
Binyam TA
ከውይይት የተጠቀሰ: መዳን በእምነት ነው በእርግጥም እውነት ነው! ጥያቄው የሚዳንበት፡ እምነት መንፈሳዊ ንጥረ ነገሩ ምንጩ ማነው? ነው ጥያቄው። ሰው ሁሉ በአዳም ወገብ ውስጥ ሳለ ከአዳም ጋር ተባብረህ ሃጥያት ሰርተሃል የእ/ር ክብርም ጎድሎሃል።
ደግሞም በሃጥያታችሁና በበደላችሁ ሙታን ናችሁ ከተባለ ዘንዳ። ሙታን ፈቃድ አላቸውን? በእነሱ ዘንድ ዕውቀት አለን? “መጽሐፈ መክብብ 9/5 …ሙታን ግን አንዳች አያውቁም!” ወይስ የእምነት ፋብሪካው ሰው ነውን? ከየትስ መጣ ከሰው ውስጥ እንደ ድማሚት የፈነዳ ከእ/ር ያልሆነ በሰው ውስጥ ያለ ከሰው የተዘጋጀ ነውን? ወይስ ምንጩ ከእ/ር ነው? እንደ ሚጥሚጣ የሚያቃጥለው ጥያቄው ያነው።
በቅድሚያ መንፈሳዊ ሙታን እንካንስ እምነት ሊኖራቸው በቅድሚያ ከሙታን በትንሳኤው ሃይል መነሳት አለባቸው። ከሙታን የሚነሱት በእ/ር ሃይል ብቻ ነው! ከዛም ቅደም ተከተሉ ይቀጥላል። እሱ ብቻውን …ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ ነውና። “ወደ ሮሜ ሰዎች 4/16 …ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ የሚጠራ ።”
ታዲያ በኤፌሶን ያላሉት የምስራቹን ከሰሙ ቡሃላ አምነዋል አሁን በክርስቶስ ኢየሱስም ቁዱሳን ሳይባሉ ገና ሃጥአን ሳሉ መንፈሳዊ ሙታን፡ ሳሉ እምነቱን ኬት አመጡትና አመኑ? በቅድምያ ከክርስቶስ ጋር ህይወትን ሰጥቶ ከሙታን አስነሳቸው። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2-5 ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ”
“ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3/1 … ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ” “ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2-12 … ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ” እምነት በተፈጥሮው መንፈሳዊ ነው መንፈስም ነው። “2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4/13 ነገር ግን፦ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤” የእምነት መንፈስ የሚሰጥ ማነው?በእርግጥም እ/ር ነው።
“ወደ ገላትያ ሰዎች 3/2 ይህን ብቻ ከእናንተ እንድማር እወዳለሁ፤ በሕግ ሥራ ወይም ከእምነት ጋር በሆነ መስማት መንፈስን #ተቀበላችሁን? 3 እንዲህን የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁን?
5 እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ ….
ለኤፌሶን ሰዎች ሲናገር “ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥” እምነት ከእ/ር ዘንድ የተሰጠ ወይም የታደለ ነው። እምነት አንዴ የሰጠው ወይም እንደ ከረሜላ ያደለው አሁንም እራሱ እግዚአብሔር። ነው።
1ኛ “….ለቅዱሳን አንዴና ለመጨረሻ #ስ-ለ ተ-ሰ-ጠ-ው እ-ም-ነ-ት እንድትጋደሉ ለመምከር እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።”ይሁዳ 1:3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም እምነት ከራሱ ከእ/ር የተሰጠ ነው!
2ኛ በሌላ ቃል ደግሞ እንየው ብዙም ማብራራት ቃሉ አያስፈልገውው የቃሉ ስልጣን በራሱ ይናገራልና። “ወደ ሮሜ ሰዎች 12:3 እግዚአብሔር ለ-እ-ያ-ን-ዳ-ን-ዱ የ-እ-ም-ነ-ት-ን መ-ጠ-ን #እ-ን-ዳ-ካ-ፈ-ለ-ው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ።” እምነት ከእ/ር የተካፈልነው ነው!
3ኛ ጸጋውም እምነቱም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:9 ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት፥ …ያካፍለዋል።
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።” ወንድም ቢኒ።11Willy Mac, Demis Nida and 9 others8 Comments2 Shares
Tesfu Tamiru እሺ ወንድም ቢኒ እምነት ከእግዚአብሔር ነው፣ እምነት ከመስማት ነው መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል ነው ሲል መጽሐፍ ምን ማለቱ ነው!?
Binyam TA Tesfu Tamiru ሰላም ለአንተ ይሁን ወንድማችን ተስፉ፡ እውነት ነው እምነት ከመስማት ነው መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል ነው። መቸም ይገባሃል የምናወራው መንፈሳዊ ነገር ነው። ለመንፈሳው ሰው ሁሉ ነገር መንፈሳዊ ነው ለተፈጥራዊ ሰው ሁሉም ነገር ተፈጥራዊ ነው። መንፈሳዊ ማስተዋሉ ፈጣን ለሆነ ግልጽ ነው መንፈሳዊ እውቀት ለአስተዋዮች ካልሆነ ለቸልተኞች የተከለከለ ነውና በማስተዋል እንየው። “በሃጥያታችሁና በበደላችሁ #ሙታን#ነበራችሁ” የሚለው ቃል እውነት ነው? እውነት ከሆነ ሙታን መስማት ይችላሉን? አይችሉም! መንፈሳዊ ሙታን እንካንስ እምነት ሊኖራቸው በቅድሚያ ከሙታን በትንሳኤው ሃይል መነሳት አለባቸው። ከሙታን የሚነሱት በእ/ር ሃይል ብቻ ነው! ከዛም ቅደም ተከተሉ ይቀጥላል። እሱ ብቻውን …ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ ነውና ከዛም የሚሰሙም ጆሮችን የሚሰጥ እ/ር ነው። እንካን እመነት ንሰሃ እንካን ከእ/ር ካልተሰጠህ የለህም። የሐዋርያት ሥራ 11፡18 ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና፦ እንኪያስ እግዚአብሔር #ለአሕዛብ ደግሞ #ለሕይወት የሚሆን #ንስሐን#ሰጣቸው እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ።
አንተ ስታስበው ከክርስቶስ ውጭ እያለው ፍጥረታዊ ሰው በበደሉና በሀጥያቱ ከሙታን ከሆነ ከሙታን ዘንድ በፈቃድ አለን? እውቀትስ ስፍሯ አላትን? “ሙታን ግን ምንም አያውቁም” ቃሉ የሚያስተምረን ያንን እውነት ነው።
ታዲያ እንዴት ይድናሉ ለምሳሌ በተፈጥራዊው። እንካን ብናይ አልአዛር 4 ቀን በመቃብር የሞተ ሳለ ነፃ ፈቃድ የነበረውን? በፍፁም የውዱ ቃል የትንሳኤው ህይወትን ታጭቆ ቃሉ ሀይል ለብሶ ወደሱ ሲወረወር መጣ መጀመርያ ሙታን የሚነሱት በፈቃዳቸው ሳይሆን በእ/ር በሀይል ብቻ ነውና የመጣው ቃል ህይወትን ሰጠው ልቡና ሳምባውም መስራት ጀመረ በትንሳኤው ና በህይወት በሀይል አቆመው ግንዘቱንም ፍቱለት እና ይሂድ አለው።
ታድያ አልአዛር በነፃ በፈቃዱ ህይወትን ለመቀበልም ሆነ ጌታን አልቀበልም ወግድልኝ ለማለት እዚህ ላይ እውቀት ነበረው ድርሻና ሀይል ውይም ፈቃድ የነበረውን? ለመንፈሳዊ ሙታንም እንዲሁ ነው። “ሀይል የእ/ር ነው” ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለ መታዘዝ ከዘጋ ሸክላ ሰሪው ከሸክላው የላቀ ታላቅ መሆኑ በሁሉ ዘንድ ማስተዋል ይሁን።
ሸክላው ሸክላ ሰሪውን ለምን እንዲህ አድርገህ ሰራህኝ ብሎ ቢጠይቀው የስቃል እ/ርም በሰማይ ይስቃል እኔም በደስታ በተሰበሰቡት እልፍ አእላፋት ደስተኛ መልአክት ጋር ሆኜ እንደ መንፈሳዊ አባቴ እስቃለሁ። ሀይል የእ/ር ነውና በሰማይና በምድር የተወደደውን ያደርጋል የሚከለክለውም የለምና ።
እ/ር ይህንን ሞት ብሎ አይጠራውምና። እኛ ይህንን ሞት ብለን እንጠራዋለን። ይህ ግን ሞት አይደለም። አስተውሉትማ ወገኖቼ ሙውታን ሳላችሁ ህይወትን ሰጣችሁ! ሙውት ሳለሁ በክርስቶስ ህይወትን ሰጥቶኛል። ታዲያ ያ ማለት በሬሳ ሳጥን ውስጥ ታሸጌ ፅልመት በተሞላበት መቃብር ውስጥ ተቀብሬ ነበረ ማለት ነውን? ሞት ማለት አካሌ በሬሳ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ማለት አይደለም። የተቀበልኩትም ህይወት የማይበሰብስ የስጋ አካል አይደለም። አትመለከቱምን? ሰዎች ሞት ብለው የሚጠሩት ሞት አይደለም። ሰዎችም ህይወት ብለው የሚጠሩት ህይወት አይደለም። መንፈስ ቅዱስ ሲገልጥልን ብቻ የነገሮችን እውነተኛ ተፈጥሮ የጠለቀ ሚስጥራቸውን የምንገነዘበው። አንድ ሰው ከሰማይመጣ በእ/ር ፀጋም ለሰው ሁሉ ሞትን ቀመሰ ። ”
ነገሮችን ከተፈጥራዊው ሰው አንፃር ብቻ ካየናቸው እውነት እደተሰወረ ይቀመጥብናል በመንፈስ ግን እ/ር ከሚያየው አንፃር ካየናቸው እውነት አርነት ያወጣናል። ሌላ ቃል ደግሞ እንይ። “እየሱስም፥ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታኖችን ተውዋቸው። ሉቃ9/8” ማለቱ በቃሬዛው ውስጥ ያለውንም የተሸከመውንም አንድ ሙታን አላደረጋቸውምን? በርግጥም ከሰው አለም ከውሸትና ከሞት ግዛት ተኩኖሲታዩ ሉይነት አላቸው። ሁለቱም ግን ከእ/ር አለም ከእውነትና ከህይወት ግዛት ተኩኖ ሲታዩ ሙታንናቸው። የሰው ልጅም እንዲሁ በሀጥያት ምክንያት ከእ/ር ህልውና ከተባረረ ጀምሮ ያለው ኑሮ ሁሉ እንዲሁ ነው። የሚለያዩት በኮፈኑ ውስጥ ያለው የሞት ወይም የመበስበስ ኑሮ የመጨረሻው የእድገት ደረጃ ላይ በመድረሱ ግብአተ መሬቱ ሊፈፀም መድረሱ ነው። በአጭሩ ሞት ሰው ከእ/ር ጋር በመንፈስ የነበረው ህብረት የተለየበት ወይም ከህይወት ግዛት ከተባረረበት ቅፅበት ጀምሮ ያለው ጠቅላላ ሁኔታውና ማንነት ነው ። ለምሳሌ አንድ የፅጌሬዳ እንቡጥ አበባ ከግንዱ ብትቆርጡት ለአይን ሲታይ ያማረና ህያው ነው። ነገር ግን እውነታው የአበባው ዝንጣፊ ህይወትን ከሚሰጠው ከምንጩ ማለትም ከግንዱ ተቆርጦ ተለይተዋል። ከዚህ ቡሀላ ወደ መጠውለግ ፤ወደ መበስበስ ወይም ወደ ሞሞት ቁልቁል እያደገ ነው። እ/ር ያብራላችሁና በሰማይምም በምድርም እ/ር ህይወት የሚለው አንድ ብቻ ነው። እርሱም በክርስቶስ እየሱስ የሚገኘውን ህይወት ነው። ጌታችንና አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ “እኔ ህይወት ነኝ ማለቱ ሌላውን ሁሉ ሞት አያደርገውምን? እኔ እውነት ነኝ ማለቱ ደግሞ ሌላውን ውሸት ያደርገዋል ። እኔ መንገድ ነኝ ማለቱ ደግም ሌላውን ገደል ያደርገዋል።
ክብር ሁሉ ለቅዱስ ስሙ ይሁን።አሜን! ወንድም ቢኒ።
Tesfu Tamiru ወንድም ቢኒ ስለሰጠኸኝ ጥልቅ ማብራሪያ አመሠግናለሁ አሁን ተረድቻለሁ ኃይል የእግዚአብሔር ነው መንፈሳዊን ነገር ከምንጩ ከእግዚአብሔር ተነስተን ማየት አለብን Thank you again.
Willy Mac ሙታን የሚሰሩት ኃጢአት ይቆጠርባቸዋል?
ክርስቶስን ባያምኑ የማን ጥፋት ነው?
Binyam TA Peace be unto you Bro. Willy Mac በቅድሚያ መርሳት የሌለብን በማያምን ሁሉ በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበት በፍርድ ስር እየኖረ ነው። ዮሐንስ ወንጌል 3፡18 በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ፣ አሁኑኑ ተፈርዶበታል። but he that believeth not is condemned[Greek፡ to try, condemn, punish:–avenge, conclude, condemn,damn,] already።
የዘላለም ሕይወት ስጦታ ነው። ክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ስጦታና የዘላለም ሕይወት ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 6:23 የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው። Rom 6:23 For the wages of sin is death; but the gift of God is eternal life through Jesus Christ our Lord.
የኃጢአት “ደሞዝ” ምንድ ነው? ስለ ኃጢአት ስናስብ “ስጦታ” ብሎ ነገር የለምውም ለኃጢአት ያለው “ደሞዝ” ሲሆን ያም “ሞት” ብቻ ነው። ስለዚህ እንደቃሉ የኃጢአት ደሞዝ ምንድን ነው? «ዘላለማዊ ስቃይ በሲኦል?» ወይስ “ሞት?” እነሆ እንደምናነበው “የኃጢአት ዋጋ ወይም ደሞዝ ሞት ነው” በሲኦል ውስጥ ዘላለማዊ የስቃይ ህይወት አይደለም። አንድ ሰው “ዘለአለማዊ ህይወት” የሚያገኘው ከየት ነው? “ከእግዚአብሔር ስጦታ ከሆነው ከጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ” ነው.። የእግዚአብሔር ስጦታ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የዮሐንስ ወንጌል 4/10 ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት።
የዮሐንስ ወንጌል 17/3 እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። የእግዚአብሔር ፍቅር ከመንፈስህ ጋር ይሁን! I have always said: “The whole scripture is one giant spiritual parable book.”
what I’m trying to say is virtually nothing is a literal teaching, but it’s all spiritual teaching. From the opening the scripture statements concerning ” And God said, Let us make [Hebrew :be making, or making[ man in Our [spiritual] Image” to “And whosoever will [desires] let him take the water of [spiritual] life freely,” And the Spirit and the bride say, “Come!” And the one hearing, let him say, “Come!” And the one thirsting let him come; the one desiring, let him take freely the water of life. The Lord says: I Jesus have sent mine angel[messenger] to testify unto you these things in the churches. the Churches has not a clue as to what is being spoken of by the messenger Jesus thy think it’s literal but it’s all spiritual teaching. Hence, the doctrines of ancient Egyptian have replaced the Truths of God’s Word. The result is seen in the Churches teaching that God’s divine first plan to man failed utterly, and His divine plan B doesn’t seem to be fairing much better than the first one. The whole world form Adam to now is going to hell in a handbasket to suffer for all eternity in agony, and there is nothing that poor God can do to change it or correct it or save humanity. What a carnal. Any simple-minded can figure out this a Perfect God all powerful, all knowing, all loving, and all wise all-sufficient, all good, timeless, all of everything does not create eternal failings plane. Even man plan wisely, Jesus says “ For which of you, intending to build a tower, sitteth not down first, and counteth the cost, whether he have sufficient to finish it? Lest haply, after he hath laid the foundation, and is not able to finish it, all that behold it begin to mock him, Saying, This man began to build, and was not able to finish. Luke 14:28”
It may be hard to grasp the way God do things hoe he set up the evils of this modern world are exactly where God foreordained them to be as He attended how the creature was made subject to vanity, not willingly, but by reason of him God. All is heading for a perfect and flawless and marvelous eternal destiny. All the creature itself is gone be delivered from the bondage of corruption into the glorious liberty of the children of God “None of the wicked shall understand; but the wise shall understand” (Dan. 12:10). Bro. Bini.
Willy Mac የሞተ ሰው ምንም አያውቅም ብለሃል::
ስለዚህ የሞተ ሰው እንዴት ኃጢአት ይሰራል?
እንዴትስ ያምናል?
ከርስቶስ ካልቀሰቀሰው ወይም እንዲሰማ ካላደረገው አያሰማም:
እንዲያምን ካላደረገው አያምንም እስካልክ ድረስ:
ይህ የሞተ ሰው ኃጢአት መስራትም: ጽድቅ መሥራትም: ማመንም ስለማይችል በምንም ነገር ተጠያቂ አይደለም ማለት ነው::
ታዲያ ይህ ሰው ፍርዱ ሞትም ይሁን ህይወት: በራሱ ምንም ማድረግ ካልቻለ እና ለሚሆነው ነገር እራሱ ኃላፊነት የማይወስድ ወይም ተጠያቂ የማይሆን ከሆነ እንዴት ተብሎ ነው የሚፈረድበት?
Binyam TA ጥያቄ/መልስ፡ #ጥያቄ፤ Willy Mac የሞተ ሰው ምንም አያውቅም ብለሃል:: ስለዚህ የሞተ ሰው እንዴት ኃጢአት ይሰራል?
እንዴትስ ያምናል?…. #መልስ፡ሰላም፤ የመጀመርያው አዳም ለጽድቅና ለእ/ር ሞተ ለሃጥያት ግን ህያው ሆነ የሞተው ለህይወት ግዛት እንጂ ለሃጥያት ግዛት እማ ህያው ሆነዋል አእምሮውም ህይወት የነበረው ሞት ሆነ። የስጋ አይምሮ ሞት ነው፤ የመንፈስ አእምሮ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡6 (Rom 8:6 [AMP])
Now the mind of the flesh [which is sense and reason without the Holy Spirit] is death [death that comprises all the miseries arising from sin, both here and hereafter]. But the mind of the [Holy] Spirit is life and [soul] peace [both now and forever].
JMT: For the thinking (mind-set; way of thinking; disposition; understanding and inclination; the minding; the opinion; the thought) of the flesh [is] death, yet the thinking (mind-set; disposition; thought and way of thinking) of the spirit (or: the Spirit) [is] Life and Peace, የመጨረሻው፡አዳም ደግም ለሃጥያት ሞተ ‘በሞተ ጊዜ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኀጢአት ሞቶአል፤ ነገር ግን በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖራል። ‘ሮሜ 6:10 በዚህም ጽድቅን ሁሉ ፈፀመ። የመጀመርያው ሰው ሰውን ሁሉ ሐጢያተኛ አደረገ የሁለተኛው ሰው ሰውን ሁሉ አፀደቀ በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖሩ ዘንድ። “የመጀመርያው ሞት፤ ሁለተኛው ሞት እና የስጋ ሞት” ልዩነቶችን በአግባቡ ለመረዳት የሚቀጥለውን ሙሉ ሃሳብ አስተውለህ አንብብ። ተባክ። https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=2630245987061343&id=100002279031400
ጥያቄ/መልስ፡ #ጥያቄ፤ Willy Mac የሞተ ሰው ምንም አያውቅም ብለሃል:: ስለዚህ የሞተ ሰው እንዴት ኃጢአት ይሰራል?
እንዴትስ ያምናል?…. #መልስ፡ሰላም፤ የመጀመርያው አዳም ለጽድቅና ለእ/ር ሞተ ለሃጥያት ግን ህያው ሆነ የሞተው ለህይወት ግዛት እንጂ ለሃጥያት ግዛት እማ ህያው ሆነዋል አእምሮውም ህይወት የነበረው ሞት ሆነ። የስጋ አይምሮ ሞት ነው፤ የመንፈስ አእምሮ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡6 (Rom 8:6 [AMP])
Now the mind of the flesh [which is sense and reason without the Holy Spirit] is death [death that comprises all the miseries arising from sin, both here and hereafter]. But the mind of the [Holy] Spirit is life and [soul] peace [both now and forever].
JMT: For the thinking (mind-set; way of thinking; disposition; understanding and inclination; the minding; the opinion; the thought) of the flesh [is] death, yet the thinking (mind-set; disposition; thought and way of thinking) of the spirit (or: the Spirit) [is] Life and Peace, የመጨረሻው፡አዳም ደግም ለሃጥያት ሞተ ‘በሞተ ጊዜ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኀጢአት ሞቶአል፤ ነገር ግን በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖራል። ‘ሮሜ 6:10 በዚህም ጽድቅን ሁሉ ፈፀመ። የመጀመርያው ሰው ሰውን ሁሉ ሐጢያተኛ አደረገ የሁለተኛው ሰው ሰውን ሁሉ አፀደቀ በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖሩ ዘንድ። “የመጀመርያው ሞት፤ ሁለተኛው ሞት እና የስጋ ሞት” ልዩነቶችን በአግባቡ ለመረዳት የሚቀጥለውን ሙሉ ሃሳብ አስተውለህ አንብብ። ተባክ።
የሁለተኛው ሞት ሂደት ፍቺ በሰው ውስጥ / መለኮታዊ ሹኩሹኩታ
Divine Whisper ክፍል 5
(ራእይ 20 6-15) “የሁለተኛው ሞት ሂደት ፍቺ በሰው ውስጥ ” ንዑስ ክፍል ሶስት በወንድም ቢኒ።
” የዮሐንስ ራእይ 20/6 በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፥ ”
“ሁለተኛው ሞት” በአግባቡ ለመረዳት እንዲቻል የመጀመሪያ የሆነውን እና የመጀመሪያው ሞት ምክንያት ምን እንደሆነ ቢያንስ መረዳት አለብን።
አካላዊ ማንነታችን በተመለከተ ሞት ማለት በቀላሉ የሰው መንፈሱ ከስጋው መለየት ማለት ሞት ይባላል። በዚህም ምክንያት ህይወት በምድር ላይ ያከትማል ማለት ነው። ሞት ከአንድ ግዛት ወደ ሌላ ሽግግር ነው ። ከአንድ ዓለም ወደ ሌላ አንድ መንፈሳዊ ግዛት ማለፊያ ነው ። እናስተውል ለአንድ ግዛት መሞት ለሌላው ህያው መሆን ነው። “ከሥጋ ተለይተን ከጌታ ጋር መኖርን እንደምንመርጥ ርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ። to be absent from the body, is to be present with the Lord. ‘2 ቆሮንቶስ 5:8”
“….መንፈስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ፣ ፈጣሪህን አስብ። ‘ መክብብ 12:7 መደበኛ ትርጉም።” “ እንደምናስተውለው መንፈሳችን ከእግዚአብሔር የመጣ ነገር ነው ወደ እ/ርም የሚመለስ ነገረም ነው።
ይህን ካስተዋልን በተቃራኒው ከእ/ር ህይወት ለቆ የመጣው ማንነት ልክ ወደዚህ ሲቀላቀልና ወደ ምድር ሲመጣ ለህይወት ግዛት ሞቶ ለሞት ግዛት ህያው መሆን እንደጀመረ ሊሰመርበት ይገባል ይህም መንፈሳዊ ሞት የጀመረበት ቅጽበት ነው። የእግዚአብሔርን የብርሃንን ግዛት ለቆ ወደ ሞት ግዛት መግባት ያ ነው የመጀመርያው ሞት። መንፈስህም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ፣ ማለት ቀድሞውኑ ምንጭህ መንፈስህ ከእ/ር ወጥቶ የተገኘ እንደሆነ ሊስተዋል ተገቢ ነውና።
“….መንፈስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ፣ ፈጣሪህን አስብ። ‘ መክብብ 12:7 መደበኛ ትርጉም።” ምክንያቱም ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በመንፈስ በክርስቶስ ኢየሱስ “ውስጥ” የተፈጠርን [created in(within) Christ Jesus ] ልጆቹ ነንና።ኤፌሶን 2:10/ኤፌሶን 1:4-5
ሁሉ ሰው የሰው ሁሉ ብርሃን እና የእ/ር ክብሩ ክርስቶስ ጎድሎበት ወደ ከንቱነት ጽልመት ከመውደቁ በፊት ከእ/ር ክብር ከክርስቶስ አልጎደለም ነበር። በአዳም ወገብ ውስጥ ሆኖ ከመሞቱ በፊት አዳም በብርሃን[ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።] ይመላለስ ነበር። ይህች በክርስቶስ የነበረችው ሕይወት የሰው ብርሃን ነበረች ። በዚህ የሰው ሁሉ ብርሃን አዳምና ሄዋን ሲመላለሱ ነበር እስኪባረሩ ጌታን እግዚአብሔርን በመንፈስ ሲመላለስ በመንፋሳቸው ይሰሙት ነበር። ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ከገነታቸው ማለትም ከመንፈሳቸው ውስጥ ሲመላለስ ይሰሙ ነበር። የዮሐንስ ወንጌል 1/4 ኦሪት ዘፍጥረት 3/8 ገና ኤደኑ ባድማ ና ምድረ በዳ አልሆነም ነበረ። አዎን ዔደኑን እ/ር በረሀ ገና አላረገውም ነበረ። በመንፈስ የሆነ ደስታና ተድላ የተሞላ ነበር። አሁን ጌታ ይመስገን ወደ ኤደን በክርስቶስ እየመለሰን ነው። [ትንቢተ ኢሳይያስ 51/3 እግዚአብሔርም ጽዮንን ያጽናናል፤ በእርስዋም ባድማ የሆነውን ሁሉ ያጽናናል፥ ምድረ በዳዋንም እንደ ዔደን በረሀዋንም እንደ እግዚአብሔር ገነት ያደርጋል፤ ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ ይገኝበታል።]
‘ምክንያቱም፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀልንን መልካም ሥራ እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ “ውስጥ” የተፈጠርን [created in(within) Christ Jesus ]የእግዚአብሔር ፍጥረቱ ነን። ‘ኤፌሶን 2:10
(Eph 2:10 [KJV])For we are his workmanship, created in Christ Jesus unto good works, which God hath before ordained that we should walk in them.
‘በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በክርስቶስ “ውስጥ” [in(within Him) Christ] መርጦናልና። በፍቅር፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ፣ እንደ በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ወሰነን፤ ‘ኤፌሶን 1:4-5
Eph 1:4 even as He chose us out (selects, picks us out), within Him. before [the] casting down (a laying of the foundation; a conception) of [the] ordered system (world), [for] us to continuously be set‑apart (holy) ones and flawless ones (ones without stain; blameless ones) in His sight (presence) [in love; or, putting this phrase at the beginning of vs. 5:]
‘ሞት በአንድ ሰው በኩል እንደ መጣ፣ የሙታንም ትንሣኤ በአንድ ሰው በኩል ሆኖአልና። ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤ ‘1 ቆሮንቶስ 15:21-22እንዲሁ ደግሞ፦ ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15/45
በዚህ ጉዳይ ላይ እ/ር የሚያውቀው ሁለት የሰዎችን ዘር አዳሞችን ብቻ ነው። ሁለቱም የዘር መጀመሪያ ና መጨረሻ ናቸው። የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው፤ ሁለተኛው ሰው ከሰማይ የሆነ ጌታ ነው።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15/47 The first man is of the earth, earthy: the second man is the Lord from heaven. የመጀመሪያው የሰው ልጆችን ወደ ሞት ይዞ ወረደ ሁለተኛው ወደ ህይወት ይዞ አወጣ። አዳም ሁሉን ወደ ሃጥያት ይዞ ለመውደቅ አቅም እንደ ነበረው ሁሉ ክርስቶስ ይበልጡኑ ሁሉን ወደ ጽድቅ ህይወት ይዞ ሊነሳ የበለጠ ሃይል አለው። ‘እኔ ግን ከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሰውን ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ[እጎትታለሁ፤- በሃይልና በጡንቻ drag, forcefully it is muscular ።” ዮሐንስ12:32 ኅይል የእ/ር ነው!
ስለዚህ ሁለቱ ሞቶች አይመሳሰሉም ሁለተኛው ሞት የመጀመሪያውን ሞት ስራ ሁሉ ይቀለብሰዋል። በተመሳሳይ የመጨረሻው አዳም የመጀመርያውን አዳም ስራ ይቀለብሰዋል። በብዙ መልኩ ‘ቀጥሎም፣ “እነሆኝ፤ ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ” አለ፤ ሁለተኛውን ለመመሥረት የመጀመሪያውን ሻረ። ‘ዕብራውያን 10:9
የመጀመርያው አዳም ለጽድቅና ለእ/ር ሞተ ለሃጥያት ግን ህያው ሆነ የመጨረሻው፡አዳም ደግም ለሃጥያት ሞተ ‘በሞተ ጊዜ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኀጢአት ሞቶአል፤ ነገር ግን በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖራል። ‘ሮሜ 6:10 በዚህም ጽድቅን ሁሉ ፈፀመ። የመጀመርያው ሰው ሰውን ሁሉ ሐጢያተኛ አደረገ የሁለተኛው ሰው ሰውን ሁሉ አፀደቀ በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖሩ ዘንድ።
ሁለተኛው ሞት ከሚበሰብሰው ወደ ማይበሰብሰው ሽግግር ነው። ከስጋዊ አእምሮ ወደ መንፈሳዊ አእምሮ ሽግግር ነው። ለውጡ ለአንዱ አለም ሞቶ ለሌላኛው ከፍ ላለው መንፈሳዊ ግዛት ህያው መሆን ነው። ለእ/ር ከሞተው የአዳም ንቃተ ህሊና ለእ/ር ህያው ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ ንቃተ ህሊና መነሳት መነጠቅ ነው። ጌታ እየሱስ በስጋ በምድር እያለ የሰው ልጅ የሚኖረው በሰማይ[መመንፈስ ግዛት] ነው ይላቸው ነበር። የክርስቶስ ንቃተ ህሊና የሚያድረው በሰማይ[መመንፈስ ግዛት] ነው። ሃሌሉያ! የዮሐንስ ወንጌል 3:13 ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው። ልጅነት እንዲህ ነው ሁለት እግሩ በምድር ቆሞ የሰው ልጅ በመንፈስ አሁን ተነጥቆ የሚኖረው በሰማይ[ the One continuously being (constantly existing) within the heaven] ነው ብሎ እርፍ! “And no one has ascended (stepped up) into the heaven, except the One descending (stepping down) from out of the midst of the heaven: the Son of Mankind (the Son of the human; Humanity’s Son; the Son of man) – the One continuously being (constantly existing) within the heaven . John 3:13
#ሞት ሃይል አልባ የተደረገው በሞት ነው። “ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን።እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።
ወደ ዕብራውያን 2:9, 14-15” እንዳስተዋልነው ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥ የተገባ ስለነበር ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ቀመሰ ይህ ሞትን ሊያስቀርልን ሳይሆን ሰው ሁሉ ሁለተኛ ጊዜ እንዲሞት እርግጥ ሆነ በዚህም ሁለተኛ ሞት የመጀመርያው ሞት ስራ ሁሉ በእኛ ውስጥ ከመሰረቱ ፈንቅሎ እንዲያበቃ አደረገው። ጳውሎስ የዚህ እውነት ፍንጣቂ ጨብጦ እንዲህ አለ።
‘የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ ምክንያቱም አንዱ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ እርግጠኞች ሆነናል፣ ከዚህም የተነሣ ሁሉ ሞተዋል። በሕይወት ያሉትም ለሞተላቸውና ከሙታን ለተነሣላቸው እንጂ ከእንግዲህ ለራሳቸው እንዳይኖሩ እርሱ ስለ ሁሉ ሞተ። ‘2 ቆሮንቶስ 5:14-15
ጎልጎታ ሁሉ ሰው ለራሱ ወይም ለእኔነት እንደሚሞት አረጋግጠዋል። የክርስቶስ ህይወት በነፃ የተሰጠን ነው ።ጳውሎስ እለት እለት ለስጋዊው ሰው አእምሮና ግዛቱ የሞመቱ ለክርስቶስ አእምሮ ህያው ለህይወት ግዛት ህያው የመሆን ሚስጥር ያ ነው። በእ/ር መንፈሳዊ ግዛት ንቃተ ህሊናችን ለእ/ር ህያው እንድንሆን የተሰጠን ህይወት እንድንኖር ነው። “በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ” አሁን የሆነውን መቁጠር የቻለ ተጠቀመ። ወደ ሮሜ ሰዎች 6/11 እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ። ቁጠሩ ቁጠሩ! ሞቱንም ወደ ህይወት መነሳቱንም ልንለማመደው የግድ ነው። በመጀመርያው አዳም ዘንድ የተለማመድነው ሞት የተባለው የራስ ህይወት፡ የሚያበቃው በሁለተኛው አዳማ ለራስ ህይወት ማለትም ለሞት ለስጋዊው አእምሮ በመሞት ነው። ይህ የሚያበቃው ለህይወት ህያው በመሆን ነው። ለተትረፈረፈ ህይወትም ህያው በመሆን ነው።
‘ሰው አንድ ጊዜ ሊሞት ከዚያም በኋላ በፍርድ ፊት ሊቆም ተወስኖበታል። ‘ዕብራውያን 9:27 ይሄ ማለት በፊት እንደምንረዳው በአካል መሞት አለብን ማለት አይደለም። ጳውሎስ ሲነግረን ‘እነሆ፤ አንድ ምስጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም[አካላዊ ሞት]፤ ነገር ግን ሁላችንም እንለወጣለን፤ ‘1 ቆሮንቶስ 15:51 ሰው ሁሉ ወደ ሞት ግዛት ሲወለዱ ሞትን ቀምሰዋል ሁሉ በአዳም ሞቱ እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ መጣ። በክርስቶስ ህያው ካልሆነ በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁንም ተፈርዶበታል በኩነኔ እየኖረ ነው። ‘ እውነት ክርስቶስ ነው ለምን እውነት እላችኋለሁ፤ ብሎ በራሱ ማለ? “እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤ አሁንም መጥቶአል፤” አሁንም መጥቶአል? ከሞት ግዛት ወደ ሕይወት ግዛት ተሻገረዋል?
“እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም[aionios የዘመኑ(የዘልአለም ህይወት የተወጋው በጊዜ ውስጥ ስለሆነ የዘመኑ የእ/ር ህይወት ተባለ)] ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤ አሁንም መጥቶአል፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ። ‘
ጌታ እንዲህም አለን የዮሐንስ ወንጌል 8/51 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም[ይህን ቃል የአማርኛ ተርጋሚዎች ከኪሳቸው የጨመሩት ነው] ሞትን አያይም።[መሆን የነበረበት፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ሞትን አያይም።]
John 8:51 Verily, verily, I say unto you, If a man keep my saying, he shall never see death.
ዮሐንስ 5:24-25እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።25 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8/6 ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። Rom 8/6 For to be carnally minded is death; but to be spiritually minded is life and peace.
በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። በክፍል ሁለት እንደ ሐፍ ቅዱስ ቃል የሁለተኛው ሞትና የእሳት ባህር ፍቺ ላይ እንዳሳየነው
“የሁለተኛው ሞት ፍቺ፤ በዚህ ቦታ ላይ ሁለተኛው ሞት ማለት የመጀመርያው ሞት እና ሲኦል በእሳት ባህር ውስጥ ሲደመሰሱ ማለት ነው። “በራእይ 20/4 ሞትና ሲኦልም የእሳት ባህር ውስጥ ተጣሉ። ይህም “የእሳት ባህር” [ይህ ሃሳብ ሲተረጎም ለሁለተኛ ጊዜ የተጨመረ ነው።] ሁለተኛው ሞት ነው።” “death and hell were cast into the lake of fire. THIS IS THE SCOND DATH.”k.j.v. ትክክለኛው ትርጉም ለአንባቢያን እንዲገባ መሆን የነበረበት “ሞትና ሲኦልም በእሳት ባህር ውስጥ ተጣሉ። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።” እንደ ምናስተውለው ሞትና ሲኦል ወደ እሳት ባህር ሲጣሉ ሁለተኛው ሞት ይባላል። ይሄ መንፈስ ቅዱስ እራሱ ሲያጽፈው ሁለተኛው ሞት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሰጠው ፍቺ ነው።
አስተውሉ ሁለተኛው ሞት ማለት ሰዎች በማይጠፋው እሳት ለዘልአለም ሲቀቀሉና ሲሰቃዩ ማለት አይደለም። አሊያም እንደ ሚባለው ክርስቶስን ያልተቀበሉ ከሞት ቡሃላ የሚጠብቃቸው ኑሮ አፈ ታሪኩ የዘልአለም ሞትና ስቃይ አይደለም። አሁን አይናችን ተከፍቶ ማየት ችለናል ሁለተኛው ሞት ማለት የአንደኛው ሞትና የሲኦል የሞት ግዛት ሁሉ በእሳት ባህር ውስጥ ተጥለው ሲደመሰሱና ሲጠፉ ማለት ነው ። በህይወት መጽሐፍ ያልተገኘ ሁሉ የመተላለፍና የሃጥያትና የሲኦል ተፈጥሮ ማንነቱ የተናወጣቸው አመል ሁሉ የአመፃ ሚስጥር ሁሉ ወደ የመለኮት የማጣርያ የእሳት ባህር ይጣላሉ።
“እ/ር መንፈስ ነው። ዮሃ 4/24” መንፈሳዊው ነገር ለቁሳዊው አለም ለማስረዳት በአካላዊ ቋንቋ መስሎ ያስረዳናል። የብዙ አማኞች ችግር ይሄ ነው። ለዚህም ነው በመንፈስ መገለጥ እንድንረዳቸው በተምሳሌነት የተጠቀመባቸው ምልክቶች፣ SYMBOLS ቀጥታ ከመተርጎም የመጡ ብዙ ችግሮች የተከሰቱት። መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ መጽሐፍ ነው። አስተውሉት እስቲ “የእሳት ባህር” የሚለውን ቃል እንየው “ባህር ምንድነው?” ስፋትና ጥልቀት ያለው በውሃ የተሞላ ቦታ ነው። ይሄኛው ልዩነቱ በእሳት መሞላቱ ነው። በምልክት ወይም በገላጭ ቋንቋ ጌታ ተጥቅሞ ተናገረው። እስራኤል ቀይ ባህር በጌታ ለሁለት ተከፍሎ መንገድ አድርጎላቸው በውስጡ ባለፉ ግዜ ሐዋርያው በጥምቀት አልመሰለውምን ? 1ኛ ቆሮ 10/2 እነዚህም በመለኮታዊ ማጣርያ በእሳት ባህር የሚያልፉትም እንደዚሁ ነው። ለእ/ር እንዲ ሰለጥኑለት በልምድ ውስጥ ያሳልፋቸዋል።
የእ/ር በእሳት የመቀመሙና የመፈተኑ ባህርዩንና አላማውን ስናይ “ወደ እሳት አመጣለሁ እንደ ብርም አነጥራቸዋለሁ። እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ። እነሱም ይጣራሉ እኔም እመልሳላቸዋለሁ፤ እኔም “ህዝቤ ናቸው” እላለሁ። እነሱም “እ/ር አምላካችን ነው” ይላሉ። ዘካ13/9 እንደ ምናስተውለው እንደ ወርቅ በእሳት ከተፈተኑና ከነጠሩ ቡሃላ በጨረሻ እ/ር “ህዝቤ ናቸው” ለማለት አላፈረባቸውም እነሱም በመንፃታቸው “እ/ር አምላካችን ነው” ሲያስብላቸው ይታያል እንጂ እሳቱ ሲያጠፋቸው አይታይም። በአንጥረኛ ወርቁ ወደ እሳቱ የመግባቱ አላማ ወርቁ ወደ ተፈለገበት አላማ ከፍ ወዳለ ውበት ቅርጽ ለማድረስ እንጂ ወርቁን ለማጥፋት አይደለም።
መቼም እ/ር ሰውን በእሳት ባህር እንደ ማያጠፋው የታወቀ ነው። በየትም ቦታ የእ/ር ቃል እንደዛ አይልም። ያ የእውነት ተፃራሪ ነው። “ቃልህ እውነት ነው በእውነትህ ቀድሳቸው።” የባቢሎንን ማስፈራርያ ወጥመድ ስብከትን ነው። አስቡት እስቲ ሰውን ማምለጫ በሌለው የዘልአለም ሞትና እሳት ውስጥ ፈጥረህ ና ከተህ የመጨረሻውን ጠላት ሞትን እንዴት ትደመስሳለህ?የእ/ር መለኮታዊ እሳት ሰዎች ሁሉ ይፀዱበታል፤ ይነጥሩበታል፤ ጽድቅን፤ ይማሩበታል እንጂ አይጠፉበትም። ጌታ ዋጋ የከፈለውና የመጣው የሰውን ሕይወት ለማዳን ነው እንጂ ለማጥፋት አይደለምና “ኢየሱስ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና እናንተ ከምን ዐይነት መንፈስ እንደሆናችሁ አታውቁም፤ የሰው ልጅ የመጣው የሰውን ሕይወት ለማዳን ነው እንጂ ለማጥፋት አይደለምና” አላቸው፤ ‘ሉቃስ 9:55” ሰው ጌታ የመጣው የሰውን ሕይወት ለማዳን ሳይሆን ለማጥፋት ነው የሚል ከሆነ ከምን ዐይነት መንፈስ እደሆነ አነጋጋሪ ነው አያውቅምም።”በአጠቃላይ የእሳት ባህር ፍቺ “የመሎከት የማጣርያ ብህር፣ a lake of divine purifcation” ነው። ፍርድ የሚለው ሃሳብ መከልከል የለበትም።“
ስለዚህ ሃሳብ በብዙ ሰዎች ብዙ ተጽፎ አንብቢያለሁ ሚዛን የሚደፋና፡ብሎም የማይደፋም ቀልሎ የተገኘም አጋጥሞኛል። በእ/ር ቃል ሲመዘን ማለቴ ነው። በዚህ ሃሳብ ላይ በብዙ ሰዎች ዘንድ ሰፊ የሆነ ግራ የተጋባ አመለካከት እንዳለ ግልጽ ነው። ለብዙ ወገኖች ይጠቅማል በማለት ይህን የመረዳት ብርሃን አብረን እንድናየው እወዳለሁ መልካም ነገር አለውና። ከቀድሞው አባቶች ሲኦል ዘልአለማዊ ነውን? (is hell eternal or will GOD’S plan fail?) በRev-Charles pridgeon ከነቮበር ወ 1920 እትም መጽሐፋቸው። የእሳት ባህርን በተመለከተ ከገለጡት እጅግ ከሚያስደንቀው የመረዳት ብርሃን የተሞላበት የሊቅ ወይም
የእስኮላር ስራቸው ለተሻለ ግንዛቤ ለብዙ አስተዋዮች እንደ ታገዙበት ሁሉ እኔም ከታገዝኩበትና ከተረዳሁበት መካከል ለወገኖች ጥቅም ልጠቅስ እወዳለሁ። “የእሳት ባህርና ዲኑ (BRIMSTONE) የሚያመለክቱት እሳቱ ከዲኑ ጋር ሲነድ ነው። ዲን፡brimstone ወይም ድኝ፡ sulphur የሚለው የእሳቱ ባህርይ ነው።
የግሪኩ ቃል THEION ሲተረጎም ዲን፡brimstone ተብሎ የተተረጎመ ሲሆን ያው የግሪኩ ቃል እራሱ THEION መለኮት ማለት ነው። በጥንታውያን ግሪኮች መካከል ድኝ ፡sulphur የተቀደሰ ነበረ። እናም ለማጠን፤ ለማንፃት፤ ለማጥራት ለአምላካቸው ያውሉት ነበር። ለዚህም አላማ ያጥኑ ነበር። homer’s lliad[16:228] አንድ ሰው በእሳትና በዲን ዋንጫውን እያፀዳ እንደሆነ ሊናገር ይችላል። THEION ከሚለው ቃል የተሳበው ግስ {ግስ፡ ማለት የቌንቋ አረባብ የዘርና ነባር መሰረት ቃል ነው። } THEIOO ሲሆን ማለትም ማወደስ፤ መለኮትን መስራት፤ ለአምላክነት መለየት ማለት ነው። [liddel and scott Greek English Lexicon, 1897 Edition] ተመልከት/ቺ።
ለማንኛውም ግሪካዊ ወይም በግሪክ ቋንቋ ለሰለጠነ ሰው “የእሳት ባህርና ዲን” ሆኖ መረዳት የነበረበት “የመሎከት የማጣርያ ብህር፣
a lake of divine purifcation” ነበር። ፍርድ የሚለው ሃሳብ መከልከል የለበትም። እ/ር መንገዱ ሁሉ እውነትና ፍርድ ነውና። በጥንታዊ ግሪክ ቋንቋ መለኮታዊ ማጣርያና ለመለኮት ማዋል የሚል ነው ፍቺው። በተራው አገላለጽ ይህ የቃሉ ትርጉም ገንጥለው አውጥተውታል። አመፀኛ ሃፍረት የለውም ተብሎ እንደ ተፃፈ ምንም ነገር ሳያስቀሩ ግን የዘልአለም ስቃይ ጋር አዛምደውታል።” የተጠቀሰው ተፈፀመ። by Brother Binyam T. Alemayehu