የሁለተኛው ሞት ፍቺ / መለኮታዊ ሹኩሹኩታ ክፍል 4


መለኮታዊ ሹኩሹኩታ ክፍል 4
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሁለተኛው ሞትና የእሳት ባህር ፍቺ

2, የሁለተኛው ሞት ፍቺ

by Brother Binyam T. Alemayehu 1/13/2018

በዚህ ቦታ ላይ ሁለተኛው ሞት ማለት የመጀመርያው ሞት እና ሲኦል በእሳት ባህር ውስጥ ሲደመሰሱ ማለት ነው። “በራእይ 20/4 ሞትና ሲኦልም የእሳት ባህር ውስጥ ተጣሉ። ይህም “የእሳት ባህር” [ይህ ሃሳብ ሲተረጎም ለሁለተኛ ጊዜ የተጨመረ ነው።] ሁለተኛው ሞት ነው።”  “death and hell were cast into the lake of fire. THIS IS THE SCOND DATH.”k.j.v. ትክክለኛው ትርጉም ለአንባቢያን እንዲገባ መሆን የነበረበት “ሞትና ሲኦልም በእሳት ባህር ውስጥ ተጣሉ። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።” እንደ ምናስተውለው ሞትና ሲኦል ወደ እሳት ባህር ሲጣሉ ሁለተኛው ሞት ይባላል። ይሄ መንፈስ ቅዱስ እራሱ ሲያጽፈው ሁለተኛው ሞት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሰጠው ፍቺ ነው።

አስተውሉ ሁለተኛው ሞት ማለት ሰዎች በማይጠፋው እሳት ለዘልአለም ሲቀቀሉና ሲሰቃዩ ማለት አይደለም። አሊያም እንደ ሚባለው ክርስቶስን ያልተቀበሉ ከሞት ቡሃላ የሚጠብቃቸው ኑሮ አፈ ታሪኩ የዘልአለም ሞትና ስቃይ አይደለም።  አሁን አይናችን ተከፍቶ ማየት ችለናል ሁለተኛው ሞት ማለት የአንደኛው ሞትና የሲኦል የሞት ግዛት ሁሉ በእሳት ባህር ውስጥ ተጥለው ሲደመሰሱና ሲጠፉ ማለት ነው ። በህይወት መጽሐፍ ያልተገኘ ሁሉ የመተላለፍና የሃጥያትና የሲኦል ተፈጥሮ ማንነቱ የተናወጣቸው አመል ሁሉ የአመፃ ሚስጥር ሁሉ ወደ የመለኮት የማጣርያ የእሳት ባህር ይጣላሉ።

“እ/ር መንፈስ ነው። ዮሃ 4/24” መንፈሳዊው ነገር ለቁሳዊው አለም ለማስረዳት በአካላዊ ቋንቋ መስሎ ያስረዳናል። የብዙ አማኞች ችግር ይሄ ነው። ለዚህም ነው በመንፈስ መገለጥ እንድንረዳቸው በተምሳሌነት የተጠቀመባቸው ምልክቶች፣ SYMBOLS ቀጥታ ከመተርጎም የመጡ ብዙ ችግሮች የተከሰቱት። መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ መጽሐፍ ነው። አስተውሉት እስቲ “የእሳት ባህር” የሚለውን ቃል እንየው “ባህር ምንድነው?” ስፋትና ጥልቀት ያለው በውሃ የተሞላ ቦታ ነው። ይሄኛው ልዩነቱ በእሳት መሞላቱ ነው። በምልክት ወይም በገላጭ ቋንቋ ጌታ ተጥቅሞ ተናገረው። እስራኤል ቀይ ባህር በጌታ ለሁለት ተከፍሎ መንገድ አድርጎላቸው በውስጡ ባለፉ ግዜ  ሐዋርያው በጥምቀት አልመሰለውምን ? 1ኛ ቆሮ 10/2 እነዚህም በመለኮታዊ ማጣርያ በእሳት ባህር የሚያልፉትም እንደዚሁ ነው። ለእ/ር እንዲ ሰለጥኑለት በልምድ ውስጥ ያሳልፋቸዋል።

የእ/ር በእሳት የመቀመሙና የመፈተኑ ባህርዩንና አላማውን ስናይ “ወደ እሳት አመጣለሁ እንደ ብርም አነጥራቸዋለሁ። እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ። እነሱም ይጣራሉ እኔም እመልሳላቸዋለሁ፤ እኔም “ህዝቤ ናቸው” እላለሁ። እነሱም “እ/ር አምላካችን ነው” ይላሉ። ዘካ13/9 እንደ ምናስተውለው እንደ ወርቅ በእሳት ከተፈተኑና ከነጠሩ ቡሃላ በጨረሻ እ/ር “ህዝቤ ናቸው” ለማለት አላፈረባቸውም እነሱም በመንፃታቸው “እ/ር አምላካችን ነው” ሲያስብላቸው ይታያል እንጂ እሳቱ ሲያጠፋቸው አይታይም። በአንጥረኛ ወርቁ ወደ እሳቱ የመግባቱ አላማ ወርቁ ወደ ተፈለገበት አላማ ከፍ ወዳለ ውበት ቅርጽ ለማድረስ እንጂ  ወርቁን ለማጥፋት አይደለም።

http://wongelradio.org/

ደግሞም ማንኛውም ተምሳሌት ሲነገር የሚወክለውን ገፀ ባህሪን ያመለክታል እንጂ ቀጥታ የተመሰለበትን አያመለክትም።

በምድራዊ ቌንቋ ለምሳሌ አንበሳ ነው! ሲባል አንበሳ የደፋርና የብርቱ ምሳሌ ነው። እርሱ በግ ነው ሲባል የዋህ ቅን ሰው ነው ለማለት ነው ወይም ለምሳሌ ማቴ 23/15 ከእናተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የገሃነም ልጆች ስለምታደርጉ … በዚህ ተምሳሌት ጌታ የሚናገረው ስለከፋ ማንነት ወይም ስለክፉው ባህሪና ተፈጥሮ መሆኑ ግልጽ ነው።

በመንፈሳዊ ቋንቋ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ አንበሳውም በጉም እሱ ነው። አንበሳነቱ በሃይል በችሎታ የተሞላ፡ አለምንና ሁሉን ያሸነፈ፡ እንደ በግነቱ በልቡ የዋህና ትሁት መሆኑና ሰላም ወዳድነቱና የሰላም አለቃ መሆኑ የሚወደውን ፍጡራኑን ሁሉ በልባቸው ዙፋን ላይ በፍቅር መግዛቱ ደግሞም ከሁሉ በላይ ለአባቱ ፈቃድ ብቻ ያደረ መሆኑ ከዚያም ባሻገር ወዘተ…

ሌላ ምሳሌ ብናይ ስንዴውን[መልካሙን ዘር] በጎተራ ይከተዋልና ገለባውን [የአመፃ ሚስጥሩን] ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል። ያም የሞት የሲኦል የሃጥያት መጨረሻቸው የሚያሳይ ነው።

እ/ር እሳት ነው። የመጨረሻውን ጠላት ሞትን በእሳት ባህር ይደመስሰዋልና፡ ሞት ፈጽም ካልተደመሰሰ ህይወት ማለትም እ/ር እንዴት ሁሉን በሁሉ ይሆናል?እውነቱ ግን  የግዴታ ሞት ሁሉ በህይወት ይበላል ይዋጣል። ‘አምላካችን የሚያጠፋ[የሚባላ consuming] እሳት ነውና።’ ዕብራውያን 12:29 Heb 12/29 For our God is a consuming fire.

see GREEK 2654 katanalisko kat-an-al-is’-ko from 2596 and 355; to consume utterly:–consume.

ብርሃን ለጨለማ የበላይ ነው፡ እሳቱም ነው ይበላዋልም ህይወትም እንዲሁ ለሞት የበላይ ነውና።

እ/ር እርሱ ሁሉን በሁሉ ሲሆን ሃጥያት የለም ሃጥያተኛም የለም፡ የሃጥያት ሃይል ሞት የለም ሲኦልም የለም። ሁሉ በእ/ር ይዋጣል።

የዮሐንስ ራእይ 21/3 ታላቅም ድምፅ ከሰማይ፦ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤

4 እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።

5 በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ። ለእኔም፦ እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ።

መቼም እ/ር ሰውን በእሳት ባህር እንደ ማያጠፋው የታወቀ ነው። በየትም ቦታ የእ/ር ቃል እንደዛ አይልም። ያ የእውነት ተፃራሪ ነው። “ቃልህ እውነት ነው በእውነትህ ቀድሳቸው።” የባቢሎንን ማስፈራርያ ወጥመድ ስብከትን ነው። አስቡት እስቲ ሰውን ማምለጫ በሌለው የዘልአለም ሞትና እሳት ውስጥ ፈጥረህ ና ከተህ  የመጨረሻውን ጠላት ሞትን እንዴት ትደመስሳለህ?የእ/ር መለኮታዊ እሳት ሰዎች ሁሉ ይፀዱበታል፤ ይነጥሩበታል፤ ጽድቅን፤ ይማሩበታል እንጂ አይጠፉበትም። ጌታ ዋጋ የከፈለውና የመጣው የሰውን ሕይወት ለማዳን ነው እንጂ ለማጥፋት አይደለምና “ኢየሱስ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና እናንተ ከምን ዐይነት መንፈስ እንደሆናችሁ አታውቁም፤ የሰው ልጅ የመጣው የሰውን ሕይወት ለማዳን ነው እንጂ ለማጥፋት አይደለምና” አላቸው፤ ‘ሉቃስ 9:55” ሰው ጌታ የመጣው የሰውን ሕይወት ለማዳን ሳይሆን ለማጥፋት ነው የሚል ከሆነ ከምን ዐይነት መንፈስ እደሆነ አነጋጋሪ ነው አያውቅምም።

እ/ር ሁሉን ነገር የሚያድስበት ዘመን እንዳለ ጌታ እንድናስተውል ይወዳል ፈቃዱን ከጥንት አሳውቆናልና። ማስተዋል የፃድቅ እድል ፈንታው ነውና።  “ፃድቃን ሁሉን ያስተውላሉ ሐጥአን ግን ምንም አያስተውሉም” የእ/ርን መንገድ በእውነትና በፍርድ መሆኑ የማይስት አምላክ መሆኑን የማያስተውል የክፉው ባህሪ ነው [ያ ቢስትሊ ኔቸር፤ አውሪያዊ ተፈጥሮ፤ አዳማዊ ባህሪ ደግሞ ኢነርጃይዝ የሚሆነው በማን እንደሆነ ከቃሉ እናውቀዋለን] እ/ርን የሚሹ ግን በማስተዋላቸው ፈጣኖች ናቸው። መጽሐፈ ምሳሌ 28/5 ክፉዎች ሰዎች ፍርድን አያስተውሉም፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን ሁሉን ያስተውላሉ። ሁሉን ያስተውላሉ።  Prov 28/5 Evil men understand not judgment: but they that seek the Lord understand all things ማወቅ ያለብን የእ/ር ፍርድ ማለት ለዓለም ሕዝቦች ውጤታማና ድንቅ የጽድቅ አስተማሪ ማለት ነው። ‘…. ፍርድህ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ፣ የዓለም ሕዝቦች ጽድቅን ይማራሉ። ‘ ኢሳይያስ 26:9

እ/ር ሁሉን ነገር የሚያድስበት ዘመን አለ ሁሉን ጥቅስ አሁን ለማቅረብ ግን ካለብዙ ትጋት አይሆንም። ከዘፍጥረት ጀምሮ ከነሙሴ፡ በነብያት ሁሉ፡ በአባቶች አስቀድሞ የተናገረው ትንቢት ነው። ሰዎች ለምን፡ በእ/ር ማዳን እንደ ሚቀኑና እንደ ሚደነግጡ ሳስበው ይደንቀኛል።  ለነገሩ የእምነታችን ደራሲ ጌታ የእ/ር መንግስ ከምትመስላቸው መካከል አንዱን እንዲህ፡ ተርኮታል

የማቴዎስ ወንጌል 20

1 መንግሥተ ሰማያት ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤት ሰውን ትመስላለችና።

2 ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው።

3 በሦስት ሰዓትም ወጥቶ ሥራ የፈቱ ሌሎችን በአደባባይ ቆመው አየ፥

4 እነዚያንም፦ እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም እሰጣችኋለሁ አላቸው። እነርሱም ሄዱ።

5 ደግሞም በስድስትና በዘጠኝ ሰዓት ወጥቶ እንዲሁ አደረገ።

6 በአሥራ አንደኛውም ሰዓት ወጥቶ ሌሎችን ቆመው አገኘና፦ ሥራ ፈትታችሁ ቀኑን ሁሉ በዚህ ስለ ምን ትቆማላችሁ? አላቸው።

7 የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው አሉት። እርሱም፦ እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም ትቀበላላችሁ አላቸው።

8 በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ አዛዡን፦ ሠራተኞችን ጥራና ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደመወዝ ስጣቸው አለው።

9 በአሥራ አንደኛው ሰዓትም የገቡ መጥተው እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።

10 ፊተኞችም በመጡ ጊዜ አብዝተው የሚቀበሉ መስሎአቸው ነበር፤ እነርሱም ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።

11-12 ተቀብለውም፦ እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፥ የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው ብለው በባለቤቱ ላይ አንጐራጐሩ።

13 እርሱ ግን መልሶ ከእነርሱ ለአንዱ እንዲህ አለው፦ ወዳጄ ሆይ፥ አልበደልሁህም በአንድ ዲናር አልተስማማኸኝምን?

14 ድርሻህን ውሰድና ሂድ፤ እኔ ለዚህ ለኋለኛው እንደ አንተ ልሰጠው እወዳለሁ፤ በገንዘቤ የወደድሁትን አደርግ ዘንድ መብት የለኝምን?

15 ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዓይንህ ምቀኛ ናትን?

‘እግዚአብሔር አስቀድሞ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረ፣ ሁ-ሉ-ን ነ-ገ-ር እ-ስ-ከ-ሚ-ያ-ድ-ስ-በ-ት ዘ-መ-ን ድ-ረ-ስ እርሱ በሰማይ ይቈይ ዘንድ ይገባል። ‘ ሐዋርያት ሥራ 3:21 Acts 3/21 Whom the heaven must receive until the times of restitution of all things, which God hath spoken by the mouth of all his holy prophets since the world began.

 

ሚልክ 3/2 ነገር ግን እርሱ[እ/ር] እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ[እ/ር] በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው? 3 እርሱም[እ/ርም] ብርን እንደሚያነጥርና እንደ ሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ። በዚህ ተምሳሌታዊ አነጋገር ፈጣሪ እንደ አንጥረኛ ብቻ ሳይሆን የሚመጣው እንደ አንጥረኛ “እሳትም” ሆኖ ነው የሚመጣው። ደግሞም እንደ ልብስ አጣቢ ብቻ ሳይሆን የሚመጣው እንደ አጣቢ ”ሳሙናም“ ነው የሚመጣው። እንደ ባለተክሎ የሚቀመጠው እሱ ነው! እሳቱም እሱ ነው! አጣቢውም እሱ ነው! ሳሙናውም እሱ ነው!

ለመሆኑ በተፈጥራዊው አለም አንጥረኛ ወይም ባለ ተክእሎ ሰው አላማው ምንድ ነው? ብርን በእሳት ሲያነጥረው ብሩን ወይም ወርቁን ድራሹን ለማጥፋት ነውን? አይደለም! ብሩን ለማንጠርና ለሚፈልገው ውበትና ክብር ሊያውለው እንጂ! በቅድሚያ ወርቁን ሊፈትን በእሳት ውስጥ ይከተዋል። ወርቁንም በእሳት ሲፈትን አርቲፊሻል የወርቅ ቅብ ከሆነ  የሸፈነው እየተቀረፈ እየወደቀ የውስጥ ክብሩ እየተብለጨለጨ ቢጫ እየሆነ እየባሰበት እየደመቀ እሳቱ ዉበቱን እየገለጠው ይመጣል ዚንኩ ሁሉ[መራራ ማንነት] ከአፈሩ [ምድራዊ ማንነት ሁሉ] ጋር ተፈልቅቀው ይገነጣጠላሉ። ባለ ተክእለውም ሰው በሂደቱ ጊዜ  ወርቁ እሳት በዝቶበት እንዳ ይበላሽ ፊቱን አስጠግቶ አይኑን ተክሎ ያየዋል ወርቁ የሰውየውን መልክ ካንፀባረቀ ወርቁ ለሚፈልገው ክብር መድረሱን ያውቃል ያን ጊዜ ብቻ ያወጣዋል። እ/ርም የሰውን ዘር በእሳት ባህር ማንጠሩ ላማጥፋት ሳይሆን መልኩና አምሳሉን በሰው ውስጥ ለማየት ነው። መልኩን ካየ ቡሃላ የእሳት ባህሩ ውስጥ ዳግም ለመክተት አያስፈልገውም። እ/ር ይመስገን።

 

የልብስ አጣቢና ተግባሩስ ምንድን ነው? የማርቆስ ወንጌል 9/2 …..ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ልብሱም አንጸባረቀ፤ 3 አጣቢም- በምድር- ላይ – እንደዚያ- ሊያነጣው- እስከ-ማይችል- በጣም- ነጭ -ሆነ። ከዚህ ቃል እንደ ምናስተውለው በምድር ላይ የአጣቢ ተግባሩ ልብሱን ፈጽሞ ማንፃት ነው እንጂ ልብሱን ማጥፋት አይደለም። እ/ር የዘልአለም አላማው ከመጀመርያውም ‘እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ፣ “ሰውን በመልካችን፣ በአምሳላችን እንሥራ፤ በባሕር ዓሦች፣ በሰማይ ወፎች፣ በከብቶች፣ በምድር ሁሉ ላይ፣ እንዲሁም በምድር በሚሳቡ ፍጡራን ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ። ‘ ዘፍጥረት 1:26 መቸም በአባት የነበረው በመልካችን፣ በአምሳላችን የመጀመርያው አዳም እንዳልሆነ ግልጽ ነው እሱ ተሰርቶ ያለቀ የመለኮት ፕሮዳክት አይደለምና በመልካችን፣ በአምሳላችን ማለት ሁለተኛው አዳም ማለትም ክርስቶስ ማለቱ ነው። ክርስቶስ የእግዚአብሔር ፍፁም ገላጭ የመለኮት ክብሩ የነፍሱ ፍጽም ነፀብራቅና መገለጥ ነውና። አሜን።

(Heb 1:3 [Amharic])

እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል …

Heb 1/3. [JMT}

 Who, being a beam (radiance; effulgence; outshining) from the Glory, and an exact impress (as from a stamp or die) of His substructure (the substance standing under as a foundation) and continuously bearing (carrying) the whole (all things; everything; or, as a masc.: all men) by the thing which is spoken belonging to His power (the saying pertaining to His ability; in the spoken word of His power), making a cleansing (purification) of failures (of the misses of the target; pertaining to the sins), seated Himself within the right part of greatness resident within high places.

(Heb 1:3 [NET])

The Son is the radiance of his glory and the representation of his essence, and he sustains all things by his powerful word, and so when he had accomplished cleansing for sins, he sat down at the right hand of the Majesty on high.

(Heb 1:3 [HCSB])

The Son is the radiance of God’s glory and the exact expression of His nature, sustaining all things by His powerful word. After making purification for sins, He sat down at the right hand of the Majesty on high.

(Heb 1:3 [NET])

The Son is the radiance of his glory and the representation of his essence, and he sustains all things by his powerful word, and so when he had accomplished cleansing for sins, he sat down at the right hand of the Majesty on high.

(Heb 1:3 [ESV2011])

He is the radiance of the glory of God and the exact imprint of his nature, and he upholds the universe by the word of his power. After making purification for sins, he sat down at the right hand of the Majesty on high,

 (Heb 1:3 [Webster])

Who being the brightness of his glory, and the express image of his person, and upholding all things by the word of his power, when he had by himself made purification of our sins, sat down on the right hand of the Majesty on high;

(Heb 1:3 [Weymouth])

He brightly reflects God’s glory and is the exact representation of His being, and upholds the universe by His all-powerful word. After securing man’s purification from sin He took His seat at the right hand of the Majesty on high,

(Heb 1:3 [YLT])

who being the brightness of the glory, and the impress of His subsistence, bearing up also the all things by the saying of his might–through himself having made a cleansing of our sins, sat down at the right hand of the greatness in the highest,

 እንግዲያው አላማው አንድም ሰው ሳይቀር ወደ መልኩና አምሳሉ ማምጣት እስከ ሆነ ድረስ፡ እያንዳንዱን ሰው በእሳቱ ማሳለፉ አይቀርም። በእሳቱ ማጥመቁም አይቀርም ልዩ ነቱ ፃድቁ እሳቱ ሰባት እጥፍ ቢነድም ያለ ትግል ይገባበታል ድል የነሣውም በሁለተኛው ሞት አይጐዳምና። ሃጥኡ ግን ቢፈቅድም ባይፈቅድም መልአክቶቹ እጅና እግሩን ይዘው ሻሞ ሆ ብለው ወደ እሳቱ ይወረውሩታል።[አገላለጽ ነው] ‘ ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና። መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል።’ ማርቆስ 9:49

መደምደሚያ

በአጠቃላይ የእሳት ባህር ፍቺ “የመሎከት የማጣርያ ብህር፣ a lake of divine purifcation” ነበር። ፍርድ የሚለው ሃሳብ መከልከል የለበትም። የሚለውን በክፍል 3 እንዳየነው ነው

በክፍል 4 ሁለተኛው ሞት ማለት የመጀመርያው ሞት እና ሲኦል በእሳት ባህር ውስጥ ሲደመሰሱ ማለት ነው።

የጌታ ፀጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን። አሜን!

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal