የእግዚአብሄር ክብር የክርስቶስ መልክ ነው።


የእግዚአብሄር ክብር የክርስቶስ መልክ ነው። “ሁሉ ሃጥያትን ሰረተዋል የእ/ር ክብር ጎድላቸዋል” በሃጥያት ምንያት የጎደለብን የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ነው። ሃጥያት የሚለው ጽንሰ ሃሳብ ልናስተውለው ይገባል በግሪኩ HARMATIA ሲሆን ይህ እስፖርታዊ ቋንቋ ነው፤ ትርጉሙም ምልክቱን መሳት ነው። MISSING THE MARK ማለት ነው በአንድ ቀስተኛ ቀስቶ የቀስቱን ፍላጻውን ካሽቀነጠረ ኢላማውን ወይም አላማውን ከሳተ ውድዱርን የሚያየው ህዝብ ሃርማሪቲያ HARMATIA ብሎ በታላቅ ድምጽ ይጮካል። እኛም የመኖራችን ሚስጥር የሆነው ህይወታችን ብርሀናችን ኢላማችን የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ስለሳትን ሃርማሪቲያ HARMATIA ሆነብን አሁን ግን እ/ር ይመስገን በሃርማሪቲያ HARMATIA ያጣነው የጎደለብን የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ተመለሰልን። የእ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር ክ-ብ-ር ኢ-የ-ሱ-ስ ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ነው። የሐዋርያት ሥራ 7/55 መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን ክ-ብ-ር ኢ-የ-ሱ-ስ-ን-ም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፦

ይህ ክርስቶስ አሁን በእኛ ውስጥ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ‘ለእነርሱም እግዚአብሔር የዚህ ምስጢር ክብር ባለጠግነት በአሕዛብ መካከል ምን ያህል እንደሆነ ለማሳወቅ መረጠ፤ እርሱም የክብር ተስፋ የሆነው
በ-እ-ና-ን-ተ ው-ስ-ጥ ያ-ለ-ው ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ነ-ው። ‘ቈላስይስ 1:27 ወንድም ቢኒ።

Binyam TA ይከውልክ በጌታ ወንድማችን ጌትነት። “ሁሉ ሃጥያትን(ሀርማትያ) ሰረተዋል የእ/ር ክብር ጎድላቸዋል። ሮሜ 3:23” ይህ መልእክት የተፃፈው በ57 ዓ.ም. በሐዋርያው ጳውሎስ በግሪክ ሳለ በግሪክ ቌንቌ ነው። ሮሜ 1:1 የመልእክቱ ተደራስያን ብዙ ህዝብ ይገኝባቸው የነበሩ የሮም ቤተ ክርስትያን ምእመናን ናቸው። 1:7 የዚህች የቤተክርስቲያን አባላት የነበሩ አይሁድ ግን በቁጥር ትንሽ ነበሩ። 4:1/ 1:13 ለምን እስፖርታዊ ቃል ተጠቀመ የሚለውን እናየዋለን።
የመልእክቱ ልዩ ባህርይ ብሉይ ኪዳንን በስፋት ጠቅሶ በአዲስ ኪዳን በጌታ እየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ያላቸውን ፍቺ ለምእመናን ማስረዳቱ ነው። ጳውሎስ የተማረ የሌሎች ህዝቦችን ብዙ ቌንቌዋችንና ብዙ ባህሎችን ያስተዋለ ነበረ ጣልያንኛ፤ ግሪክ፣ እብራይስጥ፣ አረሚክ ወዘተ … ቌንቌዋችን ያስተውል ነበረ። የግሪክ ስፓርታዊ ቃል ሀርማትያ በሀጥያት ምትክ የዘፍጥረትን ውድቀት ለማስረዳት በመልክቱ የተጠቀመው የካሊስየም ስታዲዮሞች መስራቾችና ተጠቃሚዋች ሮማውያንና ግሪኮች ስለሆኑ በደንብ እንደሚገባቸው ስለሚያውቅ ነው።
እስፓርታዊ ምስክ በሮሜ ብቻ ሳይሆን በብዙ ቦታ ተጠቅሞ አስረድተዋል። ለምሳሌ
በእብራውያን 12:1 ላይም ተጠቅሞበታል።
“እነዚህን የመሰሉ ብዙ ምስክሮች። እንደ ደመና በዙርያችን ካሉን ሸክም የሚሆንብንን ኅጥያት አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በፅናት እኑርጥ”
እዚህ ላይ የተጠቀመው ምስል በአንድ ትልክ ቤተ ትውኔት ወይም ካልስየም ውስጥ የምሚደረገውን ውድድር ይመስላል። ምስክሮቹ የሚለው ቃል ለመግለፅ የገባው የግሪኩ ቃል “ሰምአታት” የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ሲመሰክሩ የነበረውም ስለ እምነት ኅይልና ስለ የእግዚአብሔር ታማኝነት ነበር ብሎ ያስረዳል። በመቀጠልም “በፅናት እኑሩጥ” የሚላቸውን በእስፓርታዊ ስእል ሲያስረዳቸው ይስተዋላል ። እግዚአብሄርን የመምሰል ሚስጥር ያለጥርጥር ታላቅ ቢሆንም የክርስትና ህይወት በስፖርት መስሎ ያሳያቸው እንደማራቶን የረጅም እሩጫ ርቀት እንጂ እንድ አጭር ርቀት ሩጫ እንዳልሆነ በሚገባቸው ስፓርታዊ ቌንቌ አስረዳቸው። ምክንያቱም አንዳንድ የአይሁድ ክርስቲያኖች ከስደቱ መከራ የተነሳ ውድዱሩን አቌርጠው ለመውጣት ተፈትነው ተፍገምግመው ነበርና።

During the winter of 57–58 A.D., Paul was in the Greek city of Corinth. From Corinth, he wrote the longest single letter in the New Testament, which he addressed to “God’s beloved in Rome” (1:7). Like most New Testament letters, this letter is known by the name of the recipients, the Romans. ወንድም ቢኒ።

Binyam TA ከወንድም ቢኒ። ከምናስተውለው በላ በመፅሐፍ ቁዱስ አልተፃፈልንም። የተፃፈውን ለመረዳት አይክብድ። ሆን ብለህ ነው እንዲህ አይነት አሰልቺ ተደጋጋሚ ጥያቄ የምትደጋግመው እግዚአብሔር ያውቃል እውነቱን። በተቻለኝ ላስረዳህ በግልፅ ቌንቌ ፃፍኩልህ መንፈስ ቅዱስ እንዲያበራልህ ፀሎቴ ነው። ወይስ ጌታ እንዳለው ነው? “በማርቆስ 10:38 ኢየሱስ ግን። የምትጠይቁትን አታውቁም። ”
ከአንተ የማይጠበቅ ምን አይነት ጥያቄ ነው ይሄ? 1ኛ ጥያቄህ, ሐዋርያው ጳውሎስ ሀጥያት ሲጀመር ስፓርት ነበረ አላለም ስፖርትን እንደምሳሌ ተጠቅሞ ፃፈ እንጂ። ሀጥያት እስፖርት ነው አላለም።
2ኛ ጥያቄህ። ሀጥያት ግሪክ ነበረ ወይ? ጥያቄውን በመመለሴ ሞኝ የሆንኩ መሰለኝ ቢሆንም የጌታ ፈቃድ ይሁን በማለት ልመልሰው ። ያስቃል በእርግጥን ሀጥያት ግሪክ አይደለም ግሪክኛ የሮሜ መልክት የተፃፈበት ቋንቋ እንጂ። ሀጥያት ባልተገባ ማንነት መኖር መሳት ፤መውደቅ፤ መጉደል፤ ነው ።

3ኛ ጥያቄ። ውድድርና ኃጥያት ምን አገናኘው? አሁንም ወንድም አስተውል በዘፍጥረት የአዳምን ና የሰዎች ልጆች በኅጥያት ምክንያት ከእ/ር ክብር መጉደል ለሮማውያን ሲያስረዳ ምሳሌን ተጠቅሞ ማስተማሩ ሃጥያት አይደለም፤ ጳውሎስ ብቻ ሳይሆን ጌታ እየሱስም ተጠቅሞበታል። በቅድሚያ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በአገልግሎቱ ሁሉ በምሳሌ ማስተማሩ ማወቅ በራሱ በረከት ነው። እሱንም ምን ያገናኘዋል ትለዋለህ?
“የማቴዎስ ወንጌል13/34-35 ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤በነቢዩም፦ በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ

ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።” ይህንንም በነብዩ ዳዊት ላይ ሆኖ መንፈስ በመዝሙር 77/2 ላይ አስቀድሞ ተናግሮት ነበረ። እንደ ምናስተውለው ትንቢቱ ፍፃሜ ያገኘው ጌታ ያለ ምሳሌ ስላስተማረ ነው።

በዚህም መሰረት ጌታ ከ 41 በላይ ምሳሌዎችን ተናግረዋል
ጌታ ከተናገራቸው ምሳሌዎች ለማስታወስ ያህል። ከእንቅብ በታች ያለ መብራት፤ የሰናፍጭ ቅንጣት፤ ልባምና ሰነፍ አናፂዎች፤ በአረጀ ልብስ ላይ አዲስ እራፊ፤ በአረጀ አቅማዳ ላይ አዲስ ወይን፤ ዘሪና የመሬት አይነቶች፤ የተሸሸገ እርሾ ፤ በባህር ላይ የተጣለ መረብ፤ የጠፋ በግ፤ምህረት የማያደርግ ባርያ፤ አስሩ ቆነጃጅት፤ በጎችና ፍየሎች፤ ደጉ ሳምራዊ፤ የጠፋ ድሪም፤ ወዘተ…… ጌታ መንፈሳዊውን ሚስጥር ለማስረዳት ምሳሌን ከተጠቀመ የጳውሎስ ልዩነቱ ምን ላይ ነው ?

ጌታ እየሱስ ስለ ሰማያዊ ወይም መንፈሳዊውን ሚስጥር ሲያስረዳ በነፋስ አልመሰለውምን? አንተም እንደ ኒቆዲሞስ ነድፋስና መንፈሳዊ ነገር ምን አገናኘው? እስፖርት ና ሀጥያት ምን አገናኘው? ማለት ተመሳሳይ ጥያቄ ነው።የዮሀንስ ወንጌል 3:
8 ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም ትሰማለህ፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው።

9 ኒቆዲሞስ መልሶ። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? አለው።

10 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን?

11 እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም።

12 ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? ተባረክልኝ።

Binyam TA ከፍል አንድ። ከቢኒ። ለወንድም ጌትነት ስለ ስድብህ ጌታ ይባርክህ እስከ መቼ በስጋ ስራ በስድብ መበስበስን ዘርተህ መንፈሳዊ ነገር እንደ ምታጭድ ባላውቅም እባክህን እራስህን ተቆጣጠር ስድቡን ተወውና በተቻለ አቅም በእ/ር ቃል ላይ እንቆይ። መጽሐፈ ምሳሌ 14/29 ለትግሥተኛ ሰው ብዙ ማስተዋል አለው፤ ቍጡ ግን ስንፍናውን ከፍ ከፍ ያደርጋል።
ጌታ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ እንድንወድ በብዙ ተናግረዋል ወንድም ሁሉ አባቶች የፈቃዱን ቃሉን ተከተሉ የዚያን ጊዜም አንተም እንደነሱ መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1/8 የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።
ትንቢተ ዕንባቆም 2/2 እግዚአብሔርም መለሰልኝ እንዲህም አለ፦ አንባቢው ይፈጥን ዘንድ ራእዩን ጻፍ፥ በጽላትም ላይ ግለጠው።
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2/7 የምለውን ተመልከት፤ ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ።
መጽሐፈ ምሳሌ 18/1 መለየት የሚወድድ ምኞቱን ይከተላል፥ መልካሙንም ጥበብ ሁሉ ይቃወማል።
መጽሐፈ ምሳሌ 3/13 ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን ነው፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ፤
1ኛ፣ ጥያቄህ፤ “ጌታ ኢየሱስ የሰጠውን ምሣሌ ሁሉንም ይተረጉም እንደ ነበረ መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል።”
መልስ ። በእርግጥም ልክነህ ጌታ ኢየሱስ ከመጠን በላይ ሳይሆን በአቅማቸው ልክ መስማት በሚችሉበት መጠን በሚመስል በብዙ ምሳሌ ቃሉን ይነግራቸው ነበር የሰጠውንም ምሣሌ ሁሉንም ይተረጉም ነበረ። ነገር ግን የሚተረጉመው ለደቀ መዛሙርቱ ነው እንጂ ለህዝቡ አልነበረም። ምክንያቲም “ለእናንተ[ለደቀ መዛሙርቱ፤ ተማሪ፤ ተከታይ ] የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ[ለሰፊው ህዝብ] ግን አልተሰጣቸውም። የማቴዎስ ወንጌል 13/11” ለህዝቡ ግን ከአሁን በፊት ከተረዳነው ተቃራኒ ምሳሌዎቹ የሚነገሩት የተመረጡት እንዲያስተውሉ ላልተመረጡት የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ፍቺውን ለመደበቅ ነው። እ/ር እራሱ ተራቸው እስኪደርስ እንዳያስተውሉ አድርጋቸዋልና። “በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ጨፍን ጨፍን አለኝ።”
ትንቢተ ኢሳይያስ 6/9 እርሱም፦ ሂድ፥ ይህን ሕዝብ፦ መስማትን ትሰማላችሁ አታስተውሉምም ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱምም በላቸው። 10 በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳይፈወሱ፥ የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፥ ጆሮአቸውንም አደንቍር፥ ዓይናቸውንም ጨፍን አለኝ።
ማቴዎስ ወንጌል 13/15
12 ላለው ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። 13 ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ እየሰሙም ስለማይሰሙ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ።14 መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም።
15 በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።
16 የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው።
17 እውነት እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም።
ትንቢተ ኢሳይያስ 29/11 ራእዩም ሁሉ እንደ ታተመ መጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል፤ ማንበብንም ለሚያውቅ፦ ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፦ ታትሞአልና አልችልም ይላቸዋል፤….2 ይቀጥላል በወንድም ቢኒ።

Binyam TA ክፍል 2 በወንድም ቢኒ።
2ኛ ጥያቄህ። “ምን ላይ ነው ኃጥያትን ከስፖርት መሸነፍ ጋር ያገናኘው? ” ለምን ታካብዳለህ ብራዘር ሩጫ ስፖርት አይደለምን? 1, ኃጢአት አስወግደን፥ 2, ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ….. ሸክምን[ኃጢአት] ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ ራጭ በቁምጣ ይሮጣል እንጂ የደብርሃን ብርድ ልብስ የሚያክል ካቦርት[ኃጢአት] ለብሶ ሸክም[ኃጢአት] ይዞ ቢሮጥ በሩጫ ውድሩ ይሸነፋል። ካራገፈው ግን ቀለል ብሎት ፈትለክ ብሎ ያሸንፋል። “ኃጢአት አስወግደን፥ …በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤”
ወደ ዕብራውያን 12/1-2 …እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።
ያልገባህን ቃል ደግመን እንየው። “ሁሉ ሃጥያትን(ምልክቱን መሳት፤ ሀርማትያ) ሰረተዋል የእ/ር ክብር ጎድላቸዋል። ሮሜ 3:23” በቀላል መንፈሳዊ አማርኛ ያ የሳትነው ምልክቱ እየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ የህይወት ዛፍ ነው እኛ ሁላችን በአዳም ወገብ ሳለን ተባብረን እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አብቅሎን በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ[እየሱስ ክርስቶስ ]፥ እንበላ ነበርን አሁንም አስተውል እኛ ሁላችን በአዳም ወገብ ሳለን ተባብረን እንዳትበሉ የተባለውን መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ በላን። አንዴ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ ከበላን ቡሃላ ግን የሕይወትን ዛፍ[እየሱስ ክርስቶስ ]፥ እንዳንበላ ከህይወት ተባረንን በውስጥ መንፈሳችን ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔደናችን ገነት አስቀመጠ በዚህ መንፈሳዊ ሞት ሆነ። ሞት ማለት ስጋዊ አእምሮ ነውወደ ሮሜ ሰዎች 8/6 ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና[ to be carnally minded is death ]፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
Rom 8/6 For to be carnally minded is death; but to be spiritually minded is life and peace.
አሁን ግን በጌታ ወደ ህይወት ተመለስን።
ኦሪት ዘፍጥረት 3/22 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር፤23 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ከዔድን ገነት አስወጣው፥ የተገኘባትን መሬት ያርስ ዘንድ።24 አዳምንም አስወጣው፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ። ይላቸዋል፤….3 ይቀጥላል በወንድም ቢኒ።

Binyam TA ክፍል 3 በወንድም ቢኒ።በሐዋርያው ጳውሎስ ሃጥያት የሚለው ጽንሰ ሃሳብ ለማስረዳት መርጦ የገለጠበት ቃል የወሰደው እስፖርታዊ ቋንቋ እያልኩህን አስተውል ከላይ ከገለጽኩልህ ሃሳብ ጋር አያይዘህ ተረዳው። በግሪኩ HARMATIA ይህ ቃል መጀመርያ መጽሃፍ ቅዱሳዊቃል አልነበረም ሐዋርያው ግን ምንጩ እስፖርታዊ ቋንቋ ወይም ቃል ቢሆንም ተጠቀመበት። በስፖርቱ አለም የሚጠቀሙበት ቃል ነው። ትርጉሙም ምልክቱን[ኢላማውን] መሳት ነው። MISSING THE MARK ምልክቱን መሳት ማለት ነው። ያ የሳትነው ምልክቱ እየሱስ ክርስቶስ ነው። በአንድ ቀስተኛ ቀስቶ የቀስቱን ፍላጻውን ካሽቀነጠረ ምልክቱን ወይም ኢላማውን ወይም አላማውን ከሳተ በክብ ስታድዮም ተቀምጦ ውድዱርን የሚያየው ህዝብ ሃርማሪቲያ HARMATIA ብሎ በታላቅ ድምጽ ይጮካል። እኛም የመኖራችን ሚስጥር የሆነው ምልክቱ ህይወታችን ብርሀናችን ኢላማችን የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ በእርሱ ከመኖር ስለሳትን ሃርማሪቲያ HARMATIA ሆነብን አሁን ግን እ/ር ይመስገን በሃርማሪቲያ HARMATIA ያጣነው የጎደለብን የእግዚአብሄር ክብር ምልክቱ ክርስቶስ ተመለሰልን።
Rom 3/23 For all have sinned[Greek, HARMATIA, to miss the mark ]and come short of the glory of God;
ያ የሳትነው ምልክቱ እየሱስ ክርስቶስ ነው። ብዙ ቃላት ላይ ማየት ይቻላል ሃሳቡን እንድትይዘው ትንሽ እየው።
ትንቢተ ኢሳይያስ 7/14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
የሉቃስ ወንጌል 2/12 ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።
የሉቃስ ወንጌል 2/34-35 ስምዖንም ባረካቸው እናቱን ማርያምንም፦ እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክ ት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት።
ትንቢተ ኢሳይያስ 11/10 በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ለአሕዛብ ምልክት ሊሆን የቆመውን የእሴይን ሥር አሕዛብ ይፈልጉታል፤ ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል።
በክርስቶስ ውስጥ ደግሞ እኛ ምልክቶቹ ነን።
ትንቢተ ኢሳይያስ 8/18 እነሆ፥ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ለእስራኤል በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን።
3ኛ ጥያቄ። የኃጢያት ደመወዝ ሞት ነው ይላል ። ስፖርት መሸናነፍ ሞት አለው?
ሁለት ዛፎች አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ በጠቅላላው በመንፈሳዊ ቅኔ ድራማው ዙሪያ የሚያተኩረው በዚህ የአትክልት ቦታ ውስጥ እንደሚናገረው አንዱ የሕይወት ሃሳብ የሚያመነጨው ዛፍ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ መልካምና ክፉን ሃሳብ እያመነጨ የሚያስታውቀው ዛፍ ነው። እነዚህ ሁለት ህይወት ያላቸው ሰዎችን የሚወክሉ ናቸው። የመጀመርያው የህይወት ዛፍ ዘንድ ከሚመጣው “የሚበሉትን” እውነተኛ ህይወት የሚገለጠባቸውን የሚያሳይ ሲሆን የሕይወት ዛፉ የሚወክለው ደግሞ ክርስቶስን ነው። ስለዚህም እግዚአብሔር መልካምንና ክፉን ከምታስታውቀው ዛፍ እንዳይበሉ ከተናገረ በኋላ ከበላችሁ”እየሞታችሁት ትሞታላችሁ in dying you will die.” አላቸው። ስለዚህ ከሕይወት ዛፍ ፍሬ መብላት በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ካለው ሕይወት መብላት ሲሆን እርሱ በዚህ አለም እንደነበረ መሆን ማለት ያ ነው። ሌላኛው ሰው ግን ከእግዚአብሔር ወይም ከክርስቶስ ውጭ “ሕይወት” እንዳለ የሚያምኑና በ”ዕውቀት” የሚኖሩትን ያሳያል። የ”ዕውቀት”[መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ ማለትም የእውቀት ዛፍ] ሕይወቱ ከእግዚሐብሔር ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። ስለዚህ እነዚህ ሁለት ዛፎች ሰብአዊነትን በሁለት ቡድኖች ይከፋፈላሉ። በዘፍጥረት ምዕራፍ 2 እና 3 ውስጥ በጣም ግልጽ ነው በእነዚህ አይነት ሰዎች መካከል ያለውን ልዩነት ማስተዋል ይቻላል።ተፈፀመ። ወንድም ቢኒ።

Binyam TA ኃጢአት ህግን መተላለፍ ማለት ነው። Sin IS the transgression or breaking of the law, We must always come back to Scripture, facts, definitions, and principles. “Sin IS the transgression or breaking of the law” (I John 3:41ኛ የዮሐንስ መልእክት 3/4 ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን[ ህግን መተላለፍ] ደግሞ ያደርጋል፥ ኃጢአትም ዓመፅ[ ህግን መተላለፍ ነው] sin is the transgression of the law] ነው። 1John 3/4 Whosoever committeth sin transgresseth also the law: for sin is the transgression of the law.
ኃጢአት ህግን መተላለፍ ከሆነ። የመጀመርያው ለሰው ልጅ የተሰጠው የእ/ር ህግ የቱ ነው? “ኦሪት ዘፍጥረት 2/17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።” በዚህም የመጀመርያውን ኃጢአት ህግን መተላለፍ አዳም ሰራ ። ያልተገባው የእውቀት ምንጭ መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ ዘንድ ተጠቀመ።
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3/4 ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን[ህግን ይተላለፋል] ደግሞ ያደርጋል፥ ኃጢአትም ዓመፅ ነው።
1John 3/4 Whosoever committeth sin transgresseth also the law: for sin is the transgression of the law.
ተመልከት ጌታ እየሱስ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። ሲላቸው የአባቴን ፈቃድ ምንድን ነው ? የእ/ር ቃል ወይም የእ/ር ህግ ነው።
የማቴዎስ ወንጌል 7/23 የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች [GREEK, anomia, violation of law ህህን መተላለፍ የምትለማመዱ።]፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።” አስተዋልክ ?ዓመፀኞች ማለት ህግን መተላለፍ የሚለማመዱ ናቸው።] ህጉሁሉደግሞ የሚያዘው በክርስቶስ መመላለስ ነው ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና። ወደ ሮሜ ሰዎች 10/4 የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5/17 ዓመፃ[ unrighteousness በእ/ር ፊት በትክክል አለመቆም] ሁሉ ኃጢአት[ ህግን መተላለፍ ነው] ነው፥ ሞትም የማይገባው ኃጢአት አለ።
1John 5/17 All unrighteousness[wrong standing befor God] is sin: and there is a sin not unto death.
Righteousness is right standing befor God ጽድቅ በእ/ር ፊት በትክክል መቆም ከሆነ በእ/ር ፊት ትክክል የምንሆነው በክርስቶስ ብቻ ነው። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1/30-31 ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።

 

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal