደረግንምን ?” እነዚህ ሰዎች ግን ህገ-ወጥነት በግሪክ anomia ህግ አልብነትን ስለ ሚለማመዱ lawlessness ለተስፋዪቱ ምድር ብቁ እንዳልሆኑ ይነገራቸዋል። ኢየሱስም አለ “እናንተ ዓመፀኞች, ከእኔ ራቁ” ዓመፀኞች የሚለው የተተረጎመው( ኧኖሚያ፡ ህግ አልብነትን ነው).
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3/4 ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን[ህግን ይተላለፋል] ደግሞ ያደርጋል፥ ኃጢአትም ዓመፅ ነው።
1John 3/4 Whosoever committeth sin transgresseth also the law: for sin is the transgression of the law.
ተመልከት ጌታ እየሱስ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። ሲላቸው የአባቴን ፈቃድ ምንድን ነው ? የእ/ር ቃል ወይም የእ/ር ህግ ነው።
የማቴዎስ ወንጌል 7/23 የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች [GREEK, anomia, violation of law ህግን መተላለፍ የምትለማመዱ።]፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።” አስተዋልክ ?ዓመፀኞች ማለት ህግን መተላለፍ የሚለማመዱ ናቸው።] ህጉ ሁሉ ደግሞ የሚያዘው በክርስቶስ መመላለስ ነው ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና። ወደ ሮሜ ሰዎች 10/4 የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5/17 ዓመፃ[ unrighteousness በእ/ር ፊት በትክክል አለመቆም] ሁሉ ኃጢአት[ ህግን መተላለፍ ነው] ነው፥ ሞትም የማይገባው ኃጢአት አለ።
1John 5/17 All unrighteousness[wrong standing befor God] is sin: and there is a sin not unto death.
Righteousness is right standing befor God ጽድቅ በእ/ር ፊት በትክክል መቆም ከሆነ በእ/ር ፊት ትክክል የምንሆነው በክርስቶስ ብቻ ነው። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1/30-31 ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።
የብዙ ሰዎች ጸሎት ስለ ሌሎች ፍላጎቶች በመጸለይ ላይ ያተኮረ ነው። “ ወደ ሞት የሚያመጣ ኃጢአት” ካልሠሩ በቀር ማለትም ወደ ሞት ቅጣት ብይን የሚመራውን ኃጢአት ካልሠሩ በስተቀር ይህ የምህረት ጸሎት ሊፈቀድ እና የሚያስፈልግ ነው ይለናል ዮሐንስ ፡
የመንግሥተ ሰማይን ምስጢር የተረዳ ከከበረ ሀብቱ ክምችት አዲሱንም አሮጌውንም የሚያወጣ ባለንብረት ይመስላል ከቀደመውም መዘን ብናይ መልካም ነው እንታገዛለንና። ኢየሱስ፣ “ይህ ሁሉ ገብቷችኋል?” አላቸው። እነርሱም፣ “አዎን” አሉት።እርሱም፣ “ስለዚህም የመንግሥተ ሰማይን ምስጢር የተረዳ ማንኛውም ጸሐፊ [የጥንት መዝገብ ጸሐፊ፡ ለምሳሌ እንደ በነህምያ ግዜ ጸሐፊውም በካህኑም በዕዝራ በዘመን ነበረ።]፣ ከከበረ ሀብቱ ክምችት አዲሱንም አሮጌውንም የሚያወጣ ባለንብረት ይመስላል” አላቸው። የማቴዎስ ወንጌል 13፡52
እስከ ሞት ኃጢአት የሚለው ትርጉም በጣም ግልጽ ነው ፡፡ በህጉ ለሞት የማያደርሱ ኃጢአቶች አሉ ፣ ነገር ግን እስከ ሞት የሚያደርሱ የኃጢአት ባህርይ ያላቸውን ድርጊቶች በግልጽ ያመለክታል።
በሌላ አገላለጽ ፣ ዮሐንስ የሕጉ ተማሪ እንደመሆኑ በሕጉ ውስጥ የሞት ፍርድ በወንጀለኛው ላይ እንዲፈጸም የሚያስገድድ ህጉ ውስጥ አረመኔ አረመኔ የሆኑ ብዙ ኃጢአቶች መኖራቸውን ያውቅ ነበር። ለምሳሌ ቅድመ-ማሰላሰል የነፍስ ግድያ pre-meditated murder፣ ከእንሣ ጋር የግብረ-ሥጋ ግንኙነት bestiality [በሰው እና በእንስሳ መካከል የሚደረግ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት።]፣ ግብረ-ሰዶማዊነት homosexual relations፣ ጠለፋ kidnapping ፣ ምንዝር adultery፣ ስድብ blasphemy [ስለ እግዚአብሔር ወይም ስለ ቅዱስ ነገሮች ክፉ የመናገር ድርጊት ወይም ጥፋት ጸያፍ ንግግር።]እና ሌሎችም በዚያ ውስጥ ያሉ ድርጊቶች ፡፡ መልሶ ለምህረት እድል እንዲያገኙ ማካካሻ መንገድ በህጉ ውስጥ አይፈቀድም። እንደዚህም ሆኖ እንዲህ ባሉ ጉዳዮች ላይ, ተጠቂ ሰለባዎች የመማር መብቶችን ተጠቅመው ከሕግ በታች የወደቁትን በምህረት ከራሩ ተጠቂዎች ይቅር ለማለት ወይም ቅጣት እንዲቀነስ ውስን መብት ህጉ ይሰጣቸዋል።
ቃየን አልተገደለም ነገር ግን ወንድሙን በመግደሉ ምድርን ባረሰ ጊዜ ኃይልዋን እንዳትሰጠው፤ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ እንዲሆን እ/ር በየነበት። ( ዘፍ. 4፡12 ) ፣ ዮሴፍ ወንድሞቹ አፍነው ስለሰረቁት ይቅር ብሎዋል ( ዘፍ. 50 16-21 ) ፣ የዳዊት በሰራው የገዛ ኃጢአቱ በልጁ ላይ የሞት ቅጣት ተከፍሏል ( 2 ሳሙ 12:13 -14 ) ሆሴዕ አመንዝራዋን ሚስቱን ይቅር አላት ( ሆሴዕ 3 1-3 ) ፣ እናም ኢየሱስ የሰቀሉትን ሰዎች ይቅር ብሎታል ( ሉቃስ 23:34 ) ፡፡
በመጨረሻው ሁኔታ ፣ ይቅር ሊባል የማይችለው ኃጢያት ምን ያህል ታላቅ ነው? ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት ሁሉ ዋጋ ከፍሎለታል ( 1 ዮሐ 2፡2 )። በዚህ ረገድ ለየት ያሉ ሁኔታዎች አሉ? የኢዮቤልዩ ሕግ እንኳ ሳይቀር በፀጋው ብዛት ብቻ ሊሰርዝ ወይም ሊሸፍነው የማይችል ዕዳን አለ?
በጠቅላላ የእግዚአብሔር ትልም ወይም ዕቅድ ውስጥ ይቅር የማይባል ትልቅ ኃጢአት የለም ስለሆነም ኃጢያተኛው በመጨረሻ እንደ ፍጥረት አካል ሁሉ መታረቅ እና መታደስ ውስጥ የተካተተ ነው ( ቆላ 1፡20 እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና። ) “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡10 በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው፡፡” እ/ር አሰበ ማለት ሆነ ማለት መሆኑን ልጆቹ እንውቃለን። የሁሉም ነገር መታረቅን በሚናገርበት ጊዜ ጳውሎስ ቅድመ ሁኔታ አልዘረዘረም፡፡ ግን ለጊዜ ገደቦች በተጋለጠው ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ፣ ብዙ ኃጢአተኞች ጽድቅን ይማሩ ዘንድ ይፈረድባቸዋል ፣ እዚህም በምድርም ሆነ በታላቁ የፍርድ ቀን ውስጥ መጻሕፍት ብዙውን ጊዜ የዘላለም ሳይሆን የዘመናት ionion ፍርድ ብለው እንደሚያስቀምጡት ለእነዚህ ሁሉ ፍርዶች ለጊዜው ቢሆን ተገዥ ናቸው ፡፡
ሞት የሚገባቸውን ሃጥያቶች ለፈጸማቸው ኃጢአት የምህረት ጸሎትን በተመለከተ ሐዋርያው በተናገረው ወቅት በዚህ ደረጃ ላይ ያለውን አቅዋም ማሳየቱ ነበር ፡፡ በሌላ አገላለጽ አንዳንዶች የሞት ቅጣቱን ለመቀበል ወደ ፍርድ መቅረብ አለባቸው ፣ እናም ለእነዚያ ሰዎች መለመን የለብን የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም ላይሆን ይችላል በሚል መሃከለኛ ሃሳቡን ያስቀምጣል፡፡
ቢሆንም ፣ ዮሐንስ ስለዚህ ጉዳይ በተወሰነ ደረጃ ማቅማማት አሳይታል ፡፡ ዮሐንስ በቃላቱ ውስጥ በጣም ተጠብቆ እንዲህ ዓይነቱን ጸሎት በቀጥታ በደፈናው አይከለክልም።ግን “ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም።” ማለቱን አናያለን፡፡ በመጨረሻ ፣ እንደ አንድ የጸሎት ዋና ዓላማ አንድ ሰው እንደ እርሱ ፈቃድ መጸለይ እንዲችል የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈለግ አለበት ፡፡ እግዚአብሔር ፈቃዱን ሲገልጥ ምን ማድረግ እንዳለብን እናውቃለን ፡፡ ስለሆነም ዮሐንስ እንዲህ ዓይነቱን ምልጃ ሙሉ በሙሉ ለማገድ ፈቃደኛ አልሆነም ፡፡
በተጨማሪም ትኩረት መስጠት ያለብን ሓዋርያው ዮሐንስ እየተናገረ ያለው ለማያምኑ ሳይሆን ለአማኞች መሆኑን መዘንጋት የለብንም ፡፡ ስለዚህ ጸሎቱ ለማያምኑ “ኃጢአት ለሞት sin unto death” እንዲነሳ መተግበር አንችልም ስለሆነም ለአማኞች ብቻ መጸለይ አለብን ፡፡ በቁጥር 16 ላይ ዮሐንስ እንዲህ ብሏል ፣ “ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፡፡” ይህ የሁለተኛው ነጥቡ ዐውደ-ጽሑፍ አማኞች ሳይቀሩ “ወደ ሞት የሚያደርስ ኃጢአት አለ There is a sin leading to death ” ሊሰሩ እንደሚችሉ የሚል ነው ፡፡ ምንም እንካን ነብይ የነበረ የእ/ር መንፈስ ያደረበት ንጉስ ዳዊት ቢሆንም ራሱ በፈጸመው በመግደል እና ዝሙት ስራው እንዲህ ዓይነት ምሳሌ ይሰጠናል ፡፡
ሌላው “ማርቆ3/29 መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ግን “የዘልአለም” ሃጥያት ይሆንበታል እንጂ አይሰረይለትም” የሚለው የተሳሳተ አመለካከት አጥርተን ብንቀጥል መልካም ነው። ከዚህ የተሳሳተ ትርጉም የተነሳ የተሳሳተ ጽንሰ ሃሳብ ተወልደዋል። ለዘልአለም ይቅር የማይባል ሃጥያት አለ ብለን እንድናስብ አድርጎን ነበር። ነገር ግን የቃሉ ፍቺ በትክክል እንዲያቀብል አድርገው ከተረጎሙት ከጥቂት የእንግሊዝኛም ትርጉሞች መካከል Emp hatic Diaglott የተባለው ትርጉም ትክክለኛውን ትርጉምi እዲህ ያስቀምጠዋል። “Whoever may blasphemy the Holy Spirit no forgiveness to the age but is exposed to anian lasting judgment mar3/29” “መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ “ለዘመኑ” ይቅር አይባልም። ነገር ግን ”ለዘመኑ“ ፍርድ ይጋለጣል።“ እንደ ምናስተውለው ይቅር የማይባለው ለፍርድ የሚጋለጠው ለዘመኑ ፍርድ እንጂ ለዘልአለም ፍርድ አይደለም። በማትዮስ 12/32 ያለው ደግሞ እንዲህ ተብሎ ተተርጉመዋል ”በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ ”አለም“ ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም። አለም የሚለው ቃል ከግሪኩaion ማለትም ዘመን age ተብሎ መተርጎም ከነበረበት ቃል የመጣ ነው። ቃሉ መተርጎም የነበረበት “መንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ “ዘመን” ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም” ነው። ጌታ እየሱስ የተወለደው በህግ ዘመን ስለ ነበር በዚህ ዘመንም ቢሆን ማለቱ የህግን ዘመን ለማሳየት ሲሆን በሚመጣው ዘመን ቢሆን ሲል ደግሞ አሁን እኛ ያለንበትን የፀጋውን ዘመን ማለቱ ነው። ይህን ካስተዋልን ስለ ዘመንና ስለ ዘልአለም ያለውን ብዥታ ያጠራልናል። በግሪክ aion(ሰዋሰው noun) በግልጽ “ዘመን ወይም ያልተወሰነ ክፍለ ጊዜ ነው an age or an indefinite period of time, Young’s Concordance” እግዚአብሔር ይወድሃል/ሻል። የዮሐንስ ወንጌል 13፡1 ኢየሱስም በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው። ወንድም ቢኒ።
Willy Mac የBinyam TAን መልስ የምትረዱ ሰዎች እስኪ በራሳችሁ ቋንቋ (አገላለጽ) ምን ብሎ እየመለሰ እንደሆነ አስረዱኝ:: በተለይ like የምታደርጉ ተከታዮች like የምታደጉት እየገባችሁ ይሆናል ብዬ ስለምገምት::😃1Delete or hide this
- Bele Melaku Willy Mac ሳይገባቸው ነው ብለህ አስበህ ነው!?Delete or hide this
- Bele Melaku Willy Mac ፍርድ ነው ።ለሰራው ስራ ፍርድ ሊቀበል ይገባል ነው ።ይሄ ጉዳይ ዘላለማዊ ቅጣት እንደሆነ አያመለክትም ።ንጉስ ዳዊት እንዳለው እንደዛ አይነት ሀጢአት ለሰራ ሰው ሞት ይገባዋል እንዳለ ግን ሃጢአቱን የሰራው ንጉስ ዳዊት አልተፈረደበትም።ነገር ግን ሞት የሚገባው ሃጢአት የሰሩ ሰዎች የዘመኑ ፍርድ ወይም ቅጣት ይገባቸዋልና ስለነሱ ጰልዩ አልልም ነው ያለው።
በአለማዊ ህግም ቢሆን እንኳን ህጉን የተላለፉ ሰዎች የቅጣታቸው አይነት የተለያዬ መሆኑ ግልጽ ነው ።Delete or hide this - Willy Mac Bele Melaku እና ፍርድ የማይገባው ኃጢአት አለ ማለት ነው?
እና ፍርድ የማይገባው ኃጢአት አለ ማለት ነው?
ንጉስ ዳዊት አልተፈረደበትም ያለው ማነው?…See MoreDelete or hide this - Bele Melaku Willy Mac ጥሩ ነው ዞሮ የዘመኑ ፍርድ አግኝቶታል ።ዋናው ቅጣቱ ዘላለማዊ አለመሆኑን መገንዘብ መቻላችን ነው ።ሞት የሚገባው ሃጢአት የሃጢአቱን ዋጋ መቀበልን ያሳያል!
- Bele Melaku ሸር ስላደረከው ደስ ብሎኛል አመሰግናለሁ ቢኒ ወንድሜ! ይሄ ጥያቄ እኔና ጓደኞቸን አወዛግቦን ነበር አሁን ሰፊ ቴንታኔ አግኝቻለሁ !
- Binyam TA All such judgment are by nature correctional to learn righteousness, “For when thy judgments are in the earth, the inhabitants of the world will learn righteousness. Isa 26:9” however, judgment is subject to time, for the Scripture speaks often of aionian[age-abiding] judgment, or “age-abiding judgment.” Those Son’s of God who do not understand that ages have limits, or That in the dispensation of the fulness of times God will gather together in one all things in Christ, both which are in heaven, and which are on earth; even in him that is to say Creation Jubilee is the final act of God to the ages, It’s understandable they cannot conceive the nature of the judgment and anything beyond a brutal never-ending judgment have no purpose or goal to learn righteousness. That is why they do not comprehend the restoration of all things. Acts 3:21 The times of restitution of all things. Bro. Bini.