የምህረት ጥበብ! ማውጫ ፦ እ/ር ማለት እግዚአብሄር ማለት ነው። 09/01/2006
BROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU WRITINGS
My word is Spirit and it is Life ! John6/63. K j v. የዮሐንስ ወንጌል 6/63 እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።
የምህረት ጥበብ
“ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ” መዝ 18/25 የዚህ ቃል ሃሳብ የአማርኛችን ትርጉም ስለ ቸርነት ያስረዳናል። ቸርነት እንደ ምናውቀው ሩሁሩሁነትን፤ ለጋስነትን፤ ደግነትን፤ ያዘለ ነው። ይህ የሚያሳየን አካፍሎ ማደርን ነው። ወይም ብኩንነትን እስከ አልጨመረ ድረስ የመስጠት ህይወትን ነው። ይህም እንደ ሁኔታው ይለያያል ከትርፉ የሚያካፍል አለ ከጎደሎውም የሚያካፍል አለ። የዚህ ጹሁፍ አላማ ይህን ለማሳየት ሳይሆን በአማርኛ ቱርጉም “ቸርነት” የሚለው ቃል ስለ “መሃሪነት” እንደ ሆነና ይህ በእ/ር ልጆች ህይወት ውስጥ ምን ድርሻ እንዳለው በቃሉ ውስጥ እንድናስተውል ነው።
የኅይል ሁሉ ባለቤት እ/ር ለመሃሪው መሃሪ ሆኖ እንደ ሚገለጥ ማወቁ መልካም ነው። የእንግሊዝኛው ትርጉም እንዲህ ያስቀምጠዋል
“Ps 18/25 With the merciful thou wilt shew thyself merciful; with an upright man thou wilt shew thyself upright”
“ለመሃሪው አንተም ምህረትን ታሳየዋለህ” እ/ር ወደ ራሱ ወደ ለያቸው በቅሪቶቹ ህይወት ውስጥ በአስደናቂው የፀጋው የውስጥ ስራ እየሰራ ካለው አንዱ መሃሪዎችን ማዘጋጀት ነው። እርሱ “በምህረቱ ባለጠጋ ነውና” ልጆቹም በባህሪው ሊገኙ የተገባ ነውና፤ በዚህም ከምህረት ድህነት ወደ ምህረት በለጠግነት እስኪ መጡ በውስጣቸው ያለ ማቋራጥ በመንፈስ ዘየ ያስተምራቸዋል።
“ምህረትን እወዳለሁ ….ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ ማቴ 9/13” , ማቴ12/7 ከዚህ ቃል እንደ ምናስተውለው ጌታ ምንን ይወዳል? በእርግጥም ምህረትን ይወዳል። ስለ ምንስ ተማሩ አለ? በእርግጥም ምህረትን እንድንማር ይወዳል። እንደሚታየው ግን ብዙዎች ከጌታ ጋር ብዙ ዓመት ተጉዘው ምህረትን መውደዱ ያለ ማስተዋላቸውና ያለ መማራቸው ድንቅ ነው። እ/ር ግን በዚህም ውስጥ አላማ እንዳለው እናውቃለን። አንድ ጊዜ ነው አሉ የወገኖች ህብረት በተጧጧፈ ሁኔታ በመንፈስ ሰክረው በመካከላቸው እ/ር እየበዛ እየቀረበ መጣላቸው። በመሃል አንድ ወንድም ከአካሉ ተገንጥሎ ለብቻው የተቀባ መሆንን ፈልጎ ከህብረቱ ጠፋ። “መጽሐፈ ምሳሌ 181 መለየት የሚወድድ ምኞቱን ይከተላል፥ መልካሙንም ጥበብ ሁሉ ይቃወማል።” ና
የከበረ ነገር ያለበት ወንድም ነበረና እስከ ተወሰነ ርቀት በቀዳው ነዳጅ ተጓዘ ከዛ ግን ድርቀት ሆነ። ከህብረቱም በእድሜም በፀጋም የሸመገሉ አንድ አባት ነበሩና ወደ ቤቱ ሄዱ እዚያም ሲደርሱ እጅግ ታላቅ ብርድ ስለ ነበረ ብዙ እንጨቶችን ደራርቦ እሳት ይሞቅ ነበር። በሩም ተንኳኳ እሳቸው መሆናቸውን ያይና እንዳኮረፈ በሩን ይከፍተዋል። ሳይነጋገሩ ከቆፈኑ ለማገገም ሁለቱም ከእሳቱ መሞቅ ጀመሩ። እሳቸውም መልክታቸውን መናገር ጀመሩ ይህ ትልቁን እንጨት ታየዋለህን? ሁሉንም እንጨቶች በሃይል ተሰባስበው ካሉበት በብዛት ከሚያቀጣጥላቸው ዋንኞው እሱ ነው። ነገር ግን ከመሃከላቸው እናውጣውና እንየው ብለው በጣም በሃይል የሚቦለቦል እሳት ያለው ትልቁን እንጨት ለብቻው አውጥተው አስቀመቱት በሃይል የሚቦለቦል እሳት ያለው ትልቁ እንጨትም ቀስ እያለ እየከሰመ እየከሰመ ጠፋ። ተነስተውም ለሄድ ሲጀምሩ የሚማር ልብ ስለ ነበረው መልክቱን እዳገኘውና ወደ ወገኖችም ህብረቱም እንደ ሚመለስና ከገወገኖች ጋር ጌታን ለመቋደስ እንደ ጓጋ ነግሮ አመስግኖ ተሰናበታቸው።
“ትንቢተ ኢሳይያስ 55/6 እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤” እ/ር ሲቀርብና ሲናገር መስማት ቢገባንም ባይገባንም አብሮ መጓዝ መልካም ነው። እ/ር ሰላም ነው እንጂ ግራ የመጋባት አምላክ አይደለምና። ሁሉን እይታ በተመለከተ የነገሮች እውነተኛ ተፈጥሮ እሱ እንደ ሚያየው እናይ ዘንድ በጊዜው አጥርተን እንድናይ አይናችን መንፈሳዊ ኩል ይኩለናል እይታችንንም ሊያጠራው ይችላልና። “የዮሐንስ ራእይ 3/18 …እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።” እኛም ከሱ እውነትን እንገዛታለን እንጂ አንሸጣትም።
ደረጃው ይለያይ እንጂ መሃሪዎች ለመሆን ያለው ጦርነትና መታገላችን በሁላችንም ዘንድ የሚገርም ነው። ስለ ፍርድ ካለን ግንዛቤ የተነሳ ፍርድን እናዛለንና። በቀላሉ “በተማራቹበት ምህረት መጠን መሃሪዎች ሁኑ” ተብሎ እንደ ተፃፈ በቀላሉ በተማርንበት ምህረት መሃሪዎች ሆነን ለፍጥረት መገለጥ ሲገባን ማለት ነው።
ነብዩ ዮናስ የጌታን ቃል ተቀበለ። “የጌታን ቃል” መቀበል ድንቅ ነገር ነው። ያ ግን በራሱ በምህረት የተሞላን መሆናችንን አያሳይም። ዮናስ የተቀበለው የምህረት ቃል ነበር ወደ ተርሴስ ያስኮበለለው። “ትንቢተ ዮናስ 4/2 ወደ እግዚአብሔርም ጸለየና፦ አቤቱ፥ እለምንሃለሁ፤ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽም፥ ምሕረትህም የበዛ፥ ከክፉው ነገርም የተነሣ የምትጸጸት አምላክ እንደ ሆንህ አውቄ ነበርና ስለዚህ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል ፈጥኜ ነበር።”
ይህ ሰው እውነተኛ ነብይ ነበረ። የነነዌ ከተማ በሶስት ቀን እንደ ምትገለበጥ በተነበየ ጊዜ ከእውነት ዘንድ ነበር። ነገር ግን እ/ር አጠፋለሁ ማለቱ ወደ ንስሃ አምጥቶ ንስሃን ሰጥቶ ጽድቅን አስተምሮ እምራለሁ ማለቱ እንደሆነ ባስተዋለ ጊዜ ተቆጣ። ንስሃንም ጭምር የሚሰጥ እ/ር እራሱ ነውና። “የሐዋርያት ሥራ 11/18 ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና፦ እንኪያስ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሰጣቸው እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ።” ዮናስ ቢቆጣም እ/ር ቃል አቀባዩ አገልጋዩ በምህረቱ እንደሱ ባለጠጋ ይሆን ዘንድ መጠየቁን ቀጥለዋል። “ትንቢተ ዮናስ 4/4 እግዚአብሔርም፦ በውኑ ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን? አለ።” እንደ ዘመኑ ክርስቲያን እኔን ሃሰተኛ ነብይ ሊያስብል እደገና በፍጥረት ሁሉ ላይ ምህረትን አውጅ ይለኛል እንዴ? የሚል ሙግት በውስጡ ያዘ።
ብዙ ወገኖች ከመጀመርያው በእ/ር መንፈስ እንደዛ ያልተፃፈውን የአብዛኛው የሰው ልጆች ፍፃሜ የዘልአለም ስቃይ ነው። ብለው ስለ ሰበኩ አሁን ምህረትን ለመስበክ ጭንቅ እንደ ሆነባቸው። ዮንየ ነብዩ ጭንቅ ሆነበት። ስለ ዚህም እ/ርም ለማስተማር በታላቅ አሳ ነባሪ ሆድ ወስጥ አሳልፎ ደግሞም ፀሐይም በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ትኩስ የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጅቶ፤ ዮናስን እስኪ ዝል ድረስም በፀሐይ ራሱን አስመታው፤ ከፍ ያለ የፀሐይ ቮልቴጅ ስለ ለቀቀበት ዮናስ ለራሱ ሞትን ፈለገና፦ ከሕይወት ሞት ይሻለኛል አስባለው። በአንድ ቀን የሰራለት የቅል ዣንጥላም አንስቶበታልና።
“ዮናስ4/9 እግዚአብሔርም ዮናስን፦ በውኑ ስለዚች ቅል ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን? አለው። እርሱም፦ እስከ ሞት ድረስ እቈጣ ዘንድ ይገባኛል አለ።10 እግዚአብሔርም፦ አንተ ትበቅል ዘንድ ላልደከምህባት ላላሳደግሃትም፥ በአንድ ሌሊት ለበቀለች፥ በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው ቅል አዝነሃል።11 እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሀያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን? አለው።”
በምህረት የተሞላ ማንነት እስኪ መጣብን ድረስ የእ/ር ስርአቶች ምንኛ አስጨናቂዎች ናቸው? ጊዜው ሲደርስ እኮ በምህረት ፍፁማን መሆናችን አይቀርም። ጌታ እየሱስ በምህረቱ ፍፁም ነበር። እሱ እንደ ዘፍጥረቱ ሰው የመጀመርያው አዳም ጅምር መልክና አምሳል አልነበረም ከእ/ር ክብር ጎድለዋልና ሁለተኛውና የመጨረሻው አዳም ግን ያበቃለት እንደ ወረደ ጠፈፍ ያለ ከማይጎድለው የመለኮት ህይወት የተሞላ ነበረ። እ/ር መግለጥ የፈለገው ፍፁሙ መልክና አምሳልም ነው። እንድንመስልለት ከመጀመርያው በልቡ የነበረው መልክና አምሳል ይህ ነበርና። በማስተዋላችን ፈጠን ሆነን በእርሱ እንገኝ ዘንድ ቅዱስ ቃሉ ተነግሮብናል። ወይ በእሳት እንደ ተቀመሙ ሰዎች ደግሞም እንደ በሰሉ ልጆች በመገለጡ እንማራለን ወይ እንደ ዳዊት እንዲህ ማለታችን አይቀርምና።“መዝሙረ ዳዊት 119/71 ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።”
አያችሁ አባታችን በምህረት የተሞላ እንደሆነ እኛም ልንሆን የተገባንን ተፅፎልናልና። “(Luke 6:36 [KJV]) Be ye therefore merciful, as your Father also is merciful 37 Judge not, and ye shall not be judged: condemn not, and ye shall not be condemned: forgive, and ye shall be forgiven: አባታችሁ ርኅሩኅ እንደሆነ እናንተም ርኅሩኆች ሁኑ። አትፍረዱ፤ አይፈረድባችሁም፤ አትኰንኑ፤ አትኰነኑም። ይቅር በሉ፤ ይቅር ትባላላችሁ።” ይህ ቃሉ ለራሱ ይናገራል።
መደምደሚያው እንደ አባታችን በምህረት እንሞላ። አንድ ሰው በእብራዊን ቋንቋ የጌታን ድምጽ ሰማሁ ካለ ፈጽሞ ሰምቶ ፈጽሞ መታዘዙን የሚያሳይ ነው። ሰምቶ ካልታዘዘም ፈጽሞ አልሰማም። በመገለጥ እንዲሰማም በሌላ ሂደት ያልፋል። “በመከራ ጆራቸውን ይከፍታል። እዮብ36፡15 በእብራይስጥ መከራ የሚለው ውጥረት ይለዋል። አንዳንድ ጊዜ ለምን ይሄ ሁሉ ውጥረት በመንገዳችን እንደ ሚያልፍ እንደነቃለን። እንደ ዛም ሆኖ ነገር ሁሉ ተያይዘው ለበጎ እንዲደረግ እንረዳለን። በብዙ መከራ ማለፋችንም ለብዙ አላማ እንደሆነ እናውቃለን። ከዛ ውስጥ አንዱ ጆራችን እዲከፈት ነው። ጳውሎስ የደቀ መዛምርቱን ልብ በማበረታታትና በእምነታቸወ ጸንተው እንዲሩ በመምከር “ወደ እ/ር መንግስት ለመግባት በብዙመከራ (ግሪክ፦ pressure, እደአገባቡ ቃሉ ሲተረጎም ውጥረት ግፊት መገፋፋት ተጽኧኖ የሚያመጣ ውጥረት )ማለፍ አለብን “” ሐዋ14፡22 ይህም ውጥረት ከአሮጌው አውጥቶ ወደ አዲሱ ተጭኖ ያስገባናል። እ/ር አምላክ ጥበበኛ ነው። አንዱን ውጥረት ከአንድ ነገር ለማውጣትና በተመሳሳይ ሰአትም የስጋን ፈቃድ ሰብሮ የመንፈስን ድምጽ ወደ መስማት ግዛት ያመጣናል።
BROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU WRITINGS, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND WRITERS ONLY !