ክፍል 1 ከጥያቄ/መልስ የተወሰደ። ►►► ጥያቄ፤ በሆነ ጹኡሁፍህ ላይ አንዴ ያነበብካት እየቆረቆረችኝ ተቸገርኩ ከብዙ ግዜ ቡሃላ ልጣይቅህ ዛሬ ጻፍኩኝ። ጽሁፉን ይዤው ስላስቀመጥኩት እንዲህ የሚል ነበር። “እነሆ “ነፃ” ፈቃድ ብሎ ነገር አለን የሚል እምነት በበኩሌ የለኝም ፡፡ በውስጣችን በረቀቀ የመንፈስ አሰራሩ “መሻትን፤ መፍቀድን wills” የሚሰራው እግዚአብሔር ነው ። ብለህ ለማስረጃ ቃሉ እንደሚል ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና። ጠቅሰህ ነበር።
ከዛም ምርጫዎች Choices ከነፃ ፈቃድ free will ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም ፡፡ ሁሉም ምርጫዎች የሚከሰቱት በተጸኖ ወስጥ ነውና። በሁኔታዎች ተጸኖ ውጭ የተከሰተ ምርጫ የሚባል ነገር የለም! የኤደን ትእይንትን ለአብነት ብንወስድ ምርጫው እንዲከሰት በተጸኖ ተገንዶ ሲደረግ መከልከል አልተቻለም። በተለምዶ ሰው የአከባቢው ውጤት ነው መባሉ ከዚህ ብዙም የራቀ አይደለም።”
ጥያቄ የጫረብኝ ጉዳዩ እንደዚህ ከሆነ እግዚአብሔርን እራሱ እንዴት ልንወደው እንችላለን? ፍቅር ነፃ ምርጫን ያለ ምንም ውጫዊ ኃይል ተጸኖ ከነፃ ፈቃድ free will ተጠቅሞ ይተገብራልና፣ ካልሆነ ግን በተጸኖ ከመረጠ እውነተኛ ፍቅር አይደለም ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ እይታህን መስማት በጣም እፈልጋለሁ ፡፡ በረከቶች ይጨምሩል።
►►►መልስ፤ ውድ ወንድማችን። ይህንን ከፈቃዱ ቃል የሌለ መሠረተ ቢስ ግምትን ብዙ ጊዜ ምላሽ ሰጥቸበታለሁ ፡፡
ለምሳሌ ያክል የአንተ የወንድማችን ፣ ሚስትህ፤ ባለቤትህ ትወድሃለች? መልስህ ግልጽ ነው። አዎ? እሷ ውድድድ እንድታደርግህ ወይም እንድትወድህ የሚያደርጋት ምክኛት ምንድን ነው? እውነተኛ ሁንና ሚስትህ እና ልጆችህ ስለ አንተ የሚወዱልህ “ምንም ነገር” እንደሌለ ቢነግሩህ ምን ይሰማሃልል? ጥሩ ስሜት እንዲሰማህ ያደርጋል ትላለህ? ያለ ምንም ምክንያት እነሱ በነፃነት የሚወዱልህ “ምንም ነገር” ሳይኖር ይወዱሃልን ?
እውነታው ባለቤቴን እንድወዳት የሚያደርጉኝ “ብዙ” ነገሮች አሉ ፡፡ ከመጀመርያም እኔ ፍቅር ውስጥ እንድገባ ተጸኖ ያመጡብኝ እነዚያ “ብዙ ነገሮች” ምክኛቶች “CAUSE” ናቸው። ለመጥቀስ ያክል ልባም ሴት በመሆንዋና እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ሆና ስላስተዋልኩኝ ደግሞም በአሁኑ ጊዜ ያሏትን መልካም ባህሪዎች ማንነትዋ ባይኖራት ኖሮ የምወዳትን ያህል ባልወደድኳትም ነበር። ሌላው ቀርቶ ከመጀመሪያውም አላገባትምም ነበር፡፡
እውነቱን እንነጋገርና በእውነት እኛ እግዚአብሔርን ያለ ምክኛት እንዲያው ነው የምንወደውን? “ነፃነት” በተባለ በአንዳንድ ምስጢራዊ የምናብ ምኞት አማካይነት ነው እሱን ለመውደድ የመረጥነው? ወይስ አንድ ነገር አስቀድሞ ስላደረገን በዚያ ምክንያት እሱን እንድንወድደው በተግባር ፍቅሩን ስለገለጠ ነው? መልሱን በድፍረት ለመናገር ፍጹም የተረጋገጠ የእግዚአብሔር ቃል ስላለን መገመት እዚህ ላይ አያስፈልገንም ፡፡ 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:19 መልሱን ይሰጠናል “እርሱ #አስቀድሞ #ወዶናልና #እኛ #እንወደዋለን።” “ፍቅርም እንደዚህ ነው። እ/ር እርሱ ራሱ እንደወደደን ስለ ሀጥያታችንም ማስተሳረያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደላከ እንጂ እኛ እ/ርን እንደወደድነው አይደለም።” 1ኛ ዮሀ4/10 እርሱም የሀጥያታችን ማስተሰረያ ነው። ለሀጥያታችን ብቻ አይደለም። ነገር ግን ለአለሙ ሁሉ ሀጥያት እንጂ። 1ኛ ዮሀ2/2” እንደምታስተውለው ቃሉ በተጽእኖ የተፈጠረው ፍቅር እውነተኛ ፍቅር አይደለም ከሚለው ሀሳብህ ጋር ሙሉ በሙሉ ይቃረናል ፡፡ የሆነ ሆኖ ፣ የእግዚአብሔር ቃል አንጀትን ቂቤ የሚያጠጣ እውነተኛ መልስ ነው።
“እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና በአጸፌታው በምላሹ እኛም እሱን ተከትለን እንወደዋለን።” ምክንያቱ ግልጽ ነው። በሌላ አገላለጽ እግዚአብሔር እርሱን እንድንወደው አደረገ ፡፡ Don’t you think he’s ways are marvelous? And Pretty neat love, huh? Isn’t our God Great? እግዚአብሔራችን ታላቅ አይደለምን? ደስ ይበልህ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው። ወንድም ቢኒ።
