ከሰው ነፃ ፈቃድ የተነሳ እ/ር ሁሉን ማዳን አይችልም የሚለው ሃሳብ ከእ/ር አቅም ጋር ሲነፃፀር ኢምንት ነው የሚጋጭም ነው።


ጥያቄ/መልስ። ወንድም ቢኒ። ከሰው ነፃ ፈቃድ የተነሳ እ/ር ሁሉን ማዳን አይችልም የሚለው ሃሳብ ከእ/ር አቅም ጋር ሲነፃፀር ኢምንት ነው የሚጋጭም ነው። እ/ር ለሰው ፈቃድ ጌታዋ መሆኑን በየዘመናቱ የነገስታትን የህዝብን ልብ እንደ ወንዝ ወዳሻው ሲመራው ሃይሉን አሳይተዋል። በነፈርሆን ልብ ላይ ፡ በነሊድያ ልብ ላይ፤ በናቡክደኖፆር ልብ ላይ በሌሎችም የሰረው መንፈሳዊ ትያትር ልኡል ወይም ፈጽሞ የበላይ ለመሆኑ በቂ ማስረጃ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስን በፊት ካስተማሩን ተቃራኒውን እንደ ሚናገር ሳውቅ እኔም ደንግጫለሁ። ቃሉን እንደ ልበ ሰፊዎቹ የቤርያ ሰዎች መመርመር አለብን። ከእ/ር የሆነ የእ/ርን ቃል ይሰማልና። ትንቢተ ኤርምያስ 10/23 አቤቱ፥ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፥ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም። Jer 10/23 O Lord, I know that the way of man is not in himself: it is not in man that walketh to direct his steps. መቼም የእ/ር ቃል ከመጣ መጣ ነው። ዳዊት ቃል ከመጣለት ቡሃላ ወዶ አይደለም “ከአስተማሪዎቼ ይልቅ አስተዋይ አደረከኝ” ለመታበይ ሳይሆን የሰውና የእ/ር ሃሳብ ሰማይ ከምድር ርቆ በማግኘቱ ነው ።

በቀድሞ መረዳት በገባቸው አቅም ለደከሙልን አስተማሪዎች ጌታ ይባርካቸው ሆኖም ስለ ሰው ነፃ ፈቃድ ሃያልነት ፈቃዱ ለደህንነቱ እንቅፋት እንደሆነ በዚህም ከእ/ር ምህረትን ሳያገኝ ለዘልአለም በሲኦል በስቃይ እንደ ሚቀቀል ሲሰበክብን መኖሩ አይካድም እውነቱ ግን ሰው በጊዚያዊ ባለው በምድራዊ ኑሮው  በጥቃቅን ነገሮች ላይ እ/ር ፈቅዶ ባስቀመጠው ሁኔታ ዛቢያ ተጽኖ ስር የፈቃዱን ውስን ምላሽ ብሎም ውስን ስልጣን አለው እንጂ በእ/ር የዘልአለም እቅድ ላይ ግን የሰው ፈቃዱ የበላይ አይደለም። እ/ር እኮ እ/ር ነው።

“ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2/13 ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና። Phil 2/13 For it is God which worketh in you both to will and to do of his good pleasure.” በጎ የተባለው ያሰበው የፈቃዱም ምስጥር ደግሞ ነግሮናል እ/ር አሰበ ማለት ደግም ሆነ ማለት ነው።  “ኤፌ1/9 በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤10 በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።”

ይህን እንመልከት “ወደ ሮሜ ሰዎች 9/16 እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ። Rom 9/16 So then it is not of him that willeth, nor of him that runneth, but of God that sheweth mercy.” እንግዲህ ምሕረት ለወደደ willeth ወይም ለሮጠ አይደለም፥   ከሚ ምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ። but of God that sheweth mercy.” እንዴ ምንድ ነው ነገሩ እ/ር ከፈቃዳቸው ውጪ ሰዎችን ሊያድን ይችላል? ሊነሳብን ይችላል። መልሱ አይደለም ነው። እንደዛ ማድረግ አያስፈልገውም። ሰው ሁሉ እ/ር እራሱን ሲገልጥለት መቶ በመቶ ፈቃደኛ ይሆናልና። መንፈሳዊ እውርነቱ ሲበራ ወይም የዶንቆሮው ጆሮ ሲከፈት ለሙታንም ህይወትን ሲሰጠው ለከንቱነት የተገዛው ተፈጥራዊው ማንነት ፋንታ መንፈሳዊ አእምሮ ሲሰጠው ሲመለስለት ሁሉ የሰማይ አምላክን ያመሰግናል። ሓዋርያው ጳውሎስ ከሃጥያተኞች ሁሉ ዋንኛ የምሆን እኔን የማረው አቅሙን ለማሳየት ምሳሌውን ለማሳየት ነው አላለንምን? ጌታ ፈቃዱን ሳይጠይቅ በታቅ ብርሃን፡ ጳውሎስ ላይ አልወደቀብትምን ታድያ ምንም እንካ  ሳኦል[ጳውሎስ] ከሃጥያተኞች ሁሉ ዋንኛ ቢሆንም ጌታን ተቀበል ብሎ ፈቃዱን ጠየቀውን? ትእይንቱን እናስተውል እ/ር እራሱን ሲገልጥለት ሃጥያተኛው ሳኦል[ጳውሎስ] መቶ በመቶ ፈቃደኛ ሆኖ እያለቀሰ “ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ!!!”  በቃ ፍጥረትም እዲሁ ነው እ/ር እራሱን ሲገልጥለት መቶ በመቶ ፈቃደኛ ይሆናል።

ማወቅ ያለብን የእ/ር ታላቅ አሰራር መካከል “ጌታ ጌታየን ሁሉን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው” ማለትም ከእግሩ ስር የሚያመለክተው ሁሉን ከስልጣኑ ስር እስኪ ያደርግለት ድረስ ማለት ነው የሁሉ ትርጉም ደግሞ ሁሉ ነው።

“1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/3 ….በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ። 1Cor 12/3 ….that no man can say that Jesus is the Lord, but by the Holy Ghost” እናስተውል በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቆናል አሁን ጠላቶቹ የሆኑት አድስዋቸው ከክርስቶስ ስልጣን ስር ሲጠቀለሉ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ሆነው ኢየሱስ ጌታ ነው እያሉ ለበጉ ክብርን ተንበርክከው ይሰጣሉ። “የዮሐንስ ራእይ 5/13 በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ። Rev 5/13 And every creature which is in heaven, and on the earth, and under the earth, and such as are in the sea, and all that are in them, heard I saying, Blessing, and honour, and glory, and power, be unto him that sitteth upon the throne, and unto the Lamb for ever and ever.” እንግዲህ የመጨረሻው ጠላይ ሞት ከነ መውጊያው ከሃጥያት ጭምር ሲደመሰስ እ/ርም እራሱን ለፍጡራኑ ሲገልጥለት መቶ በመቶ ፈቃደኛ ሆኖ እያለቀሰ  በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በመንፈስ ቅዱስም ሆነው በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ይላሉ። ወንድም ቢኒ።  አሜን!!!

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal