በቅድሚያ መርሳት የሌለብን በማያምን ሁሉ በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበት በፍርድ ስር እየኖረ ነው። ዮሐንስ ወንጌል 3፡18 በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ፣ አሁኑኑ ተፈርዶበታል።


Binyam TA

December 3, 2019 ·

ከውይይት የተጠቀሰ፡ Peace be unto you Bro. Willy Mac በቅድሚያ መርሳት የሌለብን በማያምን ሁሉ በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበት በፍርድ ስር እየኖረ ነው። ዮሐንስ ወንጌል 3፡18 በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ፣ አሁኑኑ ተፈርዶበታል። but he that believeth not is condemned[Greek፡ to try, condemn, punish:–avenge, conclude, condemn,damn,] already።
የዘላለም ሕይወት ስጦታ ነው። ክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ስጦታና የዘላለም ሕይወት ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 6:23 የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው። Rom 6:23 For the wages of sin is death; but the gift of God is eternal life through Jesus Christ our Lord.
የኃጢአት “ደሞዝ” ምንድ ነው? ስለ ኃጢአት ስናስብ “ስጦታ” ብሎ ነገር የለምውም ለኃጢአት ያለው “ደሞዝ” ሲሆን ያም “ሞት” ብቻ ነው። ስለዚህ እንደቃሉ የኃጢአት ደሞዝ ምንድን ነው? «ዘላለማዊ ስቃይ በሲኦል?» ወይስ “ሞት?” እነሆ እንደምናነበው “የኃጢአት ዋጋ ወይም ደሞዝ ሞት ነው” በሲኦል ውስጥ ዘላለማዊ የስቃይ ህይወት አይደለም። አንድ ሰው “ዘለአለማዊ ህይወት” የሚያገኘው ከየት ነው? “ከእግዚአብሔር ስጦታ ከሆነው ከጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ” ነው.። የእግዚአብሔር ስጦታ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የዮሐንስ ወንጌል 4/10 ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት።
የዮሐንስ ወንጌል 17/3 እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። የእግዚአብሔር ፍቅር ከመንፈስህ ጋር ይሁን! I have always said: “The whole scripture is one giant spiritual parable book.”
what I’m trying to say is virtually nothing is a literal teaching, but it’s all spiritual teaching. From the opening the scripture statements concerning ” And God said, Let us make [Hebrew :be making, or making[ man in Our [spiritual] Image” to “And whosoever will [desires] let him take the water of [spiritual] life freely,” And the Spirit and the bride say, “Come!” And the one hearing, let him say, “Come!” And the one thirsting let him come; the one desiring, let him take freely the water of life. The Lord says: I Jesus have sent mine angel[messenger] to testify unto you these things in the churches. the Churches has not a clue as to what is being spoken of by the messenger Jesus thy think it’s literal but it’s all spiritual teaching. Hence, the doctrines of ancient Egyptian have replaced the Truths of God’s Word. The result is seen in the Churches teaching that God’s divine first plan to man failed utterly, and His divine plan B doesn’t seem to be fairing much better than the first one. The whole world form Adam to now is going to hell in a handbasket to suffer for all eternity in agony, and there is nothing that poor God can do to change it or correct it or save humanity. What a carnal. Any simple-minded can figure out this a Perfect God all powerful, all knowing, all loving, and all wise all-sufficient, all good, timeless, all of everything does not create eternal failings plane. Even man plan wisely, Jesus says “ For which of you, intending to build a tower, sitteth not down first, and counteth the cost, whether he have sufficient to finish it? Lest haply, after he hath laid the foundation, and is not able to finish it, all that behold it begin to mock him, Saying, This man began to build, and was not able to finish. Luke 14:28”
It may be hard to grasp the way God do things hoe he set up the evils of this modern world are exactly where God foreordained them to be as He attended how the creature was made subject to vanity, not willingly, but by reason of him God. All is heading for a perfect and flawless and marvelous eternal destiny. All the creature itself is gone be delivered from the bondage of corruption into the glorious liberty of the children of God “None of the wicked shall understand; but the wise shall understand” (Dan. 12:10). Bro. Bini.what I’m trying to say5Demis Nida, Hailegiorgis Tefera and 3 others9 Comments2 Shares

Willy Mac ስለዚህ በራሱ ማመን ካልቻለ እግዚአብሔር እስከሚያሳምነው መጠበቅ እንጂ ሌላ ምን ሊያድርግ ይችላል::
ተኝቶ ፍርዱን መጠበቅ? 🤔

Binyam TA ያልከው በከፊል እውነት ነው ሁሉ እውነት እንዲሆን ግ ን የእ/ር ቃል በሙላት ሊኖረን የሚገባው ለዚህ ነው። “43 ኢየሱስ መለሰ አላቸውም፦ እርስ በርሳችሁ አታንጐራጕሩ።44 የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።” “ደግሞ፦ ስለዚህ አልኋችሁ፥ ከአብ የተሰጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም አለ። የዮሐንስ ወንጌል 6፡65”#ማሳመን#የእግዚአብሔር#ሥራ ነው ። “የዮሐንስ ወንጌል 6:29 ኢየሱስ መልሶ። ይህ #የእግዚአብሔር #ሥራ እርሱ በላከው #እንድታምኑ ነው አላቸው።” John 6፡29 Jesus answered and said unto them, This is the #work of #God, that ye #believe on #him whom he hath sent.
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡9 ልጆቹ መንፈስ ከሆነው አባታችን ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነን።

#አብ#ካልሳበው ወደ ጌታ እየሱስ አንተን እኔን ጨምሮ ማንም መምጣት አይችልም። “የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 6 :44 የላከኝ አብ ከሳበው #በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥”
እኛ የዳነው “በእምነታችን በኩል በጸጋ ነው” (ኤፌ 2 8), ነገር ግን ከእግዚአብሄር እስካልተሰጠን ድረስ እምነት የእኛ አይደለም. ሮሜ. 12: 4, “እግዚአብሔር ለእያንዳንዱም የእምነትን መጠና አካፈለው ለገሰው” እግዚአብሔር ለእኛ እምነት ከሰጠን በኋላ የእኛ ይሆናል! በጣም ቆንጆና ቀላል ሆኖ ልንረዳው ከምንችለው በላይ ባለመፃፉ ደስ ይላል።
‘ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ መጀመሪያ በኵራት የሆነው ክርስቶስ፣ ከዚያም በኋላ እርሱ ሲመጣ የክርስቶስ የሆኑት። ‘ 1 ቆሮንቶስ 15:22-23
አዳም ሁሉን ወደ ሃጥያት ይዞ ለመውደቅ አቅም እንደ ነበረው ሁሉ ክርስቶስ ይበልጡኑ ሁሉን ወደ ጽድቅ ይዞ ሊነሳ የበለጠ ሃይል አለው። ‘እኔ ግን ከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሰውን #ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ[ እጎትታለሁ: በጡንቻ በሃይል to drag , muscular ።” ዮሐንስ12:32 #ሁሉ ወደ ራሱ ጎትቶታል ስቦታል።
አንዳንዶች የተቀላቀለ ጥያቄ ያቀርባሉ ሁሉም ድነትን ተቀብሎ ከሆነ ምስክር መሆንና ወንጌልን መስበክ ለምን አስፈለገ? ይላሉ። በተጨማሪም እ/ር ሁሉን የሚያድን ከሆነና ሲኦልም ሞትም በእሳት ባህር የሚደመስሰው ከሆነ ለምን እናመልከዋለን እንደልባችን አንሆንም የሚሉ መተላለፍን በዋንጫ ለመጨለጥ የሚናፍቁም አሉ። ይህ የሚያሳየው እ/ርን የሚከተሉት ፍርድና ሲኦልን ፈርተው እንጂ ለእ/ር ፍቅር ስላላቸው እንዳልሆነ ከልባቸው የተገለጠው ሰልፍ ያሳያል። በብሉይ ኪዳን የታቦቱ ማደርያ ድንካን በ16 የብር ችካሎች ተወጥሮ የጸና ከመሆኑ የተነሳ የመጣ ነፋስ አይነቀንቀውም ነበር። የአዲስ ኪዳን ማደርያ ድንካኑም የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ ሲለን sixteen characteristics of love እያሳያን ነው። በ16 የፍቅር ፍሬዎች ወይም ችካሎች የጸና ሊሆን ይገባል። An overcomer Son may possibly go through life without demonstrating or manifesting the gifts of the Spirit although this is not likely to be true or to happen but love is absolutely indispensable it’s absolutely necessary for Sons.

1ፍቅር ይታገሣል፥ 2ፍቅር ቸርነትንም ያደርጋል፤ 3ፍቅር አይቀናም፤ 4ፍቅር አይመካም፥ ወይም አይታበይም፤
5ፍቅር የማይገባውን አያደርግም[ጋጠ ወጥ አይደለም]፥ 6ፍቅር የራሱንም አይፈልግም፥ 7ፍቅር አይበሳጭም፥ 8ፍቅር በደልን አይቆጥርም፤ 9ፍቅር ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል 10ፍቅር ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ 12ፍቅር ሁሉን ይታገሣል፥ 13ፍቅር ሁሉን ያምናል፥ 14ፍቅር ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ 15ፍቅር በሁሉ ይጸናል።16ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤
ወደ ተለመደው የደህንነት ጥያቄ ስንመለስ እያንዳንዱ በራሱ ተራ ስለሚድን ማለትም ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ተራውን ስለማናውቅ ወንጌልን እንሰብካለን።ለሁሉም ሰዎች የእግዚአብሔር ፍቅር ይሰበካል ይታወጃል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፤ የእውነትን ቃል በቅንነት ማስተዋልና መለየት፤ እውነትን በፍቅር ማስተማር፤ በክርስቶስ ተቀባይነትን፤ እና ይቅርታን ለማድረስ እንጥራለን! የእግዚአብሄር ትግስት ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ እንደሆነ እናውቃለንና።
አሁንም አስተውል ሃጣያተኛው በራሱ ንስሃ ሊገባ አይችልም እ/ር ካልሰጠው በቀር። ለሕይወት የሚሆን ንስሐን የሚሰጠው እ/ር ብቻ ነው። እንግዲህ ትምክህትህ ከየት ነው የሚመካ በእ/ር ይመካ። “የሐዋርያት ሥራ 11፡18 ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና፦ እንኪያስ እግዚአብሔር #ለአሕዛብ ደግሞ #ለሕይወት የሚሆን #ንስሐን#ሰጣቸው እያሉ #እግዚአብሔርን አከበሩ።” በወንድም ቢኒ።

Willy MacBinyam TA ስለሰበክህ ተራውን መቀየር ትችላለህ እንዴ?

Binyam TAWilly Mac የመኪና ማርሽ እንደሚቀየር? ወይስ እንደ ተራ አስጠባቂ አብ ያልሳበውን ወረፋ ልታስቀድመው ነው ብራዘር? አንተ ተጨንቀህ በቁመትህ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የማትችል
እንግዲህ ትንሹን ነገር ስንኳ የማትችል ከሆንክ፥ ስለ ምን በሌላ ትጨነቃለህ? አብን ተክተህ ያለጊዜው ልትስበው? አብ ከሳበው እውነት ነው።

Willy MacBinyam TA ስለዚህ መስበክህ ጥቅሙ ወይም ፋይዳው ምንድነው?

ጥያቄ/መልስ፡ ጥያቄ፡Willy Mac ወንጌልን አንሰብክም አንቀበልም እንቢ ብንልስ? ከተወሰነው ውጪ መሆን አይቻል? #መልስ፤ እምቢ? ወንድማችን የነብዩ ዮናስ ቅባት በላይ እላይህ ልታነሳሳ ነው? ሃሳቡን እንደማትስተው እ/ርን ስለአንተ አምነዋለሁ። “2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡11 በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና።” ዮናስ ነነዌን ለምን አልገለበጥካትም አንተ ድሮውንም ብዮ ነበር መሀሪ መሆንህን እውቅ ነበር ብሎ እንደተቆጣ እና እንደኮበለለው ዮናስ ልንሆን አይገባም። ዮናስ እውነተኛ ነብይ ነበረ። ቃል ስለመጣለት ጥፋትን ያዘለ ፍርድ ለህዝቡ ሁሉ ተነበየ በዛው አንደበቱ ምህረትን ትሰብካታለህ ሲባል እምቢ ቡራ ከረዮ አለ። ወደ ሲኦል አውርዶት ሰበረው እንደፈረስ ተገርቶ ፈቃዱ ከተሰበረ ቡሃላ የእ/ር ፈቃድ ህያው ሆኖ ጸና። ከውቅያኖስ መካከል ከባህር አውሬ አሳ ነብሪ ሆድ ወስዶ ዘጋው። ከሲኦል ሆኜ እፀልያለሁ እስኪያስብለው ድረስ ከእግዚአብሔር ሀሳብ ጋር ለመታረቅ ጭንቅ ሆነበት ነበርና። ወደርሱ የመጣችው ፍርድ ግን ፅድቅን ተማረባት። እግዚአብሔር አጠፉለሁ ሲል እምራለሁ ፅድቅን አስተምራለሁ ማለቱን አስተውለዋልና ነፍሱ እኔን ሀሰተኛ ነብይ ሊያስብል ምህረትን አውጅ ይለኛልን? ብሎ ተቆጣ። እኛም በዮናስ ዱካ እንዳንገኝ እግዚአብሔርን እንፍራ።
እግዚአብሔር እውነት ነው ፍቅር ነው። ፍቅርን ብታሰቃዮት ግን በእውነት አምላካችን የሚባል እሳት ነው። ደግሜም ሰልሼም እላለሁ ወንጌል የሚሰበከው ለነፃነት መልካም የምስራች ስለ ሆነ ነው እንጂ የሆረር ፊልም ይመስል ለፍርሀት ባርነት አይደለም። አብ ለሳባቸው ሁሉ መዳናቸውን ለሚሰሙት መልካም ነውና። ምሳሌ25:25 የቀዘቀዘ ውኃ ለተጠማች ነፍስ ደስ እንደሚያሰኝ፥ ከሩቅ አገር የመጣ #መልካም#ምስራች እንዲሁ ነው።
ወንጌል ከመሰረቱ መልካም ዜና ነው። ምንም ኩፉ ዜና የለበትም!ወንጌል ‘gospel’ የሚለው ቃል ኢቫንጀል ከግሪክ (‘evangel’ from the Greek) ቃል የተተሮገመ ሲሆን፡ ይህም ከሁለት የቃላት ውህድ የተገኘ ነው። መልካም እና መልእክት(‘eu’ – good, and ‘angelion’ – message). ስለዚህ ወንጌሉ በቀላል ቋንቋ መልካም መልእክት ማለት ነው። ሌላው ምሳሌ ለትምህርታችን የተጻፈው ህይወት የኢምተኛው የሳኦል ህይወት ነው። “በጽናትና ቅዱሳት መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ እንዲኖረን፣ ቀደም ብሎ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና።ወደ ሮሜ ሰዎች 15፡4” ሃዋሪያው ጳውሎስ የክርስቶስ ተቃዋሚ እምቢተኛ በዛ ዘመን ማን ነበረጌታ ግ ን ጳውሎስ ዕቃ ነው ብሎታል የእቃ እምቢተኝነት አስበው እስቲ። ። የሐዋርያት ሥራ 9፡15 ጌታም፦ ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ #ዕቃ ነውና ሂድ፤ ይህን እንመልከት “ወደ ሮሜ ሰዎች 9/16 እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ። Rom 9/16 So then it is not of him that willeth, nor of him that runneth, but of God that sheweth mercy.” እንግዲህ ምሕረት ለወደደ willeth ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚ ምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ። but of God that sheweth mercy.” እንዴ ምንድ ነው ነገሩ እ/ር ከፈቃዳቸው ውጪ ሰዎችን ሊያድን ይችላል? ሊነሳብን ይችላል። መልሱ አይደለም ነው። እንደዛ ማድረግ አያስፈልገውም። ሰው ሁሉ እ/ር እራሱን ሲገልጥለት መቶ በመቶ ፈቃደኛ ይሆናልና። መንፈሳዊ እውርነቱ ሲበራ ወይም የዶንቆሮው ጆሮ ሲከፈት ለሙታንም ህይወትን ሲሰጠው ለከንቱነት የተገዛው ተፈጥራዊው ማንነት ፋንታ መንፈሳዊ አእምሮ ሲሰጠው ሲመለስለት ሁሉ የሰማይ አምላክን ያመሰግናል።
ሓዋርያው ጳውሎስ ከሃጥያተኞች ሁሉ ዋንኛ የምሆን እኔን የማረው አቅሙን ለማሳየት ምሳሌውን ለማሳየት ነው አላለንምን? ጌታ ፈቃዱን ሳይጠይቅ በታቅ ብርሃን፡ ጳውሎስ ላይ አልወደቀብትምን ታድያ ምንም እንካ ሳኦል[ጳውሎስ] ከሃጥያተኞች ሁሉ ዋንኛ ቢሆንም ጌታን ተቀበል ብሎ ፈቃዱን ጠየቀውን? ትእይንቱን እናስተውል እ/ር እራሱን ሲገልጥለት ሃጥያተኛው ሳኦል[ጳውሎስ] መቶ በመቶ ፈቃደኛ ሆኖ እያለቀሰ “ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ!!!” በቃ ፍጥረትም እዲሁ ነው እ/ር እራሱን ሲገልጥለት መቶ በመቶ ፈቃደኛ ይሆናል። ማወቅ ያለብን የእ/ር ታላቅ አሰራር መካከል “ጌታ ጌታየን ሁሉን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው” ማለትም ከእግሩ ስር የሚያመለክተው ሁሉን ከስልጣኑ ስር እስኪ ያደርግለት ድረስ ማለት ነው የሁሉ ትርጉም ደግሞ ሁሉ ነው።
ፍጥረት በፈቃዱ አልወደቀም በፈቃዱም አይድንም ከመንፈሳዊ ሞት የሚያድን እግዚአብሔር ብቻ ነው። ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ እግዚአብሔር ስላስገዛው ነው እንጂ በራሱ ፈቃድ ወዶ አይደለም፤ እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን ለእግዚአብሔር ባለመታዘዝ ሚስጥር ዘግቶታልና።
አሁን ተስፋው ፍጥረት ራሱ ከጥፋት ባርነት ነፃ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው። ለዚህም ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።ከሰው ነፃ ፈቃድ የተነሳ እ/ር ሁሉን ማዳን አይችልም የሚለው ሃሳብ ከእ/ር አቅም ጋር ሲነፃፀር ኢምንት ነው የሚጋጭም ነው። እ/ር ለሰው ፈቃድ ጌታዋ መሆኑን በየዘመናቱየነገስታትን የህዝብን ልብ እንደወንዝ ወዳሻው ሲመራው ሃይሉን አሳይተዋል። በነፈርሆን ልብ ላይ ፡ በነሊድያ ልብ ላይ፤ በናቡክደኖፆር ልብ ላይ በሌሎችም የሰረው መንፈሳዊ ትያትር ልኡል ወይም ፈጽሞ የበላይ ለመሆኑ በቂ ማስረጃ ነው።
“1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/3 ….በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ። 1Cor 12/3 ….that no man can say that Jesus is the Lord, but by the Holy Ghost” እናስተውል በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቆናል አሁን ጠላቶቹ የሆኑት አድስዋቸው ከክርስቶስ ስልጣን ስር ሲጠቀለሉ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ሆነው ኢየሱስ ጌታ ነው እያሉ ለበጉ ክብርን ተንበርክከው ይሰጣሉ። “የዮሐንስ ራእይ 5/13 በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ። Rev 5/13 And every creature which is in heaven, and on the earth, and under the earth, and such as are in the sea, and all that are in them, heard I saying, Blessing, and honour, and glory, and power, be unto him that sitteth upon the throne, and unto the Lamb for ever and ever.” እንግዲህ የመጨረሻው ጠላይ ሞት ከነ መውጊያው ከሃጥያት ጭምር ሲደመሰስ እ/ርም እራሱን ለፍጡራኑ ሲገልጥለት መቶ በመቶ ፈቃደኛ ሆኖ እያለቀሰ በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በመንፈስ ቅዱስም ሆነው በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ይላሉ።። አሜን! ወንድም ቢኒ።

Willy Mac ዮናስ እምቢ እንዲል ያደርገው እራሱ እግዚአብሔር አይደል እንዴ?
ስለዚህ መልሶ ደግሞ እሺ እንዲል አደረገው:: እሺ ቢልም እኮ እሺ እንዲል ያደርገው እግዚአብሔር ነው ማለትህ ይቀራል?
ታዲያ እንደናንተ ፍልስፍና ትምህርትም በራሱኮ ምንም ጥቅም የለውም::
ምክንያቱም ሌላው እንዲህ ስለሆነ እንዲህ እሆናለሁ: ወይም በፊት ሰው እንዲህ በማለቱ ወይም እንዲህ በማድረጉ ስለተቀጣ ወይም መልካም ስለተደረገለት: እኔም እንዲህ ባደርግ ወይም እንዲህ ባላዳረግ እንዲህ እሆናለሁ እንዲህ ይሆንልኛል: እያሉ ትምህርት መውሰድ ትርጉም አይኖረውም:: በተባለው መልክ አሉም አላሉም ወይም በተባለው መልክ አደረጉም አላደረጉም የሚቀይረው ነገር የለም:: ለዚህ ነው በእናንተ አስተሳሰብ መሠረት የዮናስም መታዘዝ ወይም አለመታዘዝ ምንም ያመጣው ለውጥ የለም የምለው::

Binyam TAWilly Mac. እግዚአብሔር ሉኡል መሆኑን ለማመን ዘግይተህም ቢሆን እሩቅ አይደለህም። የእግዚአብሔርን ቃል የፍልስፍና አልከው የእግዚአብሔር ቃል አልከው የእግዚአብሔርን ቃል የምታይበት state of mind ውጤት ባሻገር ስያሜ መስጠት አይችልህም። በክርስቶስ ብቻ መጋረጃው የተወሰደ ነውና።

Alemayeyhu Abebe Bini
(1 ቆሮ 2 )
————
14 ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።

15 መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም።

Hailegiorgis Tefera …እልልልልልልል…
የእግዚአብሔር ልጆች ጽሑፍ ሁልጊዜ ድንቅ ነው ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ።
ምክንያቱም
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነው ።
…እልልልልልልል…

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal