Discussion Quotes፡ Binyam TA Solomon Beyene ሰላም ወንድም ሰሌ። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5/21 ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት[የእግዚአብሔር የውሸት ምስል፡፡ ] ራሳችሁን ጠብቁ።


Discussion Quotes፡ Binyam TA Solomon Beyene ሰላም ወንድም ሰሌ። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5/21 ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት[የእግዚአብሔር የውሸት ምስል፡፡ ] ራሳችሁን ጠብቁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡18 እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን። THAT IS DELIVERANCE! መዳን ማለት ያ ነው። እ/ር ደረጃ በደረጃ ወደ መልኩ ሊለውጠን ቃል ገብተዋል። እ/ር ተናገረ ማለት ደግሞ ሆነ ማለት ነው። “2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1/2-3 የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 4 ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።” ከክፉ የመዳናችን ሚስጥር በፍጻሜው በባህሪው እንገኝ ዘንድ ነው። ባለፈው ጊዜ ካየነው በዚህ ላይ ይጠቅመናል ልጥቀሰው።እ/ር የሰው ልጆችን ማዳን ወይም መዋጀት ያስፈለገው ከሲኦል አድኖ ወደ መንግስተ ሰማያት ለማሻገር አይደለም። በልምድ የሚነገር ካልሆነ በስተቀር የእ/ር ቃል በቀጥታ እደዛ የሚል በተወዳጁ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ከራሳቸው ሃጢያትና በውስጣቸው ከሚሰራው የአመጻ ሚስጥር በማንጻት አላቆ ወደ እ/ር መለኮታዊ ተፈጥሮና ባህሪ ለማምጣት ነው እንጂ። “የማቴዎስ ወንጌል 1፡21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” አስተዋላችሁ ህዝቡ መዳን ያስፈለጋቸው ከገዛ ሃጢያታቸው እንጂ ከሲኦል አይደለም።“የሐዋርያት ሥራ 3፡26 ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።” Acts 3፡26 Unto you first God, having raised up his Son Jesus, sent him to bless you, in turning away every one of you from his iniquities. ደግሞም ወደ ቲቶ 2፡14 መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።“ የእንግሊዝኛው ግልጽ መልእክቱን ስለሚያሳይ እንመልከተው “that hemight redeem us from all iniquity, and purify unto himself” ከቃሉ እንደምናስተውለው የተዋጀነው ከአንድ ማንነት ወደ ሌላ ማንነት ነው። ይህም ከአመጻ ሁሉ from all iniquity, አጥርቶ ወይም አንጽቶ ወደ ራሱ purify unto himself ነው እንጂ። የተዋጀነው ከቦታ ወደ ቦታ የጂኦግራፊ ወይም የካርታ ለውጥ ከሲኦል ወደሆነ ሩቅ ጠፈር ላይ የሚገኝ ገነት የተባለ ቦታ ወይም ፕላኔት ሰፈር ለመቀየር አይደለም። የተዋጀነው አመጻ ከተሞላ ማንነት ወደ ራሱ መልክና አምሳል ለማምጣት ነው። የመንጻሩም ሂደት በእሳቱ በማሳለፍ አመጻውን ሁሉ በመብላት ወደ መልኩ ማምጣት ነው።Mal 3፡2 But who may abide the day of his coming? and who shall stand when he appeareth? for he is like a refiner’s fire, and like fullers’ soap: 3 And he shall sit as a refiner and purifier of silver: and he shall purify the sons of Levi, and purge them as gold and silver, that they may offer unto the Lord an offering in righteousness.ትንቢተ ሚልክያስ 3፡2 ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው? 3 እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ። የእሳቱአላማ ማንጠር ነው። አሜን!” “ከየኖኅ ዘመን እንደ ነበረ! ክፍል 2 የተጠቀሰው ተፈጸመ።”ዳዊት መዝሙረ ዳዊት 51፡10 አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። Ps 51፡10 Create in me aclean heart, O God; and renew a right spirit within me. የገባው ነገር ስላለ ነው። በእርግጠኝነት ከክርስቶስ የህይወት ውሃ እየቀዳን የምንጠጣ ከሆነ ንጹህ ልብ ሊኖረን ግዴታ ነው። መዝሙረ ዳዊት 103፡1 ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ፥ የተቀደሰ ስሙን። Ps 103፡1 Bless the Lord, O my soul: and all that is within me, bless his holy name. በኛ ውስጥ ሁለንተናችን ቅዱስ ስሙን ሉያመሰግን የተገባው ነው።ነብዩ ህዝቄል ከራእዮቹ በአንዱ እ/ር ወደ ግንቡ አመጣው ግንቡን ንደለውና የማሳይህ ነገር አለ አለው “ የቀደሙት እስራኤል በጨለማ የሚያደርጉትን በሃሳብ አደባባያቸው የሚያደርጉትን አሳየው።” ሕዝቄኤል8/1፡16 የሰው ልጅ ሆይ፥ የሚያደርጉትን፥ ከመቅደሴ ያርቁኝ ዘንድ የእስራኤል ቤት በዚህ የሚያደርጉትን ታላቁን ርኵሰት ታያለህን? ነብዩ ባየው ነገር ክው ብሎ ደንግጦ ነበር። የተንቀሳቃሾችና የርኩሳን አራዊት ምሳሌ የእስራኤልንም ቤት ጣዖታት ሁሉ ተስለው በሃሳባቸው ግድግዶች ተለጥፈው ነበር። እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በጨለማ እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱ። እግዚአብሔር አያየንም እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል ይላሉና አለኝ። እርሱም፦ ደግሞ ተመልሰህ ከዚህ የበለጠውን የሚያደርጉትን ታላቅ ርኵሰት ታያለህ አለኝ። እነዚህ በእ/ር በተመረጠ ህዝብ መካከል ሽማግሌዎች ናቸው በልባቸው ከሚካሄደው ቢስትሊ ኔቸር አውሪያዊ ተፈጥሮ ግን ሲገለጥባቸው እናያለን። መጽሐፈ ምሳሌ 23፡7 ሰው በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነው፡በትክክል የውስጥ አደባባዮቻችን ሊነጹና ሊጸዱ ይገባል። እ/ር ይመስገን የእ/ር ቃል ፈጣንና የሚሰራ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ የተሳለና መለየት ያለበትን ሃሳብ ሁሉ የሚለይ ነው። ወደ ዕብራውያን 4፡12 የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤Heb 4፡12 For the word of God is quick, and powerful, and sharper than any twoedged sword, piercing even to the dividing asunder of soul and spirit, and of the joints and marrow, and is a discerner of the thoughts and intents of the heart.ስለ የልብ ጣዖቶች ጌታ ተናግሮት ነበረ ፥ ትንቢተ ሕዝቅኤል 14:4-5 ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁሉም በጣዖቶቻቸው ከእኔ ተለይተዋልና የእስራኤልን ቤት በልባቸው እይዝ ዘንድ ከእስራኤል ቤት ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ የሚያቆም ሰው ሁሉ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ ብለህ ንገራቸው።Ezek 14:4 Therefore speak unto them, and say unto them, Thussaith the Lord God; Every man of the house of Israel that setteth up his idolsin his heart, and putteth the stumblingblock of his iniquity before his face,and cometh to the prophet; I the Lord will answer him that cometh according tothe multitude of his idols; 5 That I may take the house of Israel in their ownheart, because they are all estranged from me through their idols. በ1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡21 ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ። ይላል ጣዖታት ማለት የውሸት አምላ ምስል ማለት ነው።የማርቆስ ወንጌል 9፥49 ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፥ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል። ጌታ እውነት ነኝ ብለዋል ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ እሳት ይቀመማል ካለ አሰራሩ ይለያይ እንጂ ማንም ከእ/ር እሳት የሚያመልጥ የለም ። ሁሉን በእሳት የሚያሳልፍ ጌታ እየሱስ እራሱ ነው። “የማቴዎስ ወንጌል 3፡11 እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤” ደግሞም Heb 12፡29 For our God is a consuming fire. ወደ ዕብራውያን 12፡29 አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ( consuming የሚባላ) እሳት ነውና። በመገለጡ ወይም በመምጣቱ ሃጢያታችንና አመጻችን ከልባችን ይበላዋል። ከክፉውም ያድነናል። ብርሃን ለጨለማ እሳቱ ነውና ይበላዋል ጨለማ በብርሃን ፊት ህልውና የለውም። “ኦሪት ዘዳግም 33፡2 እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ከሲና መጣ፥ .. ከአእላፋትም ቅዱሳኑ መጣ፤ በስተ ቀኙም የእሳትሕግ ነበረላቸው። Deut 33፡2 And he said, The Lord came from Sinai, …and he came with ten thousands of saints: from hisright hand went a fiery law for them. ቃሉ እሳት ነው።አምላካችን ድንገት ወደ መቅደሱ በእሳታዊ ባህርዩ ይመጣል ፍርድንም ከእ/ር ቤት ይጀምራል። በተመሰረትንበት መንፈሳዊ መሰረት ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የእሳቱ(የመለኮቱ ፤የመንፈሱ) ወጤቶች በሆኑ የመለኮት ባህሪያት ተምሳሌቶች በሆኑት በወርቁ በብር በከበረ ድንዳይ ሰርተን እንደሆነ እሳቱን ያልፋሉ እንዲያውም በክብር ይደምቃሉ ወይም የሰው ክብር ተምሳሌት በሆኑ በእንጨት በሳርም በአገዳም ካነጽን አገዳው ተረረረር እያለ ይነድልናል ሳሩም እየተንጣጣ ይነዳል ስራችን እሳቱ ሲገልጠው ከበላው ያማል መሰረታችን ግን ክርስቶስ ጽኑ ነውና አየየይ እያልን በሲቃ እንድናለን። የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል ። ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ግን ደመወዙን ይቀበላል።ትንቢተ ሚልክያስ 3 Mal32 ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው? 2 But who may abide the day of his coming? and who shall stand when he appeareth? for he is like a refiner’s fire, and like fullers’ soap:3 እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ .. ልጆችን ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ። 3 And he shall sit as a refinerand purifier of silver: and he shall purify the sons…, and purge them as gold and silver, that they may offer unto the Lord an offering in righteousness. አሜን ጌታ ሆይ ከክፉው አድነን:: የማርቆስ ወንጌል 9፥49 ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፥ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል። አንተን እንመስል ዘንድ በባህርይህ ቀምመን! አሜን! ተፈጸመ። ወንድም ቢኒ።


የባህል መዳኒት ወይስ ዘመናይ መድሃኒት? I think God is funny he knows practical jokes ሰው ኮሶ ሲይዘው እንዲያሽረውና እንዲገላገል ኮሶ ያጠጡታል። ሙሴም በጠላቶቻቸው ፊት እንዲነወሩ አሮን ስድ ለቅቋቸዋልና ሕዝቡ ስድ እንደ ተለቀቁ ባየ ጊዜ ወርቁን አደቀቀው፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨው እንዲያሽራቸውም ወርቁን አጠጣቸው🤣 ፥ ኦሪት ዘዳግም 9፡21 ያደረጋችሁትንም ኃጢአት ጥጃውን ወሰድሁ፥ በእሳትም አቃጠልሁት፥ አደቀቅሁትም፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት፤ ትቢያውንም ከተራራ በሚወርድ ወንዝ ጣልሁት። ኦሪት ዘጸአት 32፡20 የሠሩትንም ጥጃ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨው፥ በውኃውም ላይ በተነው፥ ለእስራኤልም ልጆች #አጠጣው።🤔😀
  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal