በ “ምርጫ choice” እና “በነፃ ምርጫ free choice” መካከል ያለውን ልዩነት ለጊዜው አልተረዳህም። ሁለት፤ በ “ፈቃድ will” እና “በነጻ ፈቃድ free will” መካከል ያለውን ልዩነት ለጊዜው አልገባህም ፡፡ ሶስት፤ እግዚአብሔር ሉዓላዊ Sovereign ነው ማለት ምን ….


ከጥያቄ/መልስ የተወሰደ ክፍል 2። ሰላም፤ Willy Mac እነዚህ መንፈሳዊ ነገሮች እንደመሆናቸው መጠን በማስተዋል እንድትረዳው በሰማያት ያለው አባታችን እንጂ ሥጋና ደም ይህን አይገልጥልህምና የክብርን #አባት እና አምላክን #በማወቅ #የሚመጣውን የጥበብና የመገለጥን #መንፈሱን እንዲሰጥህ ጸሎቴ ነው። ፈቃዱ ከሆነ በትክክለኛው አቅጣጫ ልጠቁምህ በጥቂቱ እሞክራለሁ ፡፡
ያልተረዳከው ብዙ ነገር በአዕምሮህ ውስጥ እየተካሄደ እንደሆነ ግልጽ ነው ፡፡
አንድ፤ በ “ምርጫ choice” እና “በነፃ ምርጫ free choice” መካከል ያለውን ልዩነት ለጊዜው አልተረዳህም።
ሁለት፤ በ “ፈቃድ will” እና “በነጻ ፈቃድ free will” መካከል ያለውን ልዩነት ለጊዜው አልገባህም ፡፡
ሶስት፤ እግዚአብሔር ሉዓላዊ Sovereign ነው ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለጊዜው አሁንም የተረዳከው አይመስልም።
“እንደ በጎ ፈቃዱ #መፈለግንና #ማድረግን #በእናንተ #ውስጥ #የሚሠራ #እግዚአብሔር #ነውና።…it is #God [not man] which works in you #BOTH TO#WILL [God causes us “to will’] and #TO #DO [God causes us “to do’] of His good pleasure” to bring about His intentions (Phil. 2:13).
በቅድሚያ ነጻ ፈቃድ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያልተገኘ ድቅል ቃል በመሆኑ ፍቺውን በመዝገበ ቃላት እንየው። የነፃ ምርጫ ፍቺ ። የአሜሪካ ቅርስ ኮሌጅ መዝገበ-ቃላት American Heritage College Dictionary “ ነፃ ምርጫ ማለት n. 1. የመምረጥ ችሎታ ወይም ውሳኔ ፤ ነፃ ምርጫ። 2. በውጭ ምርጫዎች ተጽኖ ያልተገደቡ ነፃ ምርጫዎችን የማድረግ ሀይል ነው ይለዋል።
ማርያም-ዌብስተር ኮሌጅተር መዝገበ-ቃላት Meriam-Webster Collegiate Dictionary/ 11ኛው እትም የበለጠ ትክክለኛ ትርጉም አለው: ” ነፃ ፈቃድ ማለት n. በሰዎች ነፃነት ያለ ተቀዳሚ መንስኤዎች ወይም መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ሳይኖር የመወሰን የምርጫ ሃይል ነው።” እርፍ!
የእግዚአብሔር ፈቃድ የሰው ልጆች በፅድቅ እንዲኖሩ ነው። መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ሳይኖር የሰው ታሪክ በራሱ ነጻ ፈቃድ ወይም ምርጫ የሚነግርለት ትውፊት የለውም። እ/ር እራሱ ፍጥረት ለከንቱነት እንዲገዛ አድርጎታል በአሰራሩም በመጨረሻ ተስፋውን ሲያስጨብጠው ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ መሆኑ ከእቅዱ ግልጽ ነው። ኤፌ1፡10 ሮሜ 8፡21 አሁንም አስተውል ሰው ሁሉ ሁሉንም እይነት የራሱን ምርጫዎች ያደርጋል፡፡ ነጥቡ ምርጫ የለውም ወይም ምርጫ የለም አይደለም። ወይም የሚታዩና የማይታዩ ሁኔታዊ ተጽኖዎች የራሳቸው ድርሻ ቢኖራቸውም ምርጫዎችን ሰው አያደርጋቸውም ለማለት አይደለም ፡፡ እውነቱ ግን ሰው የእርሱን ምርጫዎች እንዲያደርግ ከተጽኖ ውጪ ነው ማለት አይደለም ፡፡ አዕምሮ አለን ፣ እናም ሚሊዮኖችን ምርጫዎችን በየቀኑ እናደርጋለን ፣ እናም ፈቃድ ድብን አድርጎ አለን[ነጻ ግን አይደለም] ፣ ግን ፈቃዳችን ከእነዚህ ነገሮች ውስጥ አንዳቸውም በባዶ አይሰሩም። ለእያንዳንዱ አስተሳሰባችን እና ምርጫችን አንድ ምክንያት (CAUSE) አለ። ፈቃድ አለን ግን ከእግዚአብሔር ውጭ የሆነ ነገር ለማከናወን ወይም ለማድረግ ነፃ አይደለም ፡፡ ግን ሌላ እውነት ደግሞ ብዙ ነገሮችን የምናደርግ መሆኑ ግልጽ ነው። እናስባለን ፤ እንፈጥራለን ፤ እናሰላስላለን ፤ እርምጃ እንወስዳለን ፤ ምርጫዎች እናደርጋለን ፤ የተለያዩ ነገሮችን እናደርጋለን ፤ ነገሮችን እንለውጣለን ፤ ነገሮችን እናሻሽላለን ፤ ወ.ዘ.ተ. … ግን እኛ ይህን በማድረጋችን ከእግዚአብሄር ሉዓላዊነት ራዳር ውጭ ነን ማለት አይደለም።
አሁንም አስተውል እግዚአብሔር በቀጥታ ይህንን ምርጫ የሰውን እጁን ጠምዝዞ ለሰው ምርጫውን አያደርግለትም ፡፡ ሁሉም ሰው የመምረጥ ችሎታ አለው ፣ ግን ያ ምርጫው በብዙ ውስብስብ ምክንያቶች ላይ የተመሠረተ የተመሮከዘም ነው። በዚያ ምክኛት ነው የሰው ምርጫው ነፃ ያልሆነው። እሱ እ/ር ከባባዊ የተጸኖ ሃይላትና ምክንያቶች በመፍጠሩ ሀላፊነት ይወስዳል ያ ማለት ግን እሱ እ/ር በቀጥታ ለእነዚያ የሰው ምርጫዎች አስገድዶ አይመርጥላቸውም ስለዚህም ሰዎች ለምርጫቸው ተጠያቂዎች ናቸው ጽድቅን እንዲማሩም ለእርማት ፍርድ ይገዛሉ ከሚቀበሉት መከራም[ውጥረት] መታዘዝን ይማራሉ፡፡
ወደ ፈተና ስንመጣ ማንም ሲፈተን፣ “እግዚአብሔር ፈተነኝ” አይበል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንም፤ እርሱም ማንንም አይፈትንም፤ ነገር ግን እያንዳንዱ EVERY man የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት HIS OWN LUSTS ሲሳብና ሲታለል ነው። ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች። ያዕቆብ 1 13-15
እግዚአብሔር ማንንም ኃጢአት እንዲሰራ አያደርግም ፡፡ የሰው ልጅ በፍቃደኝነት VOLUNTEERS ሆነው ይሰራሉና፣ ሰው ኃጢአትን ለመሥራትን በራሱ ክፉ ምኞት ይፈልጋል ፣ እናም የሰው ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች፣ እናም ያለ የእግዚአብሔር ቅዱስ ኃይል ቀጥተኛ አስገዳጅነት፣ የሰው ልጆች አስጸያፊ የኃጢአት መሣሪያዎች SINNING MACHINS ናቸው።
እውነት ነው ፣ እነዚህ እውነቶች ከሥጋዊ አዕምሮው ዘንድ ለመረዳት ይችል ዘንድ በጣም ከፍ ያሉ መንገዶች ናቸው ፡፡ ሰዎች ሁል ጊዜ ስለ እግዚአብሔር ሥነ ምግባር “ጥያቄን ይጠይቃሉና” ምክኛቱም “እንግዲህ የሚወደውን ይምረዋል፥ የሚወደውንም እልከኛ ያደርገዋል። እንግዲህ ስለ ምን እስከ አሁን ድረስ ይነቅፋል? ፈቃዱንስ የሚቃወም ማን ነው? ትለኝ ይሆናል። ነገር ግን፥ አንተ ሰው ሆይ፥ ለእግዚአብሔር የምትመልስ ማን ነህ? ሥራ ሠሪውን፦ ስለ ምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ ይለዋልን? ሮሜ 9 18-21፡፡”
እንደ ዲያቢሎስ ያሉ እና አለም የመሳሰሉ ተጽኖ ሊያመጡ የሚችሉ እንደዚህ ያሉ ነገሮችን ጠቅሰካል፡ ጥያቄው ተጸኖ አምጪ ያልከውን ዲያብሎስን ወይም ሰይጣን ማን ፈጠረው? ሰይጣን የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን እንዳያስብና በአውሬያዊ ባህሪ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛና ዕንቅፋትና ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ እንዲሆን አድርጎ ማን ፈጠረው? መልሱ እ/ር! ዘፍጥረት 3፡1 ማቴዎስ 16፡23 የዮሐንስ ወንጌል 8፡44 አለምና መላዋንስ ከነሁኔታዋ ማን ፈጠራት? እነዚህ እነዙህን ትንንሽ ሃይላት እ/ር ተጸኖ እንዲያመጡ ከፈጠራቸው ይመደባሉ።
“እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ ፣ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ …”ዘፍ. 1፡31 መርዛማ እባቦች እንኳን ሳይቀሩ ማለት ነው። እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ። አስተውል ያም ከመልካም አንዱ ነው በወቅቱ። ከተጽኖ ወጥመድ ዝርጋታ ውስጥ ተዋናይ ነውና። “ያደረገውን ሁሉ አየ …በጣም ጥሩ” መሆናቸው አንዘንጋ ፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ያደረገው ሁሉ “መልካም” ነበር ። እርፍ!
ሔዋን ራሷ ያለ ምክንያት “በነፃነት” ኃጢያትን ለማድረግ እንደምትመርጥ አስባ ይሆን? ለመሳትዋ ተጽኖ ያመጣው ምክንያት ምን ነበር “ሴቲቱም አለች፦ እባብ አሳተኝና በላሁ።” ማን ነው አሳቹን በገነት ውስጥ ያስቀመጠው? የሄዋን ለማዳ የቤት እንስሳ ይሆን?
የሚታየው ነገር የተፈጠረው ከሚታየው እንዳልሆነ እንገነዘባለን ዓለማት[ዘመናት፤ ጊዜ] ተጽኖ ከሚያመጣው ጊዜን ጨምሮ ለሁሉ የለውጥና የተጽኖ ጉልበት ዘመን ጊዜን መድቦለታል ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው። ትንቢተ ዳንኤል 2፡21 ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፤
በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተፈጠሩ[እንደተዘጋጁ] በእምነት እንረዳለን፤ ስለዚህ የሚታየው ነገር የተፈጠረው ከሚታየው እንዳልሆነ እንገነዘባለን። Heb 11፡3 “Through faith we understand that the worlds [ages] were framed [prepared] by the Word of God, so that things which are seen were not made of things which do appear [are visible]”
እ/ር በፍጥረቱ ሁሉ ላይና በሁኔታዎች ሁሉ ላይ ሉዓላዊ ጌታ ነው እና ሁሉንም ነገር ተቆጣጣሪ የሆነ ልእለ-ተፈጥሮ ጉልበት እና ኃይል ነው ፡፡ ክፉ ሰዎች ክፋትን ምርጫቸው አድርግገው ይፈጽማሉ ወይም ልክ እንደ ብዙ ክፉ የሥነ-መለኮት ምሁራን የመበለትን ገንዘብ ይበዘብዛሉ ሌሎችም በልዩ ልዩ ምኞትም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች እየማረኩ ንዋያቸውን መስረቅ ይወዳሉ ወዘተ….። እግዚአብሔር ይህን አድርጉ አላለም የዓመፅ ምሥጢር ምክኛት በፈቃዳቸው እሱን ማድረግ ይወዳሉ። ለዚህም ምርጫቸው በሃያሉ በፍርድ ስር ይወድቃሉ ይታረማሉም።

ለአንዳንዶች ባለአእምሮ ለመሆን ለሚፈልጉና ከመጽሓፍ ቅዱስ ባሻገር ለዚህ መረጃ የሳይንሳዊ ማስረጃ አለን? ለሚሉ ዘመናይ ጴንጤዎች መልሱ ይህ ነው። የሁሉም ሕግና ቁስ አካል matter የመጀመሪያ መገኛ ምንጭ እግዚአብሔር ነው ፡፡ ቅዱሳን መጻሕፍትን በእውነቱ እንደ እ/ር ቃል እናምናለን ስለሚሉ ለክርስቲያኖች ነፃ ምርጫ እንደሌላቸው ለማስረዳት መጽሐፍ ቅዱስን እጠቀማለሁ ፡፡ ለመርዛማው አምላክ የለሽ athiestic የዝግመተ ለውጥን evolutionary የሳይንስ ሊቃውንት ነን ለሚሉ ደግሞ ነፃ ምርጫ እንደሌላቸው ለማሳየት መጽሐፍ ቅዱስን አልጠቀም በቀጠናቸው የሳይንሳዊ ህግን እጠቀማለሁ ፡፡ በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤
ሁሉ ነፃ ምርጫ የተጽዕኖዎች ውጤት ነው እንጂ በስነ-ልቦናም psychologically ቢሆን ነፃ ምርጫ ከተጽኖ ውጪ እራሱ ሊከሰት አይቻልም ፡፡ ስለዚህም ነፃ ምርጫ ማለት ግራ የገባው እራሱን የኮፈሰ የዘመናት ቅዥት ነው። ልጆች የሁሉም ነገር ተጽኖ ደራሲ እግዚአብሔር መሆኑን እናውቃለን ። በሌላ አገላለጽ የእኔን ጨምሮ ለሁሉም የተጽኖ ስውር ነገሮች ወይም ምክኛቶች ሀላፊነቱን እ/ር ይወስዳል። በምርጫየ ሁኔታዎችን መምረጥ ግን እችላለሁ። በእነዚያ ሁኔታዎች ውስጥ ስመርጥ ግን በነፃነት አይደለም ምክንያቱም እኔ የምመርጠው በእውነተኛ ሃይል በእግዚአብሔር ቁጥጥር በዙርያዮ በፈጣራቸው ውስጣዊ እና ውጫዊ ተጽዕኖዎች ላይ በመመርኮዝ በተወሰነ ገደብ ብቻ ነው ፡፡
የምክንያት እና ውጤት ህግን Law of [Cause and Effect] መገንዘብ ካለብን የሁኔታዎች እና ተፅእኖዎች ስራቶች አካሄድ ሁለንተናዊ ሕግ እንደሚያሳየው ለእያንዳንዱ ውጤት ግልጽ የሆነ የሚታይ ይሁን የማይታይ የተጽኖ ምክንያት ከበስተጀርባው አለው። በተመሳሳይም ለሁሉም ምክንያቶች ግልጽ የሆነ ውጤት አለ ። ሀሳቦችዎ ፣ ባህሪዎችዎ እና እርምጃዎችዎ በእያንዳንዱ ሰው እንደሚታወቀው ሕይወትን የሚያሳዩ እና የሚፈጠሩ ልዩ ተፅእኖዎችን ተመርኩዘው ይፈጥራሉ እንጂ እንዲሁ አይከሰቱም።
ሰዎች ይደክሙበት ዘንድ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ከባድ የሥራ ጫና አየሁ። #ሁሉንም #ነገር በጊዜው ውብ አድርጎ #ሠራው፤ በሰዎችም ልብ #ዘላለማዊነትን አኖረ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያደረገውን ማወቅ አይችሉም። መጽሐፈ መክብብ 3፡11
የሰው አካሄዱ በእግዚአብሔር ይመራል፤ ሰውስ የገዛ መንገዱን እንዴት ማስተዋል ይችላል? መጽሐፈ ምሳሌ 20፡24
በደህንነቱስ ቢኖን አሁን ደርሶ ነው እንዴ ፍጥረት ነፃ ፈቃድ አለኝ ብሎ የሚፎክረው? ይህ ሃሳብ ከንቱ ነው። ከመጀመርያ ጳውሎስ ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ እግዚአብሔር ስላስገዛው ነው እንጂ ፍጥረት ነፃ ፈቃዱን ተጠቅሞ ለከንቱነት አልገዛም ብሎ እግዚአብሔርን ማስቆም በነጻ ፈቃዱ ፍጥረት አቻለም፤ ከእግዚአብሔር ክብር ክርስቶስ የወደቀው በነጻ ፈቃዱ እስካልሆነ ድረስ ወደ ክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር ክብር መመለሱና መነሳቱም በነጻ ፈቃዱ አይደለም። በበደሉና በሃጥያቱ የሞተ ነው ሙታን ነጻ ፈቃድ አላቸው? አሳቀኝ አለ። ጳውሎስ ጌታ በብርሃን ተጸኖ በብርሃኑ በቃሪያ ጥፊ ሲያጮለው። ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ አስባለው እንጂ አባት ጌታን ተቀበል አላለውም እግዚአብሔር እራሱን ለፍጥረት ሲገልጥ ሁሉ ምን እደርግ ዛንድ ትወዳለህ ነው ይላል። ነው መልሱ። ምህረት ለወደደ፣ ለሮጠ ወይም ለፈቀደ አይደለም ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ። ያለተጽኖ የሚወስን እውነተኛ ነጻ ፈቃድ ያለው እ/ር ብቻ ነው። አብ ካልሳበው በቀር በነፃ ፈቃዱ የመጣ አንድ ስጋ ለባሽ መንፈስ አልታየም። የስጋ ለባሽ ክብሩ እንደ ጠዋት ጤዛ ነው። እውነተኛ ክብር በክርስቶስ ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ክብር ብቻ ነው።100%✔️ps90:3 Thou turnest man to destruction; and sayest, Return, ye children of men. እንተ ሰዎችን ወደ አሰር(ጥፋት) ታወርዳለህ እነሆ ሰዋች ሆይ ተመለሱ ትላለህ። ታላቁ የህይወት ደራሲ እግዚአብሔር ነው። ድንቅ ትእይንት። አባታችን ሆይ ስራህ ድንቅ ነው እንወድሃለን። ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal