
ወንዱ ማነው? ሴቲቱስ? መንፈሳዊ ፍቺ (ኦሪት ዘፍጥረት 3:15) ጥያቄ በወንድም ደምስ፤ መልስ ወንድም ቢኒ ፤
ክፍል አንድ 04/11/2018
” በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።” (ኦሪት ዘፍጥረት 3:15) ወንዱ ማነው? ሴቲቱስ?
ሕያው ነውና፥ የሚሠራም የእግዚአብሔር ቃል ፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ባህርዩን ይዞ፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥማችንን እስኪለይ ድረስ እየወጋን፥ የልባችን አሳብ የህዋሳቶቻችንን ስሜት መመርመሩን በመቀጠሉ በጌታ ደስ ይለኛል በአባት የሆነ የልብ ደስታ እንደ ሁልጊዜ ግብዣ ነው።
ዝም ልል ነበረ ነገሩን ሳየው እ/ር ጨክነዋል እያደረገ ላለው ነውጥ ልጆቹም በአካሔዳቸው መስለውታል። ወገኖች በጥልቀጥ በሚገርም እይታ በጠቅላላ አካል አንፃርና ከዚያም በላይ አሳይተውናል። እኔ ደግሞ በሌላ ሽክርክር በእኛ ውስጥ ያለውን የጠለቀ የውስጠተ ውስጣችን የእ/ርን እውነት በጥቂቱ ልጨምርበት ይፈቀድልኝ። እየሱስ ክርስቶስን ልምሰል ካላችሁ እይታችሁ ሁሉ 360 ዲግሬ በእ/ር ገና ይዞራል የሱ እይታ የኛ እስኪሆን ገና የምድርና የሰማያት መረዳታችንን ቀስ በቀስ ማናወጡ የሚጠበቅ ነው። ለተፈጥራዊው ሰው ሁሉ ነገር ተፈጥራዊ ነው ለመንፈሳዊ ሰው ደግሞ በአንፃሩ ሁሉ ነገር መንፈሳዊ ነው። እንግዲህ መንፈሳዊያን ብቻ ያንብቡት ዛሬ ዛሬ የጌታ አካሄድ ከአዛሄልም ሰይፍ[ቃል] ያመለጠውን ሁሉ። ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩም ሰይፍ[ቃል] ያመለጠውን ሁሉ ኤልሳዕ ይገድለዋል። እየሆነ ነው።
ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥እናገራለሁ የሚለው ጌታ ትላንትም ዛሬም ነገው ያው ነው በዮሐንስ ራእይ ብቻ ከሆነ በምልክት የሚናገረን ከመሰለን ብዙያመልጠናል። መንፈሳዊው ነገር ልናስተውለው ከምንችለው በላይ ትላቅ ነውና። ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ የዮሐንስ ራእይ ያለው ታሪካዊ እውነታው ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ እርከን የሚነካ ፍቺም እንዳለው ማወቁበረከት ነው የእ/ር ጠቅላላ ምክሩን አጥርተን ለማየት ያስችለናልና። ቃሉ ሲነግረን የቀደሙት የህይወታቸው ታሪክ ሁሉ ደራሲው ጌታ ሲሆን ተደራስያኑ ፍጥረት ሁሉነው ይህም አካሄዳቸው እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ ያለነውን ሊናገረን ሊገሥጸን ሆነ ተጻፈም ይለናል የሰዎች አካሄዱ ሁሉ የተነደፈው የታቀደው ከእግዚአብሔር ዘንድ ነውና ። መጽሐፈ ምሳሌ 20/24 የሰው አካሄዱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ እንግዲያስ ሰው መንገዱን እንዴት ያስተውላል?
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10/11 ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ።
‘ይህ ሁሉ ምሳሌ ይሆን ዘንድ በእነርሱ ላይ ደረሰ፤ የዘመናት ፍጻሜ የደረሰብንን እኛን ለማስጠንቀቅም ተጻፈ። ‘1 ቆሮንቶስ 10:11 መደበኛ ትርጉም
(1Cor 10:11 [AMP])Now these things befell them by way of a figure [as an example and warning to us]; they were written to admonish and fit us for right action by good instruction, we in whose days the ages have reached their climax (their consummation and concluding period).
(1Cor 10:11 [YLT])And all these things as types did happen to those persons, and they were written for our admonition, to whom the end of the ages did come,
(1Cor 10:11 [Weymouth])All this kept happening to them with a figurative meaning; but it was put on record by way of admonition to us upon whom the ends of the Ages have come.
(1Cor 10:11 [NET])These things happened to them as examples and were written for our instruction, on whom the ends of the ages have come.
[KJV 1Cor 10/11 ]Now all these things happened unto them for ensamples: and they are written for our admonition, upon whom the ends of the world are come. ወንድም ቢኒ …2
ክፍል ሁለት ወንዱ ማነው? ሴቲቱስ? ጥያቄ በወንድም ደምስ፤ መልስ ወንድም ቢኒ ፤
ወደ ሮሜ ሰዎች 5/19 በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።
Rom 5/19 19. For JUST AS through the unwillingness to listen resulting in disobedience (or: the erroneous hearing leading to disobedience (to hear alongside)) of the one man THE MANY were rendered (established; constituted; placed down and made to be) sinners (failures; ones who miss the target or a sense of false identity (bringing us into death,)), THUS ALSO through the submissive listening resulting in obedience of the One THE MANY will be rendered (placed down and established as; constituted; appointed to be bringing us into eternal life through Jesus Christ our Lord) just ones (ones who have been right-wised; ones in the Way pointed out; righteous ones; ones in right relationship).
የአዳም አለመታዘዝ አንድ እንግዳ ድምጽ የእርሱን እውነተኛ የክብር አካየድ አቅጣጫ እንዲለውጥ በማድረግ አዕምሮውን መቆጣጠር እንዲችል በመፍቀዱ ነው። በዘፍ 3 :1 ውስጥ “እባብ” እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ከፈጠራቸው የዱር አራዊት ሁሉ ተንኰለኛ ነበረ፤[አሃ አሁን ገባን ከመጀመርያው በእግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) የተፈጠረ የዱር አራዊታዊ ባህሪ ሁሉ የያዘ ተንኰለኛ ነበረ እንጂ ወድቆ የተለወጠ አትደለም።(እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት[ምንጭ] ነውና። የዮሐንስ ወንጌል 8/44)] “እባብ” በእብራይስጥ ስትሮንግ Strong’s ሲተነትነው “እባብ” የሚለውን ቃል ሲፈታው “ቱስ ቱሽ የሚል፤ አሾክሻኪ፤ መለኮታዊነትን መለማመድ ። ምልክቶችን መከታተል, በተሞክሮ መማር፤ በትጋት መከታተል፤ እድልን መለማመድ፤ እንደ ገጽ ምልክት መውሰድ” በማለት ይገልጻል።[Strong’s , HEBREW “serpent” as “to hiss, . whisper , to practice divination, divine, observe signs, learn by experience, diligently observe, practice fortune-telling, take as an omen.”] ስለዚህም ይህ ቃል ወደ ኤደን ገነትን የገባውን ህያው አካል ያለው ፍጥረት የሚያመለክት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር በመጀመርያ በተገለፀው አካየድ መስመር ውጭ የሚሠራ የስጋዊው አእምሮ እንቅስቃሴ ነው። ስንቶቻቹሁ ይሄ ቱስ ቱሽ የሚል፤ አሾክሻኪ፤በጆሮ ግንዳችሁ መሃል ዘመናቹሁን ሲያስታቹሁ አስተውላቹሁታል? ሰምታቹሁት ታውቃላችሁ? እኔ በየቀኑ ሃሳቡን እንዳልስት በእ/ር መንፈስ ምስክርነት ላይ እቆማለሁ። ሞት ማለት የስጋ አእምሮ ነውና። ወደ ሮሜ ሰዎች 8/6 የሥጋ አእምሮ ማሰብ ሞት ነውና፥ የመንፈስ አእምሮ ሃሳብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።Rom 8/6 For to be c-a-r-n-a-l-l-y m-i-n-d-e-d i-s d-e-a-t-h; but to be s-p-i-r-i-t-u-a-l-l-y m-i-n-d-e-d i-s l-i-f-e and p-e-a-c-e.
አዎን ስጋዊ አእምሮ ነው የእ/ር ጠላት መለኮት በእናንተ ውስጥ እንዳይሰራ ያለማቌረጥ የሚተጋው እኛን ብቻ ሳይሆን አለሙን ሁሉ ያሳተው የጥንቱ እባብ በተንኮል አድጎ አሁን በዘንዶ ባህሪ እሳት እየተፋ ፍጥረትን ያሳተው ቱሽ የሚል፤ አሾክሻኪ፤ እሱነው አሁን ጌታ ይመስገን አሳቡን አንስተውም ሌላ የሚያስትበት ሁሉ የሚፀነሰው ከሃሳቡ ነውና ።
እያንዳዱ ሰው በእባቡ[የስጋዊው አእምሮ እንቅስቃሴ ] በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ከዚህ በኋላ ምኞት ተፀንሳ ኃጢአትን ስትወልድ፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ስትወልድ እባቡ አፈራችን መሬታችን[[ስጋችን] እየላሰ ደልቦ ስውር ዘንዶ ሆኖ] አለሙን ሁሉ ሲያስተው ማን ከህያዋን ምድር ማን አስተዋለ?
ወደ ሮሜ ሰዎች 8/7 ስለ ሥጋ ማሰብ[ የስጋ አእምሮ carnal mind] በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና[ የእ/ር ጠላት enmity against God ]፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤
Rom 8/7 Because the carnal mind is enmity against God: for it is not subject to the law of God, neither indeed can be.
ወንዱ ማነው? ሴቲቱስ? ጥያቄ በወንድም ደምስ፤ መልስ ወንድም ቢኒ ፤……3
ክፍል 3
በዘፍጥረት አባት ምን እያለን? በኦሪት ዘፍጥረት ውስጥ ስናስተውል ሰው ከእግዚአብሔር ውስጥ ወጥቷል። ከአጽናፈ አጽናፍ ቢታሰስ በየትኛውም ሰማያት ውስጥ ሌላ የሕይወት ምንጭ የለም ያለ እ/ር የለም። ስለዚህ ከውድቀት በፊት ሰው የፈጣሪን ፈቃድና ዓላማ እንዲፈጽም የሚያስፈልገውን ከአምላክ ውጭ የሚያገኝበት የሆነ ሌላ ምንጭ ምንም ነገር አልነበረም። በዔድን የአትክልት ስፍራ ያሉ ዛፎች በእግዚአብሔር የተተከሉ ሲሆን ከመጀመሪያውም አዳምን በሕይወትን ለማኖር የሚያስችሉ እንዲበሉ የተዘጋጁ ለመብላትም ተስማሚ ነበሩ። መንፈሳዊ አመልካቹነቱን እንዳናይ ግን ሁላችን የጋረደን እውቀት አለ ይም ከእውቀት ዛፉ የተገኘ ለሺ አመታትም ጡንቻ ያወጣ የፈረጠመ መረዳት ነው። በርካታ የስነ-መለኮት ሰዎች የዔድን ገነት ጽንሰ-ሐሳብ እና ተጨባጭ ሂደቱ ቃል በቃል በመተርጎም ስላስተማሩን ሙሉውን መንፈሳዊ ፍቺ እንዳናይ ለሺ አመታት እይታችንን የማይረባ እንዲሆን አድርገውታል። አስቡት ሰማይንና ምድርን የፈጠረው ታላቁ አምላክ በርካታ ዛፎችን የያዘ የአትክልት ቦታ ለመንከባከብ ሰውን አዞ ፈጥሮዋል ። ነገር ግን መርሳት የሌለብን በዚህ የአትክልት ስፍራ ሁለት ዛፎች አሉ አንዱ የህይወት ዛፍ እና ሌላኛው የመልካምና የክፉ እውቀት ዛፍ። የሚገርም በዘመናት የሸመገለ የክብር አባት የሚገርም አስተማሪ። በበዘመናት የሸመገለ ስል ጥያቄ እንደ ማይፈጥርባችሁ እርግጠኛ ነኝ። “ትንቢተ ዳንኤል 7/9 ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ።” በዘመናት የሸመገለው አባት በመንፈሱ እንኳን መምጣቱን ቀጠለ ፍርድ ለልዑሉ ቅዱሳን እየሰጠ ነውና ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወስዱበት ዘመን መጥተዋል እባባና ጊንጡ መረገጡ ይቀጥላል ቅዱሳን ከእንግዲህ አያሸነፋቸውም። በእ/ር ሃይል በቅዱሳኑ በኩል ፍርድ እየሆነ ነው፥ ቅዱሳኑ ፍጻሜም ድረስ ያፈርሱትና ያጠፉት ዘንድ ግዛቱን ያስወግዱታል።
“ትንቢተ ዳንኤል 7/22 በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ፥ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወስዱበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ አሸነፋቸውም። 26 ነገር ግን ፍርድ ይሆናል፥ እስከ ፍጻሜም ድረስ ያፈርሱትና ያጠፉት ዘንድ ግዛቱን ያስወግዱታል።27 መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለትማል።28 የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው። እኔም ዳንኤል በአሳቤ እጅግ ተቸገርሁ፥ ፊቴም ተለወጠብኝ፤ ዳሩ ግን ነገሩን በልቤ ጠብቄአለሁ።”
እ/ር ውጤታማ አስተማሪ ነው በዘፍጥረትም መንፈስ ሳለ ሊያስረዳን የፈለገውን በህይወታቸው በኑራቸው በምሳሌ ደረሰው ተረከው በስጋ ወራቱም ቢሆን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥እናገራለሁ ያለው ጌታ ትላንትም ዛሬም ነገው ያው ነው። እንደገና ወደ አባቴ[ወደ መንፈሴ] እመለሳለሁ ብሎ ወደ መንፈስ ክብሩ ተመለሶ በራእይ መጽሐፍም በገላጭ ምልክት signs and symbols ማስረዳቱን ሲቀጥል እናስተውላለን። ጌታ በእውን በሰዎች ታሪክ ሆነ በተምሳሌት የደረሰው ሁሉ ምልክት ወይም ተምሳሌትነት አለው ይህም የሚነገረው በጥሬው ካለው ትርጉሙ ውጪ ሌላ መንፈሳዊ ነገርን የሚወክል ታሪክ ፤ምስል፤ ቃል ወይም ሃረግ ነው።
ከመንፈሳው ሚስጥሩ አንፃር ደስ የሚል ትምህርታዊ የፍጥረት የካርቱን ፊልም የጀመረው ዘፍጥረት ላይ ነው። አስቡት እስቲ ሕይወትን የሚያፈራው “የሕይወት ዛፍ” ምን እንደሚመስልና “መልካምና ክፉን የሚያፈራው” ዛፍ ምን እንደሚመስል? ፍቺው ያ የተማርነው ተፈጥራዊው ብቻ አይመስለኝም! መቼም ለተፈጥራዊው ሰው ሁሉ ነገር ተፈጥራዊ ነው ለመንፈሳዊ ሰው ሁሉነገር መንፈሳዊነው ብለናል። የዔድን የአትክልት አጠቃላይ ታሪክ በምሳሌነት በዚህ መልክ ካልሆነ በሌላ መልኩ መደበኛ መረዳት መረዳቱን ለማስተላለፍ የማይችል ስውሩን እውነት የሚያስረዳ ወሳኝ ትምህርት የምናገኝበት የ66ቱ መጽሃፍት ሁሉመሰረት የያዘ መንፈሳዊ ትእይንት የሚያስረዳ ታላቅ ትምህርት ቤት ነው። የሃይማኖት ሀሳብ በዚህ ነጥብ ላይ የማይፈወስ እቋሪ ውሃ እንደሆነ አውቃለሁ። ይህ የተፃፈው ለንስር ፃድቃን ነው። “በበሰሉት መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፥ ነገር ግን የዚችን ዓለም ጥበብ አይደለም የሚሻሩትንም የዚችን ዓለም ገዦች ጥበብ አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን።“
ወንዱ ማነው? ሴቲቱስ? ጥያቄ በወንድም ደምስ፤ መልስ ወንድም ቢኒ …4
ክፍል 4
አስተውሉ እኔ በኤደን ገነት ውስጥ ያለውን ታሪክ እውን አልነበረም አላልኩም ። በጌታ መንፈስ መገለጥ በእያንዳንዱ ታሪክ ጥቃቅያኖቹ ሳይቀሩ ከዘፍጥረት መጽሐፍ ለእኛ የሚናገረው መንፈሳዊ መልክት አለው እያልኩ ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዛፎች እንዴት እንደተገለጹ እንመልከት ጌታ እየሱስ ዛፎች የሰው ተምሳሌት አድርጎ ተጠቅሞ አሳይቶናል። ‘
‘እነሆ፤ ምሣር የዛፎችን ሥር ሊቈርጥ ተዘጋጅቶአል፤ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል። ‘ማቴዎስ 3:10
መዝሙረ ዳዊት1፥3 እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
52፥8 እኔስ በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለመለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፤ ለዓለምና ለዘላለም በእግዚአብሔር ምሕረት ታመንሁ።
‘በውሃ ዳር እንደ ተተከለ፣ ሥሩንም ወደ ወንዝ እንደ ሰደደ ዛፍ ነው፣ ሙቀት ሲመጣ አይፈራም፤ ቅጠሉም ዘወትር እንደለመለመ ነው፤ በድርቅ ዘመን አይሠጋም፤ ፍሬ ማፍራቱንም አያቋርጥም።” የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነው፤ ፈውስም የለውም፤ ማንስ ሊረዳው ይችላል? ‘ኤርምያስ 17:8-9
‘የዱር ዛፎች ሁሉ ረጅሙን ዛፍ፣ ዝቅ ዝቅ ያለውንም ዛፍ ከፍ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ የለመለመውን ዛፍ አደርቃለሁ፤ ደረቁንም አለመልማለሁ።” “ ‘እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ እኔው አደርገዋለሁ።’ ”’ሕዝቅኤል 17:24
ትንቢተ ዳንኤል 4/19 የዚያን ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል አንድ ሰዓት ያህል አሰበ፥ ልቡም ታወከ። ንጉሡም መልሶ፦ ብልጣሶር ሆይ፥ ሕልሙና ፍቺው አያስቸግርህ አለው። ብልጣሶርም መልሶ አለ፦ ጌታዬ ሆይ፥ ሕልሙ ለሚጠሉህ፥ ፍቺውም ለጠላቶችህ ይሁን። 20 ትልቅ የነበረው የበረታውም፥ ቁመቱም እስከ ሰማይ የደረሰው፥ መልኩም እስከ ምድር ሁሉ ድረስ የታየው፥
21 ቅጠሉም አምሮ የነበረው፥ ፍሬውም የበዛው፥ ለሁሉም መብል የነበረበት፤ በበታቹም የምድር አራዊት የተቀመጡ፥ በቅርንጫፎቹም የሰማይ ወፎች ያደሩበት ያየኸው ዛፍ፤22 ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ታላቅና ብርቱ የሆንህ አንተ ነህ፤ ታላቅነትህ በዝቶአል፥ እስከ ሰማይም ደርሶአል፥ ግዛትህም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ነው።
እውነትን ለመስማትና ለመስማማት ጆሮዎች ላለው ግልጽ ነው በመጽሐፍ ቅዱስ “ዛፎች” ብሎ ተምሳሌት ሲናገር ስለ ሰዎች ይናገራል። ይህንን ካስተዋልን ዘንዳ አሁን ይህን እውቀት በኤደን ገነት ውስጥ ተግባራዊ እናድርግና እንየው።
ወንዱ ማነው? ሴቲቱስ? ጥያቄ በወንድም ደምስ፤ መልስ ወንድም ቢኒ …5
ክፍል 5
ሁለት ዛፎች አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ በጠቅላላው በመንፈሳዊ ቅኔ ድራማው ዙሪያ የሚያተኩረው በዚህ የአትክልት ቦታ ውስጥ እንደሚናገረው አንዱ የሕይወት ሃሳብ የሚያመነጨው ዛፍ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ መልካምና ክፉን ሃሳብ እያመነጨ የሚያስታውቀው ዛፍ ነው። እነዚህ ሁለት ህይወት ያላቸው ሰዎችን የሚወክሉ ናቸው። የመጀመርያው የህይወት ዛፍ ዘንድ ከሚመጣው “የሚበሉትን” እውነተኛ ህይወት የሚገለጠባቸውን የሚያሳይ ሲሆን የሕይወት ዛፉ የሚወክለው ደግሞ ክርስቶስን ነው። ስለዚህም እግዚአብሔር መልካምንና ክፉን ከምታስታውቀው ዛፍ እንዳይበሉ ከተናገረ በኋላ ከበላችሁ”እየሞታችሁት ትሞታላችሁ in dying you will die.” አላቸው። ስለዚህ ከሕይወት ዛፍ ፍሬ መብላት በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ካለው ሕይወት መበብላት ሲሆን እርሱበዚህ አለም እንደነበረ መሆን ነው። ሌላኛው ሰው ግን ከእግዚአብሔር ወይም ከክርስቶስ ውጭ “ሕይወት” እንዳለ የሚያምኑና በ”ዕውቀት” የሚኖሩትን ያሳያል። የ”ዕውቀት” ሕይወቱ ከእግዚሐብሔር ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። ስለዚህ እነዚህ ሁለት ዛፎች ሰብአዊነትን በሁለት ቡድኖች ይከፋፈላሉ። በዘፍጥረት ምዕራፍ 2 እና 3 ውስጥ በጣም ግልጽ ነው በእነዚህ አይነት ሰዎች መካከል ያለውን ልዩነት ማስተዋል ይቻላል።
አሁን ወደ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15/45 እንዲሁ ደግሞ፦ ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል[ኦሪት ዘፍጥረት 2/7 ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።]፤ ኋለኛው አዳም(ኢየሱስ ክርስቶስ) ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።
47 የፊተኛው ሰው[አዳም] ከመሬት መሬታዊ ነው፤ ሁለተኛው ሰው(ኢየሱስ ክርስቶስ) ከሰማይ ነው። ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ የመጀመሪያው ሰው አዳም ” ተሠራ “made” (ghin’-om-ahee … meaning to become, i.e. to come into existence) በሂደት ሕያው ነፍስ መሆኑን ያሳያል ግን አዳም በመጀመሪያ ዘፍ1:26 የተፈጠረው እንደዚያ አልነበረም በእግዚአብሔር በመንፈስ አምሳልና መልክ ነበረ እግዚአብሔር አዳምን ወንድና ሴት አድርጎ የፈጠረው ። መልካምና ክፉን የሚያስታውቀውን ዛፍ መብላቱ ከመጀመሪያው ጀምሮ የተፈጠረበትን መንፈሳዊ ባህሪና ማንነት ተቀይሮ “ሕያው ነፍስ” ሆነ ሳይወድቅ በፊት ልጆች ቢያዘጋጅ ኖሮ በእግዚአብሔር መንፈስ አምሳልና መልክ ልጆችን ያመጣ ነበረ ከውድቀቱ ቡሃላ ስለሆነ ልጆችን ያዘጋጀው ሁላችንም ልጆቹም “ሕያው ነፍስ” ሆንን።
ህያው ነፍስ ማለት ከነፍሱ ክብር በሚገኝ የሚኖር አኗኗሩ ከነፍሱ እንዳገኘው የሚኖረው ማለት ሲሆን ይህም አእምሮን፤ ስሜትን እና ፍቃዶችን ያካትታል። ስለዚህ በዔድን ገነት የተከናወነው ነገር በመጀመሪያ እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰው የክርስቶስ አእምሮ እንዳይጠቀም ማጥቃት ነው። አዕምሮ በእግዚአብሄር አተኩሮ ላይ ብቻ በህይወት እየተመላለሰ የሚኖር ነበረ። አዳም እንደተፈጠረ እንደ መንፈስ ይመላለስ ነበር። ነፍስን የምትወክለው ሔዋን መንፈስን ከሚወክለው ከአዳም አፈንግጣ ተለየች ከሱ የነበራት ህብረት ወደጎን አስቀምጣ ሌላ ጋር በንግግር ታጨች እሱም “ከእባቡ” ነው ይህም የእራሷ የተፈጥሮ አእምሮ ሲሆን ይህም ከመንፈስ የተለየ ነበር። ይህ መለያነት ከመንፈስ ጥበብ እና መግባባት ነጠላት። ይህም ያስከተለው ውጤት በእባቡ እንድትደገፍ አደረጋት ከአምስት የስሜት ሕዋሶች፤ ማየት፤ መስማት፤ መዳሰስ፤ ጣዕም እና ሽታ ላይ ብቻ የሚሰራ በመሆኑ ይህ አካሄድ ደግሞ ወደ መንፈስ ቅዱስ ጥበብ ህይወት እንዳትገባ የሚከለክል ሆነ። እነዚህ ከተፈጥሯዊ የነፍስ የስሜት ህዋሳቶች ወደ ረቂቁ የእግዚአብሔር መንፈስ ሊደርሱበት አይችሉም። ስለዚህ እርሷ በምድርዋ ውስጥ ካሉት የማንኛውም እንስሳዊ አውሪያዊ ባህሪ የበለጠ ርኩስ በሆነው “እባብ” ምህረት ላይ ወደቀች። ያ “እባብ” ትክክለኛውን እውቀት ካላችሁ ፈጽሞ “ሞትን አትሞቱም” ብሎ አለምን ሁሉ ማታለል ችሏል።ወንዱ ማነው? ሴቲቱስ? ጥያቄ በወንድም ደምስ፤ መልስ ወንድም ቢኒ …6
ክፍል 6
አሁን ጌታ “እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።” ደግሞም “ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።”
ይህ ክብር ተስፋ ካለው አሁን ግን ተስፋችን መልሶ ሊያስጨብጠን በውስጣችን የእግዚአብሄር ክብር የክርስቶስ መኖሩን ሚስጥሩን ነግሮናል። ከዚህም ሚፈልቀው መንፈሳዊ የህይወት ወንዞች ከክርስቶስ ህይወት መቅዳት ይበዛልን ዘንድ በዚህም እርሱ ህይወታችን እውቀታችን መረዳታችን ሁለንተናችን ይሆንልናል።
የእግዚአብሄር ክብር የክርስቶስ መልክ ነው። “ሁሉ ሃጥያትን ሰረተዋል የእ/ር ክብር ጎድላቸዋል” በሃጥያት ምንያት የጎደለብን ወርቅ ብር አልነበረም የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ነው። ሃጥያት የሚለው ጽንሰ ሃሳብ ልንረዳው ይገባል በግሪኩ ሃማርቲያ HARMATIA ሲሆን ይህ እስፖርታዊ ቋንቋ ነው፤ ትርጉሙም [ምልክቱን መሳት ነው። MISSING THE MARK ]በአንድ ቀስተኛ ቀስቶ የቀስቱን ፍላጻውን ካሽቀነጠረ ኢላማውን ወይም አላማውን ከሳተ ውድዱርን የሚያየው ህዝብ ሃማርቲያ HARMATIA ብሎ በታላቅ ድምጽ ይጮካል። እኛም መኖር በሚገባን ትተን ኢላማችን የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ስለሳትን ሃማርቲያ HARMATIA ሆነብን አሁን ግን እ/ር ይመስገን በሃማሪቲያ HARMATIA ያጣነው የጎደለብን የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ተመለስን። የእ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን ክ-ብ-ር ኢ-የ-ሱ-ስ ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ነው። የሐዋርያት ሥራ 7/55 መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን ክ-ብ-ር ኢ-የ-ሱ-ስ-ን-ም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፦
ይህ የሂወት ዛፍ ክርስቶስ አሁን በእኛ ውስጥ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ‘ለእነርሱም እግዚአብሔር የዚህ ምስጢር ክብር ባለጠግነት በአሕዛብ መካከል ምን ያህል እንደሆነ ለማሳወቅ መረጠ፤ እርሱም የክብር ተስፋ የሆነው በ-እ-ና-ን-ተ ው-ስ-ጥ ያ-ለ-ው ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ነ-ው። ‘ቈላስይስ 1:27
Colssians1/27. To whom God wills (purposed; intends) to make known by intimate experience, what [are] the riches of the glory of this Secret (or: the wealth which has it source in this sacred mystery’s manifestation which calls forth praise) within the multitudes (among the nations; in the Gentiles; among the swarms of ethnic groups), which is (exists being) Christ within you folks, the expectation of the glory (or: Christ, which continuously exists within you [is] the hope of the manifestation which calls forth praise), የዚህ ምስጢር ክብር ባለጠግነት የገባው ደስ ይበለው። ተፈፀመ። Brother Binyam T. Alemayehu