
መለያየት ዘረኝነት ነው። የስጋ ስራ ነው። የእግዚአብሔር ህግ የሚከለክላቸውና የሚፈቅዳቸው አሉ። ህግና ነብያት ሁሉ በፍቅር ተንጠልጥልዋል። በፍቅር የሚኖር ህግን ሁሉ ፈፅመዋል። ክርስቶስ የህግ ፍፃሜ ነው። በክርስቶስ መኖር በፍቅር መኖር ነው። ገላትያ5:18 በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም።
19 የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥
20 መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥
21 መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
22 የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
23 እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም