Discussion Quotes: እ/ር መንፈስ ሆኖ ሳለ ነፍስ አለው።





Discussion Quotes: መንፈስ ከፍፁም ከማይጠፉው የእግዚአብሔር ቃል የተወለደ ማነቱ የእግዚአብሔር ቃል የሆነ የእግዚአብሔር ዘር ነው። ነፍስ በሙልአት በመንፈስ ፈቃድ ስትወረስ እረፍት ታገኛለች። መንፈስ ነፍስን በፍቅሩ ሁሌ ይጠራታል ደካማ ሸክምዋም የከበደ ነውና፥ ወደ እኔ ነይ፥ እኔም አሳርፍሻለሁ። ብሎ ውድዋ በፍቅር ይስባታል።
የመንፈስ ቀሊል ቀንበር በላይዋ ትሸከም ዘንድ ከእኔ ተማሪ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ነፍስ ሆይ ዕረፍት ታገኛለሽ ይላታል። እስዋም በመንፈስ ዘንድ የሚወጣው ህያው ቃል እለት እለት ያድናታል። ፍፁም አንድ እስክትሆን ሂደቱ ህያው ሆኖ ይቀጥላል። ተዘልሎ በእረፍት መቀመጥም ሊኖር ይችላል። ያቆብ 1:21 ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ #ነፍሳችሁን#ማዳን#የሚችለውን#በውስጣችሁም(በመንፈሳችሁ) #የተተከለውን#ቃል በየዋህነት ተቀበሉ። ቢኒ።


Selam Degu የነፍስ ሚናዋ ምንድነው ?
የመንፈስ ሚናዋ እንዲሁ ?የሁለቱስ መገኛ የት ነው?

Discussion Quotes: እ/ር መንፈስ ሆኖ ሳለ ነፍስ አለው። ወንድም ቢኒ 01/14/2019 Selam Degu እህታችን ጥሩ ጥያቄ አንስተሻል ይህን ሃሳብ ለመመለስ ከምንጩ ጀምረን በጥልቀት ማየት የግድ ሊለን ነው። በቅድሚያ የፍጥረት ምንጭና መገኛ የሆነው እግዚአብሔር ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር ብሎ ሲፈጥረው ሰው እሱን እንደሚመስል ምንም ጥርጥር እንዴሌለው ለሁሉም ግልጽ ነው ብዮ አስባለሁ። ጌታ በስጋ ወራቱ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የዮሐንስ ወንጌል 4፡24 ሲል ስለእውነተኛ መልኩ ቅልብጭ ያለ መልስ ሰጥቶናል። በእ/ር ቃል ያሉና ሊታዩም ላይታይም ቢችሉም ሁለት ፍሬ ሃሳቦችን አብረን ብናይ ይጠቅሙናል ብየ አስባለሁ። እ/ር መንፈስ ሆኖ ሳለ በተፈጥሮውና በባህርዩ ውስጥ ነፍስ እንዳለው ሊታወቅ ይገባል። ነፍስ በመጽሃፍ ቅዱስ የሴት ገጸ ባህርይ ስጥዋት በተደጋጋሚ ጽፎላታል። ሌላው ተያያዥ ሃሳብ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ሲለን ምን ማለት እንደሆነ በሚቀጥልለው እንተነትነውና በቃሉ ውስጥ ልናስተውለው ተገቢ የሆነ ክፍል ነው። በቅድሚያ ከእ/ር ቃል እ/ር መንፈስ ሆኖ ሳለ ነፍስ አንዳለው ማስተዋል አለብን። ማንም ሲናገር እንደ እ/ር ቃል ይናገር ነውና በእ/ር ቃል በትኩረት አስተውለን እንየው። የክብርን አባት እርሱን በማወቅ የሚመጣው የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲበዛልን ጸሎቴ ነው።
ኦሪት ዘሌዋውያን 26፡11 ማደሪያዬንም በእናንተ መካከል አደርጋለሁ #ነፍሴም አትጸየፋችሁም።Lev 26
11 And I will set my tabernacle among you: and #my #soul shall not abhor you.
ኦሪት ዘሌዋውያን 26፡30 የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ የፀሐይ ምስሎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ #ነፍሴም ትጸየፋችኋለች።Lev 26፡30 And I will destroy your high places, and cut down your images, and cast your carcases upon the carcases of your idols, and #my #soul shall abhor you.
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2:35 የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፥ በልቤም #በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑን ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል።1Sam 2:35 And I will raise me up a faithful priest, that shall do according to that which is in mine heart and in #my #mind: and I will build him a sure house; and he shall walk before mine anointed for ever.
ትንቢተ ኢሳይያስ 42፡1 እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ #ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።Isa 42፡1 Behold my servant, whom I uphold; mine elect, in whom #my #soul delighteth; I have put my spirit upon him: he shall bring forth judgment to the Gentiles.
ትንቢተ ኤርምያስ 5፡9 በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር #ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?
የማቴዎስ ወንጌል 12፡18 እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ #ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል።
Matt 12፡18 Behold my servant, whom I have chosen; my beloved, in whom #my #soul is well pleased: I will put my spirit upon him, and he shall shew judgment to the Gentiles.
መጽሐፈ ምሳሌ 6፡16 እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም #ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች
17 ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
18 ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
19 በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።
ኮንኮርዳንስ ብታዩ እ/ር ነፍስ እንዳለው በብዙ ቦታ በቃሉ ውስጥ ታስተውላላቹሁ። እ/ር መንፈስ እንደሆነ እየሱስ እንዳሳወቀን ስቶቻችሁ ታስተውላላችሁ?እ/ርስ ሰው እንዳልሆነ ስቶቻችሁ ታውቃላችሁ ። እ/ር መንፈስ እንደሆነ ነፍስ እንዳለው ስንቶቻችሁ አስተዋላችሁ?መንፈስ ነፍስ እንዳለው ታስተውላላችሁ ? ከኔ ጋር ናችሁ ?1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች2፥6 በበሰሉት መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፥ ነገር ግን የዚችን ዓለም ጥበብ አይደለም የሚሻሩትንም የዚችን ዓለም ገዦች ጥበብ አይደለም፤we speak wisdom among them that are perfect
ሌላው በመቀጠል ማየት ያለብን ዘፍጥረት 1:26 ላይ በእ/ር መልክ ፈጠረው ሲል የእ/ር መልክ ምንድን ነው? የሚለውን ማስተዋል አለብን። ሁሉን መርምሩ ስለሚለን ቃሉን ስንመረምር ቃሉ ለሁለት ወይም ለ3 እግዚያብሄሮች የንደተጻፈ እንደሚረዱት ወገኖች በአንድ ጥግ ቲፎዞ ሆነን የምንመረምር አይሁን። ዘፍጥረት 1:26 ሁሉም እንደሚሉት እኛ ሲል 3 ስላሴን አይደል እንዴ የሚያሳየው የሚለው ሊነሳብን ይችላል? እኛ የሚለው ቃል 3ቱ ሥላሴን ወይም 3ቱን እግዚያብሄሮች የሚያሳይ መሆኑን በምን እርግጠኛ ትሆናለህ? እኛ 2ለትም ለ3ትም 4ትም 5ትም ከዛም በላይ የሚያሳይ የብዙ ቁጥር መግለጫ ሊሆን ይችላልና ብንል መልስ የለምና።
ይህ ጥቅስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለ ሥላሴ በአብያተ-ክርስቲያናት ክርክር ውስጥ ዋናው ነጥቡ ተደርጎ ይነሳል። አንድ ጊዜ አምላክ ሥላሴ እንደሆነ አድርገው ከተረዱና ካወቁ በኋላ እንደገና በእግ/ር ቃል ለመታረም ለብዙዎች ጭንቅ ነው። በውኑ እነሱ በትክክል 3 እግዚአብሔር ሲሉ እንደ ቃሉ ተረድተዋልን? መንፈሳዊ ሰው ሁሉን ይመረምራልና እንደመንፈሳዊ ሰው ለራስህ ቃሉን በቃሉ በእውነት መንፈስ በመታገዝ ቅዱስ ቃሉን በማስተዋል መመርመር መልካም ነው። እርሱን የሚፈልጉት ያገኙታል የጻድቃንን መጠበቅ ሳያሳፍር ደግሞም በሃይል ታላቅ ቢሆንም ማንንም ሳይንቅ የአምላክነቱን ጥበብን ለጠቢባን የአምላክነቱን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣልና ለማያስተውሉ ግን የአምላክ እውቀት ተከልክላለች ለዝንጉዎችም ተሰወራለች።
ወደ ፍሬ ሃሳቡ ስንመለስ ይህ ቃል የእግዚአብሔርን ሙሉነት የሚያስረዳ በድርብ ክብሩ እራሱን የገለጠበት ነው እላለሁ።
የእግዚአብሔር አምሳያ ድርብ ስለሆነ ወንዶችና ሴቶች መፍጠሩ የሱ መልክ ነው። የጥንት የስነ-መለኮት ምሁራን በስላሴ ላይ በጣም ትኩረት ስላደረጉበትት በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 የመጀመሪያ ምዕራፍ ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ላይ ዋናን ሃሳብ ሳያስተውሉት ቀርተዋል። “ከዚያም እግዚአብሔር ሰው ሰውን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር አለ. ” እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ።
እንደምናስተውለው የእግዚአብሔር መልክ አምሳል እና አምሳያ በዚህ ቃል መሰረት የወንድን እና የሴትን ገጽታ ያካትታል። ይህ ባይሆን ኖሮ ምድራዊው የእግዚአብሔር አምሳያ ተብሎ የፈጠረው ሰው አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት የያዘ ባለ አንድ ፆታ ብቻ ሆኖ ይፈጥረው ነበረ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በመልኩ? በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ;;
በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ? ግልጽ ነው። ።Gen 1 verse 27, “And God created man in His own image, in the image of God He created him; male and female He created them.” The image and likeness of God, then, includes male and female aspects of God. If this were not so, then the earthly image of God would express just one sex, either male or female.
በእርግጥ የጥንት የነገረ-መለኮት ሙሁራኑ አምላክን በአዎንታዊነት በድርብ ክብሩ ለመግለጽ እውነትን ለማሳየት አልቻሉም። እግዚአብሔር በራሱ ሙሉ ስለሆነ ማንም ሳያግዘው መለኮታዊ ሙልአቱን ተጠቅሞ ማዘጋጀት እንደሚችል ከገለፁት እየተገዘቱ መገለል እንዳይደርስባቸው እውነትን መቅበር ይመረጣሉ።ሌላው ችግር ብዙዎቹ የጣዖት አምልኮ አምላኪዎችና አማልክቶች የሴት አገላለጾች ስለሚጨምሩ ሁሉ እርስ በራሱ እየተፈራራ ችግር ነበረ።
በቁጥር 28 እግዚአብሔርም ባረካቸው ብሎ እንደ አንድ መልሶ ይጣረዋል። 28 እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።
ይህን ለማስተዋል በስሞቹ ላይ ጥናት ብታደርግ ከመጀመርያው የተናገረውና ለሙሴ ህግ የሰጠው ማነው? ህግን ለሙሴ የሰጠው እራሱን “ያህዌ (Yahweh)” ብሎ በሚነደው ቁጥቋጦ ጠርተዋል። “ያህዌ” የሚለው የፈጣሪ ስም እ/ር መጀመርያና መጨረሻ የሌለው ዘልአለማዊና እራሱን በራሱ ህላዌ(ህልውና) [self-existent] ያለው መሆኑን የሚያመለክት ነው። ይህ በአባትነት ባህርይ እ/ር እራሱን ለፍጥረት የገለጠበት 10ቱን ትእዛዛት በመስጠት ስነ-ስርአት ያወጀበት ባህርዩ ነው። ይህ ያህዌ አዲስ ስም ነበር ሲያስተዋውቃቸው። በዚህ ስም ለአብርሃም ለይሳቅ ለያቆብ አልተገለጣላቸውም ነበር። “’እግዚአብሔርም (Hebrew፣ ኤሎሂም elohiym el-o-heem) ሙሴን አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) ነኝ። ሁሉን የሚችል አምላክ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውም። ‘ ዘፀአት 6:2-3 ፍጥረት ገና መፈጠሩ ስለነበር በእናታዊ የአመራር ዘየ እራሱን ሲገልጥ ይታያል። ኦሪት ዘፍጥረት መላት፤እንደአገባቡ፡ የፍጥረት ህግ፤ የፍጥረት ስር፤ የፍጥረት ምንጭ፤የፍጥረት መገኛ፤የፍጥረት ውልደት፤ የፍጥረት ልደት ማለት ነው።
እንዳትረሳ አንዱ እ/ር ኤልሻዳይ፤ያህዌ ብሎ እራሱን ገለጠ ሁለት እግዚአብሔሮች አይደሉም አንድ እ/ር መሆኑን ማስተዋሉ መልካም ነው። የህግ ሰጪው ማንነት በዘፀ፤20:2 አስርሩን ትእዛዛት ሲሰጥ በህግ መቅድሙ ላይ ሲናገር ‘“ከግብፅ ከባርነት ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ (ያህዌ self-Existent በራሱ የሚኖር ። በራሱ ህልውና ያለው) እኔ ነኝ።” “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ። ‘ ዘፀአት 20:2-3”
ለአብርሃም ሲገለጥ እንደ ኤልሻዳይ አወቀው ‘አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ኤልሻዳይ” ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ፤ ‘ ዘፍጥረት 17:1 ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም የፃፈው ሙሴ ነው። ይህም ማለት እነ አብርሃም ያልበራለቻው ያህዌ የሚለው የእ/ር ስም ከገባው ቡሃላ የፃፈው ስለሆነ ያህዌ እያለ በእብራይስጥ ተጠቅሞበታል ኤልሻዳይ እና ያህዌ አንድ አምላክ እንደሆነ እናያለን ። “እኔ እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) ነኝ። ሁሉን የሚችል አምላክ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውም። ‘ ዘፀአት 6:2-3።
በዚሁ ከቀጠልን ወደ ጠለቀ መንፈሳዊውቂያኖስ መግባታችን ስለሆነ እራሳችንን ሰብሰብ አድርገን እህታችን ወዳነሳቻው ሃሳብ መንደርደርያ ካገኘን ዘንዳ አንድ ነገር በመጽሃፍ ስናስተውል ነፍስ ሶል ሚናው በተለያየ ገጸ ባህርይ ቅያፈራረቀ ሲያስረዳን በአብዛኛው በአሽጭሩ የሚያዛምዳት minde will imotion disier አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ ክፍል እደሆነ እናውቃለን ይህንንም ከቃሉ ማስተዋል ይቻላል።
#በነፍስህ #ፈቃድም፤ መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 28፡9 አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ #የነፍስንም #አሳብ ሁሉ ያውቃልና፥ የአባትህን አምላክ እወቅ በፍጹም ልብና #በነፍስህ #ፈቃድም አምልከው ብትፈልገው ታገኘዋለህ ብትተወው ግን ለዘላለም ይጥልሃል።And thou, Solomon my son, know thou the God of thy father, and serve him with a perfect heart and with a #willing #mind ….
አስተዋላችሁ? *የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና፥ የአባትህን አምላክ እወቅ በፍጹም ልብና #በነፍስህ #ፈቃድም አምልከው ብትፈልገው ታገኘዋለህ ብትተወው ግን ለዘላለም ይጥልሃል።

#ነፍስ #ትመኛለች desireth መጽሐፈ ምሳሌ 13፡4 የታካች ሰው #ነፍስ #ትመኛለች አንዳችም አታገኝም የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች።Prov 13፡4 The #soul of the sluggard #desireth, and hath nothing: but the soul of the diligent shall be made fat. ስንቶቻችሁ እ/ር አይምሮ እንዳለው በቃሉ ታስተውላላችሁ? ፈቃድ እንዳለውስ? ሰሜት እንዳለውስ? GOD gets angry እ/ር ይናደዳል
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡30 ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ #አታሳዝኑ።Eph 4፡30 And #grieve #not the holy Spirit of God, whereby ye are sealed unto the day of redemption.
#God #laugh ፣ #እ/ር #ይስቃል የሃጢያተኛው ቀኑ እንደደረሰ አትዋልና #እግዚአብሔር #በሰማይ #ይስቃል
#እ/ር #ደስ #ይሰኛል መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 3፡10 ሰሎሞንም ይህን ነገር ስለ ለመነ፥ ነገሩ #እግዚአብሔርን #ደስ #አሰኘው። እግዚአብሔርም አለው፦ ፍርድን ትለይ ዘንድ ለራስህ ማስተዋልን ለመንህ እንጂ ለራስህ ብዙ ዘመናትን ባለጠግነትንም የጠላቶችህንም ነፍስ ሳትለምን ይህን ነገር ለምነሃልና እነሆ፥
የመንፈስ ፍሬ ምን እደሆኑ ታውቃላችሁ የእ/ር መንፈሳዊ ስሜት ናቸው። አንድ ሰው ወንድም በሚሰማኝ ነገር ሳይሆን የምመላለሰው በእምነት ነው ሊል ይችላል። ዜና አለኝ ላንተ በሚሰማኝም እመለለሳለሁ ። መጽሓፍ በሚሰማህ እንዳት መላለስ በእምነት እንጂ እንደማይል አስተውላችሃል?መጽሃፉ ላይ የለም መጽሃፉ የሚነግረን በእምነት መየትን ነው። በእምነት አሻግሮ ማየትን እንጂ በሚሰማኝ እንዳልሆነ ነው የሚያስረዳን።
ወገኖቼ የእ/ር ሰላም ሚሰማህ ነገር ነው፤ The joy of the Lord is a filing የእ/ር ደስታ የሚሰማን ነገር ነው። የእ/ር ትእግስ የሚሰማህ ነገር ነው። በዛ በሚሰማኝ ሰላም፣ ደስታ፣ ትእግስ፣ እምነት፣ እመለለሳለሁ። በዛ ህያው የእ/ር መልካምነት የእ/ር አባቴና አምላኬ ንቃተ ህሊና በሂወቴ ባለ በዛ እምላለሳለሁ። የመንፈስ ፍሬዎች ከእ/ር imoton ጋር የተያያዙ ናቸው። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡17 የእግዚአብሔር መንግሥት #ጽድቅና #ሰላም #በመንፈስ ቅዱስም የሆነ #ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።
እ/ር መንፈስ ነው ሆኖም minde will imotion disier አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ በእርሱ ውስጥ በመፈራረቅ ሲገለጥበት በቃሉ ይታያል። አዎን እ/ር መንፈስ ነው ሆኖም ነፍስ አለው። ከማይጠፋው ዘር ከእ/ር የተወለደው አዲሱ ሰው መንፈሳችሁ ነፍስ አለው። አሮ ጌው ስጋዊው ሰው ነፍስ እንዳለው ታውቃላችሁ ?the mind of the flsh ስጋዊ አይምሮ ፣ መጽሓፍ ሲነግረን the will of the flsh የስጋ ፈቃድ ፣ምኞት አትፈጽሙለት ይለናል።

የስጋ ሰራ ምን እደሆኑ ታውቃላችሁ ?የስጋ ስሜት መገለጥ ፍሬዎች ናቸው።
የመንፈስም የስጋም minde will imotion disier የመንፈስ አይምሮ፣ የስጋ አይምሮ አለ፣ የመንፈስ ፈቃድም የስጋም ፈቃድ አለ፣ የመንፈስ ስሜት አለ የስጋ ስሜትም አለ፣ የመንፈስ ምኞት አለ የስጋ ምኞት አለ። እያንዳዳቸው የነፍስ ክፍል ናቸው (አሮ ጌው ስጋዊው ሰው ነፍስ አለው አዲሱ ሰው መንፈሳችሁ ነፍስ አለው።)
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡17 ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው። 1Cor 6፡17 But he that is joined unto the Lord is one spirit.
ወደ ጌታ ህብረት ስንመጣ አንድ መንፈስ ስሆን ወደ እ/ር የነፍሱ ፈቃድም እዋሃዳለሁ። አሁን የእ/ር minde will imotion disier አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ በመንፈሴ አለ ማለት ነው። በተመሳሳይ ጊዜ አሮጌው ስጋዊው ሰው ነፍስ አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ አሉ። ስንቶቻቹ እነዚህ ሁለቱ በውስጣችሁ ሲፈራረቁ አይታችሃል። እውነት ነው አሁን ችግሩን ለይተነዋል በያዕቆብ መልእክት 1፡7-8 ላይ A double minded (GR- soo-khos ነፍስ፣ ሶል) man is unstable in all his ways ሁለት አሳብ (አይምሮ ነፍስ) ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ነው ይለናል። ከእ/ር ጋር አንድ አለመሆን ወይም በፈቃዱ አለመወረስ ምን ማለት እንደሆነ አሁን ችግሩ ታየ !ሁለት ነፍስ ወይም አሳብ አይምሮ የሚዋልለውን ሰው ኧስተዋልነው እንደ ፔንዱለም ወዲህ ደዲያ ይወዛወዛል የቱን እንደሚጨብጥ ሚስጥር ሆኖበታል። የትኛውን እንደሚታዘዝ ግራ ይገባዋል ዛሬ ለመንፈሳዊው ሰው ነገ ለስጋዊው ሰው ያድራል በሁለቱ መካከል እተፈራረቀ ተወዲህ ወዲያ ይንገላታል ዛሬ ለዚህ ነገ ለዚያ ይታዘዛል ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ሲመኛኙበት፥ እርስ በርሳቸው ሲቃወሙበት፤ ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ ላይ እንደመውጣት ይሆንበታል ስለዚህም የሚወደውን ሊያደርግ አይችልም ይህም በህይወት አካሄድ ላይ የራሱ ትጽኖ ሊኖረው ይችላል።በያዕቆብ በሁላት ማንነት የሚወላውል ማንነት በቀድሞ ዘመንም ታይተዋል። መጽሐፍ ስለ ሮቤል ሲናገር የጸና እይታና አቃም ስለሌለውና በምግባሩም ስለረከሰ እንደውሃም ይዋልላል ለመሪነትም አይሆንም ሲለው እናስተውላለን። ኦሪት ዘፍጥረት 49:4 ያቆብ ሮቤልን ሲረግመው እናያለን፤ “እንደ ውኃ የምትዋልል ነህ፤ አለቅነት ለአንተ አይሁን፤” ሙሴ ግን መንፈሳዊ ስልጣኑን ሲለማመድ እርግማኑን ከሮቤል ላይ ሲያነሳለት ይታያል። ኦሪት ዘዳግም 33፡6 ሮቤል በህይወት ይኑር፥ አይሙት፤ሰዎቹም በቍጥር ብዙ ይሁኑ። እኛ ግን እንደውሃ አንዋልልም ነጠላ አይምሮ ነው ያለን በእ/ር መንፈስ ምስክርነት ላይ ቆመናል። አሜን።

አንድ ወንድም አንድ ግዜ ሲያስተምሩ እንዲህ አሉ። በእንግሊዝኛ ነው የሰበኩት እንደ ማስታውሰው አስቀምጠዋለሁ። “ወደ ሮሜ ሰዎች 12Rom 12፡1 እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው። 1 I beseech you therefore, brethren, by the mercies of God, that ye present your bodies a living sacrifice, holy, acceptable unto God, which is your reasonable service.
2 የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። 2 And be not conformed to this world: but be ye transformed by the renewing of your mind, that ye may prove what is that good, and acceptable, and perfect, will of God.


የእግዚአብሔር #የነፍሱ #ፍጹም ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ #በልባችሁ mind መታደስ ተለወጡ የቃሉ ምንጭ ከጥንት GR-metamorphoo ከሚለው የመጣ ሲሆን EN- Metamorphosis የሚለው ትርጉም ያዘለ ነው ጌታ ብርሃን መሆኑን ወደ ብርሃንነት ተለውጦ ባሳየበት በማርቆስ 9:2-3 transfigured ብሎ የተተረጎመው ነው ቃሉ በግሪክ አንድ ነው።
2 ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ልብሱም አንጸባረቀ፤ 2 And after six days Jesus taketh with him Peter, and James, and John, and leadeth them up into an high mountain apart by themselves: and he was transfigured before them.
3 አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ። 3 And his raiment became shining, exceeding white as snow; so as no fuller on earth can white them.
ለዚህ Metamorphosis በተፈጥሮ the most clasick example in nature is የቢራቢሮ ለውጥ ነው ከኧባ ጨጋሬ በምድር ላይ ተስቦ ከሚሄድ ወደ ሚበር ፍጥረት የመቀየርዋ ሂደት ነው የተጠቀመበት from catrepiler to buterfly Metamorphosis እደሆነ 7ኛ ከፍል ተምረናል። cocoon እጭ ውስጥ ኧባ ጨጋሬ አካሉን ይከትና ጭንቅላቱ ወደ ውጪ ያስቀራል ጭንቅላቱ ይወድቅና (ስጋዊ አይምሮ ማጣት አለብን) የቀረ አካሉ ሲወጣ በተአምር በሚመስል ቢራቢሮ ሆኖ ይወጣል።
ያለውጥ transformion ከኧባ ጨጋሬ በምድር ላይ ተስቦ ከሚሄድ ወደ ሚበር ፍጥረት የመቀየርዋ ሂደት የሚገርም ነው። ከአንድ ፎርም ወደ ሌላ ፎርም ያለ ለውጥ ነው። እየተለወጥን ነው እንዴት በአይምሮ መታደስ be ye transformed by the renewing of your mind
Transformed መለወጥ ወይም Metamorphosis አለ የሚመጣውም በአንድ መንገድ ነው renewing of your mind በአእምሮ መታደስ ተለወጡ
በአእምሮ መታደስ ከሌለ ለውጥ የለም Metamorphosis ከ mind ጋር አገናኝዋቸው እ/ር አእምሮ ላይ ካልሰራ ለውጥ የለም transformion፣ Metamorphosis የለም
የክርስቶስ አእምሮ መንፈስ ቅዱስን ያደምጥ እደነበረ የክርስቶስ አእምሮ ያለንም በእርሱ ዘንድ የነበረ ሃሳብ በእኛ ይሁን።
Renovatio መታደስ renewing ቤት ስታድሱ ምን ታደርጋላችሁ ?መጀመርያ የምታደርጉት ብዙ እቃ ታስወጣላችሁ እቃው ይወጣል ጥግ የሚዘው ይይዛል ብል የበላው ግድግዳ ካለ ይተረተርና እንደአዲስ ይጠገናል በፊና ታሳምሩታላችሁ በቀለም ይቀለማል ። ጣራው መታደስ ካስፈለገው ገንጥላችሁ ይታደሳል ። ያ ነው የማደስ ሂደት ማለት የመተካት ህግ። be ye transformed by the renewing of your mind በአይምሮ እድሳት ላይ አንዱን መርሳት አዲሱን ማስታወስ ሂደት ነው።the prosese is forgeting and remembering እንደምታውቁት አንድን ነገር ስትረሱት ታጡት አላችሁ አንድን ነገር ስታስታውሱት ቦታ ታስይዝታላችሁ። አሮጌውን አስተሳሰብ ወይም መራጃ በማስወገድ በኧዲሱ የመተካት ህግ ነው። አሮጌውን ሃሳብን በሃሳብ የመሻር ስልጣንን መለማመድ ያለተቀደሰውን በተቀደሰው በእ/ር ቃል መተካት። አንዳንዴ በአይምሮ እድሳት ላይ አንዱን መርሳት አዲሱን ማስታወስ ሂደት እሱ ብቻ ላይሆን ይችላል ከአይምሮ ዳር ባለ እድሳት በተለይ ማለት ነው። ትንሹ ለጅ ቢላ ቢያነሳ ምን ታደርጋላችሁ ወይኔ ብላችሁ ወ ይ ዘላችሁ ቢላውን ትነጥቁታላችሁ ወይም
ጥበብን ትጠርዋታላችሁ የሚወደውን አሻንጉሊት ታነሱና ታሳይታላችሁ ሃሳቡ በዛ ሲያዝ ቢላውን ታስለቁቅታላችሁ በአይምሮ እድሳት ላይ አንዱን በማስተዋወቅና በማስረሳት አዲሱ በተካት ሂደት ተጠቀማችሁ። ይህን አሮጌውን በአዲስ የመተካት ሂደት ነው ጌታ አይምራችን ለማደስ የሚጠቀምበት ሂደት።” የተጠቀሰው ተፈጸመ።
መጽሐፈ ምሳሌ 16፡32 ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስዱ ይበልጣል። Prov 16፡32 He that is slow to anger is better than the mighty; and he that ruleth his spirit than he that taketh a city.
እኛ ግን ነጠላ አይምሮ ነው ያለን በእ/ር መንፈስ ምስክርነት ላይ ቆመናል። እኛ ግን ነጠላ አይምሮ ነው ያለን በክርስቶስ ምስክርነት ላይ ቆመናል። አሜን!
*አሁን የእ/ር እያደረገ ያለው የአሮ ጌውን ስጋዊው ሰው አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ እያስወገደ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ የአዲሱ ሰው ላይ የነፍሱ ክብር ማለትም አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ወዘተ እንዲወርሰን በዚህም የልጁ ህይወት በእኛ ያለመከልከል ይገለጥ ዘንድ እየሰራ ነው ። እርም ክብሩ ይሰፋል።
የጌታ እየሱሱ ክርስቶስ የመሳካቱ ትልቅ ሚስጢር የአባቱ ፈቃድ ብቻ ማድረጉ ባቻ ሳይሆን ከሱ ካልሰማም ምንም አያደርግም። እኔ ከአባቴ የመየውንና የምሰማው ሁል ጊዜ አደረጋለሁ። ያ ነው የክርስቶስ አይምሮ።
ኦሪት ዘፍጥረት 3፡1 እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። Gen 3፡1 Now the serpent was more subtil than any beast of the field which the Lord God had made. And he said unto the woman, Yea, hath God said, Ye shall not eat of every tree of the garden?
ሴቲቱንም፦ በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። ጥያቄው በመንፈስ ስልጣን ላይ ጥያቄ እንዲፈጥር ያነጣጠረ ነበር ወደ አዲስ ኪዳን ስትመጡ ግን የክርስቶስ አእምሮ የሰይጣንን ሃሳብ ሁሉንም ድል ነሳቸው። እኛ የተሸውደው የመጀርያው አዳም አእምሮ ዘር ሳይሆን ያለን የማይሸወደው የክርስቶስ ዘር አእምሮ ነው ያለን! 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:16 እንዲያስተምረው የጌታን ልብ[#አይምሮ #mind] ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ[#አይምሮ #mind] አለን።1Cor 2:16Open in Logos Bible Software (if available) For who hath known the mind of the Lord, that he may instruct him? But #we #have #the #mind #of #Christ. ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal