
Binyam TA የእግዚአብሔር እርቅ ለሰው ልጆች ብቻ ነው ወይስ ፍጥረትን ሁሉ ያጠቃልላል? “ለመሆኑ የሁሉ ነገር መታረቅ እስከ ምን ድረስ ርቆ ይሄዳል ለሰው ልጆች ብቻ ነው ወይስ ለፍጥረት ሁሉ? “እውነት የሆነውን አስቡ” ቦሎናል ደግሞም “ቃልህ እውነት ነው” ይላልና እውነቱን በቃሉ እንድናይ እ/ር ይርዳን። “ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1/19-20 እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና።
Col 1/19 For it pleased the Father that in him should all fulness dwell;20 And, having made peace through the blood of his cross, by him to reconcile all things unto himself; by him, I say, whether they be things in earth, or things in heaven.”
መቸም እንደ ነዚህ ያሉ እውነቶች መንፈስ ከቃሉ ሲገልጥ የሚሆነው የታወቀ ነው። ጌታ አገልግሎቱን በጀመረበት ቀን የሆነው ቢደገም አይገርመኝም። የነብዮን ኢሳያስ መጽሐፍ በሰጡት ጊዜና መጽሐፍን በተረተረ ጊዜ ሲኦል ሁሉ ቡሃላ መዝጋትዋ ላይቀር አፍዋን እንደ ከፈተችበት ሁሉ ያ የሃይማኖት መንፈስ አሁንም እንደ ሚንጫጫ ይጠበቃል።
ለመሆኑ ቆላስይስ ምዕራፍ አንድ በሰማይና በምድር ያሉት ወደ ራሱ ያስታረቃቸው እነማን ናቸው? መቸም በምድር ያሉት ሲል በአብዛኛው ከሰው ጋር የተያያዘ እንደሆነ እናውቃለን በሰማይ የሚታረቁት እነማን ናቸው? “ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1/15-16 እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድርያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤
Col 1/15 Who is the image of the invisible God, the firstborn of every creature:16 For by him were all things created, that are in heaven, and that are in earth, visible and invisible, whether they be thrones, or dominions, or principalities, or powers: all things were created by him, and for him:”
ደህንነት ከሰው ልጆች ጋር ብቻ የተያዘ ሲሆን እርቅ ግን ከፍዝጥረት ሁሉ ጋር ነው። ከቃሉ እንደ ምናስተውለው እርቁ ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ከዛም በላይ መሆኑን በቃሉ ከማስተዋላችን በፊት ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤የሚላቸውን ከቃሉ ውስጥ ሁሉ የሚላቸውን በዝርዝር እንየው። በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። ካለን ቡሃላ በሰማይ ከመንፈሳዊው አለም ይጀምርና የማይታዩትን ካሳየን ቡሃላ በሚጨበጠው አካላዊ አለም በምድር ያሉትን የሚታዩትን እንዲሁ ያሳየናል። ከዛም ይቀጥልና ሲዘረዝራቸው ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ብሎ አለቅነት ደግሞም ሥልጣናት፥ ጠቅሎ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ደግሞም ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤ ይለናል።
በዚህ ቃል ውስጥ የሚገርመው በሰማይ ከጠቀሳቸው ውስጥ አለቅነትና ሥልጣናትን፥ ወዘተ… መቸም የእ/ርን ቃል የሚፈታው የእ/ርን ቃል በማመሳከር ነውና በኤፌሶን 6 መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ነው ብሎ በዝርዝር ይገባበታል። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6/12 መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።” በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና። ጥያቄው በምድር የሚታረቁትን እናውቃለን በሰማይ የሚታረቁት እነማን ናቸው እንደ ሰው አልጠፉምና ይድናሉ አይልም ታርቀዋል ግን ይላል። በሰማይ ያሉት አለቆችና ከሥልጣናት የዚህም የጨለማ ዓለም ገዦች ፡ በሰማያዊም ስፍራ ያሉ የክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ሳይቀር እርቁ አጀንዳ ውስጥ አስገብታቸዋል። እንዴት? “ሚስጥሩ ለእ/ር ነው የተገለጠው ለእኛ ነው” የዘመን ፍፃሜ የአጀንዳው ጠቅላላ ምክሩ ይህን ይመስላል። እወዳችሀለሁ ተባረኩልኝ። ወንድም ቢኒ።