
አቤቱ የሚናገር እግዚያብሄር።
የእ/ርን ድምፅ መስማት፤
ጌታ እ/ር በተለያየ ስም እራሱን ለፍጥረት የገለጠበት የአመራር ዘርፍ፤
እ/ርን መስማት እርሱን መውደድ ያመጣብናል፤ በወንድም ቢንያም አለማይውሁ የተፃፈ ። ቁጥር 1/2003 እ.አ.አ.
ትምህርት ቤት በነበርኩበት ጊዜ አንድ ፁሁፍ የእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋ ሊቅ በሆኑት በዶ/ር ስተፈኒ ጆንስ አነበብኩና ለብቻየ ተባርኬ ከምቀር ከራሴ መረዳት ጨማምሬበት ላስፋውና ለወገኖች ባቅቀርበው ይጠቅማል መልካም ነገርም ይቀርላቸዋል ብየ አሰብኩ እ/ር አባት እንደረዳኝ መጠን እንደሚከተለው አዘጋጅቼዋለሁ።
“ሙውታን የእግዚያብሄርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰአት ይመጣል እርሱም አሁን ነው። የሚሰሙትም በህይወት ይኖራሉ።” (ዮሀንስ 5/25) እ/ር ይመስገን! ዛሬ የቆምንበት በፍጥረት ታሪክ ውስጥ እጅግ አስደናቂና አስፈላጊው ጊዜ ነው። እ/ር የክርስቶስ አካልን ከፍ ወዳለ መንፈሳዊ የብስለት ደረጃ እየሳባት ያለበት ዘመን ነው። የእ/ር ድምፅ እንደመለከት እየተሰማ ነው። የመንፈስን ነገር የሚያዩ አይኖች ና የሚሰሙ ጆሮ ከእርሱ የተሰጣቸው በእርግጥም የልኡሉን ድምፅ ይሰሙታል። በእርግጥም እ/ርን የመፍራት መንፈስ ያደረበት በማስተዋሉ ፈጣን ይሆናልና ፈቃዱን ፈጥነን እናስተውል ዘንድ በማስተዋልም እንዳንዘገይ ለልባችን ድምፁ ህያው እንዲሆን ልባችንም እንዲፀና በፍቅርም ተባብሮ በማስተዋል ወደሚገኝ ወደ መረዳት ባለጠግነት ሁሉ እንድንደርስ የእ/ር ሚስጥር በክርስቶስ ተሰውሮ ያለውን የጥበብና የእውቀት መዝገብ እንድንበዘብዝ የእረኛችንን ድምፅ የምንሰማ በጎች እና በፈቃዱ የተወረስን እንድንሆን እፀልያለሁ። አሁን በሸግግር ወቅት ላይ ነን። የለውጥም ጊዜ ላይ ነን።ወደ አዲሱ የአምላካችን የመንግስቱ ስርአት እየገባን ነን። ጌታ እ/ርም በፈጣሬ ቃሉ ይናገራል። ሀይለኞትም የእ/ርን መንግስት እየተጫኑ እየገቡባት ነው።
“በሮሜ10/17 እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእ/ር ቃል ነው።”እምነት ሁሉም ይህንን ቃል ሰምውታል ብዙዎች አውቀውታል። በጠቅላላው በሂይወታቸው የተለማመዱት ግን ጥቂቶች ናቸው።“እብራዊያን 3/4 ሲነግረን እስራኤል ወደ እ/ር እረፍት ያልገቡት ባለማመናቸው ጠንቅ ነው።” ይላል ምክንያቱም ወደ እረፍቱ እንዲገቡና እረፍቱን እንዲለማመዱ እ/ር የሚጠብቅባቸው የእምነት ደረጃ አልነበራቸውም ። ግን ለምን? እ/ር በሙሴ እጅ የሰራውን ተአምራት አላዩምን? ቀይ ባህርን የፈጠረው ፍጥረቱን ሲከፍለው አላዩምን ከጭንቀታቸው በደረቅ ምድር እንደሚያልፍ አላሻገራቸውምን? ከሰማይ የወረደውን መና አልበሉምን? በእሳታዊ ህልውና በፅዮን ተራራ የወረደውን እ/ርን አላዩምን? በእርግጥም አይተዋል። ይህም ከሰው እንዳይደለ ከእ/ር እንደሆነ አምነዋል።
ዳሩ ግን በነሱ ሳይሆን ሁሉን በሚችለው ወደ ታየላቸው ክብር ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲገቡ የሚያስችላቸው እምነት አልነበራቸውም ከእ/ር አጀንዳ አንጻር ወደ እረፍቱ የሚገቡበትን የእምነት መጠን አላካፈላቸውም ነበርና። ጥያቄው ለምን? በአይምሮ መግባባትና በእምነት መካከል ልዩነት አለ።አንድ ሰው ጌታ እየሱስ የእ/ር ልጅ እንደሆነ ስለኛ እንደሞተ እንደተነሳ ሊያምን ይችላል። ነገር ግን ወደ መንፈሳዊትዋ የተስፋይቱ ምድር የሚያስገባ እምነት ላይኖረው ይችላል።እንደ ነገሩ እስቲ አስተውሉት ተራራን ለመነቅነቅ ብሎም ለመፈንቀል የሰናፍጭ ቅንጣት መጠን የምታህል እምቡጥልየትንሽየእምነት ብቻ የሚበቃ ከሆነ ፍልፈል የከመረችው የሚያህል ሚጢጢ ችግር ሲያጋጥመን ሁል ጊዜ የምንጨነቅና ምንም ለማድረግ የማንችል ሆነን እራሳችንን የምናገኘው ከሆነ ምንኛ ከሰናፍጭ ቅንጣት መጠን የምታንስ የእምነት መጠን ይሆን ያለን አሊያ እንደ በአል ነብያት ይመስል እ/ርን በማስመሰል እንዲያደርግልን ትግል ላይ እራሳችንን እናየዋለን እንደ ኤሊያስ በቀላሉ ፀልዮ ስራው ተፈፅሞ እንደማኘት ፈንታ።
“ዮሐንስ10/27 በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል።” በጎች(አማኞች ሁሉ የእረኛቸውን (የጌታ እየሱስ ክርስቶስን) ድምፅ መስማት ከላይ ተሰጥትዋቸዋልና መንፈሳዊ መብታቸውን ያወቁ ብፁአን(ደስተኞች ናቸው።“ሮሜ 8/14 በእ/ር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ የእ/ር ልጆች ናቸውና” የእ/ር ልጆች በስጋ ሳይሆን የሚመሩት በመንፈስ ነው። ጌታ አይምሮ አይደለም ጌታ መንፈስ ነው የሚናገረውም ለመንፈሳችን ነው። ድምፁን በመስማትም ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል። እውነትም አርነት ያወጣናል። ችግሩ ብዙ ክርስቲያኖች ግብፅን(አለምን) ለቀው እንደወጡ ቀይ ባህርን ተሻግረው (1ቆሮ10/12,ያም ተጠምቀው ማለት ነው ከባህር ዳርቻው ቤት ይሰራሉ።(DENOMNATION ~ሰው ሰራሽ የሀይማኖት ወግና ስርአት ባህል) ከዛ በነሱ ቤት የተስፋይቱ ምድር ገብተዋል ወይም የገቡ ይመስላቸዋል እራሳቸውምንም የእ/ር ወገን ሳይሆን የሰው ወገን ሆነው ያገኙታል። ይህም የልባቸው የመጀመሪያ ክፍል እ/ር እስከያዘ ዛናዊ ድረስ ሚልኩን ጠብቆ ቢሄድ መልካም እንደሆነ የሚያስተውሉና የሚጠብቁ ጥቂቶች ናቸው።
እ/ር የልባቸው የመጀመሪያ ክፍል ላይ ልኡል የሆነበት ሰዎች ከጊዜ ቡሀላ አንዳዶች እርካታ ያጣሉ። ከፋሲካውም ሆነ ከቀይ ባህሩም ከመጠመቁም የበለጠ የእ/ር ክብር መለማመድ እንዳለ ማስተዋል ይጀምራሉ። ክብሩንም ይራባሉ።(ፅድቅን እንደ እህል የሚራቡ ብፁአን ናቸው። ይጠግባሉና !)። ስለዚህም የሚመራቸውን መንፈስ የደመና ና የእሳት አምዱን መከተል ይጀምራሉ። ወደ ፅዮን ተራራ ስር የመራቸው እርሱ ነበር ።እ/ር በደመናና በእሳት አምድ የወረደበት ህዝቡም ሁሉ የእ/ርን ድምፅ በገዛ ቋንቋቸው ከዛ ውስጥ ሲናገራቸው የሰሙት ደግሞም አስርቱ ትእዛዛት የገለጠበት ቡሀላም ህዝቡ የበአለ ሀምሳ ቀን (ጴንጤቆስጤ ቀን/የዳስ በአልዘሌ23/15፤ዘዳ16/10፤ዘፀ13/16 ተመልከትየሚያከብሩበት ነው።ይህ ቀን መሆን የነበረበት ከዚያም ባሻገር እስራኤልሁሉ ሁለተኛውን የእምነት ደረጃ የሚሳተፉበት የሚለማመዱበት ወደ ተስፋይቱ ምድር መንገዳቸውን የሚያቀኑበት ነበር። እነሱ ግን የማይወሰነውን የእስራኤልን ቅዱስ ወሰኑት።
ወንድማችን ጳውሎስ “ በሮሜ 1/17 የእ/ር ፅድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣል ” አስተውሉ እ/ር ከአንድ የእምነት ደረጃ ከፍ ወዳለ የእምነት መጠን ሊያስገባን እራሱን ይገልጣል። ያም ድምፁን እንዳሰማን መጠን ነው ።
ደግሞም እኛም እንደተናገረን መጠን ስንሰማው ከእምነት ወደ እምነት እንቀሳቀሳለን። “እስራኤል ወደ ፅዮን ተራራ ስር በመጡ ጊዜ እ/ር ባህሪውን ወይም ህጉን በመስጠት ለነሱ አቋሙን ገለጠላቸው። ለነሱ እራሱን እንደገለጠ ለማንም የምድር ህዝብ እራሱን አልገለጠም። ይህም ህጉን በመስጠት ሲሆን ህዝቡ ግን ወደ ሁለተኛው የእምነት ደረጃ ለመግባት በፍርሀት የተሞሉ ሆኑ።በዘፀ፤20/18-19 ተመልከት)ህዝቡም ሁሉ ነጎድጋዱ ና መብረቁን የቀንድ መለከቱን ድምፅ ተራራውም ሲጠስ አዩ ህዝቡም ባዩ ጊዜ ተርበድብደው ርቀው ቆሙ ሙሴንም አንተ ተናገረን እኛም እንሰማለን። እንዳንሞት ግን እ/ር አይናገረን አሉ። ሙሴም ለህዝቡ እ/ር ሊፈትናችሁ ሀጢያትንም እንዳትሰሩ እርሱን መፍራት በልባችሁ ይሆን ዘንድ መጥተዋልና አትፍሩ አለ።
ህዝቡም ርቀው ቆሙ ሙሴም እ/ር ወዳለበት ወደ ጨለማው ገባ” ህዝቡም ላለ ሞሞት ስለፈሩ ከሚናገረው እ/ር ሸሹ። ድምፁን ላለመስማት ራቁ። እንደምናስተውለው እ/ር በእሳት ወርዶበት ወዳዘጋጀላቸው የጴንጤቆስጤ የእምነት ደረጃ በእምነት መግባትን እቢ አሉ። (ዋሪያት ስራ፤ም 2እ/ር በእሳት የወረደበት አይነት) የመሎኮትን ህግ ከመስማት ተቃወሙ። ህጉ በልባቸው እንዳይፃፍ ከሚናገረው እ/ር ከድምፁ ሸሹ። ህጉ በልባቸው በመንፈስ እሳት በውስጥ በልባቸው ሳይሆን በውጭ በድንጋይ ፅላት እንዲፃፍ ሆነ። ቅዱሱን ላለመስማት በመቃወም ለዘመናቸው የመጣውን ክብር ባለመታዘዝ ባለመስማት ገፉት።
የጴንጤቆስጤ ሙልአቱም ለሚታዘዝ ትውልድ ለሌላ ዘመን ተላልፎ ለትሁታኑ ሃዋሪያት የተጠበቀ ሆነ። የእ/ር መንፈስ በልባቸው ለውጥን እንዳያመጣ በመንፈስ የሆነውን መገረዝ እንዳይሰራ ሆነ። ከዚያ ይልቅ ህጉ በውጪ ሆኖ በድንጋይ ላይ ሆኖ ስለስራቸው የሚናገራቸው ሆነ። ከዚህ የተነሳ የተዘጋቸላቸውን የጴንጤቆስጤ የእምነት ደረጃ ስላልተለማመዱት ጴንጤቆስጤ ወደ ሌላ ዘመን ተላልፎ 1500 አመት የጌታ እየሱስ ሞትና ትንሳኤ ቡሃላ ሙልአት ሆነ። ደቀመዛምርቱ በሃዋሪያት ስራ እንደምናገኘው በላይኛው ክፍል ተሰብስበው በአንድ አላማ ተሰብስበው ድምፁን ለመስማትና የዴንጤቆስጤ መለኮታዊ መገለጥን ለመቀበል የተዘጋጁ ሆኑ። አባቶቻቸው በእሳት ወርዶ ሲናገር አንሰማም ያሉትን እነሱ ግን በዚያ ቀን ታዘዙ። በምድረ በዳ ውሀ እንደተጠማች ዋላ ተጠምተው ጠበቁት የፃድቁን መጠበቅ የማያሳፍረው ጌታም መንፈሱን በእሳት ነበልባል ምላስ መልክ አሳይቶ አፈሰሰባቸው።
የህይወትንም ውሃ ጠጥተው ረኩ ለብዙዎችም በረከት ሆኑ። እንዳስተዋልነው እ/ር ከማሀከላቸው ካስነሳው ከሙሴ ስር የነበረው ህዝብ የእ/ርን ድምፅ ላለስማት ስለተቃወሙና ህጉ በልባቸው እንዳይፃፍ አሻፈረኛ ስላሉ በሚቀጥሉት አመታት ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት አልቻሉም። ቅዱሱን እንዳይበድሉ ህጉን ቃሉን በልባቸው አልሰወሩምና ህጉን ግን በውጪ በየግድግዳው፤ በቤት መቃኖች፤በአሸንክታብ የሙሴ ህግ ልዩልዩ ጥቅሶች ፅፈው በግንባራቸው ማሳር ሆነባቸው። ፤ዘፀ13/9-16፤ዘዳ6/48፤ )። ምድሪቱን እንዲሰልሉ የተላኩት አስራ ሁለት ሰላዮች ምድሪትዋ የተትረፈረፈች መሆንዋን አዩ። ለማስረጃም የምድሪትዋን የወይን በኩራት ይዘው መጥተዋል።(ዘሁ 13/20)።
አስሩ ሰላዮች ግን ክፉ ወሬ አመጡ።በሰነፍ ምክርም የህዝቡን ታማኝ ሁኔታ አወኩት።አባቶቻቸውም በዚያ ዘመን እደነበረው አሰራር የንስሃ ቀን አውጀው የአስሩን ወሬ ከመስማት እምቢ ቢሉና {እዚህ ያደረሰን ደግሞም “ለመኖራችን ሚስጢር የሆነው እ/ር ”በሀይሉ ብርታት ወደ ምድሪትዋ ያስገባናል!።} ብለው መለከት ቢነፉ ኖሮ እዮቤሉ(ሰው ሁሉ ወደ ክብሩ የሚመስስበት የነፃነት አመት እ/ር እራሱ ያወጀው የእረፍት ጊዜ (ዘሌዋ፤ 25/8-13) በሆነላቸው ነበር። የሆነ ሆኖ ወደምድሪትዋ ለመግባት እምነቱ አልነበራቸውም። በቀድመው ጊዜ በፅዮን ተራራ ስር የእ/ር ድምፅ ላለመስማት ተቃውመዋል።
ያም የመጀመሪያው የጴንጤቆስጤ ነበር። አንድ ሰው ዘሎ ከፋሲካ ወደ ከንአን መግባት አይችልም ።የግዴታ በሚታዘዝ ህይወት የሂደቱን ደረጃ ጠብቆ እዛ ይገባል እንጂ።በነገራችን ላይ ፋሲካ በእብራይስጥ “ፓሳህ” ማለት ሲሆን ትርጉሙም ማለፍ ማለት ነው ) እስራኤላውያን በግብፅ አገር በግ አርደው በደጃፋቸው ደም በመርጨት ከሞት መልአክ ያመለጡበት ከግብፅም ባርነት ነፃ የወጡበት በአል ሲሆን። ፋሲካ (passoverይህም ሊመጣ ላለው ከመበስበስ(ከሞት ከሀጢያት ባርነት እንዴት ነፃ እንደሚያወጣን ትንቢታዊ የሆነ ገላጭ ስእል የሚያሳይ ጥላው ነው። አካሉ ግን ለአለም ሀጢያት ሁሉ የታረደው የእ/ር በግ ጌታ እየሱስ ፋሲካችን ነው። ይህም ከሞት ወደ ህይወት ያሳለፈን ነው።(ዮሀ 1/29 እነሆ የአለምን ሀጢያት የሚያስወግድ የእ/ር በግ ብሎ ያስቀምጠዋል። ዘዳ12/1-13, 1ኛቆሮ5/7,1ኛጴጥሮ1/18-19 ተመልከት) ወደ ሃሳቡ እንመለስና አንድ ሰው ከፋሲካ ምሽት ዘሎ ወደ ተስፋይቱ ምድር መግባት አይችልም። ወይም ከግብፅ ዘሎ ከንአን መግባት አይችልም። ፅዮን ተራራ ስር የተሰጠውን መገለጥ ዘግቶ አልፎ ዘሎ ከንአን መግባት የለም። ይህን ሊያደርጉ የወደዱ በአዲስ ኪዳን ህግ አልባህግ የሌላቸው ተብለዋል።(1ዮሀ3/4 እኛ ዛሬ ከእነሱ ብንማር ማትረፍያ ይሆንልናል።
የአሮጌው ኪዳን ላይ የደረሰው ምሳሌ እኛን ሊያስጠነቅቀን ነውና የተፃፈው። 1ቆሮ10/11 ከመፅሀፍ ስናስተውል የተለያየ የእምነት ደረጃ ያላቸው ክርስቲያኖችን እናያለን። በፋሲካ የሚመሰሉ (ከአለም የወጡ) እንዲሁም የጴንጤቆስጤ የእምነት ደረጃ የተለማመዱ ደግሞም በዚያው ላይ እየጨመሩ የእ/ር ጠላት የሆነውን ስጋዊ አይምሮን በሙልአት ድል ሊነሱ በሂደት ላይ ያሉትን እናስተውላለን። እነሱም የስጋውን መጋረጃ አልፈው ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ በመንፈስ ሊገቡ በጉ ወደ ሚመራቸው ተከትለውት በመሄድ ላይ ይገኛሉ። እስቲ እንዲገባን የቀደሙትን ድል ነሺዎችን አካትተን እንይ። በራእይ ምእ2፤3 ለሰባቱ ቤተክስቲያኖች መልእክት አለን። መልእክቱም ለሁሉም ቤ/ክ ነው። በመልክቱ መጨረሻ ግን እንዲህ ይላል “ድል ለነሳው ይህንና ይህንን እሰጠዋሁ” ይላል። በሌላ አነጋር የሚያሳየን በአቢያተክርስቲያን ሁሉም ድል ነሺ እንዳልሆነ ያሳየናል። በአዲስ ኪዳን ሃዋሪያው ጳውሎስ በቅድሚያ ትኩረት የሰጠው ለአዲስትዋ ቤ/ክ ነው። ያም በክርስቶስ እየሱስ ላሉ አማኞች ማለት ነው። በዚያን ጊዜ ጴንጤቆስጤ እ/ር ያደረገው አዲስ ነገር ነበር። እነዚህ አዲስ ክርስቲያኖች በጴንጤቆስጤ እንደ ድል ነሺዎች አርጎ ማሰብ አያስደንቅም። በጴንጤቆስጤ ቅባት ስር ለዘመናቸው ድል ነሺዎች ነበሩና።እነዚህ ሰዎች ከአሮጌው ትእዛዝ ከአይሁድ ስርአት የተጠሩ ናቸው።
ከሌዊ ስርአትና ትእዛዝ የተጠሩ እ/ር ወደ ሚያደርገው አዲስ ነገር የተጠሩ ነበሩ። ለቀናቸው ድል ነሺዎች ነበሩ። ከአሮጌው ኪዳን አገልግሎት የተጠሩ ከአሮጌው አምልኮ የተጠሩ ከአሮጌው እምነታቸው እ/ር ወደ አዲስ ስርአት ትእዛዝ ሲጠራቸው ከዛ ችለው ሊወጡ ችለዋል። ያ በሙሴ ዘመን በፊደላት በድንጋይ ላይ የተፃፈው የሞት ና የኩነኔ አገልግሎት ክብሩን እ/ር የመንፈስ አገልግሎት በማምጣት ሲሽረውና ሲያስረጀው ከእ/ር ኣዲስ አካሄድ ጋር ለመቀጠል ችለዋል። ሌሎቹ ግን ያ ይሻር የነበረው ክብር እና ብሉይ ሲነበብ ያስቀመጠው የልባቸው መጋረጃ ወደ ክርስቶስ ዘወር በማለት የመንፈሳዊ እይታ ግርዶሹን አልፈው እንዳይሄዱ የ“እቋሪ ውሃ አይፈወስም” ተብሎ እንደተፃፈ ይህም ስለማይንቀሳቀስ ማለት ነው። በነገራችን ላይ ወራጅ ውሃ ስለሚንቀሳቀስ ይፈወሳል።} አይሁዶች እዛው መታቆርን መጣበቅን መረጡ። መስቀሉ ጋር ሲደርሱም ተደነቃቀፉበት። በአይሁድም እምነት ተጠላልፈው ቀሩ። ”
“በነገራችን ላይ እስከ ሚገባኝ ድረስ ለዘመናችን በእ/ር ቃል በአይምሮ መታደስ በሚገኘው ከክብር ወደ ክብር እየተለወጠ ያንን መንፈስ የሆነውን የጌታ መልክ ፈፅሞ የመሰለ በመንፈስ ሙልአትም ፈፅሞ የተወረሰ ድል ነሺ በአለም ላይ የተገለጠ የለም። ሁላችንም ድል ለመንሳት የምንሰልል ነን እንጂ እንዲያዉም ብዝዎች የዚህ መገለጡ ስለሌላቸው ሃሳቡን እግዚያብሄር ማንሳት መቀስቀስ በመንፈሱ ሲጀምር የሚማር ልብ ከመያዝ ይልቅ የሰለጠነባቸው የስጋ ስራ ይገለጣል። ያለማወቃቸውን በማውገዝ በማሳደድ ይገልጣሉ። ጌታ እንደተናገረውም “ይህን ሲያደርጉባችሁ ደግሞ እ/ርን የሚያገለግሉ እየመሰላቸው ነው።” እንዳለ ያለእውቀት በሆነ ቅናት ሲያጠፉ ሳያቁትም ትንቢቱ ሲፈፀምባቸው ይታያል።ድል ለመንሳት ያሚሰልሉት ደግሞ አይን ያላየውን በሰውም ልብ ያልታሰበውን እ/ር ለሚወዱት ወዳ ዘጋጀው በመንፈሱም ወደ ገለጠው አለም ሳይፈጠር በክርስቶስ ወደተዘጋጀላቸው ክብር ለመግባት መንግስቱን የሚጫኑ ሀይለኞች በመንገዳቸው ሲያጠበጥቡ በመንፈስ ይታያሉ።
እንደ ጌታ እየሱስ ሁሉ እዚሁ ሁለት እግራቸው በቆመበት ይህን የስጋ መጋራጃ አልፈው ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ለመግባት የተያዙበትን የስጋ ፈቃድ ሁሉን የሚችለው እር እንዲሰብረው እየተሰጡ እንደ ጌታቸው ከሚቀበሉት መከራ መታዘዝን እተማሩ እንደ ጌታቸውም ፈቃድህ ይሁን እንጂ የኔ ፈቃድ አይሁን”ማለትን እተማሩ እውነት የሆነውን ሚያስቡ።
እ/ርን ለሚወዱት እንደ ሀሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ተያይዞ ለጥቅማቸው በሂወታቸው እንደሚሰራ ያወቁ። የቅዱሱን እ/ር የዘላለም አጀንዳ፤ ሃሳብ፤አላማ የልጁ መልክ እንዲመስሉ እንደነ ያስተዋሉ ሮሜ፤8/28-30 እንደሚያስረዳን ልጁ በብዙ ዎንድሞቹ መካከል በኩር(ታላቅ ወንድም) ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ያወቃቸዉን የልጁን መልክተፈጥሮእንዲይዙ አስቀድሞ እንደወሰነ የጠራቸውንም አፅድቆ እንዳከበራቸው ያስተዋሉ።
በእርሱ ወደ ታየላቸው መንፈሳዊትዋ ምድር በመንፈሱ እየተመሩ በመንፈስ እንዲገቡባትና የቤ/ክ ራስ የሆነው ጌታ እየሱስ አካሉ ክብሩን ለብሳ እና ተወርሳ በሮሜ፤8/19-21 እንደሚናገረን “ፍጥረት ሁሉ የእ/ር ልጆች መገለጥ በናፍቆት እንደሚጠባበቅ ይህም ፍጥረት ራሱ ከመበስበስ ባርነት ነፃ ወጥቶ ለእ/ር ልጆች ወደ ሆነው ወደ ከበረው ነፃነት እንዲያደርሱት” የሚያደርገውን ብቸኛውን በርሱ የታየላቸው ፍፃሜ የመጀመሪያውን የመንፈስ ፍሬ ያገኙ ሁሉ ሰውነታቸዉም ቤዛነቱን የልጅነት የክብር ሙልአት እንዲለብስ እንደፍጥረት ሁሉ በናፍቆት እየተጠባበቁ በውስጣቸው ይቃትታሉ። በዚህ ዘመን መጨረሻ ላይ ወደ ሚቀጥለው የእ/ር አሰራር ለመግባት በመንፈሱ አንቅቶ ድል እንነሳ ዘንድ ሁላችንን ይርዳን። የቀደሙት ለዘመናቸው የተዘጋጀውን የመንፈስ ፈተና ብዙዎች እንደተደናቀፉ።ጥቂት ህያው ምስክርችም ግን አካየዳቸውን ከእርሱ ጋር ያደረጉ በእ/ር ዘንድ እንጂ በሰው ዘንድ አልተገኙም።
የእ/ር ፈቃድ እንደገፉት ከመሆን እ/ር ይጠብቀን “በእ/ር የሚመካ እንጂ በራሱ የሚመካ ቢፈተን እንካን አያመልጥምና እንዴት ሰዎች ሊወድቁ ይችላሉ ? እስራኤል የእ/ር ድምፅ ወደ እሳቱ ቀርበው እንዳይሰሙ እንደራቁ ስስጋ እንዳይሞቱ እንደፈሩት ዛሬም አንዲሁ ነው። ሙሴ እንደቀረበው ያለፍርሃት ወደ እሳቱ እንደ መቅረብ ፈንታ ማለት ነው ወደሌላ አቅጣጫ ሮጡ። እ/ር አምላክ የሚባላ እሳት ነው። አንድም ቀን ሰው ወደ እርሱ የቃሉን ድምፅ ለመስማት ሲቀርብ በሚገባ ድምፁ ስጋን እንደሚገድል ደብቆ አያውቅም። እውነተኛ የእ/ር መገለጥ ስጋን ፈቃድ ሁሌ እንዲሞት ይጠይቃል። በልባችን ህጉን ሲፅፍ ስጋ ሁሉ በፊቱ ዝም ይላል።
ጳውሎስ ቀን በቀን ድምፁን ስለሚሰማ እለት እለት ስጋው ይሞት ነበር።(1ኛ ቆሮ15/31አንብብ። የጣኦት አምላኪዎች አምላክ አያዩም አይሰሙም አይበሉም አያሸቱም አይናገሩም ዘዳ 4/28” የመፅሀፍ ቅዱስሱ እ/ር ብቻ ያያል በዘመናት መካከልም ይናገራል። በሙሴ ዘመን እ/ር በፅዮን ተራራ በወረደ ጊዜ ከእሳት ውስጥ የቃሉን ድምፅ ሰጣቸው። እራሱን ገለጠላቸው ።“ዘዳ 5/24-25 ከእሳት ውስጥ ድምፁን ሰምተናል። እ/ር ከሰው ጋር ሲነጋገር ሰውየውም በሂወት ሲኖር አይተናል። ” በሌላ አነጋገር በቀደመው ቀን ለህዝቡ እራሱን የገለጠበት ቀን ሰውን ሳይገድለው ሊያነጋግረው እንሚችል አስተውለዋል።ግን እሱ ሲገለጥ ከሰዎች ዘንድ የስጋ ፈቃድ የሚባላ እሳት እንደሆነ ከሰዎቹ መልስ እናነባለን።25.አሁን እንግዲህ ይህቺ ታላቂቱ እሳት ታቃጥላለችና ለምን እንሞታለን እኛ የአምላካችንን እ/ር ድምፅ ብንሰማ እንሞታለን። ከስጋ ለባሽ ሁሉ እኛ እንደሰማን በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የህያው አምላክን ድምፅ ሰምቶ በህይወት የኖረ ማነው” ሰዎቹ በግማሽ ትክክል ነበሩ። የህያው እ/ር ድምፅ ስጋን እንደሚገድል ትክክል ነበሩ።
የመጀመሪያ የጴንጤቆስጤ የበስተጀርባው አላማ ይህ እንደሆነ አልተረዱም። እ/ር ያቀደው ድምፁን በማሰማት ስጋን በመግደል ከሰጋቸው ፈቃድ ተፅኖ ተላቀውና ከግርዶሹ ከመጫጫኑ ከብዥታው ውጪ ወደ መንፈሳዊው ፈቃዱ እንዲገቡና በመንፈሳዊ አለም ፈቃዱ እንዲመላለሱና እንዲዋኙ ነበር። ችግሩ ሰዎቹ ለስጋ ፈቃድ እንዳይሞቱ ፈሩ እዛው ስጋዊነት ላይ ሊቀሩ።አንድ ያላወቁት ነገር ደግሞ እሽሩሩ የሚሉለት ስጋቸው በእውነታው በመንፈስ ሲታይ የሞተ እንደሆነ አያውቁም። ደግሞም እውነተኛ ህይወት ያለው ለስጋ ፈቃድ በመሞት እንደሆነ አልተገነዘቡም። የዘመኑ አማኞች ችግርም ይሄ ነው። ለስጋ ፈቃድ ተሞቶ ነው በመንፈሳዊ ፈቃድ መወረስ የሚመጣው። ይሄ ነው በክርስቲያን እምነት ውስጥ መጀመሪያ ሲሰሙት እውነት የማይመስል እውነት። አንድ ሰው ህይወትን በመሻት ብቻ አያገኝም ለስጋው ፈቃድ በሞሞት እንጂ ።ለዚህም በሩ ጌታ እየሱስ ነው የክርስቶስ እየሱስ የሆኑቱ ስጋን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሰቀሉት ገላ5/24 ግን መስቀሉ ለብዙዎች መደናቀፊያ ሆነባቸው። እውነተኛ የእ/ር ቃል የስጋን ፈቃድ የማይገድል አይቼ አላውቅም። የመታዘዝን መንገድ የሚዘጋውን ስጋን ሁሌ ያስወግደዋል።
ቃሉ የሚባላ እሳት ነው። ለስጋዊው ሰው መብረቁ ነው። በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ለሆነው ለውስጠኛው ሰው ደስታው ነው። ለመንፈሳዊው ህይወት ማስገቢያው ጎዳናው ነው። እ/ር ለሰው የመናገሩ ዋንኛ አላማ የእርሱን መንገዶች ሊያስተምረን ሊያሰለጥነን ነው።(ዘዳ 4/36°ያስተምርህ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን አሰማህ በምድር ላይም ታላቁን እሳት አሳየህ ከእሳት ውስጥም ቃሉን ሰማህ”ማስተማር(እንግሊዝኛያሰለጥንህ ዘንድ ይለዋል)የሚያመለክተው እውቀትን ማካፈል ነው።
የማሰልጠን ወይም የማስተማር መንገድ የሚጀምረው በትእዛዝ ነው። በአብዛኛው አንድ አባት ትንሽ ልጁን ምን ማድረግ እንዳለበት ሲነግረው ወይም ያለገለፃ ሲነግረው ማለለት ነው። ለትምርታችን ከተፃፈው የእግዚያብሄር ቃል “ምሳሌ 22/6 ልጅህን በሚሄድበትምራው በሸመገለ ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም” ትንሽ ልጅ ገባውም አልገባውም አባቱን መታዘዝ መማር አለበት። ቀለልያለ መታዘዝ ስለመታዘዙ ግዴታ መጀመሪያ እድሜዎቹ ላይ መማር አለበት። ከዚያም ልጁ ማደግ እንደጀመረ ጥያቄዎችን መጠየቅ ይጀምራል። አባቱም ልጁ ከታዘዘ ቡሀላ ይመልስለታል። በመጨረሻ ትንሹ ልጅ ወደ መንፈሳዊ ብስለት ሲቀርብ አባቱ ወለልያለ መረዳትን ይሰጠዋል። ልጁ በዚህ የአባቱን እቅድ ማየት ይጀምራል። በዚህም መረዳት የአባቱን ፈቃድ ከግልፅ ትእዛዝ ውጪ በፈቃዱ መፈፀም ይጀምራል። በመጨረሻ እንደ በሰለ ወንድ ልጅ ወይም ሴት ልጅ አባቱ ሲያደርገው ያየውን ብቻ ያደርጋል። እንዲሁም አባቱ ሲናገር ያየውን ብቻ ይናገራል። ከአክብሮት ጋር አሁን የሰማይ አባቱን መልክ ይዘዋል። ከአባቱም ጋር ሙሉ በሙሉ ይስማማል።ጌታ እየሱስ እንካን “እኔ የአባቴን ፈቃድ እንጂ የራሴን አላደርግም” አለ።ልጁም የአባቱን ፈቃድ ያለግዴታ መፈፀም ይጀምራል። ይህም በደስታ ከፍቅር የተነሳ የአባቱን ፈቃዱን ይፈፅማል።
ጌታ እር በተለያየ ስም እራሱን ለፍጥረት የገለጠበት የአመራር ዘርፍ
እ/ር አባት እና አምላካችን በመፅሀፍ ቅዱስ እራሱ የተገለጠባቸውና የተጠራባቸው ብዙ መለኮታዊ ስሞች አሉ። መፅሀፍ ቅዱስ ስም የሚገልፀው ተፈጥሮ ና ባህሪይን ነው) እነዚህ ስሞች ልዩ ትርጉም ና ብርቱ መልክት ጥልቅ ሚስጥር ያላቸው ናቸው። ከአማርኛችን ስነ ፅሁፋዊ ዘዬ የተነሳ በመፅሀፍ ቅዱስ በአብዛኛው በልዩ ልዩ ስፍራ የሚገኙ ታሪኮች በቅኔ መፃህፍት ውስጥ ያሉ ግጥሞች በቡሉይ ኪዳን የእብራይስጡን በአዲስ ኪዳን የግሪኩን ስነ ፁሁፋዊ ቅርፅ ተከትለው በግጥም አደራደር ስልት እንዲሰደሩ ተደርገው ተተርጉመው ተቀምጠዋል። ስርአተ ነጥቦች የአንቀፅ አከፋፈሎችና ርእሶች ከሞላ ጎደል የእንግሊዝኛ ትርጉሞች መሰረት በማድረግ የተሰሩ ናቸው። ከአማርኛ ፊደላት ባህሪ የተነሳ እ/ር እራሱን የገለጠባቸው መለኮታዊ ስሞቹ አብዛኛዎቹ የት የት እንደተጠቀሱ ለመለየት አይቻልም። ስሞቹ እግዚያብሄር፤ አምላክ፤ ጌታ ወዘተ…ተብለው ተተርጉሞዋል። ከእ/ር ስሞች ለምሳሌ ኤሎሂም፤ያህዌ፤አዶናይ፤ኤልሻዳይ ወዘተ. እንዳሉ የታወቀ ነው። ከአዲሱ መደበኛው ትርጉም ከመቅዱሙ የተጠቀሰ] ።ዛሪ ለማየት የምንፈልገው ኤልሻዳይ ና ያህዌ በሚል እ/ር የተገለጠባቸውን ስሞችን ነው። ከተቻለም ሌሎችን ለመግለጥ እንሞክራለን።
ከሙሴ በፊት ቅዱስ እ/ር አባት ና አምላካችን በመጀመሪያ እራሱን ለአብራሀም ይሳቅ ለያቆብ የተገለጠው ኤልሻዳይ (elshaddai በሚለው ስሙ ነበር ። ዘፀ 6/3 ተመልከት የስሙም ትርጉም ሁሉን የሚችል እ/ር ተብሎ ተቶርጉሞዋል)። በኦሪት ዘፍጥረት እንደምናስተውለው የፍጥረት መገኛ ምንጭ እ/ር እራሱ ነው። በነገራችን ላይ “ኦሪት ዘፍጥረት” የሚለው የአማርኛ ስም ከእብራይስጡ ና ከግሪኩ ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው። “ኦሪት”ማለት እንደ አገባቡ ህግ፤ ፍትህ፤ትእዛዝ ማለት ሲሆን’ፍጥረት ”ማለት ደግሞ እንደ አገባቡ መፍጠር፤መፈጠር፤አፈጣጠር ፤ፈጠራ፤ ፍጡርነት፤ ጥንት፤ዘር፤ስር፤ምንጭ፤ልደት፤ትውልድ ማለት ነው።ፍጥረት”ከሚለው ቃል ፊት የሚገኘው “ዘ`የግእዝ ዘርፍ አያያዥ መስተዋድ ሲሆን የአማርኛ አቻው “የ ነው። ስለዚህኦሪት ዘፍጥረት”ማለት የፍጥረት ህግ፤የአፈጣጠር ደንብ፤የፍጥረት ስር ፤የፍጥረት ምንጭ፤ የፍጥረት መገኛ፤ የፍጥረት ውልደት፤ የፍጥረት ልደት፤ የፍጥረት ትውልድ ማለት ነው።
ኤልሻዳይ ወይም ሁሉንቻይ ይህ የጌታ ስም የሚያሳየን የተገለጠበት ባህሪው ና ተፈጥሮው በዘፍጥረት ለፍጥረቱ የተገለጠው እንዲገባን መንፈሳዊውን እውነታ በሰው ቋንቋ እናስቀምጠውና ለፍጥረቱ በእናታዊ የአመራር ዘይቤ የተገለጠበት ዘመን ነው።ሁሉ ከእርሱ” የሚለው ቃል በግሪኩ ሁሉ ከእርስ ወጥተዋልና”የሚል ሃሳብ አለው። ይህም እ/ር የፍጥረት መገኛ ምንጭ መሆኑን ያስተምረናል። ህፃን ልጅ በመጀመሪያ እምቦቀቅላ የማደጊያ ዘመኖቹ እንደሚደረግ እንክብካቤ እ/ርም በዛ መልክ ፍጥረቱን ቀስ በቀስ ወደ ሚፈልገው የብስለት ደረጃ እስኪ ያመጣው ድረስ ሲያሳድገው ሲኒከባከበው እናስተውላለን።እ/ርም ከብዙ አመት ቡሃላ ለሙሴ ያህዌ ”በሚል ስሙ ተገለጠለት። ይህም እ/ር እንደ አባት እራሱን የገለጠበት ጊዜ ነው። ለህዝቡም ስነስርአትን በህግ ምክንያት ሊያስይዝ የተገለጠበት ነው።
ይህም ማለት እኛ ወደ ክርስቶስ እንድንመጣ የምንበስልበት ነው። “ገላ 3/24 ተመልከት. ህግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣን ሞግዚታችን ሆነዋል።”ከህጉ ስርአት ውጪ ህግ አልባ ልጅ ሆነን ነው የምናድገው ወይም አጥፊ ልጅ ሆነን ነው የምናድገው። አሊያም ለሌሎች መብት ንብረት ግዛት ያለን ክብር ትንሽ ይሆናል ወይም ጋጠወጥ ባህርይው ይታይብናል። የእ/ር ህግ የተሰጠው (philo,ፊሎ የተባለውን ፍቅር ደረጃ ሊያስተምረን ነው። በዚያም መንገድ ወደ አጋፔ (Agape)መለኮታዊ ፍቅር አድገን ባህሪያችን ሆኖ የበሰሉ የእ/ር ልጆች ሆነን የማይታየውን የአባታችንን መለኮታዊ ባህሪ በስጋችን ይገለጥ ዘንድ ነው።በነገራርችን ላይ ህግ በራሱ ከፍ ያለውን ሉአላዊ የመለኮት ፍቅር አይገልፅም። ህግ የሚገልፅልን (philo)ፍቅርን ነው። እነኝህ የግሪክ ቃላት በአዲስ ኪዳን የሚገኙ ናቸው። ሁለቱም “ፍቅር” ተብለው ተተርጉመዋል።philo ፍቅር ማለት ወንድማዊ ፍቅር ማለት ነው።
Agape ፍቅር ማለት መለኮታዊ ፍቅር ማለት ነው።አጋፔ ከሁኔታዎች ውጪ አንዴ የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ መውደድ የቻለ ነውና አለሙን እንዲሁ ወዶ አንድያ ልጁን ሰጠ። በመጨረሻ እ/ር “ኤል ኤልዮን” (elelyon ,the most high GOD)ይህም በሉአላዊ አምላክነቱ የተገለጠበት ነው። በዘፍ14/18 የሉኡል አምላክ እ/ር ካህን ተብሎ የተተረጎመው ነው። ይህም ጌታ እየሱስ ታላቁ ሊቀ ካህን እኛም ልጆቹ በአመራሩ ስር ካህናት የሆንበት ስርአት ነው። እነኝህም የእ/ር ልጆች ከክርስቶስ ጋር በምድር የሚገዙ ናቸው። ራእይ 5/10፤20/6 እብ7/1-3ተመልከት።እ/ር ለፍጥረቱ የሚገለጠው በእነዚህ የማይለወጡ መንፈሳዊ አሰራሮቹ እንደሆነ ከቃሉ እናስተውላለን። ማንም ህፃን በተፈጥሮ የተመጣጠነ የእናት ጡት ወተት ዘሎ ወይም አልፎ እንጀራ መብላት አሊያም ብርንዶ መቁረጥ ቅልጥም መቀልጠም አይጀምርም። ወይም የህፃንነት እና የእምቦቀቅላ የአፍላ ጊዜ እድሜው ላይ በዳዴ መሄድ ሳይጀምር ዘሎ መራመድና መሮጥ አይጀምርም። በቅደም ተከተል እዛ ይደርሳል እንጂ።
ደግሞም ልጅ ሳለ የተወደደ የወላጁን ግሳፄ አልፎ ባደገ ጊዜ የሚፈለግበትን ባህሪ ይደርሳል ማለት አይቻልም። አንድን ህፃን ወደ ብስለት ደረጃ ለማምጣት ጊዜ እና ሂደት እንደሚወስድ ሁሉ እንዲሁ መንፈሳዊ ልጆችን ወደ ብስለት ለማምጣት ጊዜ ይወስዳል። ይህንንም ሂደት በሙሴ ስር ከነበሩት የእስራኤል ልጆች ላይ አይተነዋል።ሰወስቱ መንፈሳዊ የደስታ በአላቸው እ/ር ያለማመዳቸው 3 የብስለት ደረጃዎችን ያሳዩናል። ፋሲካ የሚያሳየን የመጀመሪያ ደረጃ መንፈሳዊ የእድገት ደረጃን ነው ።በዚያ ከእ/ር ጋር ያለንን የመጀመሪያው በጌታ የሆንበት የግል ህብረታችንን ያሳየናል። በእምነት መፅደቅን ያሳየናል። እስራኤል በበጉ ደም አምነው እንደዳኑ ይህ የመጀመሪያ ደረጃ የሚያሳየን በክርስቶስ መንፈሳዊ ህፃናት የሆኑትና ለቀለባቸውም የቃሉ ወተት እንደሆነ ነው። እንዲሁም ብዙ ትእዛዝ እ/ርን ያዛሉ አንድ ህፃን ሁሌ መታቀፍ እንደሚሻ መመገብ ግፋ ሲል መጋት እንዲሁ መለወጥ ይገባችሀል። ይህ እጅግ ያልበሰ የግንኙነት ደረጃ ነው። ቤቢ ክርስትያን አሁን ዳግም እንደተወለደ ያምናል ከዛም እንደሆነ ሆኖ አንድ ምኞት አለው ስልጣን መንፈሳዊ ርስቱ ሁሉ ለእ/ር ልጆች የተጠበቀ እንደሆነ ሀሳቡ አለው” ገላ 4/1 ነገር ግን እላለሁ ህፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም ነገር ግን እስከተቀጠረለት ቀን ድረስ ከጠባቂዎችና ከመጋቢዎች በታች ነው”።
የበአለሀምሳ ቀን የጴንጤቆስጤ በአል ልምምድ ደግሞ ነበር አሁንም አለ። በቀደሞቹ በዘመናቸው ይሄ ደግሞ ለአባቶች ህግ በድምፅ የተሰጠበት ነው። ጴንጤቆስጤ በአል የእ/ር ልጆችን ለሁለት ክፍል የከፈለ ነው። የሚታዘዙትና አመፀኞች። ይህ ትእይንት በምድረበዳ በእስራኤል ታሪክ ውስጥ እናስተውላለን። ህዝቡ አባትን መስማት በተቃወሙ ጊዜ ሙሴ ግን ታዞ ነበር። ቡሃላም እያሱና ካሌብ መንፈስን የሚሰሙበት ጆሮ እንደነበራቸው አይተናል። ክፉ ወሬ ይዘው ከመጡት 10 ሰላዮች ጋር አላበሩም። በምክራቸውም አልገቡም። በቤተክርስትያን በዴንጤ ቆስጤ ዘመን አንድ አይነት ምሳሌ ሲገለጥ እናስተውላለን። ጌታ እ/ር ለሰባቱቤተ/ክ መልክትን ሰጠ ግን ድል ነሺዎቹ ብቻ ጌታን የሰሙትና የታዘዙት። ድል ነሺዎቹ ብቻ ናቸው እውነተኛ ዴንጤቆስጤዎች። ድል የነሱት ብቻ ናቸው የመለኮትን ህግ ለመስማት የፈቀዱት። በሙሴ ስር የነበሩት እስራኤል ተቀባይና የሚማር ልብ ቢኖራቸው ኖሮ እ/ር ህጉን በልባቸው በፃፈው ነበር።
በውስጣቸውም ተፈጥሯቸው ባረገው ነበር። የቃሉ ሂይወት በነሱ ላይ ተዋህዶ ሂወታቸው በሆነ ነበር። በመጀመሬያ ቃል ነበር ።ቃልም እ/ር ነበር። ህይወትም በቃል ውስጥ ነበረች። በቃሉ ውስጥ ያለችው የእ/ር ህይወት ለሰው ብርሀኑ ነች። የእ/ር ህይወት በቃሉ ውስጥ ነው። አሁን የእ/ር ቃል ሲሰሙ እነሆ በእ/ር ህይወት ተነኩ። እስራኤልም ህጉን (ቃሉን) ቢሰሙት ኖሮ ከነሱ ጋር ተዋህዶ እንደ ተፈጥሮቸው ይሆንላቸውና በቀላሉ በታዘዙት ነበር። በዚህም ስርአት ያላቸው በሆኑ ነበር። የሆነ ሆኖ እስራኤል በቀጥታ የእ/ርን ድምፅ ከራሱ መስማትን ተቃወሙ ከዛ ይልቅ የመረጡት ሙሴን ወደ ሲና ተራራ መላክና በነሱ ምትክ እንዲሰማ ነበር። ስለዚህ ህዝቡ የእ/ርን ድምጥ የሰሙት በተዘዋዋሪ በሙሴ በኩል ሙሴ እ/ር እንዲህ ይላል ብሎ የነገራቸውን ነበር።
ህጉም በውጪያቸው ቀረ። እ/ር እንዳዘዘ ከውጪ የሚጫንና የሚያስገድድም ሆነባቸው። ልክ አመፀኛ ልጅ ትእዛዝ ሲነገረው አሻፈረኝ ብሎ በራሱ መንገድ እንደሚሄድ ሆኑ። ህጉ በስጋዊ አይምሮ ሲታይ ሻካራና የማይስማማ ይመስላል በፃድቁ እ/ር አባት ህጉ ታስቦ የተሰጠው ግን የአመፀኛ ልጆችን ፈቃድ ለመስበር ነበር። ስለዚህም እነሱም በተግባር ከጌታ እየሱስ ጋር ሆነው እንዲህ ማለትን እንዲችሉ’ሉቃ22/42.ነገር ግን የኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ” ወይም እንደ ዳዊት መዝ118/71 ስርአትህን እማር ዘንድ ያስጨነከኝ መልካም ሆነልኝ ካአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ህግ (ቃል ይሻለኛል” ይህ ነው ከተቀበለው መከራ የተነሳ መታዘዝን የተማረ ልጅ የመቃተት ጭሆት። ለኛ የአባታችን ግሳፄ በመጀመሪያ ባልበሰለው እይታችን አሳዛኝ ነው። ነገር ግን በተፈቃሪው የመለኮት ህግ ግሳፄ ህጋዊ የእ/ር ልጆች በስልጠና ላይ መሆናችንን እንደሚያሳየን ከህያዋን ዘንድ ከትውልዱ ማን አስተዋለ ? “እብ12/5-8 ተመልከት ከግሳፄ ውጪ ወደ መንፈሳዊ ብስለትና ወደ ፍፅምና አሊያ አንመጣም።
ለትምርታችን ይህን እናገራለሁ ዛሬ የብዙ ክርስቲያኖች ችግር ለራሳቸው ከእ/ር በቀጥታ ከመስማት ይልቅ በሰው ላይ ያረፈው ወይም በአንድ ሰባኪ ወይም በአንድ የሀይማኖት ተቋም ሆኖ የሚታይበት መሰረታዊ ምክንያት መካከል የምናስተውላቸው ችግሮች አሉ። በሌላ አነጋገር ስለነሱ ወደ ተራራ ሄዶ የእ/ርን ቃል በምትካቸው እንዲሰማ ሰውን ይጠብቃሉ። ሰባኪውም በሳምንት አንዴ ወይም ሁለቴ ይወርድ ይመጣና የእ/ር ቃል ምን እንደሆነ ይናገራል። ይሀውም ሰባኪው የታመነ የእ/ር ቃል ካመጣ ነው። ያም ቃል በህዝቡ ላይ ይሰበካል ቃሉም ከውጪ ምንጭ ወደነሱ ይመጣል። የእ/ር ቃል ከውጪ ምንጭ መስማት ችግር የለበትም። መረሳት የሌለበት እ/ር በሌሎች ሰዎች ይናገራልና ደግሞም ያስተምራል። ኤፌ4/12.የእ/ርን ልጅ በማመንና በማወቅ በሚገኝ የክርስቶስ ሙላት ወደሚሆን ሙላቱ የክርስቶስ አካል በርሱ ወደታየላት ፍፅምናብስለት) ለማምጣት ሰዎችን የተለያየ ፀጋ ተሞልተው እንደ ስጦታ ተሰጥተዋልና ።ችግሩ ያለው ሰዎቹ ሰውየውን ሲሰሙት ነው። በእርሱ ውስጥ የሚናገረውን የእ/ር ድምፅ ሳይሆን ስጋዊ ፈቃዱን ማለት ነው።
ይህም ሰዎቹ ያሉበት መንፈሳዊ የብስለት ደረጃ የስጋንና የመንፈስን ፈቃድ የመለየት ደረጃቸው ያላደገ መረዳት ሲሆን ነው።በትክክል በውስጣችን ባለ የእ/ር ድምፅ ስንመራ መንፈስ እራሱ በውስጣችን ይመሰክርልናል። እንዲያውም ሰባኪው ሳያውቅ እርሱ እየሰበከ ጌታ ብዙ ያስተምረናል። የሚናገረውም ቃል እኛ ጋር ሲደርስ በመንፈስ መብራት በውስጣችን በርቶ ይነበባልዮሀ14/17.እርሱ አለም የማያየውና የማያውቀው ስለሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው። ነገር ግን ከእናት ዘንድ ስለሚኖር በውስጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቁታላችሁ..ዮሀ16/13 እርሱ የእውነት መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችሀል..የሚመጣውንም ይነግራችሀል, ዮሀ17/17በእውነትህ ቀድሳቸው ቃልህ እውነት ነው”።መንፈስ የማይመሰክርልንም የሚመስለን ጊዜ አለ እዛጋ ነው እንግዲህ ችግሩ መነሳት የሚጀምረው። ሰባኪው (ዲኖሚኔሸኑ ህዝቡ የእ/ርን ድምፅ ለራሳቸው እንዲሰሙ ነፃነቱን ከሰጠ በህዝቡ ዘንድ የአመለካከት ልዩነት ይታያል ። ይህ እ/ር እራሱ በራሱ የሚፃረር ሆኖ አይደለም።
ነገር ግን እኛ, ሁል ጊዜ መንፈሳዊውን ነገር የመስማት ችሎታችን የልባችን ሁኔታ ስለሚወስነው ነው። 2ኛ እ/ር አብዛኛውን ጊዜ ለአንዱ የተወሰነ መረዳት ለሌላው በዛው ጉዳይ የጠለቀ እይታንና መረዳትን ስለሚሰጥ ነው።የተለያዩ አመለካከቶች በቀደመው ቤተክርስቲያን ላይ ነው የጀመረው። እንዲያውም በሀዋሪያት መካከል ነበር ።
በ4ኛው ክፍለ ዘመን ቤተክርስቲያን ከስደቱ ቡሃላ ያ መቆም ሆነ። ክርስትና ወደ ሀይማኖት መጠምዘዝ ጀመረ። በቤተክርስቲያን መማክርት ምክር ዘዴዎች መዘያየብ ተጀመሩ። የሰዎችን ልዩነት ወደ አንድ እይታ ለማምጣት ኦርቶዶክስ(orthodoxy) ተብሎ የሚታወቀው ይህም ክርስቲያኖችን በመግደል በእሳት በመሰዊያው ላይ ሲሰዋቸው ማየት በዚያ ዘመን የተለመደ ነበረ።ከነዚያ ጊዚያት ቡሀላ ቤተክርስቲያን ሰዎች ለራሳቸው የእ/ርን ድምፅ ለራሳቸው መስማት ብሎ ነፃነት አስተዋቻቸው። በዚህ መሰረት መለያየት ጉልበት አገኘ። ከእ/ር የመስማቱ መብት በአንድ ሰው ላይ አረፈ። የሮማ ቢሾፑ ላይ ሰውየውም የእውነት የመጨረሻ ስልጣን ሆነ። እዛጋ ክርስትና ወደ ሀይማኖት ተከረበተ (ተገለበጠ፤ተቀየረ፤ሌላ ገፅታ ያዘ ሰውም ከእ/ር ድምፅ ይልቅ የሰው ድምፅ እንዲሰማ በግፊቱና በተፅኖው ተገደደ።
ይህንም የእ/ር ድምፅ ካለመስማት የተነሳ የመጣውን ሉይነት መፍትሄ ለመስጠት በመጀመሬያ የቤተክርስቲያን መማክርት በ325AD(ከጌታ ልደት ቡሀላቢሾፑ በፖለቲካ ሀይል የኦርቶዶክስኛ ደንቦችን አወጁ። አዋጆችም ማመቻመች፤ መሸንገል ለሁለት ወገኖች አንዳንድ ነገሮችን በመተው አለመግባባትን ማስወገድ) ድጎማ በመስጠት የነፃ ትምህርት እድልሰኮላርሺፕ በመስጠት የሞት ፍርድን በመፈፀም በውግዘት የተሞላ ነበር። ከመለኮታዊ አመራር ይልቅ የስጋዊ አመራር ተገለጠ።ዘሁ 12/3በዘመኑ ከነበሩ ሰዎች ይልቅ ትሁት የነበረው የሙሴን ምሳሌ ቢከተሉ በተሻላቸው ነበር። ገና ጌታ ህጉን ሳይሰጥ አንድ ነገር ሲነሳ ወደ እ/ር ይፀልይ ነበር ።ለምሳሌ ዘሁ9/6-14 ተመልከት። ቢሾፑ ይህንን ቢያረጉ ኖሮ እ/ር የገዛ ትቢታቸውን ገልጦላቸው ንስሀ እንዲገቡ ባረጋቸው ና ስለምኞታቸው መፈፀም እንዳደረጉት በገለጠላቸው ነበር። ይህም እ/ርን ከመስማት ይልቅ እንዳደረጉት ከጥፋታቸው እንዲመለሱ አርጎ በአርሱ ልብና አይምሮ ያለውን በመንፈሱ ባፈሰሰላቸው ነበር።
እነርሱ ግን ከዛ ይልቅ በራሳቸው መማክርት ለቤተክርስቲያን ወግ ባህል ሰዋዊ ዘይቤ መዘየብ መመስረት ጀመሩ። ልክ በጌታ እየሱስ ጊዜ ይቃወሙት እንደነበረው በአሮጌው ኪዳን የሂደት ዘመን የተመሰረተው ሀይማኖት አይነት ማለት ነው።
ከ1500አመት ቡሀላ የተሻሻለው ዴንጤቆስጤ ከሮም ሃይማኖታዊ ቤተክርስቲያን ተነጠለ። ከዛ ወዲያው የተለያዩ አስተያየቶች ነበሩ። አብዛኛዎቹ የሀይማኖት ድርጅቶችም ሰዎች እይታቸውን ብቻ እንዲከተሉ የተለያየ የስደት መጠን ያመጡባቸው ነበር። ያወግዙዋቸው ነበር። ባገኙትም ኣጋጣሚ ያጠቁዋቸው ነበር ።በአገራችንም ይህ የስጋ ስራ ተገልጦ እንደታየ መረጃው ያላችሁ ታውቁታላችሁ። በመጨረሻም አሁን በምንኖርበት በምእራቡ ክፍለ አለም በአሜሪካ ሰው ሁሉ ህሊናው እንደፈቀደ የእርን ድምፅ ይሁን የሰውን ድምፅ መስማት እንደፈለገ የወደደውን እዲሰማ ነፃነት ታወጀ። ይህም ሰውን ሰምተው መታዘዝ ከመረጡ ነፃነታቸው የተጠበቀ እንደሆነ አወጀ ።
ይሄም የመጨረሻውን ችግር መፍትሄ አልሰጠም እርግጥ ቢያንስ ሰዎች አንድ የሀይማኖት መሪሳይሆን ያለ ተፅኖ እ/ርን ለመስማት ይችሉ ዘንንድ ነፃነት አገኙ። ከዚያም ማንኛውም (denomination) በአንድ ሀይማኖታዊ ቡድን የሚያምኑ ሰዎች የሚጠሩበት ስም ነው እራሳቸውን እንደ እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን መመስረት ጀመሩ ። መዋቅሮቻቸውንም ለመግጠም ደህንነት የሚጠይቅ አደረጉ። ለመሪዎች ውሳኔ እንዲገዙ የሰዎችንም ጥበብ እንዲቀበሉ ያልተቀበሉትም የስህተት እንደሆኑ መስበክ ተጀመረ ።መካከለኛ መረዳት ያላቸውን አማኞችን ፑልፒቱ ላይ ክርስቶስን ከመስበክ ይልቅ የሚያሰሙዋቸው ትምርታቸው ጥቅማቸውን የተጠበቀ እንዲሆን ሲሉ የሚሰብኩት በተጠንቀቅ ተጀምሮ በተጠንቀቅ የሚያልቅ ሆነ።
ይህም ብዙዎች ላይ ከፈጠረው ፍርሃት የተነሳ ባላቸው ውስንነት ላይ ውስንነትን ጨመረ ይህም ለመንፈሳዊ እድገታቸው አዝጋሚነት ከሌሎች ሁኔታዎች ጋር ማወፋሬያ እስራት ሆነ።በዚህና በመሳሰሉት ሂደቶች ውስጥ ክርስትና ከአንድ ነጠላ ኦሮቶደክስኛ ሀይማኖት አሰራር ወደ ተለያየ የበዙ ትንንሽ ሀይማኖቶች ተሰበጣጥረው በዙ። ሁሉም እውነተኛ ቤተክርስቲያን የራሳቸው መዋቅር እንደሆነ የሚያስብ ሆነ። በዚህም ባህል የተነሳ ብዝዎቹ እውነተኛ ቤተክርስቲያን የሚለው ሀሳብ ማለት ሰዎች መሆናቸው መገለጡ የላቸውም። እንዲያውም ካለው መንፈሳዊ ቅናት የተነሳ መዋቅሮች እንደ እውነተኛ ቤክርስቲያን ወሰዱ። በነገራችን ላይ መዋቅሮች ላይ ችግር የለበትም አሊያማ ዘብራቃ ሂደት ሊሆን ነው። መዋቅር ሚዛናዊ ሂደታቸውን ከጠበኩ መልካም ናቸው ። እ/ርያለው ፍላጎት ከግለሰቦች ጋር ያለው ህብረት ለእያንዳዳቸው መናገርን ነው ። እያንዳዳቸው እራሳቸውን ችለው የእ/ርን ድምፅ በነፃነት እንዲሰሙ ነው። በጎች (አማኞች) ሁሉ የእረኛቸውን ድምፅ ይሰሙ ዘንድ መንፈሳዊ መብታቸው መሆኑን ማወቁ ላይ ሀይል አለው።
ይህ ሲባል ደግሞ የማይለወጡ የእ/ር አሰራሮች አሉ። እ/ር በሰዎች ይናገረናል፤ በተፈጥሮም ይናገረናል። ለራሳችን በሚገባን በብዙ መንፈስ እንደወደደ ረቂቅ አሰራሩ ይናገራል። “መንፈሱ አንድ ነው። አሰራሩ ግን ልዩ ልዩ ነውና። እ/ር በሌሎች ሰባኪዎች ወይም አስተማሪዎች ሲናገርና ሲያስተምር በውስጣችን ባለ በሁለት ምስክርነት ተደግፈን በስማት አለብን። ይህም መለኮታዊ ህግ ነው። “ምስክርነት በሁለት ይፀናልና “ግን ይህ መሎኮታዊ ህግ የሚሰራው የመሎኮት ህግ (ቃል)በልባችን ከተፃፈ ነው“የእ/ር ቃል በሙልአት ይኑርባቹሁ”። (በነገራችን ላይ የሚያነብ ህይወት ያለው ሰው የተባረከ ነው። በማንበብ ውስጥ ሀይል አለና) ሁላችንም እ/ር በሁለት ምስክርነት double witenss)እንዴት በተግባር እንደምንጠቀምበት ሊያስተምረን ይገባል። ልጆችሽ ከእ/ር የተማሩ ይሆናሉ ሰላማቸውም የበዛ ይሆናል..ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አፅናኝ ሁሉን ያስተምራችሀል..እንግዲህ መምህራችሁ አንድ ነውና ሌላውን መምህር ብላችሁ አትጥሩ..ያስተምርህ ዘንድ በእሳታዊ ቃሉ ድምፁን አሰማህ. የእ/ር ቃል በሙልአት ይኑርባችሁ ተብሎ እንደተፃፈ በሁለት ምስክርነት ድምፁን ከስጋ ና በዚህ ምድር ካሉ ብዙ ድምፆች መካከል ለመለየት ና የእ/ርን አይምሮ የልቡን ሀሳብ ከምድራዊ ነገር ለይተን የምናውቀው ቃሉ በውስጣችን ሲያድርና የህጉ እቅድ ምን እንደሆነ ስናውቀው ነው።
ንፁሁን የእ/ር ድምፅ ለመስማት ሙሉ በሙሉ የሚደገፈው በልባችን አቋምና አስተያየት እንዲሁም አስተሳሰብ ነው። ከእ/ር ህግ ጋር እንስማማለን ወይ? ወይስ ፈቃዱን በመቃረን እንገፋዋለን? ከሆነ ህጉ አልገባንም ወይም ላለመታዘዝ ህጉን እንተወዋለን “ቅንነት ለዘላለም ፊቱን እንዲያይ አፅንተዋልና ”እ/ር መንገዱን እንዲያስተምረንና እንዲገልፅልን አይምሮውንና ልቡን እንድናውቅ እንጠይቀዋለን።አሜን! ይሄ ነው እውነተኛ የጴንጤቆስቄ ጣእም።
እ/ርን መስማት እርሱን መውደድ ያመጣብናል.።
ልጆችን ወደ ተገቢው ክብር ለማምጣት ተገቢውን መፅሃፍ ቅዱሳዊ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ልጆችን በመቅጣት ስነስርአት ማስያዝ ተገቢ ነው። አንዳንድ ቤተሰቦች ልጆቹ በልጅነታቸው በተገቢው መንገድ መቅጣት ይፈራሉ። ይሀውም ልጆቻቸው እንዳይጠሉዋቸው በመፍራት ነው። ልጆችን መቅጣት በመፅሀፍ ቅዱሳዊ ደረጃ ጠብቆ እስከሆነ ድረስ ትክክል መሆኑን መገንዘብ ወሳኝነት አለው። ማሰቃየትን እስካልጨመረ ድረስ ማለት ነው ።ቅጣትና ማሰቃየት ትርጉማቸው በመፅሀፍ ቅዱስ መመዘን አለባቸው ።በእርግጥ ይህ ከጥናታችን ውጪ የሆነ አርስት ነው። በዚህ ግን ቁም ነገር ያዘለ ነጥብ ማስቀመጥ እንፈልጋለን። ካስተዋልን አብዛኛውን ጊዜ ወላጆቻቸውን የሚወዱ ልጆች በቀድሞ የልጅነት ዘመናቸው በተገቢው በወላጆቻቸው ተቀጥተው ያደጉ ናቸው።ከሰማዩ አባታችንም ያለን ህብረትና ግኑኝነትም እንደዚሁ ነው።
እ/ር ሲቀጣ በመጀመሪያ ያሳዝነናል ከእርሱም ለመሸሽ እንፈልጋለን። በፍፃሜው ስናስተውል ግን እ/ርን እንወደዋለን ።የሚቀጣን ወደ ብስለት ለማምጣት ለጥቅማችን ነውና።እ/ር ምንም ሲያደር መነሻ ልቡ መለኮታዊ ፍቅሩ መሆኑን ወደማስተዋል ሲያመጣን በአባታችን ደስ ይለናል። (ደግሜ እላለሁ እ/ር ምንም ሲያደርግ መነሻ ልቡ ፍቅር ነው። ካስፈለገ ሰልሼ እላለሁ እ/ር ፍቅር ነው።
ጌታ እየሱስ የተናገረው ታላቁ ትእዛዝ የሚገኘው “ በዘዳ6/4-5 እስራኤል ሆይ ስማ አምላካችን እር አንድ እር ነው። አንተም እ/ር አምላክህን በፍፁም ልብህ በፍፁም ነፍስህ ውደድ በፍፁም ሀይልህም ውደድ”ይህ የሚገርም ቃል ነው። በጣም የምናተኩረው እ/ርን ውደድ የሚለው ትእዛዝ ላይ ነው። የሚገርመው ግን እ/ርን መውደድ እንዴት እንደሚመጣብን ረስተንዋል ወይም ትኩረት አልሰጠነውም። የትእዛዙ ቁልፍ ያለው በመጀመሪያው ሀረግ ላይ ነው እስራኤል ሆይ ስማ”እርሱን መስማት እርሱን ወደ መውደድ የሚያመጣን የመጀመሬያው ደረጃ ነው። መጀመሪያ እንሰማለን ይህም እምነትን ያዘጋጃል ከዛ ያ እምነት በእሳት ይፈተናል ይህም ያ እምነት እንደ ንፁህ ወርቅ ንፅህ እምነት እንደሆነና እንዳልሆነ ይሀውም በስጋዊነት የተደገፈ መረዳት እንዳይሆን በእሳቱ ይነጥራል ይህም ፈተና ትግስትን ያዘጋጃል ወይም ፅናትን።
ከዛ ቡሀላ ነው ተስፋውን የምንቀበለው “እብ6/12,እምነትና በትግስት የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞችቸልተኞች፤ዝግምተኞችቻል ባዮች) እንድትሆኑ አንፈልግም። 13,እ/ር ለአብርሀም ተስፋን በሰጠው ጊዜ የሚምልበት ከእርሱ የሚበልጥ ሌላ ባለመኖሩ በራሱ ማለ 14እንዲህም አለ በእርግጥም እባርክህለሁ ዘርህንም አበዛዋለሁ 15አብራሀምም በትእግስት ከጠበቀ ቡሀላ የተሰጠውን ተስፋ አገኘ”። ተፈፀመ። በክርስቶስ ስራ በውስጣችን በፈሰሰው የእ/ር ፍፁም ፍቅር ሰላም ለናንተ ይሁን እንላለን!አሜን! አቤቱ የሚናገር እ/ር! በወንድም ቢንያም አለማየሁ ተፃፈ። በነፃ የሚታደል!