The Lords Parable of Forgiveness
የማቴዎስ ወንጌል 18 Matt 18
21 በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ። ጌታ
ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት?
እስከ ሰባት ጊዜን? አለው።
21 Then came Peter to him, and said, Lord, how oft shall
my brother sin against me, and I forgive him? till seven
times?
22 ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት
እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም።
22 Jesus saith unto him, I say not unto thee, Until seven
times: but, Until seventy times seven.
23 ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ሊቈጣጠር
የወደደን ንጉሥ ትመስላለች።
23 Therefore is the kingdom of heaven likened unto a
certain king, which would take account of his servants.
24 መቈጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ
ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ።
24 And when he had begun to reckon, one was brought
unto him, which owed him ten thousand talents.
25 የሚከፍለውም ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም
ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው
አዘዘ።
25 But forasmuch as he had not to pay, his lord
commanded him to be sold, and his wife, and children, and
all that he had, and payment to be made.
26 ስለዚህ ባሪያው ወድቆ ሰገደለትና። ጌታ ሆይ፥
ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው።
26 The servant therefore fell down, and worshipped him,
saying, Lord, have patience with me, and I will pay thee all.
27 የዚያም ባሪያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፥
ዕዳውንም ተወለት።
27 Then the lord of that servant was moved with
compassion, and loosed him, and forgave him the debt.
28 ነገር ግን ያ ባሪያ ወጥቶ ከባልንጀሮቹ ከባሮቹ
መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና። ዕዳህን
ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው።
28 But the same servant went out, and found one of his
fellowservants, which owed him an hundred pence: and he
laid hands on him, and took him by the throat, saying, Pay
me that thou owest.
29 ስለዚህ ባልንጀራው ባሪያ ወድቆ። ታገሠኝ፥
ሁሉንም እከፍልሃለሁ ብሎ ለመነው።
29 And his fellowservant fell down at his feet, and
besought him, saying, Have patience with me, and I will pay
thee all.
30 እርሱም አልወደደም፥ ግን ሄዶ ዕዳውን
እስኪከፍል ድረስ በወኅኒ አኖረው።
30 And he would not: but went and cast him into prison,
till he should pay the debt.
31 ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሮችም ያደረገውን አይተው
እጅግ አዘኑ፥ መጥተውም የሆነውን ሁሉ ለጌታቸው
31 So when his fellowservants saw what was done, they
were very sorry, and came and told unto their lord all that
ገለጡ። was done.
32 ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ። አንተ ክፉ ባሪያ፥
ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤
32 Then his lord, after that he had called him, said unto
him, O thou wicked servant, I forgave thee all that debt,
because thou desiredst me:
33 እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን
ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው።
33 Shouldest not thou also have had compassion on thy
fellowservant, even as I had pity on thee?
34 ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው
ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው።
34 And his lord was wroth, and delivered him to the
tormentors, till he should pay all that was due unto him.
35 ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር
ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።
35 So likewise shall my heavenly Father do also unto you, if
ye from your hearts forgive not every one his brother their
trespasses.
ጌታ እየሱስ ለጴጥሮስ እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም። ሲል 490 ጊዜ ይቅር እንዲል ነግሮታል። ይህ
ምሳሌ እጅግ ጠቃሚ ምሳሌ ነው። የእ/ር ጠቅላላ ምክር ና ለእኛ ካሳየን ወሰን የሌለው ብዙ ይቅርታ የተነሳ ምሳሌውን
ተከትለን ባህርዩን እንድናጸባርቅ እንደሚጠብቅብን በልቡ ያለውን አመለካከት እድናስተውል ግልጽ እይታን ያሳየናልና።
ደግሞም እ/ር በታሪክ ጉዞ ውስጥ በህዝቦችና በቤተክርስቲያን እንዴት እንደ እደሚሰራ ቁልፍ እይታን ያስጨብጠናል።
አንድ ንጉስ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወይም አገልጋይ ወደ እርሱ አመጡ። ትልቅ እዳ ነው ይሄ። እዳው
የሚከፍልበት ቅጽበት በመጣ ጊዜ አገልጋዩ ምህረትን ጠየቀ ኑጉሱም እዳውን ትቶለት ምህረትን አደረገለት። የሚገርመው
ግን ይሄው ሊከፍለው የማይችለው እዳ ውስጥ ተዘፍቆ የነበረው ምህረት የተደረገለት አገልጋይ ትንሽ እዳ ያለበትን
ከባልንጀሮቹ ከባሮቹ ዕዳህን አንዱን አገኘና። ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው። ስለዚህ ባልንጀራው ባሪያ ወድቆ። ታገሠኝ፥
ሁሉንም እከፍልሃለሁ ብሎ ለመነው። እርሱም አልወደደም፥ ግን ሄዶ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወኅኒ አኖረው። እርሱና
ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል አዘዘ። ንጉሱ ይሄን በሰማ ጊዜ በተማረበት ምህረት ሊምር
ባልወደደው ባሪያ ተቆጣ ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ። አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ
ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው። ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ
እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው። የምሳሌው ታሪክ አንካር ፍሬ ሃሳቡ ያለው “ማቴ 18/35 ከእናንተ
እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።
“So likewise shall my heavenly Father do also unto you, if ye from your hearts forgive not every one his
brother their trespasses.” እንደ ምናስተውለው ጌታ እየተናገረ ያለው ስለ ገንዘብ እዳ አይደለም። trespasses
ስለመተላለፍ ወይም ሃጢያት እንጂ በብዙ ቦታ ላይ ሃጢያት እንደ እዳ መጽሐፍ ይመስለዋል ይሄም አንዱክፍል ነው።
”አባት ባህርዩን እዲያይብን ይጠብቅብናል be ye merciful as your father also is merciful.judge not ,& ye shall
not be judged: condemn not, & ye shall not be condemmned: forgive & ye shall be forgiven. luke6/36”
አባታችሁ በምህረት የተሞ ላ እንደሆነ በምህረት የተሞላችሁ ሁኑ። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡32 እርስ በርሳችሁም ቸሮችና
ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ። Eph 4፡32 And be ye kind one
to another, tenderhearted, forgiving one another, even as God for Christ’s sake hath forgiven
you.” ከፍል ሁለት ይቀጥላል።
Posted on March 28, 2012
Brother Binyam T. Alemayehu
2, The Lords Parable of Forgiveness የጌታ የይቅርታ ምሳሌ
በክፍል አንድ እንደ አስተዋልነው። ጌታ እየሱስ ለጴጥሮስ እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም። ሲል 490
ጊዜ ይቅር እንዲል ነግሮታል። ይህ ምሳሌ እጅግ ጠቃሚ ምሳሌ እንደሆነ። የእ/ር ጠቅላላ ምክር ና ለእኛ ካሳየን ወሰን
የሌለው ብዙ ይቅርታ የተነሳ ምሳሌውን ተከትለን ባህርዩን እንድናጸባርቅ እንደ ሚጠብቅብን በልቡ ያለውን አመለካከት
እድናስተውል ግልጽ እይታን እንደ ሚያሳየን። ደግሞም እ/ር በታሪክ ጉዞ ውስጥ በህዝቦችና በቤተክርስቲያን ደረጃ እንዴት
እንደ እደሚሰራ ቁልፍ እይታን ያስጨብጠናል ስንል ተመልክተነው ነበር።
በማቴዎስ ወንጌል 18፡21᎒35 ምሳሌ በተማረበት ምህረት ይቅር ለማለት ኑፉጉነት የታየበት አገልጋይ እርሱም እራሱ ምህረቱ
ቀርቶ እልፍ መክሊት ዕዳውን እንዲከፍል እደገና ኑጉሱ እንደ በየነበት አይተናል።
ለብዙ ሰባኪያን ይህ አስቸጋሪ ከሆኑ ምእራፎች መካከል አንዱ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ ሰው ደህንነት ጋር ሊያይዙት
ይከጅላሉና:፡ እንደዚያም በሚያደርጉበት ጊዜ እኛ ክርስቲያኖች የበደሉንን ይቅር ካላንን ደህንነታችን እናጣለን ወደሚል
ድምዳሜ ያመጣቸዋል፡፡ የዚህ አመለካከት ችግሩ ፍጽምናን የሚያዝ በመሆኑ ነው። ይህም ክርስትያን ወገኖች ሊሸከሙት
የማይችሉት ቀንበር ይጭንባቸዋል። ይህ አመለካከት ትክክል ቢሆን ኖሮ ማንም ባልዳነ ነበረ።
በትክክልም ክርስቲያን ወገኖች ይቅር ማለትን ይለማዱ ዛንድ እንደሚገባ የተገባ እደሆነ የአደባባይ ሚስጥር እደሆነ ለሁሉም
ግልጽ። ይህ ጥራት ግን ሁሉም ክርስቲያኖች እንደዳኑ የሚያሳዩት አይደለም። ይቅር ለማለት ችሎታው ቀላል የሚሆነው
ዋንኛ በሆኑ የህይወት ጉዳዮች ላይ ላልተበደሉ ብቻ ነው። ለአብዛንኝዎቹ ይቅር ማለት የሚችሉት መንፈስ ቅዱስ
በህይወታቸው ወስጥ በጊዜ ሂደት በአሰራሩ ሲፈውሳቸው ነው። መራራነትና ይቅር አለማለት ከደህንነት መምጣት ጋር
አብረው የሚጠፉ አይደሉም። የአንድ ሰው የመጽደቁ ጉዳይ ይቅር ከማለት ችሎታ ጋር የተያያዘ ወይም ለአመታት በልቡ
ውስጥ የነበረውን መራራነት ቆርጦ ከመጣሉ ጋር የሚያያዝ አይደለም።
ጽድቅ በእምነት ነው። አንድ ሰው ከጽደቀ ቡሃላ እ/ር አምላክና አባት በመንፈሱ በክስቲያኑ ልብ ውስጥ መስራት ይጀምራል
የስጋንም ስራ ከስሩ ይነቃቅላል። መራራነትና ይቅር አለማለት የስጋ ስራ ናቸውና። ይህም ከSanctification (to make
holy; set apart as sacred; consecrate.to purify or free from sin: Sanctify your hearts)ከማንጻት ከመለየት
ሂደት ጋር ወይም የልብንም ሸለፈት በመንፈስ ከመግረዝ ጋር የሚዛመድ ነው። እንጂ ከJustification ከመጽደቅ ጋር
አይዛመድም። ስለዚህ የጌታ ምሳሌ እንዴት በደህንነት ወስጥ መቆየት እንደምንችል እያሳየን አይደለም። So likewise shall my
heavenly Father do also unto you, if ye from your hearts forgive not every one his brother their
trespasses.” እንደ ምናስተውለው ጌታ እየተናገረ ያለው ስለ ገንዘብም እዳ አይደለም። trespasses ስለመተላለፍ ወይም
ሃጢያት እንጂ በብዙ ቦታ ላይ ሃጢያት እንደ እዳ መጽሐፍ ይመስለዋል ይሄም አንዱ ክፍል ነው። ”አባት ባህርዩን
እዲያይብን ይጠብቅብናል be ye merciful as your father also is merciful.judge not ,& ye shall not be judged:
condemn not, & ye shall not be condemmned: forgive & ye shall be forgiven. luke6/36” አባታችሁ በምህረት
የተሞ ላ እንደሆነ በምህረት የተሞላችሁ ሁኑ። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡32 እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥
እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ። Eph 4፡32 And be ye kind one to another,
tenderhearted, forgiving one another, even as God for Christ’s sake hath forgiven you.” ከፍል 3
ይቀጥላል።
በማቴዎስ ወንጌል 18፡21᎒35 ምሳሌ እየሩሳሌም ይቅር የማትለው ባሪያ ናት Jerusalem is the Unforgiving Servant
“የማቴዎስ ወንጌል 23፡37 ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም
የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ
ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።
Matt 23፡37 O Jerusalem, Jerusalem, thou that killest the prophets, and stonest
them which are sent unto thee, how often would I have gathered thy children
together, even as a hen gathereth her chickens under her wings, and ye would
not!”
Posted on March 28, 2012
Brother Binyam T. Alemayehu
