የዘልአለም ፍርድ፡ Eternal Judgment ወይም ፍፃሜ አልባ ቅጣት Endless punishment ብሎ ነገር መፅሐፍ ቅዱስ አያስተምርም።


Discussion Quotes “የዘልአለም ፍርድ፡ Eternal Judgment ወይም ፍፃሜ አልባ ቅጣት Endless punishment ብሎ ነገር መፅሐፍ ቅዱስ አያስተምርም።” በነገራችን ላይ “የልጁ ዓለም፣ የኪሩቤሎች ዓለም፣ የመልአክት ዓለም፣ የሰው ዓለም” ብለሃል ይህ “አለም” መርምር የተሳሳተ ትርጉም ነው ወንድሜ። ተባረክ። እሱ ብቻ አይደለም ጥቂቶችን ለምሳሌ የዘልአለም ፍርድ፡ Eternal Judgment ወይም ፍፃሜ አልባ ቅጣት Endless punishment ብሎ ነገር መፅሐፍ ቅዱስ አያስተምርም። የፍርድን ተፈጥሮ ከማስተዋላችን በፊት ዘመን እና ዘልአለም የሚሉትን ሁለት ቁልፍ ቃላቶች ልዩነታቸውንና ተናጋሪው መንፈስ የሆነው እ/ር ከተናገራቸው አካያ ማየቱ እጅግ ጠቃሚ ነው። “የዘልአለም ፍርድ“ ቅጣት እውነት እንደሆነ ለማረጋገጥ ከሚጠቀሱት ቃላቶች ዋንኛው “ዘልአለም” የሚለው ቃል የእንግሊዝኛውም የአመርኛውም ላይ ከተፈጠረው የትርጉም ስተት የተገኘ ጽንሰ ሃሳብ ነው። ”መጽሐፍትን እና የእግዚአብሄርን ሐይል ካወቅን አንስትም“ በሚለው ፁሁፍ ላይ እንደገለጽኩት የትርጉም ስራዎችን እንደ ፍጽም ስራ እንዳንደገፍባቸው ታሪካዊ አመጣጣቸውን  በማስተዋል መቃኘታችን ለዚህና ለሌሎ ች ሃሳቦች እንደ መንደርደርያ እንዲጠቅመን፡ነው።

 

በአዲስ ኪዳን ”ዘልአለም Eteernal, Everlasting” የሚለው ቃል ከዋናው የግሪኩ ቅጂ ላይ “aionions” ከሚለው ቃል የተረጎመ ነው የቃሉ ስር ወይም፡ ንብረትነቱ “EION” ነው። ትርጉሙም “ዘመን age” ማለት ነው። ሁለቱ የተለያየ ትርጉም ያላቸው ናቸው ማለት አይደለም ። aion(the noun form) ሰዋሶው ወይም ነባር ስም ሲሆን aionions (the adjective form ቅጽል ነው። ሁለቱ ቃላት ሰዋሶው እና ቅፅል ናቸው። ለምሳሌ ሳምንት ሰዋሰው  ሲሆን ሳምንታዊ ደግሞ ተቀፅላው ነው። ልክ እለት፦ እለታዊ, አመት ፦አመታዊ እንደሚባለው መለት ነው። Greek word “aion” (Strongs #165) or its adjective form “aionios” (#166).

በመረዳት ብርሃን ማስተዋል ያለብን ዘመን ማለት ዘልአለም ማለት አይደለም። ብዙ ጊዜና  ብዙ ወቅቶች አሉ። ነገር ግን አንድ ዘልአለም ብቻ አለ።  ዘልአለም ጅማሬ የለው ፍፃሜም ቢሆን የለውም። ነገር ግን ጊዜ ዘመን ወቅቶች ሁሉም ጅማሬ አላቸው ፍፃሜም አላቸው። ጊዜ ሲያበቃ ዘልአለም ይጀምራል የሚለው አባባል ፈጽሞ ስህተት ነው። ምክንያቱም ዘልአለም ጅማሬ የለውም የሚያበቃም አይደለም። ዘልአለም ጊዜ ሲመጣ  የሚጀምር አይደለም። ዘመናት በዘልአለም ውስጥ የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው። ልክ ሴኮንድ በደቂቃ ውስጥ ቦታ እንዳለው ደቂቃም በሰአት ውስጥ የራሱ ቦታ እንዳለው ሰአትም በአመታት ውስጥ የራሱ ቦታ እንዳለው። አመታት እና ዘመናት ያልቃሉ በዘልአለም ውስጥም የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ጊዜ እናስተውል ዘንድ በነዚህ ቃላቶች መካከል ያለው ልዩ ነት ግልጽ እይታ ሊኖረን ወሳኝ ነው። ዘመን የሚመደበው በጊዜ ውስጥ ሲሆን ዘልአለም ግን ጊዜ አልባ ነው። በመጽሐፍ ስለ ዘመን የተናገሩትንና ሰለ ዘልአለም የተናገሩትን ለይተን ማስተዋሉ የእ/ርን ጠቅላላ ምክር እናስተውል ዘንድ እጅግ ይጠቅመናል።

 

በጣም የሚያሳዝነው አብዛኛዎቹ የእንግሊዝኛም ሆነ የአመርኛ ትርጉሞች ብዙ የሚመሰገኑበት ቢኖርም  ዘመንን በተመለከተ ሲተረጉሙ ግድ የለሽ ሆነው ዘልአለም እያሉ በመተርጎማቸው በእ/ር ህዝብ ላይ ለዘመናት ትልቅ ግራ መጋባትን አስከትለዋል። ይህም ብዙ ትውልዶችን ለአያሌ ዘመናት የተዛባ መረዳት ውስጥ ቆልፎ አስቀምጠዋቸዋል። ለመጥቀስ ያህል የእንግሊዝኛም ሆነ የአመርኛ ትርጉሞች KJV ላይ እዲሁም በዚህ መጽሐፍ ተጽኖ ስር የተተረጎሙ ሁሉ ላይ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ስለሚሳደብ ሰው የተናገረውን ቃል እንዲህ ያስቀምጡታል። እግዚያብሄር ያሳያችሁ አንዱ ቃል ወደ ስንት ተበታትኖ እንደ ተተረጎመ age {2 ጊዜ beginning of the World {2} ጊዜ, for ever and ever,(8) course{1}ጊዜ World {32} ጊዜ eternal {42}ጊዜ, world began{1}ጊዜ forever{27}, for evermore{2}, እነዚህ ሁሉ ዘመን ወይም እንደ አገባቡ ከዘመን ዘመን፤ ለዘመናት፤ ለዘመኑ፤ ወዛተ ተብሎ በቀላሉ በዚህ መልክ መተርጎም ነበረበት።

“ማርቆ3/29 መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ግን “የዘልአለም” ሃጥያት ይሆንበታል እንጂ አይሰረይለትም” ከዚህ የተሳሳተ ትርጉም የተነሳ የተሳሳተ ጽንሰ ሃሳብ ተወልደዋል። ለዘልአለም ይቅር የማይባል ሃጥያት አለ ብለን እንድናስብ አድርጎን ነበር። ነገር ግን የቃሉ ፍቺ በትክክል እንዲያቀብል አድርገው ከተረጎሙት ከጥቂት የእንግሊዝኛም ትርጉሞች መካከል Emp  hatic Diaglott የተባለው ትርጉም ትክክለኛውን ትርጉምi እዲህ ያስቀምጠዋል። “Whoever may blasphemy the Holy Spirit no forgiveness to the age but is exposed to anian lasting judgment mar3/29” “መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ “ለዘመኑ” ይቅር አይባልም። ነገር ግን ”ለዘመኑ“ ፍርድ ይጋለጣል።“ እንደ ምናስተውለው ይቅር የማይባለው ለፍርድ የሚጋለጠው ለዘመኑ ፍርድ እንጂ ለዘልአለም ፍርድ አይደለም። በማትዮስ 12/32 ያለው ደግሞ እንዲህ ተብሎ ተተርጉመዋል ”በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ ”አለም“ ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም። አለም የሚለው ቃል ከግሪኩaion ማለትም ዘመን age ተብሎ መተርጎም ከነበረበት ቃል የመጣ ነው። ቃሉ መተርጎም የነበረበት “መንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ “ዘመን” ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም” ነው። ጌታ እየሱስ የተወለደው በህግ ዘመን ስለ ነበር በዚህ ዘመንም ቢሆን ማለቱ የህግን ዘመን ለማሳየት ሲሆን በሚመጣው ዘመን ቢሆን ሲል ደግሞ አሁን እኛ ያለንበትን የፀጋውን ዘመን ማለቱ ነው። ይህን ካስተዋልን ስለ ዘመንና ስለ ዘልአለም ያለውን ብዥታ ያጠራልናል። በግሪክ aion(ሰዋሰው noun) በግልጽ “ዘመን ወይም ያልተወሰነ ክፍለ ጊዜ ነው an age or an indefinite period of time, Young’s Concordance”

BROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU WRITINGS, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING

 

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal