የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የተለያዩ አይነቶች መምጣት ከጥንታዊ የግሪክ ቃል በትርጉም ውስጥ የደበዘዙና ብሎም የጠፉ ቃላቶች!!! 11/26/2019
ለእናንተ የእግዚአብሔር መንግሥት ምስጢር እንድታውቁ ተሰጥታችሃል። ያስታውሱ ጌታ ለደቀመዛሙርቱ አንድ ምስጢራዊ የኮነ መንፈሳዊ ፍንጣሪን ብርሃን በቃሉ ውስጥ ያበራላቸዋል ፣ ይህን አንድ ምሳሌ ካወቁ ሁሉንም ምሳሌዎች ያውቃሉ። የማርቆስ 4/13 አላቸውም። ይህን ምሳሌ አታውቁምን? እንዴትስ ምሳሌዎችን ሁሉ ታውቃላችሁ? Do you not discern and understand this parable? How then is it possible for you to discern and understand all the parables? ይህንን መንፈሳዊ መመርያ የሚያውቁ ከሆነ እርሱ መንፋሳዊ መሆኑንና መንፈሳዊ መምጣቱ ምስጢር ያውቃሉ ፡፡
፩፣ ፓሮሴሲያ [ህልውና፤መገኘት]PAROUSIA.[ presence] ይህ ቃል በቅዱስ ቃሉ [አዲስ ኪዳን] ሃያ አራት ጊዜ ተጠቅሷል ፡፡ ቃሉ የተገኘው ከPAREMI ከሚለው ግስ verb የመጣ ሲሆን ፍቺው [በእጅ ነው at hand] [መገኘት ማለት ነው to be present] ይህም [መገኘቱን] የሚያመለክተው ነው ፡፡ ይህ ስም (ሰዋሰው)noun የመጣውን በህልውናው መገኘቱን ያሳያል the actual personal presence of the one who comes፡፡ “ለጌታ መምጣት ታገሱ Be patient unto the COMING”
[ህልውና፤ መገኘት] ( ያዕቆብ 5፡7ፓሩሲያ የሚለው የግሪኩ ቃል የአንድን ሰው ገና መምጣት ሂደትን የሚያሳይ ሳይሆን ወይም የወደፊት መምጣትን በጭራሽ አይጠቁምም ፣ ነገር ግን ቀድሞውኑ የመጣውን ሰው መኖሩን ያሳያል።
“እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ለጌታ መምጣትፓሮሴሲያ [ህልውና፤መገኘት]PAROUSIA.[ presence] ታገሡ። ገበሬ መሬቱ መልካምን ፍሬ እስከሚሰጥ ድረስ እንዴት እንደሚታገሥ፣ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እንዴት እንደሚጠባበቅ አስተውሉ።ያዕቆብ 5፡7”
እግዚአብሔርን እንወቀው፤ የበለጠ እናውቀውም ዘንድ እንትጋ፤ እንደ ንጋት ብርሃን፣ በእርግጥ ይገለጣል፤ ምድርን እንደሚያረሰርስ የበልግ ዝናብ፣ እንደ ክረምትም ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።”ትንቢተ ሆሴዕ 6:3
Be patient (long-passioned; slow to rush), then, brothers, as long as the Lord’s being alongside (or: until the Lord’s [= Yahweh’s] presence). Consider! The worker of the land repeatedly receives (takes into his hands) the precious fruit of the land, being patient (slow to rush) upon it while (as long as) it may receive early and latter (late) rain. James 5:7 JMT
፪ ፣ APOKALUPSIS። [unveiling ተከድኖ የነበረን ነገር መግለጥ] ይህ ቃል APOKALUPTO ከሚለው ግስ የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “መክፈት to uncover ልክ መሶብን እንደ መክፈት ያህል አክንባሎውን በማንሳት መክፈት፤ሽፋኑን ለማንሳት የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ሽፋኑን በማንሳት ወይም በመግለጥ በሽፋን ምክኛት ተሰውሮ የተደበቀ ሰው ይፋ መደረጉ ነው ያሳል፡፡ ራዕ 1፡1 ጌታ ሲናገር “መጽሐፍት ሁሉ ስለ እኔ ይናገራሉ” በየትኛውም ቦታ በ እግዚአብሔር ቃል ውስጥ ወደ የትም ብትሄዱ የእየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ሆኖ ታገኙታላችሁ። ዮሐንስ ራዕይ እራሱ ተብሎ መሰየም የነበረበት የየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ነው። Rev 1/1 The Revelation of Jesus Christ….. [Revelation ]602 apokalupsis ap-ok-al’-oop-sis from 601; disclosure:–appearing, coming, lighten, manifestation, be revealed, revelation. see GREEK for 601 ይህ ክርስቶስ ተከድኖ ያለው በልጆቹ ውስጥ ነው። l ልክ ማእድ የያዘ መሶብ አክንባሎውን[ክዳኑን] ብድግ ብታደርጉት የተከደነው ማእድ ሁሉወደ እይታ እደሚመጣ ሁሉ ክርስቶስም ከተሸፈነበት መቅደሱ ቀስ በቀስ እየተገለጠ ነው። ራዕዩ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንደሆነ በመንፈሳዊ ክብሩ የሚያስተምር መጽሐፍ ነው። በሁሉም መንፈሳዊ ክቡራዊነቱ ይገልጠው፤ በሙላትነቱ ይገልጣል፤ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ውስጥ በመንፈስ ቅኔ ወርቅና ሰም ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስን ታገኛላችሁ እርሱ ራሱ የእግዚአብሄር ክብር መገለጥ ነውና። የራዕይን መልእክት የሚያነብ ልብ በሚያነበብበት ጊዜ በእያንዳንዱ ገጽ ፊቱን ያያል በእያንዳንዳቸው መስመር ከክርስቶስ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ካላየን የሚታያየው ሁሉ ከንቱ ነው። ነገር ግን አንድ ሰው ከስጋ ድካም ወደ መንፈስ ብርታት ወደ ጌታ ዘወር ሲል የስጋ መሸፈኛው ይወገዳል።
የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ “የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ (በመገለጥ)REVELATION (unveiling) 1 ጴጥሮስ 1፡13
3 ፣ ኢፓፊንያ EPIPHANEIA. ይህ ቃል በአዲስ ኪዳን ስድስት ጊዜ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ተጠቅሶ ይገኛል ፡፡ በአንድ ነገር ላይ ማብራት ፤ማንጸባረቅ፤ማብራት to shine ፣ ወደ ብርሃን ማምጣት bring to light ፣ [መታየት to appear] [ግልፅ መሆን ፤ማሳየት፤ ማንፀባረቅ to manifest] ከሚያመለክተው ነው። ስም (ሰዋሰው)noun የመጣው ቃሉ [መገለጥ manifestation ወይም ብሩህነት brightness] አመልካች ነው። ልክ ከዋክብት በህልውናው ከነብርሃኑ እዚያው ቢሆንም በቀንትር ማይታይ ሆኖ ውሎ ድንገት በሌሊት በጨለማ መካከል ፍንትው ብሎ እያፈነጠቀ የመገለጡን የሚያሳይ ነው ፡፡ ይህ ቃል በጌታ መምጣት በሚገለጠው ክብር ወይም ግርማ ለማሳየት ጥቅም ላይ ውሏል ፡፡ “ 2ኛጢሞ 1:10 አሁን ግን ሞትን ደምስሶ በወንጌል አማካይነት ሕይወትንና ኢመዋቲነትን ወደ ብርሃን ባወጣው በመድኀኒታችን በክርስቶስ ኢየሱስ መምጣት [EPIPHANEIA. በአንድ ነገር ላይ ማብራት ፤ማንጸባረቅ፤ማብራት to shine ፣ ወደ ብርሃን ማምጣት bring to light ፣ [መታየት to appear] [ግልፅ መሆን ፤ማሳየት፤ ማንፀባረቅ to manifest]] ተገልጦአል። 11እኔም ለዚህ ወንጌል የምሥራች ነጋሪና ሐዋርያ፣ አስተማሪም ሆኜ ተሾምሁ።
4 ፣ PHANEROO fan-er-o’-o ፋኔሮኦ፟፡ የተደበቀውን ወይም ያልታወቀን ነገር ለመግለጥ ወይም መግለፅ ሲሆን ማለትም የግድ መገኘትን ብቻ የሚያሳይ ሳይሆን ግንዛቤን አመልካችም ነው፣ ይህም በቃላትም ይሁን በድርጊት ወይም በሌላ በማንኛውም መንገድ የተደበቀውን ወይም ያልታወቀን ነገር ለመግለጥ ያለውን ይገልጻል 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡2 When He shall appear [PHANEROO , become apparent], we shall be like Him” 1 John 3:2 ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።
5, ERCHOMAI er’-khom-ahee ኤርሆ፟ማይ፤ እየመጣ ያለው the actual act of coming ያለማቋረጥ የመጪውን የአሁን የመምጣት ክስተት ያመለክታል። ይህ ቃል እንደ ፓራሲያሲያ PAROUSIA የመጣውን የሚያሳይ ሳይሆን የመጪውን ያለማቃረጥ የመምጣት ክስተት ለማሳየት ይጠቅማል ፡፡ እነሆ እሱ ያለማቋረጥ (በተደጋጋሚ (በተለምዶ)) ከደመናዎች ጋር እየመጣ ነው። ራዕይ 1፡7 “Behold, HE COMETH (is in the act of coming) with clouds” (Revelation 1:7 Consider (Lo; Behold)! He is continuously (repeatedly; habitually) coming WITH the clouds, and every eye shall see Him, even which ever of YOU folks pierce (or: pierced) Him. And all the tribes (people‑groups) of the Land (or: territory; earth) shall beat themselves (strike their breasts in grief or repentance) upon Him. Yes! It is so (Amen)! JMT
6 ፣ HEKO hay’-ko ሄይኮ፤ to have come መምጣቱን, have arrived መድረሱን, be present መገኘቱን፤ ይህ ቃል የተወሰነ ቦታ ላይ የመከሰቱን ወይም የመድረሻ ነጥቡን ያጎላል ፡፡ ነገር ግን እስክመጣ ድረስ ያላችሁን ጠብቁ “Hold fast till I COME (to you)” (Revelation 2:25
በሁሉም የመምጣቱ የግሪክ ቃላት መካከል ያለው ልዩነት በቀላሉ ማስተዋል ይቻላል። አንድ ሰው ይህን ካስተዋለ ያለማቃረጥ በመንፈስ ክብሩ የመምጣቱን፣ እየመጣ መሆኑን፤ ወደ ፊትም ያለማቃረጥ የሚመጣ መሆኑን ማስተዋል ይጀምራል። ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። የመጨረሻው አዳም ክርስቶስ ኢየሱስ ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ከሆነ ሰነበተ። ጌታ አሁን መንፈስ ነውና መንፈስ የሆነውን ጌታ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡17 ጌታ[ክርስቶስ ኢየሱስ ] አሁን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።2Cor 3፡17 Now the Lord is that Spirit” if even we have intimately, by experience, known Christ ([the] Anointed One) according to (down from) flesh, nevertheless we now (in the present moment) no longer continue [thus] knowing [Him] by intimate experience.
አንድን የእ/ር ልጅ ከተለመደው ተፈጥራዊ የስጋ እይታ በክርስቶስ አእምሮ መንፈሳዊ መሆኑን ተገንዝቦ ከስጋ ድካም ወደ መንፈስ ብርታት ዘወር ብሎ የቃላቶቹ ፍቺ በመገንዘቡ ስለ ክብሩና ስለ ታላቅነቱ መገለጥ፤መከኘት፤ መከሰት፤ ወዘተ… ስለሚያመለክቱ በተጻፈው ቃል ላይ ተናጋሪው መንፈስ የሆነው ጌታ ምን ማለት እንደሆነ ለማስተዋል ያስችለዋል ፡፡ እነዚህ ቃላት በምንም መንገድ ተመሳሳይ የሆነ መምጣቱን የሚያሳዩ አንድ ዓይነት ትርጉም የላቸውም ፡፡ ለምሳሌ ፣ ሁለቱም EPIPHANEia እና PAROUSIA የሚለው ቃል በጣም በሚታወቁ ጥቅሶች ውስጥ ብናይ በአሮጌ ትርጉም “2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2፡8 በዚያም ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በአፉ መንፈስ የሚያጠፋው፥ ሲመጣም በመገለጡ የሚሽረው ዓመፀኛ ይገለጣል። ይለዋል Then shall that Wicked be revealed, whom the Lord shall consume with the Spirit of His mouth, and shall destroy with the BRIGHTNESS (EPIPHANEIA) of His COMING (PAROUSIA)
የእንግሊዝኛውን ፍጹም ባይሆንም በተቀራራቢ ትርጉም ብናየው። “በዚያን ጊዜ ጌታ በአፉ መንፈስ የሚያጠፋው ክፉው ይገለጣል ፣ በኃይሉ ብርሀን (ኤፌፒያንያ EPIPHANEIA)BRIGHTNESS መምጣት (ፓሬሴሲያ)COMING (PAROUSIA)” ሆኖ እንደራዋላን።
“የህልውናው መገለጥ The MANIFESTATION of His PRESENCE ”
“የክርስቶስ መምጣት” ግልፅ ምሳሌ የበዓለ ሃምሳ ቀን ነበር ፡፡ በበዓለ ሃምሳ ቀን ክርስቶስ እንደ አፅናኙ እንደገና መጣ-
ማንም ሲናገር እንደ እ/ር ቃል ይናገር! እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ አጽናኙ ነው። በሌላ አነጋገር እራሱ መንፈስ ቅዱስ ነው። የግሪኩ ቃል ፍቺ ይህን ያረጋግጥልናል። በእርግጥ አማርኛችን ጨምሮ ብዙ ትርጉሞች እውነቱን እንዳናይ የራሳቸው የከለላ ድርሻ አበርክተዋል። አባቶቻችንም የደረሱበትን ብቻ አሳውቀውን ነበረ።
እውነት ወይም ምስክርነት የሚፀናው ወይም የሚመሰረተው በሁለት ወይም በሰዎስት ነውና ተጨማሪ የእ/ር ቃል ያስፈልገናል። የዮሐንስ ወንጌል 8:17
ጌታ ምን እንዳለ አስተውሉ። ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ #ወደ #እናንተ #እመጣለሁ። መጣ እሺ ከዛስ በኋላስ መንፈስ ስለሆነ ምን አለ? #ዓለም #አያየኝም፤#እናንተ ግን #ታዩኛላችሁ፤ በዚያን ግዜ ምን ይከሰታል? #ማወቅ ይከሰታል። ‘እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።’ ሃይሉ ያለው #ማወቁ ላይ ነው ዓለም አያየኝም፤እናንተ ግን ታዩኛላችሁ[ ማነው እሱ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ !]፤’ ቅኔውን ሲፈታው ስለራሱ እንጂ ስሌላ እያወራ እንዳልሆነ አስተዋላችሁ? ።
የዮሐንስ ወንጌል 14/18 ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። 19ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ። 20እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።
“I will NOT leave you abandoned[comfortless], or send you off as orphaned ones. I am repeatedly (habitually) and progressively coming toward you [in the form of the comforter and spirit of truth] men. (Jn 14:18Open in Logos Bible Software (if available)
ጌታችን ምን እንዳለ በግማሽ ሳይሆ በሙሉ ትኩራታቹሁ አሁን አስተውሉ። መንፈስ ማን እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሆነ ግልጽ ያደርግልናል። የስላሴ 3ኛ አካል ነው ?ጌታ እራሱ ይናገር።
20እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን[አጽናኙ በሚመጣበት ቀን] ታውቃላችሁ።
“IN THAT DAY
[the day when the comforter comes]
you shall know that I am in My Father, and you in Me, and I IN YOU” (Jn 14:20Open in Logos Bible Software (if available)
“John 14/28 Ye have heard how I said unto you, I am going, and I AM COMING TO YOU” የዮሐንስ ወንጌል 14/28 እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ።
አስተዋላችሁ ጌታ ምን አለ ? I am going, and I AM COMING TO YOU! እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ!
አሁን እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ ተብሎ መጠራቱን በእ/ር ቃል እናረጋግጥ። another Comforter[ጳራቂላጦስ] ሌላ አጽናኝ[ጳራቂላጦስ] ይሰጣችኋል ያለው ጳራቂላጦሱ ማን እንደሆነ እናያለን።
የዮሐንስ ወንጌል 14/15-16 ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ[ pray] ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.] ይሰጣችኋል፤
John 14/15 If ye love me, keep my commandments.16 And I will pray the Father, and he shall give you another Comforter[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.], that he may abide with you for ever;
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2
1 ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.] አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
1John 2/1 My little children, these things write I unto you, that ye sin not. And if any man sin, we have an advocate[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.] with the Father, Jesus Christ the righteous: ያውላቹ እንግዲህ ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ጳራቂላጦስ አጽናኙ እራሱ ነው። በተረፈ በጌታ ፍቅር ሰላም ለአንተ ይሁን። የመለካከት ልዩነት በሃዋርያትም ዘመን ንርበረ ሁሉም የእ/ር ልጆች ናቸው። በመጨረሻ ደስ የሚለው እ/ር የሚያመጣን ቦታ አለ እሱም ሁላችንም የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ስራውን እየሰራ ነው ለክርስቶስ መንፈሳዊ አካል ሕንጻ ፍጹማን ያደርገናል። ክብር ለቅዱስ ስሙ ይሁን።
እስቲ ልዩ ልዩ አመጣጡን በጥቂቱ በመንፈስ እንቃኝ። በማርቆስ 13፡26 እሱ ከደመናት ጋር ይመጣል He comes with CLOUDS፡፡ የክርስቶስ ምስክሮች #እንደ #ደመና ተመስለዋል እነዚህ በዙሪያችን ካሉልን የእምነታችንንም ደራሲ፤ ራስና ጀማሪም ፈጻሚውን ኢየሱስን እነሆ እንመልከተው። great a cloud of witnesses። ወደ ዕብራውያን 12፤1-2 እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች #እንደ #ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ በማቴዎስ 24:27 እርሱ እንደ መብረቅ መብረቅ ሆኖ ይመጣል He comes as LIGHTNING [መብረቅ በጨለማ ላይ አብርቶ ጉድህን በብርሃኑ ሃይል አብርቶ አሳይቶ ስወር ይላል] በራእይ 16:15 እርሱ እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል። He comes as a THIEF በማቴዎስ 25: 6 እርሱ እንደ ሙሽራ ሆኖ ይመጣል He comes as the BRIDEGROOM። በራእይ 22:16 እና 2:28 እርሱ እንደ የንጋትንም ኮከብ ሆኖ ይመጣል። He comes as the MORNING STAR. በሚልክያስ 4: 2 እርሱ እንደ የጽድቅ ፀሐይሆኖ ይመጣል። He comes as the SUN OF RIGHTEOUSNESS ARISING. በፊልጵስዩስ 3: 20-21 እርሱ በትንሣኤ ኃይል ውስጥ ይመጣል። He comes in RESURRECTION POWER. በ2 ተሰሎንቄ ም1፡7 እና 8 እርሱ መንፈሳዊ ስልጣን ከተሰጥቸው ከመለክትኞቹ ጋር ከመንፈስ ግዛት እንደ እሳት ነበልባል ይመጣል ፡፡ With his mighty messengers, He comes in FLAMING FIRE በሚልክያስ 3: 1-3 እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ይመጣል ይገለጣል አዎን እነሆ እርሱ ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው መጥቶ ይቀመጣል፥ በጎነት እንዲናገሩ የተመረጡን ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን እና ቡዱኖች አዎን እነሱም ልጆችን ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ። He comes to His priesthood company as REFINER’S FIRE and FULLER’S SOAP።
በ1 ተሰሎንቄ 4 16-17 ውስጥ በአየር ውስጥ ይመጣል He comes IN THE AIR። በሆሴዕ 6: 3 እና ያዕቆብ 5 7-8 እንደ ዝናብ ይመጣል ፡፡He comes as the RAIN በራእይ 19:11 እና 14 እርሱ በነጭ ፈረስ ላይ ይመጣል። He comes on a WHITE HORSE በማቴዎስ 25: 31-34 እንደ ንጉሥ ይመጣል። He comes as KING በ1 ኛ ጴጥሮስ 5፡4 እንደ የእረኞችም አለቃ ወይም አዛዥ እረኛ ሆኖ ይመጣል፡፡He comes as the CHIEF SHEPHERD በማቴዎስ 16:27 እርሱም ከመላእክቱ[GREEK፡ aggelos ከመለክቶኞቹ messenger] ጋር ይመጣል። He comes WITH HIS ANGELS[messengers]. በይሁዳ 14 እርሱ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር ነው የሚመጣው። He comes WITH HIS ten thousands of his SAINTS. በዮሐንስ 14:18 እርሱ ለቅዱሳኑ ይመጣል። He comes TO HIS SAINTS. በ2 ተሰሎንቄ ምዕራፍ 1፡10 እርሱም በቅዱሳኑ ውስጥ ይመጣል፡፡ He comes IN HIS SAINTS. በይሁዳ 14 እና 15 እርሱም በፍርድ ይመጣል። He comes in JUDGMENT በራእይ 22:12 ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ሁሌ ሊሰጠው እርሱ ዋጋ በእጁ ይዘ ይመጣል. He comes WITH REWARDS የመምጣቱ ልዩ ልዩ ክብር ብዛ ተነግሮ አያልቅም በ1 ተሰሎንቄ 4: 15-17 በመላእክት አለቃን ድምፅ በእግዚአብሄር መለከት ጩኸት ታጅቦ ይመጣል ፡፡ He comes with a shout, with the voice of the archangel, with the trump of God በተጨማሪም ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ይመጣል፡፡ He comes to the Mount of Olives። ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል። He comes to His temple ፣ በክብር ይመጣል He comes in glory ፤ እርሱ እንደ ጌታ ይመጣል He comes as Lord ፤ እርሱ በመንግሥቱም ይመጣል He comes in His Kingdom ፣ እንደሚታደሱ ወቅቶች ይመጣል He comes as seasons of refreshing, ፣ ወዘተ … ወዘተ ነው ፡፡ የጌታ መምጣት በብዙ መገለጦች ውስጥ እርራሱን በማሻሻል የሚገለጥ አይደለም ግን ታድያ ታዲያ ቀደም ሲል ከተዘረዘሩት ብዙ ማጠናከሪያ ቃላቶች የትኛው ነው ሁለተኛው ምጻት ወይም የሚመጣው? በቅዱሳት መጻሕፍት የሚነግረኝ ይኖር ይሆን?… የትኛው ነው ዳግም ምጻት?
እርሱ “ወላጅ አልባ ልጆች ይመስል አልተዋቹሁም ፤ እኔ እመጣለሁ” ማለቱ “ሁለተኛው መምጣት” ነው ማለት ነው? ፡ወይም “እነሆ እኔ እንደ ሌባ እመጣለሁ?” የሚለው ነው? ወይስ “እንደ ዝናብ በምድር ላይ እመጣለሁ” ሲል የእርሱ ዳግም ምጽዓት ነው ፡? ” ወይስ እንደ መብረቅ ፣ ወይስ እንደ የጽድቅ ፀሐይ መምጣቱ፣ ወይስ እንደ ሙሽራ መምጣቱ ፣ ወይም እንደ ንጉሥ ፣ ወይም ከቅዱሳኑ ጋር ፣ ወይም ለቅዱሳኑ ፣ ወይም ለቅዱሳኑ መምጣቱ የትኛው ነው የዳግም ምጻቱ?
ጳውሎስ ኢየሱስ “በጩኸት” እንዲሁም “በመላእክት አለቃ ድምፅ” እና “በእግዚአብሔር መለከት” እንደሚመጣ ተናግሯል። ጌታ ኢየሱስ በአንጻሩ “እነሆ ፣ እኔ እንደ ሌባ እመጣለሁ” አለ በእርግጥ የትኛው ፋራ ሌባ ነው መለከቶችን አይነፉም እና እየጮኸ የሚመጣው?
ኢየሱስ በደብረ ዘይት ተራራ በሚወጣበት ጊዜ መለከቶችን አልነፋም ፣ መላኮቹ ወይም መልእክተኞቹ ግን “በእንደዚያው ዓይነት” እንደሚመጣ ነግረው ነበር፡፡ እንደ ዝናብ እና እንደ እሳት በተመሳሳይ ጊዜ ጌታ ቢመጣ ዝናቡ እሳቱን ያጠፋው ይሆንን?
Jesus Christ has given His people the power to sit with Him in heavenly places far above all principality and powers . . . we are already caught up in Him. . . it remains for us to yield to the indwelling Holy Spirit so that which has been given can now become a reality in our daily walk. Let us avoid foolish gassings.
if you still think heaven is a piece of real estate “out there” in space somewhere, rather than within your own thinking (within your heart and mind – i.e. – a state of being), then your road to enlightenment has reached an impasse which requires a total paradigm shift in your thinking. GOD IS LOVE. ቢኒ።
