
ከውይይት የተጠቀሰ። ስለ አርሜገዶን በጥልቀት ቢጻፍ ሳምንታት አይበቃውም ትንሽየ ፍንጭ ለመጠቆም የፈለግኩት መንፈሳዊ ሚስጥራዊ አመልካችነቱን ፍንጭ ለመጠቆም ነው እንጂ ሙሉውን ትንተና ለማቅረብ አይደለም። በአምዛኛው መንፈሳዊ መረዳት እንደ ቱባ ክር ነው ጫፉን ከያዛችሁት ዝም ብሎ ይተረተራል ካልያዛችሁት ጫፉን ፍለጋ ቱባውን በማሽከርከር ጊዜ መግደል ነውና የእ/ር መንፈስ ወደእውነት ሁሉ ይምራን። በአጠቃላይ መጽሓፍ ቅዱስ በታሪክና በትንቢት የተሞላ ብቻ ሳይሆን ብዙ መንፈሳዊ ገጽታ ጠቃሚ ገጸ ባህርያት ጭምር ባላቸው ተይንቶች የተሞላ ነው። ምሳሌዎቹ ተፈጥራዊውን ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊውን እውነታ እንረዳ ዘንድ የአላፊ ግዜ ፤ የወቅቱ ሁኔታ ፤ ደግሞም የወደፊቱን የሚያመለክቱ ትንቢታዊም ሊሆኑ ይችላሉ። ጌታ እየሱስ በስጋ ወራቱም ሆነ ወደ ቀድሞው የመንፈስ ክብሩ ከተመለሰ ቡሃላ በአብዛኛው ምሳሌያዊ ወይም ምልክታዊ ዘየ የተሞላ መልክት ነው ያስተማረን። በስጋ ወራቱ ካለው ስንጀምር ለመጥቀስ ያክል ትምህርቶቹ ቃሉ ሁሉ ቋንቋው symbolic ምሳሌያዊ ወይም ምልክታዊ ነበረ። በየዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ በእምነታችን ደራሲ በክርስቶስ የሆነው ይከው ነው። የራእይ መጽሃፉን ሲጀምር እራሱ የመጽሐፉን ሙሉ መልእክት ቅልብጭ አድርጎ አስቀምጦታል። የአማርኛ ትርጉም ደብቆታል እንጂ ሲጀምር መተርጎም የነበረበት ቀጥተኛ ፍቺው “The Unveiling of Jesus Christ ” “የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ” ነው። ሙሉ ስሙ መሆን የነበረበት “የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ተብሎ ነበር።፤ An unveiling of Jesus Christ.” Revelation 1:1[jmt] Rev 1:1 The Revelation of Jesus Christ [kjv]” ይህ ሐረግ ሁሉንም ይነግረናልና። መጽሐፉ በአጭሩ ለአንድ ዓላማ ነው የተጻፈው እሱም በቅዱሳኑ ውስጥ በመንፈስ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሸፈነበት የስጋ መጋረጃ የክብሩን የመገለጥን ረቂቃዊ መንፈሳዊ ሚስጥራዊ መንፈሳዊ ሂደቱን ለመግለጥ ለማሳየት ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ ተጓዳኝ አጀቦች ሁሉ በሱ ታላቅ ክብርና ብርሃን ቦግ ብሎ መብራት ምክንያት ተጋልጠው እሱ ሲከብር እነሱ ለእይታ ተጋልጠው በብርሃን ይዋጣሉ። የጨለማ ህልውና በብርሃን ህልውና ይዋጣልና ።
በቀላል ቋንቋ የቀሩት የዚህ የእ/ር ብርሃን ክርስቶስ መገለጥ ገመናቸውን ያጋለጣቸው ትእይንቶች ናቸው። ልክ ማታ ውሃ ጠምቶህ/ሽ ወደ ወጥ ቤት ትሄድና መብራቱን ስታበራ በረሮው ይሁን ሌላው ነገር ሁሉ ግልጥ ብሎ ሲተራመስ እንደሚታይ በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ፤ የቀሩ ሁሉ ወደ መታየት መጥተው ሲተራመሱ ይስተዋላል ። በምስል በምልክት ያፃፋቸው ሁሉ የነገሮች ገፀ-ባህርይ አመልካች ወካይ ምልክቶች እና አመልካቾች ናቸው። እያንዳንዱ ዋይታ፤ እያንዳንዱ ነጎድጓድ፤መቅረዞች ፤ ፈረሶች ፤ አንበጣ፤ ፤ አራዊት ፤ ወፎች ፤ እንስሳት ፤ አርማጌዶን ፤ እባብ፤ ዘንደዎች፤ ራሶች፤ ፤ ቀንዶች ፤ ጥርስ ፤ ጅራታቸው ፤ ዓይኖች ፤ አፎች፤፤ ክንፎች ፤ ጸጉር፤ እግር ፤ እጅ ፤ በግምባራቸው ፤ ዕጣን ፤መጻሕፍት ፤የወርቅ ፤ ማኅተሞች ፤ ደፍተው ፤ ስሞች ፤ ከተሞች ፤ በአሕዛብ ፤ ነገሥታት ፤ ልሳኖች ፤የኒቆላውያንን፤ አንቲጳስ ፤ በለዓም ፤ ባቢሎን፤ ሰዶምና ፤ ግብጽ ፤ ኤልዛቤል ፤ መጽሐፍ ሕይወት ፤ የሕይወት ዛፍ ፤ የሕይወት ውኃ ፤ ሰዓታት ፤ ቀናት ፤ ወራት ፤ ወቅቶች ፤ የብረት በትር ፤ ማጭዱን ፤ ቀስት ፤ ሰይፎች ፤ ያጭዳል ፤ የመከር ፤ የሣር ፤ ዛፎች ፤ ዙፋኖች ፤ ልብስ ፤ ምስሎች ፤ ድንቅ ፤ ምልክቶች ፤ ቁጥሮች ፤ ጽዋዎች ፤ መለከት ፤ነፋሳት ፤ ወንዞች ፤ ሀይቆች ፤ ባህሮች ፤ ውኃ ፤ ደመና ፤ ጎርፍ ፤ ተራሮች ፤ ደሴቶች ፤ መብረቅና ፤ ድምፆች ፤ ያንጎደጉዳል ፤ነውጦች ፤ በረዶ ፤ ዘንዶ፤ ፤ ዘፈኖች ፤ የወይን መጭመቂያ ፤ ወይን ጠጅ ፤ ሚዛን ፤ ስንዴ ፤ ገብስ ፤ ዘይት ፤ የዓይን ሽፋሽፍት፤ ጠጠሮች ፤ መና ፤ ጉንጉን ፤ የዘንባባ ዝንጣፊ ፤ የጋለሞታዎችና ፤ ጋለሞቶች ፤ ዝሙት ፤ ቁልፎች ፤ በሮች ፤ ቤተ መቅደሶች ፤ ምኵራቦች ፤ አዕማድ [ምሶሶ]፤ ሀብታም ፤ ድሃ፤ ዕውር ፤ እርቃናቸውን ፤ትኩስ ፤ቀዝቃዛ ፤ ለብ፤ ደም፤ እሳት ፤ ዲን[ሰልፈር] ፤ እሳትና ፤ ጭስ ፤ ፀሐይ ፤ ጨረቃ ፤ ከዋክብት፤ እንስሶች፤ ምስሎች,፤ምልክቶች፤ ባቢሎን፤ዘንዶ፤ወዘተ… ከብርሃኑ መከሰት የተነሳ በምልክት መንፈሳዊውን ሚስጥር ወክለው የተጋለጡ የነገሮች ገፀ-ባህርይ አመልካች ወካይ ምልክቶች እና አመልካቾች ናቸው። ። በአጭሩ በክብር መገለጡ የኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ የመከራዎች ወይም የክርስቶስ ተቃዋሚን ሃይላት መገለጥ ለማሳየት አይደለም። እነሱ የጎንዮሽ ትእይንት ናቸው እንጂ ዋናው የእ/ር ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ነው። ሃይል የአንዱ የእ/ር ነውና። እርሱ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት የሚኖር ጌታችንና አምላካችን ሁሉን ፈጥረዋልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም የእርሱ ነው። የዮሐንስ ራእይ 4፡10-11
የማቴዎስ ወንጌል 13፡34-35 ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም፦ በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም። ይህንንም በነብዩ ዳዊት ላይ ሆኖ መንፈስ በመዝሙር 77/2 ላይ አስቀድሞ ተናግሮት ነበረ። እንደ ምናስተውለው ትንቢቱ ፍፃሜ ያገኘው ጌታ ያለ ምሳሌ ስላስተማረ ነው።
ባለፈው እንደጠቀስኩት በጥቂቱ ለመድገም ያክል ከ 41 በላይ ምሳሌዎችን ተናግረዋል የዘልአለም ስቃይ ሰባኪዎች ግን ነጥለው እውነተኛ ታሪክ ነው የሚሉት የሃብታሙ ሰውና አልአዛር የበጎችና ፍየሎች ወዘተ…. ያስፈራራሉ የሚልዋቸውን ምሳሌዎችን ነው። እውነታው ግን ጌታ ከተናገራቸው ምሳሌዎች ለማስታወስ ያህል። ከእንቅብ በታች ያለ መብራት፤ የሰናፍጭ ቅንጣት፤ ልባምና ሰነፍ አናፂዎች፤ በአረጀ ልብስ ላይ አዲስ እራፊ፤ በአረጀ አቅማዳ ላይ አዲስ ወይን፤ ዘሪና የመሬት አይነቶች፤ የተሸሸገ እርሾ ፤ በባህር ላይ የተጣለ መረብ፤ የጠፋ በግ፤ምህረት የማያደርግ ባርያ፤ አስሩ ቆነጃጅት፤ በጎችና ፍየሎች፤ ደጉ ሳምራዊ፤ የጠፋ ድሪም፤ ወዘተ…… ዶክትሪናቸውን ለማጽደቅ ሁሉም የዘልአለም ስቃይ ሰባኪዎች ነጥለው እውነተኛ ታሪክ ነው ብለው የሙጭኝ ይላሉ።
እውነታው ግን ጌታ ከ 41 በላይ ምሳሌዎችን ተናግረዋል አንዳቸውም በእውን የተፈፅሙ የተከሰቱ ታሪኮች አልነበሩም። ተምሳሌትን ምሳሌነቱን ትተን ወደ እውነተኛ ታሪክ ስንከረብተው ወይም ስንገለብጠው ተምሳሌነቱ ይጠፋል።
ሁላችንም እንደምናውቀው ምሳሌ ወይም ተምሳሌት የሚነገረው በጥሬው ካለው ትርጉሙ ውጪ ሌላ ነገርን የሚወክል ቃል ወይም ሃረግ ነው። ለምሳሌ አንበሳ የጀግና ምሳሌ ነው፤ በግ/እርግብ የየዋህነት የንጽህና ምሳሌ ነው።
በተፃራሪው ታሪክ ማለት ደግሞ ባለፉት ዘመናት እውን የነበሩ ክስተቶች ትውፊት፤ የሚዘገብ ክንዋኔ፤ ለምሳሌ ቀድሞ የነበረ ወግ፤ ጀብድ፤ ጀግንነት፤ የሃገር ኩራት፤ ወዘተ….ማንኛውም የሚያኮራ ይሁን አሳፋሪ ክስተት ሁሉ በዘመኑ ባለ ትውልድ እንደ “ነበረ” የሚታሰብና የሚነገር የሚዘገብ የአላፊ ጊዜ “ክስተት” ታሪክ ይባላል።
ጌታ እየሱስ በየትኛውም ቦታ ለፈሪሳውያን ይሁን ለህዝቡ ሲያስተምር ያለ ምሳሌ ሲያስተምር አታዩም። ምሳሌዎቹ ግን ብዙ ገፅታ ሊያሳዩ ይችላሉ። የአላፊ ግዜ ፤ የወቅቱ ሁኔታ ፤ ደግሞም የወደፊቱን የሚያመለክቱ ትንቢታዊ ሊሆኑ ይችላሉ። አንድ ነገር ሲመስል ወይም እንደ ሌላ ነገር ሲያስቀምጠው ዘይቤያዊ አነጋገር፣ ተለዋጭ መልክት የሚያመላክት ነው። ለምሳሌ ከእ/ር ቃል ለመጥቀስ ያክል
ዘይቤያዊ አነጋገር፣ ተለዋጭ – “ሕይወት ሁሉ ሣር ነው” ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤ 1ኛ ጴጥ 1:24 ስለሆነም እንደምናስተውለው የዚህ መልክት ተምሳሌት ነው እንጂ ቃል በቃል ሊወሰድ አይችልም። It IS a metaphor and CANNOT be literal.
ምሳሌ – ” እርሱም፦ ያለ ጥርጥር ይህን ምሳሌ፦ “ባለ መድኃኒት[ሃኪም] ሆይ፥ ራስህን ፈውስ፤ “ሉቃስ 4:23)
ምሳሌያዊ ፤ ይህም ነገር ምሳሌ ነው፤ እነዚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ኪዳኖች ናቸውና። (ገላ 4 22-28)
እንደ ራዕይ (ሰማይም ተከፍቶ በአራት ማዕዘን የተያዘ ታላቅ ሸማ የሚመስል ዕቃ ወደ ምድር ሲወርድ አየ ሐዋ 10 /11-16)
ምልክት (ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ #ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። ማቴ 12 ፡39)
ዓይነቶች – (በአዳም እና በክርስቶስ እንደሚመሳሰል ሮሜ 5 /12-21)
እንደ ጥላ (ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና። ዕብ 10: 1)
የሚመስሉ – ( እንግዲህ በሰማያት ያሉትን የሚመስለው ነገር በዚህ ሊነጻ እንጂ በሰማያት ያሉቱ ራሳቸው ከእርሱ ይልቅ በሚበልጥ መስዋዕት ሊነጹ የግድ ነበረ። ዕብ 9:23)
የዮሐንስ ራእይ 1፡10 በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ። የጌታ ቀን በውስጡ ብዙ ጥልቀትን ያካተተ ቢሆንም አይነተኛ ነገሩ በመንፈስ ከመሆን ጋር የተያያዘ ነው። በጌታ ቀን መሆን ማለት በመንፈስ ውስጥ ነው። የዮሐንስ ራእይ 1፡10 በጌታ ቀን በመንፈስ ውስጥ ነበርሁ። KJV Rev 1፡10 I was in the Spirit on the Lord’s AMP 10: I was in the Spirit [rapt in His power] on the Lord’s Day (Rev 1:10 [Weymouth]) In the Spirit I found myself present on the day of the Lord,
አርማጌዶን፤ “የጌታ ቀን ለውሳኔ ሸለቆው ቅርብ ነው የብዙ ብዙ ሕዝብ ውካታ በውሳኔ ሸለቆ አለ። ” ኢዩኤል 3:14 Joel 3:14 Multitudes, multitudes in the valley of decision: for the day of the Lord is near in the valley of decision
የጌታ ቀን፥ የእግዚአብሔርን ፍፁም ፍቃድ እንዲያመጣ ለማድረግ በመንፈስ ሃይል በአስደናቂ ሁኔታ ባንቀላፋችው ቤተክርስቲያን የዚያም ተጸኖ በተወሰነ መልኩን በቀየረ ሁኔታም በአለም ላይ የሚመጣና ዋናው አርሜጌዲዮን ግን መንፈሳዊ ነው በእያንዳንዱ አማኝ ህይወት የመጣ አሁንም ያለ ደግሞም መምጣቱን ሚቀጥል ፍልሚያ ነው። ተፈጥራዊው እይታ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈው የአርማጌዶን ጦርነት በአሁኑ ጊዜ ያለ ወይም የሚመጣ የወታደራዊ ኃይሎች ፍልሚያ ወይም የጦር አውሮፕላኖች ቦምቦች ባሕር ሰርጓጅ መርከቦች እና ታንኮች ያካተተ ተፈጥራዊ ጦርነት አይደለም። አርማጌዶን የቃላት ጦርንርት ነው። የብርሃንና ጨለማ ጦርነት ነው። ብርሃን ለጨለማ እሳቱ ነውና በብርሃን መገለጥ ጨለማ መበላቱ አይቀሬ ነው። የእውነት እና የሐሰት ውጊያ ነው። አሳቹ አታላዩና እውነት ጋር ያለ በመታገል ነው። ዛሬ አርማጌዶን በእያንዳዱ ሰው ህይወት እየተካሄደ ነው። በምድር ላይ ያለ እያንዳንዱ ሰው የራሱ ወይም የራሷ የግል አርማጌዶን እየሆነበት ነው። የወንድ የሴቶች እና የህፃናት የአዋቂዎች አዕምሮ ሰዎችን ወደክርስቶስ የመማረክ መንፈሳዊ ጦርነት ነው። ወንድም ቢኒ።
J. Preston Eby፡ Battle of Armageddon፡ “The battle of Armageddon is the battle of the great day of the Lord, which comes as a thief upon an unsuspecting world and a sleeping church. It is representative of that time of struggle and fierce conflict which God’s elect and the whole world must pass through, by which, this present evil world system is actually brought to an end and the new day is inaugurated in righteousness and glory. This day of the Lord is when “the lofty looks of man shall be humbled, and the haughtiness of men shall be bowed down, and the Lord alone shall be exalted in that day. It is the day of overturning, when the foremost shall be least, and least foremost; when the mighty shall become weak, and the meek and lowly become mighty. It is the day when the kingdoms of the world crumble and fall, and when God’s kingdom is established never to fall. Armageddon is the beginning of the overturning when the Lord first comes in judgment upon the entire political, economic and ecclesiastical system of this present evil age”