
የሁለተኛው ሞት ሂደት ፍቺ በሰው ውስጥ / መለኮታዊ ሹኩሹኩታ ክፍል 5
(ራእይ 20 6-15) “የሁለተኛው ሞት ሂደት ፍቺ በሰው ውስጥ ” ክፍል ሶስት
by Brother Binyam T. Alemayehu 04/05/2018
” የዮሐንስ ራእይ 20/6 በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፥ ”
“ሁለተኛው ሞት” በአግባቡ ለመረዳት እንዲቻል የመጀመሪያ የሆነውን እና የመጀመሪያው ሞት ምክንያት ምን እንደሆነ ቢያንስ መረዳት አለብን።
አካላዊ ማንነታችን በተመለከተ ሞት ማለት በቀላሉ የሰው መንፈሱ ከስጋው መለየት ማለት ሞት ይባላል። በዚህም ምክንያት ህይወት በምድር ላይ ያከትማል ማለት ነው። ሞት ከአንድ ግዛት ወደ ሌላ ሽግግር ነው ። ከአንድ ዓለም ወደ ሌላ አንድ መንፈሳዊ ግዛት ማለፊያ ነው ። እናስተውል ለአንድ ግዛት መሞት ለሌላው ህያው መሆን ነው። “ከሥጋ ተለይተን ከጌታ ጋር መኖርን እንደምንመርጥ ርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ። to be absent from the body, is to be present with the Lord. ‘2 ቆሮንቶስ 5:8”
“….መንፈስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ፣ ፈጣሪህን አስብ። ‘ መክብብ 12:7 መደበኛ ትርጉም።” “ እንደምናስተውለው መንፈሳችን ከእግዚአብሔር የመጣ ነገር ነው ወደ እ/ርም የሚመለስ ነገረም ነው።
ይህን ካስተዋልን በተቃራኒው ከእ/ር ህይወት ለቆ የመጣው ማንነት ልክ ወደዚህ ሲቀላቀልና ወደ ምድር ሲመጣ ለህይወት ግዛት ሞቶ ለሞት ግዛት ህያው መሆን እንደጀመረ ሊሰመርበት ይገባል ይህም መንፈሳዊ ሞት የጀመረበት ቅጽበት ነው። የእግዚአብሔርን የብርሃንን ግዛት ለቆ ወደ ሞት ግዛት መግባት ያ ነው የመጀመርያው ሞት። መንፈስህም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ፣ ማለት ቀድሞውኑ ምንጭህ መንፈስህ ከእ/ር ወጥቶ የተገኘ እንደሆነ ሊስተዋል ተገቢ ነውና።
“….መንፈስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ፣ ፈጣሪህን አስብ። ‘ መክብብ 12:7 መደበኛ ትርጉም።” ምክንያቱም ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በመንፈስ በክርስቶስ ኢየሱስ “ውስጥ” የተፈጠርን [created in(within) Christ Jesus ] ልጆቹ ነንና።ኤፌሶን 2:10/ኤፌሶን 1:4-5
ሁሉ ሰው የሰው ሁሉ ብርሃን እና የእ/ር ክብሩ ክርስቶስ ጎድሎበት ወደ ከንቱነት ጽልመት ከመውደቁ በፊት ከእ/ር ክብር ከክርስቶስ አልጎደለም ነበር። በአዳም ወገብ ውስጥ ሆኖ ከመሞቱ በፊት አዳም በብርሃን[ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።] ይመላለስ ነበር። ይህች በክርስቶስ የነበረችው ሕይወት የሰው ብርሃን ነበረች ። በዚህ የሰው ሁሉ ብርሃን አዳምና ሄዋን ሲመላለሱ ነበር እስኪባረሩ ጌታን እግዚአብሔርን በመንፈስ ሲመላለስ በመንፋሳቸው ይሰሙት ነበር። ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ከገነታቸው ማለትም ከመንፈሳቸው ውስጥ ሲመላለስ ይሰሙ ነበር። የዮሐንስ ወንጌል 1/4 ኦሪት ዘፍጥረት 3/8 ገና ኤደኑ ባድማ ና ምድረ በዳ አልሆነም ነበረ። አዎን ዔደኑን እ/ር በረሀ ገና አላረገውም ነበረ። በመንፈስ የሆነ ደስታና ተድላ የተሞላ ነበር። አሁን ጌታ ይመስገን ወደ ኤደን በክርስቶስ እየመለሰን ነው። [ትንቢተ ኢሳይያስ 51/3 እግዚአብሔርም ጽዮንን ያጽናናል፤ በእርስዋም ባድማ የሆነውን ሁሉ ያጽናናል፥ ምድረ በዳዋንም እንደ ዔደን በረሀዋንም እንደ እግዚአብሔር ገነት ያደርጋል፤ ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ ይገኝበታል።]
‘ምክንያቱም፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀልንን መልካም ሥራ እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ “ውስጥ” የተፈጠርን [created in(within) Christ Jesus ]የእግዚአብሔር ፍጥረቱ ነን። ‘ኤፌሶን 2:10
(Eph 2:10 [KJV])For we are his workmanship, created in Christ Jesus unto good works, which God hath before ordained that we should walk in them.
‘በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በክርስቶስ “ውስጥ” [in(within Him) Christ] መርጦናልና። በፍቅር፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ፣ እንደ በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ወሰነን፤ ‘ኤፌሶን 1:4-5
Eph 1:4. even as He chose us out (selects, picks us out), within Him. before [the] casting down (a laying of the foundation; a conception) of [the] ordered system (world), [for] us to continuously be set‑apart (holy) ones and flawless ones (ones without stain; blameless ones) in His sight (presence) [in love; or, putting this phrase at the beginning of vs. 5:]
‘ሞት በአንድ ሰው በኩል እንደ መጣ፣ የሙታንም ትንሣኤ በአንድ ሰው በኩል ሆኖአልና። ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤ ‘1 ቆሮንቶስ 15:21-22እንዲሁ ደግሞ፦ ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15/45
በዚህ ጉዳይ ላይ እ/ር የሚያውቀው ሁለት የሰዎችን ዘር አዳሞችን ብቻ ነው። ሁለቱም የዘር መጀመሪያ ና መጨረሻ ናቸው። የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው፤ ሁለተኛው ሰው ከሰማይ የሆነ ጌታ ነው።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15/47 The first man is of the earth, earthy: the second man is the Lord from heaven. የመጀመሪያው የሰው ልጆችን ወደ ሞት ይዞ ወረደ ሁለተኛው ወደ ህይወት ይዞ አወጣ። አዳም ሁሉን ወደ ሃጥያት ይዞ ለመውደቅ አቅም እንደ ነበረው ሁሉ ክርስቶስ ይበልጡኑ ሁሉን ወደ ጽድቅ ህይወት ይዞ ሊነሳ የበለጠ ሃይል አለው። ‘እኔ ግን ከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሰውን ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ[እጎትታለሁ፤- በሃይልና በጡንቻ drag, forcefully it is muscular ።” ዮሐንስ12:32 ኅይል የእ/ር ነው!
ስለዚህ ሁለቱ ሞቶች አይመሳሰሉም ሁለተኛው ሞት የመጀመሪያውን ሞት ስራ ሁሉ ይቀለብሰዋል። በተመሳሳይ የመጨረሻው አዳም የመጀመርያውን አዳም ስራ ይቀለብሰዋል። በብዙ መልኩ ‘ቀጥሎም፣ “እነሆኝ፤ ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ” አለ፤ ሁለተኛውን ለመመሥረት የመጀመሪያውን ሻረ። ‘ዕብራውያን 10:9
የመጀመርያው አዳም ለጽድቅና ለእ/ር ሞተ ለሃጥያት ግን ህያው ሆነ የመጨረሻው፡አዳም ደግም ለሃጥያት ሞተ ‘በሞተ ጊዜ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኀጢአት ሞቶአል፤ ነገር ግን በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖራል። ‘ሮሜ 6:10 በዚህም ጽድቅን ሁሉ ፈፀመ። የመጀመርያው ሰው ሰውን ሁሉ ሐጢያተኛ አደረገ የሁለተኛው ሰው ሰውን ሁሉ አፀደቀ በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖሩ ዘንድ።
ሁለተኛው ሞት ከሚበሰብሰው ወደ ማይበሰብሰው ሽግግር ነው። ከስጋዊ አእምሮ ወደ መንፈሳዊ አእምሮ ሽግግር ነው። ለውጡ ለአንዱ አለም ሞቶ ለሌላኛው ከፍ ላለው መንፈሳዊ ግዛት ህያው መሆን ነው። ለእ/ር ከሞተው የአዳም ንቃተ ህሊና ለእ/ር ህያው ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ ንቃተ ህሊና መነሳት መነጠቅ ነው። ጌታ እየሱስ በስጋ በምድር እያለ የሰው ልጅ የሚኖረው በሰማይ[መመንፈስ ግዛት] ነው ይላቸው ነበር። የክርስቶስ ንቃተ ህሊና የሚያድረው በሰማይ[መመንፈስ ግዛት] ነው። ሃሌሉያ! የዮሐንስ ወንጌል 3:13 ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው። ልጅነት እንዲህ ነው ሁለት እግሩ በምድር ቆሞ የሰው ልጅ በመንፈስ አሁን ተነጥቆ የሚኖረው በሰማይ[ the One continuously being (constantly existing) within the heaven] ነው ብሎ እርፍ! “And no one has ascended (stepped up) into the heaven, except the One descending (stepping down) from out of the midst of the heaven: the Son of Mankind (the Son of the human; Humanity’s Son; the Son of man) – the One continuously being (constantly existing) within the heaven . John 3:13
ሞት ሃይል አልባ የተደረገው በሞት ነው።
“ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን።እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።
ወደ ዕብራውያን 2:9, 14-15” እንዳስተዋልነው ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥ የተገባ ስለነበር ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ቀመሰ ይህ ሞትን ሊያስቀርልን ሳይሆን ሰው ሁሉ ሁለተኛ ጊዜ እንዲሞት እርግጥ ሆነ በዚህም ሁለተኛ ሞት የመጀመርያው ሞት ስራ ሁሉ በእኛ ውስጥ ከመሰረቱ ፈንቅሎ እንዲያበቃ አደረገው። ጳውሎስ የዚህ እውነት ፍንጣቂ ጨብጦ እንዲህ አለ።
‘የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ ምክንያቱም አንዱ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ እርግጠኞች ሆነናል፣ ከዚህም የተነሣ ሁሉ ሞተዋል። በሕይወት ያሉትም ለሞተላቸውና ከሙታን ለተነሣላቸው እንጂ ከእንግዲህ ለራሳቸው እንዳይኖሩ እርሱ ስለ ሁሉ ሞተ። ‘2 ቆሮንቶስ 5:14-15
ጎልጎታ ሁሉ ሰው ለራሱ ወይም ለእኔነት እንደሚሞት አረጋግጠዋል። የክርስቶስ ህይወት በነፃ የተሰጠን ነው ።ጳውሎስ እለት እለት ለስጋዊው ሰው አእምሮና ግዛቱ የሞመቱ ለክርስቶስ አእምሮ ህያው ለህይወት ግዛት ህያው የመሆን ሚስጥር ያ ነው። በእ/ር መንፈሳዊ ግዛት ንቃተ ህሊናችን ለእ/ር ህያው እንድንሆን የተሰጠን ህይወት እንድንኖር ነው። “በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ” አሁን የሆነውን መቁጠር የቻለ ተጠቀመ። ወደ ሮሜ ሰዎች 6/11 እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ። ቁጠሩ ቁጠሩ! ሞቱንም ወደ ህይወት መነሳቱንም ልንለማመደው የግድ ነው። በመጀመርያው አዳም ዘንድ የተለማመድነው ሞት የተባለው የራስ ህይወት፡ የሚያበቃው በሁለተኛው አዳማ ለራስ ህይወት ማለትም ለሞት ለስጋዊው አእምሮ በመሞት ነው። ይህ የሚያበቃው ለህይወት ህያው በመሆን ነው። ለተትረፈረፈ ህይወትም ህያው በመሆን ነው።
‘ሰው አንድ ጊዜ ሊሞት ከዚያም በኋላ በፍርድ ፊት ሊቆም ተወስኖበታል። ‘ዕብራውያን 9:27 ይሄ ማለት በፊት እንደምንረዳው በአካል መሞት አለብን ማለት አይደለም። ጳውሎስ ሲነግረን ‘እነሆ፤ አንድ ምስጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም[አካላዊ ሞት]፤ ነገር ግን ሁላችንም እንለወጣለን፤ ‘1 ቆሮንቶስ 15:51 ሰው ሁሉ ወደ ሞት ግዛት ሲወለዱ ሞትን ቀምሰዋል ሁሉ በአዳም ሞቱ እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ መጣ። በክርስቶስ ህያው ካልሆነ በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁንም ተፈርዶበታል በኩነኔ እየኖረ ነው። ‘ እውነት ክርስቶስ ነው ለምን እውነት እላችኋለሁ፤ ብሎ በራሱ ማለ? “እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤ አሁንም መጥቶአል፤” አሁንም መጥቶአል? ከሞት ግዛት ወደ ሕይወት ግዛት ተሻገረዋል?
“እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም[aionios የዘመኑ(የዘልአለም ህይወት የተወጋው በጊዜ ውስጥ ስለሆነ የዘመኑ የእ/ር ህይወት ተባለ)] ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤ አሁንም መጥቶአል፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ። ‘
ጌታ እንዲህም አለን የዮሐንስ ወንጌል 8/51 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም[ይህን ቃል የአማርኛ ተርጋሚዎች ከኪሳቸው የጨመሩት ነው] ሞትን አያይም።[መሆን የነበረበት፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ሞትን አያይም።]
John 8:51 Verily, verily, I say unto you, If a man keep my saying, he shall never see death.
ዮሐንስ 5:24-25እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።25 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8/6 ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
Rom 8/6 For to be carnally minded is death; but to be spiritually minded is life and peace.
በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።
በክፍል ሁለት እንደ ሐፍ ቅዱስ ቃል የሁለተኛው ሞትና የእሳት ባህር ፍቺ ላይ እንዳሳየነው
“የሁለተኛው ሞት ፍቺ፤ በዚህ ቦታ ላይ ሁለተኛው ሞት ማለት የመጀመርያው ሞት እና ሲኦል በእሳት ባህር ውስጥ ሲደመሰሱ ማለት ነው። “በራእይ 20/4 ሞትና ሲኦልም የእሳት ባህር ውስጥ ተጣሉ። ይህም “የእሳት ባህር” [ይህ ሃሳብ ሲተረጎም ለሁለተኛ ጊዜ የተጨመረ ነው።] ሁለተኛው ሞት ነው።” “death and hell were cast into the lake of fire. THIS IS THE SCOND DATH.”k.j.v. ትክክለኛው ትርጉም ለአንባቢያን እንዲገባ መሆን የነበረበት “ሞትና ሲኦልም በእሳት ባህር ውስጥ ተጣሉ። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።” እንደ ምናስተውለው ሞትና ሲኦል ወደ እሳት ባህር ሲጣሉ ሁለተኛው ሞት ይባላል። ይሄ መንፈስ ቅዱስ እራሱ ሲያጽፈው ሁለተኛው ሞት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሰጠው ፍቺ ነው።
አስተውሉ ሁለተኛው ሞት ማለት ሰዎች በማይጠፋው እሳት ለዘልአለም ሲቀቀሉና ሲሰቃዩ ማለት አይደለም። አሊያም እንደ ሚባለው ክርስቶስን ያልተቀበሉ ከሞት ቡሃላ የሚጠብቃቸው ኑሮ አፈ ታሪኩ የዘልአለም ሞትና ስቃይ አይደለም። አሁን አይናችን ተከፍቶ ማየት ችለናል ሁለተኛው ሞት ማለት የአንደኛው ሞትና የሲኦል የሞት ግዛት ሁሉ በእሳት ባህር ውስጥ ተጥለው ሲደመሰሱና ሲጠፉ ማለት ነው ። በህይወት መጽሐፍ ያልተገኘ ሁሉ የመተላለፍና የሃጥያትና የሲኦል ተፈጥሮ ማንነቱ የተናወጣቸው አመል ሁሉ የአመፃ ሚስጥር ሁሉ ወደ የመለኮት የማጣርያ የእሳት ባህር ይጣላሉ።
“እ/ር መንፈስ ነው። ዮሃ 4/24” መንፈሳዊው ነገር ለቁሳዊው አለም ለማስረዳት በአካላዊ ቋንቋ መስሎ ያስረዳናል። የብዙ አማኞች ችግር ይሄ ነው። ለዚህም ነው በመንፈስ መገለጥ እንድንረዳቸው በተምሳሌነት የተጠቀመባቸው ምልክቶች፣ SYMBOLS ቀጥታ ከመተርጎም የመጡ ብዙ ችግሮች የተከሰቱት። መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ መጽሐፍ ነው። አስተውሉት እስቲ “የእሳት ባህር” የሚለውን ቃል እንየው “ባህር ምንድነው?” ስፋትና ጥልቀት ያለው በውሃ የተሞላ ቦታ ነው። ይሄኛው ልዩነቱ በእሳት መሞላቱ ነው። በምልክት ወይም በገላጭ ቋንቋ ጌታ ተጥቅሞ ተናገረው። እስራኤል ቀይ ባህር በጌታ ለሁለት ተከፍሎ መንገድ አድርጎላቸው በውስጡ ባለፉ ግዜ ሐዋርያው በጥምቀት አልመሰለውምን ? 1ኛ ቆሮ 10/2 እነዚህም በመለኮታዊ ማጣርያ በእሳት ባህር የሚያልፉትም እንደዚሁ ነው። ለእ/ር እንዲ ሰለጥኑለት በልምድ ውስጥ ያሳልፋቸዋል።
የእ/ር በእሳት የመቀመሙና የመፈተኑ ባህርዩንና አላማውን ስናይ “ወደ እሳት አመጣለሁ እንደ ብርም አነጥራቸዋለሁ። እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ። እነሱም ይጣራሉ እኔም እመልሳላቸዋለሁ፤ እኔም “ህዝቤ ናቸው” እላለሁ። እነሱም “እ/ር አምላካችን ነው” ይላሉ። ዘካ13/9 እንደ ምናስተውለው እንደ ወርቅ በእሳት ከተፈተኑና ከነጠሩ ቡሃላ በጨረሻ እ/ር “ህዝቤ ናቸው” ለማለት አላፈረባቸውም እነሱም በመንፃታቸው “እ/ር አምላካችን ነው” ሲያስብላቸው ይታያል እንጂ እሳቱ ሲያጠፋቸው አይታይም። በአንጥረኛ ወርቁ ወደ እሳቱ የመግባቱ አላማ ወርቁ ወደ ተፈለገበት አላማ ከፍ ወዳለ ውበት ቅርጽ ለማድረስ እንጂ ወርቁን ለማጥፋት አይደለም።
መቼም እ/ር ሰውን በእሳት ባህር እንደ ማያጠፋው የታወቀ ነው። በየትም ቦታ የእ/ር ቃል እንደዛ አይልም። ያ የእውነት ተፃራሪ ነው። “ቃልህ እውነት ነው በእውነትህ ቀድሳቸው።” የባቢሎንን ማስፈራርያ ወጥመድ ስብከትን ነው። አስቡት እስቲ ሰውን ማምለጫ በሌለው የዘልአለም ሞትና እሳት ውስጥ ፈጥረህ ና ከተህ የመጨረሻውን ጠላት ሞትን እንዴት ትደመስሳለህ?የእ/ር መለኮታዊ እሳት ሰዎች ሁሉ ይፀዱበታል፤ ይነጥሩበታል፤ ጽድቅን፤ ይማሩበታል እንጂ አይጠፉበትም። ጌታ ዋጋ የከፈለውና የመጣው የሰውን ሕይወት ለማዳን ነው እንጂ ለማጥፋት አይደለምና “ኢየሱስ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና እናንተ ከምን ዐይነት መንፈስ እንደሆናችሁ አታውቁም፤ የሰው ልጅ የመጣው የሰውን ሕይወት ለማዳን ነው እንጂ ለማጥፋት አይደለምና” አላቸው፤ ‘ሉቃስ 9:55” ሰው ጌታ የመጣው የሰውን ሕይወት ለማዳን ሳይሆን ለማጥፋት ነው የሚል ከሆነ ከምን ዐይነት መንፈስ እደሆነ አነጋጋሪ ነው አያውቅምም።”በአጠቃላይ የእሳት ባህር ፍቺ “የመሎከት የማጣርያ ብህር፣ a lake of divine purifcation” ነው። ፍርድ የሚለው ሃሳብ መከልከል የለበትም።“
ስለዚህ ሃሳብ በብዙ ሰዎች ብዙ ተጽፎ አንብቢያለሁ ሚዛን የሚደፋና፡ብሎም የማይደፋም ቀልሎ የተገኘም አጋጥሞኛል። በእ/ር ቃል ሲመዘን ማለቴ ነው። በዚህ ሃሳብ ላይ በብዙ ሰዎች ዘንድ ሰፊ የሆነ ግራ የተጋባ አመለካከት እንዳለ ግልጽ ነው። ለብዙ ወገኖች ይጠቅማል በማለት ይህን የመረዳት ብርሃን አብረን እንድናየው እወዳለሁ መልካም ነገር አለውና። ከቀድሞው አባቶች ሲኦል ዘልአለማዊ ነውን? (is hell eternal or will GOD’S plan fail?) በRev-Charles pridgeon ከነቮበር ወ 1920 እትም መጽሐፋቸው። የእሳት ባህርን በተመለከተ ከገለጡት እጅግ ከሚያስደንቀው የመረዳት ብርሃን የተሞላበት የሊቅ ወይም
የእስኮላር ስራቸው ለተሻለ ግንዛቤ ለብዙ አስተዋዮች እንደ ታገዙበት ሁሉ እኔም ከታገዝኩበትና ከተረዳሁበት መካከል ለወገኖች ጥቅም ልጠቅስ እወዳለሁ። “የእሳት ባህርና ዲኑ (BRIMSTONE) የሚያመለክቱት እሳቱ ከዲኑ ጋር ሲነድ ነው። ዲን፡brimstone ወይም ድኝ፡ sulphur የሚለው የእሳቱ ባህርይ ነው።
የግሪኩ ቃል THEION ሲተረጎም ዲን፡brimstone ተብሎ የተተረጎመ ሲሆን ያው የግሪኩ ቃል እራሱ THEION መለኮት ማለት ነው። በጥንታውያን ግሪኮች መካከል ድኝ ፡sulphur የተቀደሰ ነበረ። እናም ለማጠን፤ ለማንፃት፤ ለማጥራት ለአምላካቸው ያውሉት ነበር። ለዚህም አላማ ያጥኑ ነበር። homer’s lliad[16:228] አንድ ሰው በእሳትና በዲን ዋንጫውን እያፀዳ እንደሆነ ሊናገር ይችላል። THEION ከሚለው ቃል የተሳበው ግስ {ግስ፡ ማለት የቌንቋ አረባብ የዘርና ነባር መሰረት ቃል ነው። } THEIOO ሲሆን ማለትም ማወደስ፤ መለኮትን መስራት፤ ለአምላክነት መለየት ማለት ነው። [liddel and scott Greek English Lexicon, 1897 Edition] ተመልከት/ቺ።
ለማንኛውም ግሪካዊ ወይም በግሪክ ቋንቋ ለሰለጠነ ሰው “የእሳት ባህርና ዲን” ሆኖ መረዳት የነበረበት “የመሎከት የማጣርያ ብህር፣
a lake of divine purifcation” ነበር። ፍርድ የሚለው ሃሳብ መከልከል የለበትም። እ/ር መንገዱ ሁሉ እውነትና ፍርድ ነውና። በጥንታዊ ግሪክ ቋንቋ መለኮታዊ ማጣርያና ለመለኮት ማዋል የሚል ነው ፍቺው። በተራው አገላለጽ ይህ የቃሉ ትርጉም ገንጥለው አውጥተውታል። አመፀኛ ሃፍረት የለውም ተብሎ እንደ ተፃፈ ምንም ነገር ሳያስቀሩ ግን የዘልአለም ስቃይ ጋር አዛምደውታል።” የተጠቀሰው ተፈፀመ። by Brother Binyam T. Alemayehu 04/05/2018