
Terefe Bekele to Binyam TA
July 5 at 7:29 PM ·
ወንድም ቢኒ! የጌታ ሰላም ይብዛልህ ። ያልገባችኝ ጥያቄ አለኝ: የእግ/ርን ድምፅ መስማት በሚለው ትንታኔህ ላይ… ስለ ፋሲካ እና እዮቤልዩ የሰጠኸው ከእምነት ጋር አያይዘህ ትንታኔ ላይ እስራኤላውያን ካለማመናቸው የተነሳ ከክርስቶስ በኋላ መምጣቱን ገልፀሃል: እኔ ያልተረዳሁት የእስራኤል አለማመን የእግ/ር አጀንዳ የረቀየራል እንዴ? እኔ ስረዳው የነበረው ብሉይ ሥጋ የልለበሰ የእግ/ር ሃሳብ በክርስቶስ እየሱስ ወደ መገለጥ ያጣበትና በልጆች /ቤተ ክርስቲያን/ ፍፃሜ የሚያገኝ የእግ/ር (አብ ማለቴ እንደሆነ ይታወቅልኝ) የዘላለም አጀንዳ ይመስለኛል የማምነውም ይህንኑ ነው። እዚህ ላይም በአንድ ጀምበር የተደረሰ እንዳይደለ እንግባባለንና ይህም እስከ ሙላቱ የሚቀጥል ነውና በወንድሞች ጌታ ከፍ ብሎ ሲመጣ ውስጠኛው ሰው ደስታው ድንቅ ነውና መልስህን እሻለሁ።
መልስ
Binyam TATerefe Bekele ሰላም ለአንተ ይሆን ወንድም ተረፈ፡ በቅድሚያ እ/ር ሉኡል መሆኑን ሁሌም መርሳት የለብንም። በደንብ ካስተዋልከው ከጽሁፉ ላይ የዘልልካትን ፍሬ ሃሳብ በድጋሚ ልጥቀስልህ “ዳሩ ግን በነሱ ሳይሆን ሁሉን በሚችለው ወደ ታየላቸው ክብር ወደ ተስፋይቱ ምድር #እንዲገቡ#የሚያስችላቸው#እምነት#አልነበራቸውም#ከእ/ር #አጀንዳ አንጻር ወደ እረፍቱ የሚገቡበትን #የእምነት#መጠን#አላካፈላቸውም ነበርና።” የእምነታችን ደራሲ ትእይንቱን እንዴት ወደ ህልውና እንዳመጣው ነው ትንታኔውን የሰጠሁት። የእምነትን መጠን የሚያካፍለው እራሱ እ/ር ነው ከአላማው አንጻር እንዳያምኑ የሚቸረክመውም እራሱ ነው እ/ር ለእምነትም ሉኡል ነው። እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና ያም የብሉይም የአዲሱ ኪዳን ልጆችንም ይጨምራል። እንግዲህ ምንድር ነው? እስራኤል የሚፈልጉትን አላገኙትም፤ የተመረጡት ግን አገኙት፤ የቀደሙት በርሱ ደነዘዙ፤ እንዲሁ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ #እግዚአብሔር#የእንቅልፍ#መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ #ሰጣቸው ተብሎ ተጽፎአል። ወደ ሮሜ ሰዎች 11 7-8
ወንድሞች ሆይ፥ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ #ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው፤ወደ ሮሜ ሰዎች 11፡25
ካስተዋልከው እ/ር ቤተ ክርስቲያን church ኤክሌስያ የጀመረው በአዲሱ ኪዳን ብቻ አይደለም ማህበሩ ተብሎ መተርጎሙ ፍቺውን ደብቆብናል እንጂ ተጠርቶ መውጣት በእኛ አልጀመረም። ክርስቶስም ሚስጢር ሆኖ በብሉይም ነበረ በአዲስ ምስጢሩ ለሁሉ ይፋ ሆነ እንጂ። ከዘላለምና ከትውልዶች ጀምሮ ተሰውሮ የነበረ ክርስቶስ የእ/ር ምሥጢር ነው፥ አሁን ግን ለቅዱሳኑ ተገልጦ ይታያል። የእግዚአብሔር ምሥጢር ክርስቶስ በአሕዛብ ዘንድ አዲስ ያመጣው ሳይሆን እውስጣቸው ሳለ ከማስተዋላቸው የተወሰደደ በእ/ር የተሰወረባቸው የሰው ሁሉ ሕይወት የሆነ፥ የሰው ሁሉ ሕይወትም ለሰው ሁሉ ብርሃን ነበረ ይህ ምሥጢርና ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ለህዝብ ሁለ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእኛ ውስጥ መሆኑን አበሰረ። ኢየሱስ ክርስቶስ “በሩ እኔ ነኝ” ብሎ በወገኖች በህዝቦች ሁሉ ላይ በመንፈሳቸው ላይ የተጣለውን መጋረጃ፥ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል እንደተባለው አጥፍቶ በክርስቶስ መንፈሳዊ በሩ በሩ የሚገባ ሁሉ ይድናል፥ ደግሞም ወደ መንፈሳዊው ግዛት በመንፈስ ይገባልም ይወጣልም እንደገናም በዚህም መሰማርያም ያገኛል።
በብሉይም ትላንትም ዛሬም ነገም ያው የሆነው የማይቀያየረውን መንፈስ የሆነውን ክርስቶስን ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ፥ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት እኛ ከይወት ምንጭ ከውስጣችን አንደምንጠጣ በጊዜ የአባት እቅድ መሰረት ክርስቶስን ጠጥተዋልና፥ የተሰወረባቸው ቢሆንም ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ያም ክርስቶስ ነበረ ክርስቶስን ጠጥተው አርክተውለታል።
ቤተ ክርስቲያን church [ግሪክ፡ekklesia፡ a calling out ተጠርተው የወጡ ማለት ነው። (Jewish synagogue, or Christian community of members on earth or saints in heaven) or Sons of God.
አባቶች ስለ ቤተ ክርስቲያን ካላቸው እይታ አንጻር በምድረ በዳ “ማኅበሩ” ብለው ተርጉሞውታል “ማኅበሩ” የሚለው ቃል የስተት ትርጉም ነው። እንዲገባን የምድረ በዳዋ “ቤተ ክርስቲያን” ተብሎ መተርጎም የነበረበት። የምድረ በዳዋ ቤተ ክርስቲያን The church in the wilderness
የሐዋርያት ሥራ 7፡38 ይህ ሰው በሲና ተራራ ከተናገረው መልአክና ከአባቶቻችን ጋር በምድረ በዳ #በማኅበሩ[ግሪክ፡ekklesia፡ a calling out ተጠርተው የወጡ ማለት ነው። #church#ቤተ/ክርስቲያን] ውስጥ የነበረው ነው፤ ይሰጠንም ዘንድ #ሕይወት ያላቸውን #ቃላት ተቀበለ፤ Acts 7፡38 This is he, that was in the #church in the wilderness with the angel which spake to him in the mount Sina, and with our fathers: who received the lively oracles to give unto us: ወንድም ቢኒ።