በጌታ ጸጋና እውቀት ማደግ
“Grow in grace, and in the knowledge of our Lord”
Posted on April 1, 2011 by Brother Binyam T. Alemayehu
«2ኛ ጴጥ3/18 ነገር ግን በጌታችንና በመድሃኒታችን በእየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤አሜን።»
When he the spirit of truth guide us into all truth we will follow the Lamb whithersoever he goeth ! That is sonship way! JESUS Christ IS THE WAY TO SONSHIP The orphan spirit is destructive rampant in the church and the world today, causing chaos and destruction. There is an answer to this orphan spirit, which is the spirit of adoption and the spirit of Sonship. Father God is waiting for His sons and daughters to understand who they are, and be the co-heirs He created them to be. The most perfect example of a son knowing his true identity, position, and inheritance was Jesus. Heb 12/2 Looking unto Jesus the author and finisher of our faith; let us focose on him Matt 6/22 The light of the body is the eye: if therefore thine eye be single, thy whole body shall be full of light.

«በጌታችንና በመድሃኒታችን በእየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ» የሚገርም ቃል ነው። ለልጆች ወይም ለአማኞች ሁሉ የማያቃርጥ ተግዳሮት ቢኖርብን በጌታችን ጸጋና እውቀት ለማደግት ያለውሂደት ነው። ማደጋቹ በነገር ሁሉ ይደግ ይገለጥ፤ ራስ ወደ ሆነው ክርስቶስ እደጉ፤ ስለማደግ የእ/ር ቃል ብዙ ያስተምረናል። ከእነዚህ አንዱና ዋንኛው አስፈላጊ ነገር በለልጆች ህይወት ውስጥ ልናድግብትያለ ከመንፈሳችን ውስጥ በሚወጣው ህይወት መኖር መለማመድ ነው፡ ከአይምሮ ብቻ ሳይሆን ከዚያም ባሻገር የክብር ተስፋ ካለው በውስጣችን ከሚፈልቀው መንፈሳዊ የህይወት ወንዞች ከክርስቶስህይወት መቅዳት ይበዛልን ዘንድ በዚህም እርሱ እውቅትና መረዳታችን ይሆንልናል።
ይህ በኛ አውን ይሆን ዘንድ የስጋዊው ሰው ሃሳብ መፍረስና አይምሮን ደግሞ መማረክን ሁለቱን ያጣመረ ተግባርን ያዛል። ‹2ኛ፣ ቆሮ 10/5 የሰውንም ሃሳብ በእግዚያብሄርም እውቃት ላይ የሚነሳውንከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳላን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን።> ብዙ ግዜ ይህን ሃሳብ ከውጪ ላሉት እንጠቀምበታለን ። ጠቢብ እራሱን ያያልና ። ተቀዳሚ መልክቱ ግን በእኛውስጥ ስጋ በመንፈስ መንፈስም በስጋ ላይ በለው የእሽቅድድም ትእይንት የሚያመለክት ነው። ለምን ስጋዊው አስተሳሰብ መፍረስ አይምሮ ደግሞ ይታዘዝ ዘንድ መማረክ አስፈለገው? ምክንያቱም <ስለስጋማሰብ ሞት ነውና ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ህይወትና ሰላም ነው።ሮሜ 8/6 <For to be carnally minded is death; but to be spiritually minded is life and peace.> ስጋዊ አይምሮ መያዝ ሞት ነው። በቀላሉ የሞት ፍቺው ያ ነው። ጌታ ደግሞ ሞትን ሊደመሥሥ ምጥተዋልና። ምንፈሳዊ አይምሮን መያዝ በአንጻሩ ህይወትና ሰላም ነው። የክርስቶስ አይምሮ ህይውትናሰላም ነውና።
እኛ ደግሞ የክርስቶስ አይምሮ አለን፡ <But we have the mind of Christ.1Cor 2/16> የእ/ር ልጅነታችን ከምልክቱ አንዱ በዚህ አይምሮ ለመጠቀም ማደግ መቻላችን ነው። ያም ማለትየክርስቶስ አይምሮ በመንፈስ የሚመራ እንደሆነ እናስተውላለንና እኛም እንደዚሁ ይጠበቅብናል፡፡ <ማቲ3/16 የእ/ር መንፈስ ወረደብት> ከዛም ማቲ4/1 መንፈስም ይፈተን ዘንድ ወደ ምድረ በዳወሰደው> ክዛም በመንፈስ ሃይል ተምለሰ፡ አገልግሎቱም የጌታ መንፈስ በኔ ላይ ነው፡ ብሎ ከጀመረ ቡሃላ መንፈስ ከሆነው አባቱ ዮሃ4/24 ለመሳካቱ ሚስጥር የሆነው ከአባቱ የሚሰማውን የሚያየውንብቻ ያደርግ ስለነበር ነው። የራሱን ፈቃድ አንዳች እንኻን አያደርግም ነበር። ከመንፈስ ከሰማ ይናገራል ካልሰማ ዝም ይል ነበር በዚህም ድል ነሺ ሆነ።
አባቱ ሲያደርግ ካላየም ዝም ይል ነበር አንጂ የራሱን ፈቃድ አላደረገም። < በእግዚያብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ የእ/ር ልጆች ናቸው ሮሜ8/14> ልጅነትና መንፈስ ቅዱስ የተያያዙ ናቸው። በእ/ርመንፈስ ከመመራት ውጪ የእ/ር ልጅነት የለም፡ ፡
መንፍሳዊ እድገት የአይምሮ ጅምናስቲክ ውጤት አይደለምና፡ መመራታችን በበዛልን ልክ በእድገታችንም ተገቢው ህይደትና ውጤታማም እድገት ይታይበታል። ጌታ<በማቲዮ 6/27 ከእናተ በመጨነቅ(በማሰብ) መቁመቱ ላይ አንዳች መጨመር አይችልም> ብልዋል በተፈጥራዊው ሰው አስቦ ቁመቱ ካላደገ ያም ማለት የምድሩን ካልቻለ ማለት ነው በመንፍሳዊው ላይማ አይታሰብም።< ከመንፈስየተወለደ መንፈስ ነው።ዮሃ3/6> ጳውሎስ ይህን ቀጽሎ ሲያስረዳን < በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ ገላ5/25 በዚህ በመንፈስ መኖርና መመላለስ ውስጥ ብዙ የምንማረው የምናውቀውአለ። ስለ መመላልስ፤ ስለመስማት፤ ስለመናግር፤ በእውነት በመንፈስ ያለው የየእለት ህይወት እውን ከሆነልን የከበረ ነገር ነው።
<በሮሜ8/5 እንደ ሰጋ ፈቃድ የሚኖሩ የስጋን ነገር ያስባሉና እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ> አይገርምም ? “የመንፈስን ነገር ያስባሉ ”እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግንየመንፈስን ነገር ያስባሉ !እንደ ምናስተውለው ሁለት አይነት ሰዎች ሃሳባቸው የተቀመጠብትን ይናያለን፡ እነዛ ባልተቀደሰ የስጋ ፍላጎት ላይ ሃሳባቸውን ያስቀመጡና የስጋን ምኞቱን የሚፍጽሙ ደግሞምበተቀደሰው የመንፈስ ፈቃድና ፍላጎት የሚኖሩ ሃሳባቸው የተያዘው በመንፈስ ነገር ላይ እንደሆነ እናስተውላለን። በስጋ ግዛት የሚኖሩ ባልተቀደሰው የስጋ ፍላጎት ቁጥጥር ስር ናቸው። በአንጻሩም በመንፈስገዛት የሚኖሩ በተቀደሰው በመንፈስ የሚመሩም እንዲሁ ናቸው።
ለመሆኑ በመንፈሳችን ውስጥ ምን ስላለ ነው እ/ር ደጋግሞ ለዚህ የውስጥ ህይወት ህያው እንድንሆን ደጋግሞ በተለያየ መልኩ የሚናገረንና የሚያስተምረን? እ/ር በህይወታችን ምንን ስላስቀምጠ ነው? አዎን መንፈሳዊ ሃብት ወይም መዝገብ ስላስቀመጠ ነው። ‹ በትንቢተ ኢሳ45/3 በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እ/ር እኔ እንደ ሆንኩ እንድታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርምየተደበቀችውን ሃብት እሰጥሃለሁ› ጌታ ነው የሚናገረው ስውር መዝገብ እሰጥሃለሁ የተደበቀችን ሃብት እሰጥሃለሁ፡ ለምን? በስምህ የምጠራህ እ/ር እንደሆንኩ ታውቅ ዘንድ። ምንድን ናቸው እነዚህበትንቢት የተነገሩ መዝገብና ስውር ሃብቶች?
‹በቆላ2/2-3 ልባቸው እንዲጸናና በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደ ሚገኝ ወደ መረዳት ባለጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእ/ርንም ሚስጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ። የተሰወረየጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና። › አሁን አወቅን እ/ር ሃብት መዝገብ እያል ግድ የሚለው የእ/ር ጥበብና እውቀትን ነው፡ እነዚህም በየሱስ ክርስቶስ ተሰውረው ተቀምጠዋል። በቆላ1/27ቀደም ብሎ የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናተ ውስጥ ነው ብሎ ለዘመናት ተሰውሮ የየተደበቀውን ሚስጢር ገልጦልናል። አስተዋልን? እ/ር በእኛ ያስቀመጠው ነገር አለ “ክርስቶስ” በእሱ ውስጥደግሞ ሃብትና መዝገቡ ታጭቆ አለ ውደ ብስለት ግዛት ማደጋችን ይህን ሃብት መጠቀም ያስችለናል።
ምሳሌ2/3 ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት ለማስተዋልም ድምጽህን ብታነሳ እርስዋንም እንደ ብር ብትፈልጋት እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት የዚያን ጊዜ እ/ርን መፍራት ታውቃለህ የአምላክህንም እውቀትታገኛለህ» ሃብቶች ምን እደሆኑ አስተዋልን እውቀት፤ ማስተዋል፤ የአምላክህን እውቀት ሃሌሉያ ታገኛለህ! ይሄ ሃብት ነው በክርስቶ ተሰውሮ ያለው እለት እለትም ከዚህ በውጣችን ካለው የክብሩ ሃብትእንደ በሰሉ ልጆች መጠቀም እንችል ዘንድ እ/ር ያሳድገናል። ‹1ኛ፣ቆሮ3/7 እንግዲህ የሚያሳድግ እ/ር ነው እንጂ የሚተክል ቢሆን የሚያጠትጣ ቢሆን አንዳች አይደለም።› እንግዲህ የክርስቶስ አይምሮካለን ጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ያደምጥ እንደ ነበር ማድመጥ አለብን።‹ ቆላ2/18 አካል ሁሉ በጅማትና በማሰርያ ምግብን እየተቀበለ እየተጋጠምም እግዚያብሄር በሚሰጠው ማደግ ያድጋል› የሚያሳድገን መንፈሳዊ ምግብ የምናገኘው በዚሁ መልክ ነው፡ ‹በእ/ር መንፈስ የሚመሩ እነሱ የእ/ር ልጆች ናቸውና› ፡ ልጅነታችን የተመረኮዘውም በዚህ የምንፈሱ ህይወት በመጠቅምና ለማደግም መልሱያለው በውስጣችን ካለው መጣመር ነው። መታዘዝ ከመስዋእት ይበልጣል!
መንፈስ ለቤተ/ክ የሚናገረውን ከሰማን ለዘመናችንና ለትውልዳችን ድል ነሺዎች ነን። “እ/ር ግን እውቀትና ጥበብን ይሰጣል” “ጥበብን ለጠቢባን እውቀትን ላስተዋዮች” ዳንኤል ላይ። ለገዛ ዘመናችንምልንጠቀምበት የተገባውን ምክርና ጥበብ ማስተዋልም የአምላካችንም እውቀት ቢሆን ከኛ አይሰወርም ከእርሱ የተነሳ እናድጋልን ። ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም ከእ/ር አፍ ተዘጋጅት በሚወጣ ቃል ሁሉእንጂ› የበላ ያድጋልና መንፈሳዊ እንጀራና ውሃ የሆነውን እለት እለት እንመገብ። በማስተዋላችንም ፈጣኖች አንሆናለን። ሃሌሉያ! ‹ምክር በሰው ልብ እንደ ጠሊቅ ውሃ ነው አይምሮ ያለው ሰው ግንይቀዳዋል። ምሳ»20/5 ብርታታቸው ከእ/ር የሆነና አማካሪያቸውም በምክሩ ድንቅና ግሩም የሆነው እ/ር የሆነ ምንኛ ብጹአን ወይም ደስተኞች ናቸው? አሜን! Brother Binyam T. Alemayehu