
ክፍል ሁለት። የአካል መነጠቅ(rapture) ውሸት ነው!
የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሚነጠቁት ሀጥአን ወይስ ፃድቃን? ቀሪውን እውነት ከእግዚአብሔር ቃል ያስተውሉ።
የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ! ክፍል 2
በማቴ 24፡37 የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።
38 በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ
ነበሩ፥ 39 የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ
ይሆናል። 40 በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል አንዱም ይቀራል፤
መቼም በነዚህ ሃሳቦ ች ላይ የተለመዱት አመለካከቶች የታወቁ ናቸው። እንዲያውም በስልክ
ኮንፍረንስ መጽሃፍ ቅዱስ ስናጠና ያጋጠመኝን ላጫውታችሁ በመሃል የአንድን ወንድም ስም ጠራሁና እከሌ አለህ ወይ ብየ ጠየኩ መልስ
የለም ተራህ ስለሆነ እከሌ ብየ ደግሜ ጠየኩ መልስ የለም ሰለስኵ አሁንም ጸትታ ሆነ ትእግስታቸው የተፈተነው ሁሉት ወንድሞች በተለያየ
እስቴት ቢኖሩም በአንድለይ ድምጻቸው አስተጋባ እንዲህም አሉ “ተነጥቆ ይሆናል ወንድም ቢኒ!” ብለው ሳቁ ሳላውቀው የሰጠሁት
መልስ ግን ሳቁን ብቻ ሳይሆን ዝም ያስባለው የመጽሃፉን ክፍል ማጥናት እስከ ማንቀጥል ድረስ ታላቅ ጸጥታ ሆነ ዝምታም ስለበዛ እንዳን
እህትን ጠይቄ ወደ መዝሙርም ተሻገርን ። ከክርስቶስ ጋር በሰማያዊ ስፍራ አሁን በዚያ ተቀምጠዋል በሰማይ ካለ አሁን ወዴት ነው
የሚነጠቀው? ደግሞስ ወደ ዕብራውያን 12፡22 ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥
ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥ መጥታችሃል
Heb 12፡22 But ye are come unto mount Sion, ye are come unto unto the
city of the living God, ye are come unto the heavenly Jerusalem, ወዴት ነው የሚነጠቀው? የሚል ነበር:: በአየሩም ላይ ታላቅ ጸጥታ ሆነ::
ወደ ሃሳባችን እንመለሰና እስቲ እባኮትንን እዚህ ላይ ለቃሉ ትኩረትዎን ይስጡት::
የጥፋት ውሃው ከመምጣቱ በፊት እነማን ነበሩ ሲበሉና ሲጠጡ የነበሩት? ሃጥአን ነበሩ። በጥፋት ውሃውስ በኖህ ዘመን የተወሰዱት እነማን
ነበሩ? ሃጥአን ነበሩ:: በኖህ ዘመንስ በሃዘን እያለቀሱ ጥርሳቸውን ያፋጩት እነማን ነበሩ? ሃጥአን ነበሩ:: ታዲያ የጥፋት ውሃው
ሲመጣ እ/ር የታደጋቸውና በምድር ላይ የቀሩት እነማን ነበሩ? አዎን ጻድቃን ነበሩ::
ለመሆኑ ጌታ ይህንን ምሳሌውን በምን አያይዞ እንደ ሚደመድም አስተውላችሃልን? በማቴ 24፡36፡51
42 ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። 43 ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ
ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር። 44 ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና። 45 እንኪያስ
ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው? 46 ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ
የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው፤ 47 እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል። 48 ያ ክፉ ባሪያ ግን። ጌታዬ እስኪመጣ
ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ፥ 49 ባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ ቢጀምር ከሰካሮችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥ 50 የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት
ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፥ 51 ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፥ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት
ይሆናል።
በሙሉ በማስተዋል ስታነቡት በሚቀጥሉት ቁጥሮች ላይ ጌታው ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም
ሰዓት የመጣውና፥ ከሁለትም የሰነጠቀው፥ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደረገበት፤
በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት የሆነበት አመጸኛውን አገልጋይን ነው። ታማኙ አልተወሰደም ቀርተዋል በዚሁ በምድር ላይ ሾመው። 45
እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው? 46 ጌታው መጥቶ እንዲህ
ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው፤ 47 እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል።
በታማኝቱ ድል የሚነሳው ልባሙ ባሪያ ጌታው ከአለም አክንፎ እንዲያወጣው አይመኝም
ጌታው እንደ ሾመው በዚሁ ሆኖ በመጀመርያው አዳም ምክንያት ተረግማ የነበረችው ምድር ለሁለተኛው አዳም በሰማይና
በምድር ስልጣን ሁሉ እደተሰጠው ስለሚያስተውል ከጌታው ጋር ሆኖ በምድር ላይ በሂወት ይነግሳል። በጽድቅ በሰላም በደስታ በመንፈስ
ቅዱስ ሆኖም ይገዛል። በሮሜ 14/17 አስረግጦ እንደ ሚያስረዳን የእ/ር መንገስት ማለት ያ ነውና::
እዚህ ላይ በኖህ ዘመን ላልታዘዙት የዘላለም እጣ ፈንታቸው በእሳት ውስጥ እየተቀቀሉ
የዘላለም ስቃይ ነው ማለት ነው አይደለም:: እ/ር በቁጣው የሚፈርደው እስከ ሚያድን ድረስ ነውና ። በኖህ ዘመን ላልታዘዙት የዘላለም
እጣ ፈንታቸው በእ/ር ቃል ከማየታችን በፊት ጣፋጩ ዘማሪ ዳዊት ምንም እንካ የእ/ር ቀኝ እጅ በረከትና ሃይል ቢለማመድም የግራ
(dark_ከStrong Hebrew መዝገበ ቃላት# 8040) ይመልከቱ ያም ማለት ዘ ዳርክ ሳይድ ኦፍ ጋድ የሚያመለክት ነው ግራ እጁ የፍርዱና የመአቱ
የቁጣው መገለጫ ምሳሌ ነው። ዳዊት እ/ር ጽድቅን ይማር ዘንድ ባስጨነቀው ጊዜ እነዚህ ሃሳቦችን አብላልቶ ነበር።
መዝሙረ ዳዊት 77፡6 በሌሊት ከልቤ ጋር ተጫወትሁ፥ ነፍሴንም አነቃቃኋት። 7 እግዚአብሔር
ለዘላለም ይጥላልን? እንግዲህስ ቸርነቱን አይጨምርምን? 8 ለዘላለምስ ምሕረቱ ለልጅ ልጅ ተቈረጠችን? የተናገረውስ ቃል አልቆአልን?
9 እግዚአብሔርስ ሞገሱን ረሳን? በቍጣውስ ምሕረቱን ዘጋውን? 10 ይህ ድካሜ ነው አልሁ፥ የልዑል ቀኝ እንደ ተለወጠ።
መዝሙረ ዳዊት 79፡5 አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘላለም ትቈጣለህ? ቅንዓትህም እንደ እሳትይነድዳል?
መዝሙረ ዳዊት 103፡7 ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ፥ ለእስራኤል ልጆችም አደራረጉን።
8 እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ። 9 ሁልጊዜም አይቀሥፍም፥ ለዘላለምም አይቈጣም።
10 እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፥ እንደ በደላችንም አልከፈለንም። መጽሐፈ ምሳሌ 11፡31 እነሆ፥ ጻድቅ በምድር ላይ ፍዳውን የሚቀበል ከሆነ፥ ይልቁንስ ኀጥእና ዓመፀኛ እንዴት ይሆናሉ!
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፥18 ጻድቅም
በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው?
የማርቆስ ወንጌል 9፥49 ሰው ሁሉ በእሳት
ይቀመማልና፥ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል። ጌታ እውነት ነኝ ብለዋል ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማል ካለ አሰራሩ ይለያይ እንጂ ማንም ከእ/ር እሳት የሚያመልጥ
እይመስልም ። ሁሉን በእሳት የሚያሳልፍ ጌታ እየሱስ እራሱ ነው። “የማቴዎስ ወንጌል 3፡11 እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤”Heb 12፡29 For our God is a consuming fire. ወደ ዕብራውያን 12፡29 አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ( consuming የሚባላ) እሳት ነውና። በመገለጡ ወይም በመምጣቱ ሃጢያታችንና አመጻችን
ይበላዋል። ብርሃን ለጨለማ እሳቱ ነውና ይበላዋል ጨለማ በብርሃን ፊት ህልውና የለውም።
ትንቢተ ሚልክያስ 3 Mal 3/2 ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው? 2 But who may abide the day of his coming? and who shall stand when he appeareth? for he is like a refiner’s fire, and like fullers’ soap:
3 እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ። 3 And he shall sit as a refiner and purifier of
silver: and he shall purify the sons of Levi, and purge them as gold and
silver, that they may offer unto the Lord an offering in righteousness.
እ/ር የሰው ልጆችን ማዳን ወይም መዋጀት ያስፈለገው ከሲኦል
አድኖ ወደ መንግስተ ሰማያት ለማሻገር አይደለም። በልምድ የሚነገር ካልሆነ በስተቀር የእ/ር ቃል በቀጥታ እደዛ የሚል በተወዳጁ
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ከራሳቸው ሃጢያትና በውስጣቸው ከሚሰራው የአመጻ ሚስጥር በማንጻት አላቆ ወደ እ/ር መለኮታዊ ተፈጥሮና
ባህሪ ለማምጣት ነው እንጂ። “የማቴዎስ ወንጌል 1፡21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” አስተዋላችሁ ህዝቡ መዳን ያስፈለጋቸው ከገዛ ሃጢያታቸው እንጂ ከሲኦል
አይደለም።
“የሐዋርያት ሥራ 3፡26 ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።” Acts 3፡26 Unto you first God, having raised up his Son Jesus, sent him to bless you, in turning away every one of you from
his iniquities. ደግሞም ወደ ቲቶ 2፡14 መድኃኒታችንም ከዓመፅ
ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
“ የእንግሊዝኛው ግልጽ መልእክቱን ስለሚያሳይ እንመልከተው “that he might redeem us from all iniquity,
and purify unto himself” ከቃሉ እንደምናስተውለው የተዋጀነው ከአንድ ማንነት ወደ ሌላ ማንነት ነው። ይህም
ከአመጻ ሁሉ from all iniquity, አጥርቶ ወይምአንጽቶ ወደ ራሱ purify unto
himself ነው እንጂ። የተዋጀነው ከቦታ ወደ ቦታ የጂኦግራፊ ወይም የካርታ ለውጥ ከሲኦል ወደሆነ ሩቅ ጠፈር ላይ የሚገኝ
ገነት የተባለ ቦታ ወይም ፕላኔት ሰፈር ለመቀየር አይደለም። የተዋጀነው አመጻ ከተሞላ ማንነት ወደ ራሱ መልክና አምሳል ለማምጣት
ነው። የመንጻሩም ሂደት በእሳቱ በማሳለፍ አመጻውን ሁሉ በመብላት ወደ መልኩ ማምጣት ነው።
Mal 3፡2 But who may abide the day of
his coming? and who shall stand when he appeareth? for he is like a refiner’s
fire, and like fullers’ soap: 3 And he shall sit as a refiner
and purifier of silver: and he shall purify the sons of Levi, and purge them as
gold and silver, that they may offer unto the Lord an offering in
righteousness.
ትንቢተ ሚልክያስ 3፡2 ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን
ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው? 3 እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥
የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።
የእሳቱአላማ ማንጠር ነው። አሜን!
አሁን ደግሞ በኖህ ዘመን የነበሩት የማይታዘዙት እ/ር 120 አመት የታገሳቸው እና
የፈረደባቸው ፍጻሚያቸውን በቃሉ አይተን እንለፍ ። ጌታ እየሱስ ከሞቱና ከትንሳኤው ቡሃላ በኖህ ዘመን አልታዘዝ ያሉት አመጸኞች
በእስራት ለነበሩትን ነፍሳትን (spirits መናፍስትን) ሰበከላቸው። ለነሱም የማስታረቁን ቃል ይዞላቸው ወረደ። የሚያሳየንም ክርስቶስ
ለሃጢያታቸው መሞቱን ብቻ ሳይሆን መነሳቱም ለመጽደቃቸው መሆኑን ነው።
ይህንን ቃል Weymouth’s translation. ከተባለውን ትርጉም እናስተውል 1Pe
3:18 Christ also once for all died for sins, the
innocent One for the guilty many, in order to bring us to God. He was put to
death in the flesh, but made alive in the spirit, in which He also went and proclaimed His Message to
the spirits that were in prison, 1Pe 3:20Open in Logos Bible Software (if available) who in ancient times had been disobedient, while God’s longsuffering
was patiently waiting in the days of Noah during the building of the Ark, in
which a few persons–eight in number–were brought safely through the water.”
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3 ፡18 ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን
እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥ 19 በእርሱም ደግሞ
ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤ 20 ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት
በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።
አንድአንዶች ይህንን ቃል ጠምዝዘው ሄዶ የሰበከው ከሱበፊት ለሞቱ ጻድቃን ሰዎች ለማውጣት
ነው ይላሉ። ከቃሉ እዳየነው ግን የሰበከው በእስራት የነበሩትን መናፍስት ነው:: ለሴም ፤ለሄኖክ፤ ለኖህ፤ ለአብርሃም፤ ለያቆብ
፤ለኢሳቅ ወይም ለሙሴ፤ ለእያሱ ወይ ለኤልያስ ወይም ለየትኛውም በቀድሞ ኪዳን አካየዳቸውን ከእ/ር ጋር ያደረጉ ጻድቃን ለማናቸውም አይመለከትም::
እነዚህ ሁሉ ለእ/ር ህያዋን ናቸውና በመንፈሳዊው አለም አለም ሳይፈጠር በፊት የታረደው በግ ታርዶላቸዋልና ከአፈር የተሰራው
ስጋቸው ወደ እፈር ሲመለስ ከእ/ር ያመጣው መንፈሳቸው ወደ እ/ር ተመልሰዋልና ።
የሉቃስ ወንጌል 20፡38 ሁሉ ለእርሱ ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም ይለናል። ትንሳኤው በዚህ ምድር ከክርስቶስ ጋር አብረው ይገዙ ዘንድ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰው የሚለብሰው እንጂ እነሱ በመንፈሳዊው አለም ጊዜ ሰለሌ የጊዜ ሃይል ሳይዛቸው ተመልሰውከብረዋል። ለምሳሌ ያህል የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም። ብሎ ጌታ እንደ ተናገረ ሙሴና ኤልያስ ህግንና ነብያትን የሚወክሉት እንዳለ ሆኖ ሙሴ ሞትን አይተው የከበሩትን ኤልያስ ሞትን ሳያዩ የከበሩትን ይወክላሉና ። ከስርየቱ በፊትም ህያዋን ሆነው እናስተውላለን በጉ የታረደውአለም ሳይፈጠር በፊት ነውና። “የዮሐንስ ራእይ 13፡8 ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ…” በዚህም የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን እንዳይደለ እንገነዘባለን።
በጌታ ኢየሱስም የመስቀሉን መከራ ከተቀበለልን ቡሃላ ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ መንፈሱን እንደሰጠ።
ሞተው ከነበሩት ከቅዱሳን ብዙ ስጋዎች ተነሱ የሚለው በስብሶ የነበረው ስጋቸው ከትንሳኤው ሃይል አቋድስዋቸው ለምስክርነት ይሆኑ
ዘንድ ስጋቸውን ለብሰው መነሳታቸውን የሚያሳይ ነው እንጂ መንፈሳቸው እማ እስቀድሞ ወደ መጠባት ወደ እ/ር ተመልሶ እንደነበር ግልጽ ነው።
“KJV፣ Eccl 12፡7 Then shall the dust return to the earth as it
was: and the spirit shall return unto God who gave it. መጽሐፈ መክብብ 12፡7 አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም (spirit መንፈስህ) ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።” ሰለዚህ የነዚህ ሰዎች ትንሳኤ በስብሶ የነበረው ስጋቸው የማይበሰብሰው ከእ/ር ወጥቶ ወደ እ/ር
የተመለሰው መንፈሳቸውን በትንሳኤው ሃይል እ/ር በማዋሃድ ያስነሳቸው ናቸው። የማይበሰብሰውን ለብሰው ወደ ቅዲስትቱ ከተማ ወደ ሰማያዊትዋ እየሩሳሌም መግባት ቻሉ ከዛም በምድርም ለብዝዎች ተገልጠው መታየት ቻሉ። በራእይ ሂዱና አስተውሉ በፍልስጤም ምድር ያለችው ምድራዊትዋን እየሩሳሎም ምንም ቅዲስትቱ ከተማ የሚያስብላት እንደሌለ
ታያላችሁ ሰማያቱን እየሩሳሌምን ቅድስቲቱም ከተማ ብሎ ሲጠራት እናያለን “የዮሐንስ ራእይ 21፡2 ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥” እንደዚሁ በ(የዮሐንስ ራእይ 21፡10)
ጌታ የተሰቀለባት እና ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደሉት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቃን ደም ሁሉ ያለባትና የሚደርስባት ምድራዊትዋ እየሩሳሌም እንካንስ ቅድስቲቱም ከተማ ብሎ ሊተራት ቀርቶ በታሪክ ገናና እንደመሆንዋ መጠን ታላቂቱ ከማለት በቀር በስማ ብቻ እንካ አይጠራትም “የዮሐንስ ራእይ 11፡8 በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞ ጌታቸው የተሰቀለባት ናት።”
የሙሴና የኤልያስን ህያውነት እናስተውል
የማቴዎስ ወንጌል 17፡1 ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። 2 በፊታቸውም
ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። 3 እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። 4 ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። 5 እርሱም ገና ሲናገር፥
እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
“መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 2፡11 ሲሄዱም። እያዘገሙም ሲጫወቱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።” እንግዲህ አፈርየሆነው ስጋቸው ወደ ነበረበት ምድር ሲመለስ፥ (spirit መንፈሳቸው) ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ተመልስዋልና በመንፈስ ህያዋን ናቸው በዚህም ለጌታ ሁሉ ለእርሱ
ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን እንዳይደለ እወቁያለውን እንገነዘባለን።
ነገር ግን በ “19 በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት(spirit መንፈሳቸው) ሰበከላቸው፤ 20 ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥
የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።” እነዚህ ለየት የሚያደርጋቸው ( spirit መንፈሳቸው) ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር እንደ መመለስ ፈንታ እ/ር አሰራቸው። ጌታም ሄዶ በኖህ ዘመን የእግዚአብሔር ትዕግሥት 120 ያስጨረሱትን በኖኅ ዘመን አልታዘዙም ለሚላቸው ወንጌልን ሰበከላቸው። ለምን ወንጌሉን መስበክ አስፈለገው?
እዛው ወረድ ብሎ በ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡6 መልሱን ይነግረናል።
በነገራችን ላይ መጽሐፍ ቅዱስ በብራና መልክ የተዘጋጀ ወጥ ፅሑፍ ነበረ። ለአንባቢያን እንዲመች በምእራፍና በቁጥር ተከፋፍሎ የተሰራው በ1560 ጄኔቫ መጽሃፍ
ቅዱስ በመባል የሚታወቀው አንድ የሊቃውንት ቡድን በጄነቭ ሆነው ሰሩ። ሁለተኛው እትሙም በ1652 ታተመ ይህ ነበር የመጀመርያው
የእንግሊዝኛ ትርጉም በምእራፍና በቁጥር ተከፋፍሎ የተሰራው ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡6 ስናስብ የተያያዘ ጽሁፍ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ቃሉም “እንደ ሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ስለዚህ ምክንያት ወንጌል ለሙታን ደግሞ ተሰብኮላቸው ነበርና።” “1Pet 4፡6 for this cause was the gospel preached also to them that are dead, that they might be judged according to men in the flesh, but live according to God in the spirit.”
የሃዋሪያው መልእክት ግልጽ ነው። ስጋቸው በተመለከተ ሙታን ናቸው። ህያዋን ሆነው ያሉት በመንፈስ እንደሆነና ታስረውም እንዳሉ ወንጌሉ ተሰበከላቸው። መገንዘብ ያለብን በሲኦል የዘላለም ስቃይ ይጠብቅሃል ተብለው አይደለም የተሰበከላቸው። ነገር ግን ወንጌል የምስራች መልካም ዜና የእ/ር ኁይል ለማዳን ነው የተሰበከላቸው።በስጋቸው ሳሉ ሃጢያታቸው የከፋ ስለ ነበር እ/ር ጎርፍ ልኮ በውሃ በማስጠም በጎርፉጠራርጎ ወደ ሲኦል ወሰዳቸው በዚያም ለዘላለም ሳይሆን ያሰራቸው ለሁለት ሺ ሶስት መቶ ሃምሳ ዘመናት ታሰሩ። “እንደ ሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው የሚለን ያንን ነው ። በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ በሲኦልም ላይ ስልጣን ያለው ጌታ ሄዶ ወንጌልን ሊሰብክ ሄደ እንጂለቫኬሽን አልሄደም ወንጌሉም የእ/ር ታላቅ ስራ ፍርዱ የዘላለም ሳይሆ በዘመናት ወስጥ የተወሰነ እንደሆነ እናስተውላለን ። በዚህም በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ሆኑ። ማንም ሲናገር እንደእ/ር ቃል ይናገር። አሜን!
እንደኖህ ዘመን በመምጣቱም የሚፈረድባቸው በአላማ ለማረም ጽድቅን ለማስተማር ነው። ይህን ሊፈጸም ያለ ትንቢት አስተውሉ!
ኢሳ 29/9 ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩት ጽድቅን ይማራሉና:> በእለም ያሉ ሁሉ ጽድቅ ተምረው ታይቶ ይታወቃልን
ስለዚህ ይህ ገና የሚፈጸም ትንቢት ነው።> when thy judgments are in the earth , the inhabitants of the WORLD will learn righteousness .[uprightness & right standing with GOD.] Isaiah 26/9 አስተዋላቹሁን ፍርዱ በአለም ሲገለጥ ምንን ይማራሉ ይላል? ጽድቅን! ሃሌሉያ!
Ps 130፡4 But there is forgiveness with thee, that thou mayest be feared ትፈራ ዘንድ በአንተ ዘንድ
ይቅርታ አለ። አሜን። ወንድም ቢኒ። July 28, 2011 Brother Binyam T. Alemayehu
https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=1689837247768893&id=100002279031400