
መለኮታዊ ሹኩሹኩታ ክፍል 3
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሁለተኛው ሞትና የእሳት ባህር ፍቺ
by Brother Binyam T. Alemayehu
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሁለተኛው ሞትና የእሳት ባህር ፍቺ
ስለዚህ ሃሳብ በብዙ ሰዎች ብዙ ተጽፎ አንብቢያለሁ ሚዛን የሚደፋና፡ብሎም የማይደፋም ቀልሎ የተገኘም አጋጥሞኛል። በእ/ር ቃል ሲመዘን ማለቴ ነው። በዚህ ሃሳብ ላይ በብዙ ሰዎች ዘንድ ሰፊ የሆነ ግራ የተጋባ አመለካከት እንዳለ ግልጽ ነው። ለብዙወገኖች ይጠቅማል በማለት ይህን የመረዳት ብርሃን አብረን እንድናየው እወዳለሁ መልካም ነገር አለውና። ከቀድሞው አባቶች ሲኦል ዘልአለማዊ ነውን? (is hell eternal or will GOD’S plan fail?) በRev-Charles pridgeon ከነቮበር ወ 1920 እትም መጽሐፋቸው። የእሳት ባህርን በተመለከተ ከገለጡት እጅግ ከሚያስደንቀው የመረዳት ብርሃን የተሞላበት የሊቅ ወይም
የእስኮላር ስራቸው ለተሻለ ግንዛቤ ለብዙ አስተዋዮች እንደ ታገዙበት ሁሉ እኔም ከታገዝኩበትና ከተረዳሁበት መካከል ለወገኖች ጥቅም ልጠቅስ እወዳለሁ። “የእሳት ባህርና ዲኑ (BRIMSTONE) የሚያመለክቱት እሳቱ ከዲኑ ጋር ሲነድ ነው። ዲን፡brimstone ወይም ድኝ፡ sulphur የሚለው የእሳቱ ባህርይ ነው።
የግሪኩ ቃል THEION ሲተረጎም ዲን፡brimstone ተብሎ የተተረጎመ ሲሆን ያው የግሪኩ ቃል እራሱ THEION መለኮት ማለት ነው። በጥንታውያን ግሪኮች መካከል ድኝ ፡sulphur የተቀደሰ ነበረ። እናም ለማጠን፤ ለማንፃት፤ ለማጥራት ለአምላካቸው ያውሉት ነበር። ለዚህም አላማ ያጥኑ ነበር። homer’s lliad[16:228] አንድ ሰው በእሳትና በዲን ዋንጫውን እያፀዳ እንደሆነ ሊናገር ይችላል። THEION ከሚለው ቃል የተሳበው ግስ {ግስ፡ ማለት የቌንቋ አረባብ የዘርና ነባር መሰረት ቃል ነው። } THEIOO ሲሆን ማለትም ማወደስ፤ መለኮትን መስራት፤ ለአምላክነት መለየት ማለት ነው። [liddel and scott Greek English Lexicon, 1897 Edition] ተመልከት/ቺ።
ለማንኛውም ግሪካዊ ወይም በግሪክ ቋንቋ ለሰለጠነ ሰው “የእሳት ባህርና ዲን” ሆኖ መረዳት የነበረበት “የመሎከት የማጣርያ ብህር፣
a lake of divine purifcation” ነበር። ፍርድ የሚለው ሃሳብ መከልከል የለበትም። እ/ር መንገዱ ሁሉ እውነትና ፍርድ ነውና። በጥንታዊ ግሪክ ቋንቋ መለኮታዊ ማጣርያና ለመለኮት ማዋል የሚል ነው ፍቺው። በተራው አገላለጽ ይህ የቃሉ ትርጉም ገንጥለው አውጥተውታል። አመፀኛ ሃፍረት የለውም ተብሎ እንደ ተፃፈ ምንም ነገር ሳያስቀሩ ግን የዘልአለም ስቃይ ጋር አዛምደውታል።” የተጠቀሰው ተፈፀመ።
በነገራችን ላይ THEION የሚለው ቃል የተሳበው theo ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን እግዚአብሔር (መለኮት) GOD እየተባለ በአብዛኛው የተተረጎመው ቃል ነው። ቲዮሎጂ {Theologi or Theology is the study of GOD} የስነ መለኮት ጥናት ወይም ስለ ስነ መለኮት ማጥናት ከዚህ ሃሳብ የተገኘ ነው።
የእ/ርን አሰራርና አደራረጉን ለማወቅ አንድ ሰው ቃሉን እያጠና መንፈስም መረዳትን እያበዛለት ሲመጣ የቃሉን መንፈሳዊ አመልካች በትክክል ማስተዋል ሲጀምር በመጽሐፉ ፀሐፊ በእ/ር የዘልአለም አጀንዳ በቅዱሱ ልእለ ተፈጥሮ ውበትና እንዲሁም በታላቅ ጥበቡ፤ በፍቅሩ ብልጽግና ይነደፋሉ። እ/ርንም ውድድድ ያደርገዋል። በእ/ር ዘንድ ያለው ፍርድ ለማቅናት እንደሆነ ማስተዋል ይጀምራልና።
ሰዎች ለመከራ ይቀጣሉ። እ/ር ግን በፍርዱ ያቀናል ያፀዳል።በግሪኩ ቃል የጠራ ወይም የነፃ pur በዚህ ዘመን እንግሊዝኛ ማጽዳት ወይም ማጥራት ፡ ንፁህ ማድረግ PURGE and PURIFY ለሚሉት ቃላት ስር ወይም ምንጭ ነው። የእ/ር እሳትም የሚያደርገው ይህንኑ ነው። የእ/ር ባህርይና ተፈጥሮ ያሳያል። በዛሬው ጥናታችን በጥቂቱ የእሳቱን ባህሪ በመፅሐፍ ቅዱስ የእውነት ቃል እናጠናለን። ይህን እሳት እየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ለኩሶታል። በእሳት የሚያጠምቅ ሆኖም መጥተዋል። ለሚከተሉት ሁሉ እንደ እሳት መምጣቱን ቀጥለዋል። ገናም ለፉጡራኑ ሁሉ ይመጣል። አሜን ጌታ ሆይ ማራናታ አብዝተህ ቶሎ ቶሎ ምጣ።
ማወቅ ያለብን እ/ር የሰው ልጆችን ማዳን ወይም መዋጀት ያስፈለገው ከሲኦል አድኖ ወደ መንግስተ ሰማያት ለማሻገር አይደለም። በልምድ የሚነገር ካልሆነ በስተቀር የእ/ር ቃል በቀጥታ እደዛ የሚል በተወዳጁ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።እሳቱ ከራሳቸው ሃጢያትና በውስጣቸው ከሚሰራው የአመጻ ሚስጥር በማንጻት አላቆ ወደ እ/ር መለኮታዊ ተፈጥሮና ባህሪ ለማምጣት ነው እንጂ። “የማቴዎስ ወንጌል 1፡21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” አስተዋላችሁ ህዝቡ መዳን ያስፈለጋቸው ከገዛ ሃጢያታቸው እንጂ ከሲኦል አይደለም።
“የሐዋርያት ሥራ 3፡26 ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።” Acts 3፡26 Unto you first God, having raised up his Son Jesus, sent him to bless you, in turning away every one of you from
his iniquities. ደግሞም ወደ ቲቶ 2፡14 መድኃኒታችንም ከዓመፅ
ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
“ የእንግሊዝኛው ግልጽ መልእክቱን ስለሚያሳይ እንመልከተው “that he might redeem us from all iniquity,
and purify unto himself” ከቃሉ እንደምናስተውለው የተዋጀነው ከአንድ ማንነት ወደ ሌላ ማንነት ነው። ይህም
ከአመጻ ሁሉ from all iniquity, አጥርቶ ወይምአንጽቶ ወደ ራሱ purify unto
himself ነው እንጂ። የተዋጀነው ከቦታ ወደ ቦታ የጂኦግራፊ ወይም የካርታ ለውጥ ከሲኦል ወደሆነ ሩቅ ጠፈር ላይ የሚገኝ
ገነት የተባለ ቦታ ወይም ፕላኔት ሰፈር ለመቀየር አይደለም። የተዋጀነው አመጻ ከተሞላ ማንነት ወደ ራሱ መልክና አምሳል ለማምጣት
ነው። የመንጻሩም ሂደት በእሳቱ በማሳለፍ አመጻውን ሁሉ በመብላት ወደ መልኩ ማምጣት ነው።
Mal 3፡2 But who may abide the day of
his coming? and who shall stand when he appeareth? for he is like a refiner’s
fire, and like fullers’ soap: 3 And he shall sit as a refiner
and purifier of silver: and he shall purify the sons of Levi, and purge them as
gold and silver, that they may offer unto the Lord an offering in
righteousness.
ትንቢተ ሚልክያስ 3፡2 ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን
ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው? 3 እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥
የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።
የእሳቱአላማ ማንጠር ነው። አሜን!
አሁን ደግሞ በኖህ ዘመን የነበሩት የማይታዘዙት እ/ር 120 አመት የታገሳቸው እና
የፈረደባቸው ፍጻሚያቸውን በቃሉ አይተን እንለፍ ። ጌታ እየሱስ ከሞቱና ከትንሳኤው ቡሃላ በኖህ ዘመን አልታዘዝ ያሉት አመጸኞች
በእስራት ለነበሩትን ነፍሳትን (spirits መናፍስትን) ሰበከላቸው። ለነሱም የማስታረቁን ቃል ይዞላቸው ወረደ። የሚያሳየንም ክርስቶስ
ለሃጢያታቸው መሞቱን ብቻ ሳይሆን መነሳቱም ለመጽደቃቸው መሆኑን ነው።
ይህንን ቃል Weymouth’s translation. ከተባለውን ትርጉም እናስተውል 1Pe
3:18 Christ also once for all died for sins, the
innocent One for the guilty many, in order to bring us to God. He was put to
death in the flesh, but made alive in the spirit, in which He also went and proclaimed His Message to
the spirits that were in prison, 1Pe 3:20 who in ancient times had been disobedient, while God’s longsuffering
was patiently waiting in the days of Noah during the building of the Ark, in
which a few persons–eight in number–were brought safely through the water.”
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3 ፡18 ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን
እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥ 19 በእርሱም ደግሞ
ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤ 20 ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት
በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።
አንድአንዶች ይህንን ቃል ጠምዝዘው ሄዶ የሰበከው ከሱበፊት ለሞቱ ጻድቃን ሰዎች ለማውጣት
ነው ይላሉ። ከቃሉ እዳየነው ግን የሰበከው በእስራት የነበሩትን መናፍስት ነው:: ለሴም ፤ለሄኖክ፤ ለኖህ፤ ለአብርሃም፤ ለያቆብ
፤ለኢሳቅ ወይም ለሙሴ፤ ለእያሱ ወይ ለኤልያስ ወይም ለየትኛውም በቀድሞ ኪዳን አካየዳቸውን ከእ/ር ጋር ያደረጉ ጻድቃን ለማናቸውም አይመለከትም::
እነዚህ ሁሉ ለእ/ር ህያዋን ናቸውና በመንፈሳዊው አለም አለም ሳይፈጠር በፊት የታረደው በግ ታርዶላቸዋልና ከአፈር የተሰራው
ስጋቸው ወደ እፈር ሲመለስ ከእ/ር ያመጣው መንፈሳቸው ወደ እ/ር ተመልሰዋልና ።
የሉቃስ ወንጌል 20፡38 ሁሉ ለእርሱ ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም ይለናል። ትንሳኤው በዚህ ምድር ከክርስቶስ ጋር አብረው ይገዙ ዘንድ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰው የሚለብሰው እንጂ እነሱ በመንፈሳዊው አለም ጊዜ ሰለሌ የጊዜ ሃይል ሳይዛቸው ተመልሰውከብረዋል። ለምሳሌ ያህል የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም። ብሎ ጌታ እንደ ተናገረ ሙሴና ኤልያስ ህግንና ነብያትን የሚወክሉት እንዳለ ሆኖ ሙሴ ሞትን አይተው የከበሩትን ኤልያስ ሞትን ሳያዩ የከበሩትን ይወክላሉና ። ከስርየቱ በፊትም ህያዋን ሆነው እናስተውላለን በጉ የታረደውአለም ሳይፈጠር በፊት ነውና። “የዮሐንስ ራእይ 13፡8 ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ…” በዚህም የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን እንዳይደለ እንገነዘባለን።
Brother Binyam T. Alemayehu http://wongelradio.org/
በጌታ ኢየሱስም የመስቀሉን መከራ ከተቀበለልን ቡሃላ ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ መንፈሱን እንደሰጠ።
ሞተው ከነበሩት ከቅዱሳን ብዙ ስጋዎች ተነሱ የሚለው በስብሶ የነበረው ስጋቸው ከትንሳኤው ሃይል አቋድስዋቸው ለምስክርነት ይሆኑ
ዘንድ ስጋቸውን ለብሰው መነሳታቸውን የሚያሳይ ነው እንጂ መንፈሳቸው እማ እስቀድሞ ወደ መጠባት ወደ እ/ር ተመልሶ እንደነበር ግልጽ ነው።
“KJV፣ Eccl 12፡7 Then shall the dust return to the earth as it
was: and the spirit shall return unto God who gave it. መጽሐፈ መክብብ 12፡7 አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም (spirit መንፈስህ) ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።” ሰለዚህ የነዚህ ሰዎች ትንሳኤ በስብሶ የነበረው ስጋቸው የማይበሰብሰው ከእ/ር ወጥቶ ወደ እ/ር
የተመለሰው መንፈሳቸውን በትንሳኤው ሃይል እ/ር በማዋሃድ ያስነሳቸው ናቸው። የማይበሰብሰውን ለብሰው ወደ ቅዲስትቱ ከተማ ወደ ሰማያዊትዋ እየሩሳሌም መግባት ቻሉ ከዛም በምድርም ለብዝዎች ተገልጠው መታየት ቻሉ። በራእይ ሂዱና አስተውሉ በፍልስጤም ምድር ያለችው ምድራዊትዋን እየሩሳሎም ምንም ቅዲስትቱ ከተማ የሚያስብላት እንደሌለ
ታያላችሁ ሰማያቱን እየሩሳሌምን ቅድስቲቱም ከተማ ብሎ ሲጠራት እናያለን “የዮሐንስ ራእይ 21፡2 ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥” እንደዚሁ በ(የዮሐንስ ራእይ 21፡10)
ጌታ የተሰቀለባት እና ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደሉት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቃን ደም ሁሉ ያለባትና የሚደርስባት ምድራዊትዋ እየሩሳሌም እንካንስ ቅድስቲቱም ከተማ ብሎ ሊተራት ቀርቶ በታሪክ ገናና እንደመሆንዋ መጠን ታላቂቱ ከማለት በቀር በስማ ብቻ እንካ አይጠራትም “የዮሐንስ ራእይ 11፡8 በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞ ጌታቸው የተሰቀለባት ናት።”
የሙሴና የኤልያስን ህያውነት እናስተውል
የማቴዎስ ወንጌል 17፡1 ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። 2 በፊታቸውም
ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። 3 እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። 4 ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። 5 እርሱም ገና ሲናገር፥
እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
“መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 2፡11 ሲሄዱም። እያዘገሙም ሲጫወቱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።” እንግዲህ አፈርየሆነው ስጋቸው ወደ ነበረበት ምድር ሲመለስ፥ (spirit መንፈሳቸው) ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ተመልስዋልና በመንፈስ ህያዋን ናቸው በዚህም ለጌታ ሁሉ ለእርሱ
ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን እንዳይደለ እወቁያለውን እንገነዘባለን።
Brother Binyam T. Alemayehu http://wongelradio.org/
ነገር ግን በ “19 በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት(spirit መንፈሳቸው) ሰበከላቸው፤ 20 ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥
የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።” እነዚህ ለየት የሚያደርጋቸው ( spirit መንፈሳቸው) ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር እንደ መመለስ ፈንታ እ/ር አሰራቸው። ጌታም ሄዶ በኖህ ዘመን የእግዚአብሔር ትዕግሥት 120 ያስጨረሱትን በኖኅ ዘመን አልታዘዙም ለሚላቸው ወንጌልን ሰበከላቸው። ለምን ወንጌሉን መስበክ አስፈለገው?
እዛው ወረድ ብሎ በ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡6 መልሱን ይነግረናል።
በነገራችን ላይ መጽሐፍ ቅዱስ በብራና መልክ የተዘጋጀ ወጥ ፅሑፍ ነበረ። ለአንባቢያን እንዲመች በምእራፍና በቁጥር ተከፋፍሎ የተሰራው በ1560 ጄኔቫ መጽሃፍ
ቅዱስ በመባል የሚታወቀው አንድ የሊቃውንት ቡድን በጄነቭ ሆነው ሰሩ። ሁለተኛው እትሙም በ1652 ታተመ ይህ ነበር የመጀመርያው
የእንግሊዝኛ ትርጉም በምእራፍና በቁጥር ተከፋፍሎ የተሰራው ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡6 ስናስብ የተያያዘ ጽሁፍ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ቃሉም “እንደ ሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ስለዚህ ምክንያት ወንጌል ለሙታን ደግሞ ተሰብኮላቸው ነበርና።” “1Pet 4፡6 for this cause was the gospel preached also to them that are dead, that they might be judged according to men in the flesh, but live according to God in the spirit.”
የሃዋሪያው መልእክት ግልጽ ነው። ስጋቸው በተመለከተ ሙታን ናቸው። ህያዋን ሆነው ያሉት በመንፈስ እንደሆነና ታስረውም እንዳሉ ወንጌሉ ተሰበከላቸው። መገንዘብ ያለብን በሲኦል የዘላለም ስቃይ ይጠብቅሃል ተብለው አይደለም የተሰበከላቸው። ነገር ግን ወንጌል የምስራች መልካም ዜና የእ/ር ኁይል ለማዳን ነው የተሰበከላቸው።በስጋቸው ሳሉ ሃጢያታቸው የከፋ ስለ ነበር እ/ር ጎርፍ ልኮ በውሃ በማስጠም በጎርፉጠራርጎ ወደ ሲኦል ወሰዳቸው በዚያም ለዘላለም ሳይሆን ያሰራቸው ለሁለት ሺ ሶስት መቶ ሃምሳ ዘመናት ታሰሩ። “እንደ ሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው የሚለን ያንን ነው ። በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ በሲኦልም ላይ ስልጣን ያለው ጌታ ሄዶ ወንጌልን ሊሰብክ ሄደ እንጂለቫኬሽን አልሄደም ወንጌሉም የእ/ር ታላቅ ስራ ፍርዱ የዘላለም ሳይሆ በዘመናት ወስጥ የተወሰነ እንደሆነ እናስተውላለን ። በዚህም በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ሆኑ። ማንም ሲናገር እንደእ/ር ቃል ይናገር። አሜን!
እንደኖህ ዘመን በመምጣቱም የሚፈረድባቸው በአላማ ለማረም ጽድቅን ለማስተማር ነው። ይህን ሊፈጸም ያለ ትንቢት አስተውሉ!
ኢሳ 29/9 ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩት ጽድቅን ይማራሉና:> በእለም ያሉ ሁሉ ጽድቅ ተምረው ታይቶ ይታወቃልን
ስለዚህ ይህ ገና የሚፈጸም ትንቢት ነው።> when thy judgments are in the earth , the inhabitants of the WORLD will learn righteousness .[uprightness & right standing with GOD.] Isaiah 26/9 አስተዋላቹሁን ፍርዱ በአለም ሲገለጥ ምንን ይማራሉ ይላል? ጽድቅን! ሃሌሉያ!
Ps 130፡4
But there is forgiveness with thee, that thou mayest be feared ትፈራ ዘንድ በአንተ ዘንድ
ይቅርታ አለ። አሜን። Brother Binyam T. Alemayehu
by Brother Binyam T. Alemayehu