
እየሱስ ክርስቶስ ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው?
ከፀጋ በታች እንጂ ከህግ በታች አይደላችሁም ምን ማለት ነው?
እምነትህን ከሥራ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ። ምን ማለት ነው?
ጳውሎስ: ከዮሃንስ፤ ከጴጥሮስ ጋር ሃሳቡ ይጋጫልን ?
ጳውሎስ በሮሜ 6:14 ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።15 እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላይደለን ኃጢአትን እንሥራን? አይደለም። በወንድም ቢንያም አለማየሁ[ቢኒ] 06/10/2018
ለመግቢያ እንዲሆነን ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና ከሚለው ሃሳብ እንጀምራለን። ብዙ ክርስቲያኖች የጳውሎስን የቃላት አደራደርና የመነሻ ሃሳቡ እንድምታ አይረዱቱም። ጳውሎስ ህግን ጠንቅቆ የተማረ ስለ ነበረ በክርስቶስ አእምሮ ሲናገረው የህግ ሰጪው ህሊና ይዞ ነው። ህግን የሰጠው ክርስቶስ እየሱስ ነውና።
እየሱስ ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው?
ጌታ እየሱስ በምን ስልጣን ነበር የተራራው ስብከት ተብሎ በሚታወቀው በማቲዮስ 5-7 ትምህርቱ ላይ የህጉን ፍቺ ትክክለኛ ትርጉም ሲያርም የነበረው? እየሱስ ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው! ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በስጋ የመጣው ወደ መንፈስ ሊመራን ነው። በመጀመሪያው ቃል የነበረው እግዚአብሔር እንደ ነበረ። የዮሐንስ ወንጌል 1፡1 በመጀመርያ ቃልም ሥጋ ሆኖ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ እንደመጣ የማያምን ሁሉ ሃሰተኛ መንፈስ ነው የክርስቶስ ተቃዋሚውም መንፈስ ነው፤ ። ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ነው። “1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4/2 የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥3 ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ”
*እየሱስ ፈጣሪም ነው ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰውም ያህዌ እሱ ነው! “የዮሐንስ ወንጌል 1/3 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።” ይህንን እውነት ለማስተዋል በቀደሙት ክፍሎች በብዙ አይተነዋል እንዲሁም እያንዳንዱን መጽሐፍት ብትመረምሩ ጌታን በዛ ውስጥ ታገኙታላችሁ። የእብራይስጥ ቋንቋ እራሱ ይህንን እውነት ያረጋግጠዋል። አንድ የእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋ ማንም መረዳቱ የተሰጠውና ቃሉን የሚያጠና ሊቅ ሁሉ ሊያውቀው የተገባው የእየሱስን መለኮታዊ ምንጭ ነው። “የእብራይስጥ ቋንቋ በአብዛኛው የአንድ ቃል ፍቺ ሃብታም ከመሆኑ የተነሳ ከአንድ በላይ ደራርቦ ሃሳብን ሊያሳይ ይችላል። የእብራይስጥ ቋንቋ ቃላት ስእላዊ ገላጭ ያለውና የድምጽ ገላጭም አጣምሮ የያዘ ሊሆንም ይችላል፡፡
ለምሳሌ ሁሉም ፈደሎች ቁጥርም ናቸው ቃላትም ናቸው። ለምሳሌ አልፍ “alef” የመጀመርያው ፊደል ነው ያው ፊደል የመጀመርያው ቁጥር አንድ ማለትም ነው። “alef” የሚለው ያው ቃል በሬ ማለት ሲሆን ስእላዊ ገላጩም ጥንካሬን፤ ብርታትን [ymbolizes, strength] የሚያመለክት ነው። ሁለተኛው ቤዝ ወይም ቤት “beth” ቁጥር ሁለት ነው። “beth” የሚለው ቃል እራሱ ቤት ፤ቤተ ሰዎችና ፤ቤተሰቦችን [house or household] ያካተተ ፍቺ አለው።
በእብራይስጥ ቋንቋ ህግ ማለት ቶራ Torah ነው። በእብራይስጥና ቋንቋ ቶራ[ Torah] ሲፃፍ tav-vav-resh-hey ሆኖ ይፃፋል። ይህ ከተያያዛበት ለየብቻው ቃሉ ሲተረጎም Tav ማለት ምልክት ወይም መስቀል ማለት “a mark or sign” [of the cross] ሲሆን። በዋናው በመጀመርያው ጥናታዊ ያልተበረዘ በእብራይስጥ ቋንቋ “መስቀል” ተብሎ ነበር የተፃፈው። በዘመናይ በእብራይስጥና ቋንቋ ተለይቶ ይገኛን። ይህም የሆነው በባቢሎን 70 አመት ምርኮ ጊዜ የባህል ወረራ ስለደረሰ ከአረሚክ ቋንቋ ጋር ተዳቅሎ ተበረዘ።
ሁለተኛው “vav” የሚለው በግልጽ ትርጉሙ እንደ አገባቡ የተሰቀለው፤በሚስማር፤የተጠረቀመው፤የተቸከለው “a nail or peg.” ሲሆን ሶስተኛው “resh” የሚለው በግልጽ መሪ ወይም ራስ “a head, or leader.” ማለት ነው። በመጨረሻም “hey” በቃሉ መጨረሻ ሲቀመት ትርጉሙ ከሱ ወይ ከዛ የወጣ የተገኘ ማለት ነው። “what comes from.” በእብራይስጥና ቋንቋ ህግ ማለትም Torah ከሚለው ቃል ፍቺ እንደ ምናስተውለው “በመስቀል ላይ ከተሰቀለው መሪ ወይም ራስ የተገኘ” ማለት ነው። “what – comes – from – the – Leader- nailed- to- the – Cross” ማለት ነው ። በሌላ አነጋገር እየሱስ ህግን የሰጠውና በመስቀል ላይ የተሰቀለው መሪ ወይም ራስ እሱ መሆኑን በዚህ ታላቅ ሚስጥር ውስጥ የእ/ር ድንቅ ስራ ይስተዋላል። ሃሌሉያ! ወንድም ቢኒ።
ከፀጋ በታች እንጂ ከህግ በታች አይደላችሁም ምን ማለት ነው?
ከፀጋ በታች እንጂ ከህግ በታች አይደላችሁም የሚለው ቃል እንደ እይታቸው ልክ ብዙ ወገኖች ፍቻቸውም ይልለያያል። አንዳንዶች ባለአእምሮ ወይም ቃል በቃል የሚተሮጉሙ ሊትራሊስት በመባል የሚታወቁት አማኞች የተፈጥራዊ ሰው እይታ literalist [A person who translates text literally or not spiritually discerned] ይህ እይታ በአብዛኛው ፊደል ቃል በቃል የሚወስድ ወገን ሲሆን። ያላቸው እይታ ሌላው ቀርቶ የዮሃንስ ራእይን ምንም እንካን ጌታ ለባርያው በመላኩ በኩል በምልክት ጌታ ቢያጽፈውም ሁሉ ነገር ተፈጥራዊ እንጂ መንፈሳዊ እይታ የለውም ብለው ቃል በቃል ይረዱታል። [not figurative or metaphorical] የሚል አቃም ያሳያሉ። ይህም ሁሉ ነገር መንፈሳዊ ነው ከሚሉ ወገኖች ጋርም የአመለካከት ልዩነት በዚህ ምክኛት አለ። ከፀጋ በታች እንጂ ከህግ በታች አይደላችሁም በሚለው በዚህም ላይ ሃሳባቸው ተመሳሳይ ሆኖ ለሁለት የተከፈለ እይታ አላቸው። አንደኛው ወገን
“በሕጉ መሠረት” ህግን የመጠበቅ ግዴታን ያመለክታል ይላሉ። ነገር ግን ህጉን የማክበር አቅምና ግዴታ ከሌለን ለምን ኃጢአት እንዳንሠራ ይከለክለናል? የኃጢአት የዘወትር ፍቺው በጳውሎስ ጽሑፎች ውስጥም ሆነ በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ህግን መተላለፍ ነው። የአማርኛ ትርጉሞች በስተት ቀጥተኛ ትርጉሙን ደብቀውታል እንጂ በዋናው ቃንቃ ሆነ በእንግሊዝኛው ህግን መተላለፍ ኃሃጥያት ነው ይለዋል። 1 ዮሐ 3: 4 እንዲህ ይላል:4 ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን[ህግን መተላለፍ] ደግሞ ያደርጋል: ኃጢአትም ዓመፅ[ህግን መተላለፍ] ነው። 1John 3:4 Whosoever committeth sin transgresseth also the law[ህግን መተላለፍ]; for sin is the transgression of the law ኃጥያት ህግን መተላለፍ ነው።
የዮሃንስ ዓረፍተ-ነገር ከጳውሎስ አስተሳሰብ ጋር ሙሉ ለሙሉ ስምምነት እንዳለው ማሰተዋል አለብን። በሮሜ3 በሕግ ምክንያት የኃጢአት እውቀቱ ይመጣልና ብለዋል። ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና። ( ሮሜ 3 20 ) እና “ነገር ግን በሕግ ባይሆን ኃጢአትን ባላወቅሁም ነበር፤ ሕጉ፦ አትመኝ ባላለ ምኞትን ባላወቅሁም ነበርና።” ( ሮሜ 7 7). ሕጉ ኃጢአትን ምን ማለት እንደሆነ ይገልፃል። ክርስቶስ የህግ ፍፃሜ ነው። በክርስቶስ ባለው ፍቅርም የሕግ ፍጻሜ ነው።እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ። በፍቅር የሚኖር ህግን ሁሉ ፈጽመዋልና። “ወደ ሮሜ ሰዎች10፥4የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።” “13፥10 ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።” ጽድቃችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነውና ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም የተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ ፃድቃን የሆነው ከእርሱ ነው እንጂ ከኛ አይደለም።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1/30-31 ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።
ታዲያ ኃጥያት ማለት ህግን መተላለፍ ከሆነ።ጳውሎስ በሮሜ 6:14 ራሱን እንዴት ተቃርኖ ፃፈ ወይስ ምን እያለን? በእርግጥ እሱ እያለ ያለው ህግን የማክበር ሃላፊነት ከእንግዲህ የለብንም ማለቱ ነው? ማለትም ከኃጢአት መቆጠብ የለብንም እያለ ነው? እዚህ ላይ ነው ከህግ በታች አይደለንም የሚለው ሃሳብ ለብዙ ሰዎች ግንዛቤው ትክክል ያልሆነው።
“በሕግ ሥር” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ሕግ ወደ እናንተ ያለው አቅጣጫ አመለካከትን ነው እንጂ እናንተ ወደ ሕግ ያላቹሁን አመለካከት አይደለም። በህግ በኃጢአት (በወንጀል) የተከሰሰ አንድ ኃጢአተኛ “በህጉ ስር” ነው። አጥፊው ለወንጀሉ ሲባል ከህግ ስር ሆኖ ካሳ ለተጎጂው እንዲከፍል የሚያስገድደው ህጉ በእሱ ላይ በተቃውሞ ይቆማል። ዕዳውን ሙሉ በሙሉ በእጥፍ በመክፈል ወይም ዕዳውን ሰርቶ በመክፈል ወይም የቅርብ ዘመድ እዳውን ከፍሎ ከዕዳ የሚገላግለው አንድ ሰው ከአገሩ ከወገኑ ካለው “በሕግ ሥር” የነበረው ሰው ነፃ ወጥቶ አሁን እዳው ስለተከፈለ ከዚህ ቡሃላ”በሕግ ሥር” አይደለም “ከጸጋ በታች ነው.” ተብሎ ይፈታል። እንዲህ ባለው ሁኔታ ፍርድ ቤቱ በይኖ ጉዳዩን ይዘጋዋል። ምክንያቱም ምንም ዓይነት ተጨማሪ ሥራ ስለማይኖር እና ምንም ተጨማሪ ፍላጎት ህጉ ከሌለው ከፀጋ በታች ባሉት ላይ ህጉ ስልጣን የለውም። አንድ ሰው ወንጀል (ኃጢአት) ሲፈጽም ብቻ ነው “በሕግ ሥር” ተብሎ ህጉ ዳኛ ፊት እንዲቀርብ ያስገድደዋል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን እንደ እ/ር ቃል ለምሳሌ, አንድ ሌባ 1,000.000 ብር በመስረቁ ተፈርዶበት ከሆነ የእግዚአብሔር ሕግ ሁለት እጥፍ ለተጎጂው እንዲመልስለት ይፈረድበታል (ዘጸአት22/4 …።የሰረቀውን ያህል ሁለት እጥፍ ይክፈል።) ለተጠቂው ሁለት እጥፍ $ 2,000,000 ገንዘቡን ለመክፈል ባይኖረው በዳኛው በተወሰነው መሰረት ረጅም ጊዜ ዕዳውን በስራ መክፈል ይኖርበታል። ሌባው ለ3 አመታት በስራ እንዲቀጣ ከተፈረደ ሌባው “በህጉ መሠረት” ለ3 አመታት “በሕግ ሥር” ነው ይባላል። የህግ እስረኛው የፍርድ እገዳ በመክፈሉ ምክኛት ሲጠናቀቅ ወደ ፍርድ ቤት ይመለሳልና ጉዳዩ ይታያል። ዕዳውን መክፈሉን ወይም አለመክፈሉን ዳኛው ያጣራና የመጨረሻውን ብይን ይወስናል። ዳኛው ጉዳዩን መረምረው እዳውን መክፈሉን እርግጠኛ ሲሆኑ ይህ ሰው ዕዳው ተከፍሏል ስለዚህ “በጸጋው ሥር ” ነው ከእንግዲህ “በሕግ በታች” አይደለም ብለው ይበይናሉ ምክንያቱም ዕዳው ተከፍሏል።
ሕጉ ሁሉንም ሰዎች የኃጢአት ባለእዳ ናችሁ ብሎ ሃጥያተኞች ያረገናል። ይሁን እንጂ ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን “ከሕግ ሥር” ወይም “ከሕግ በታች” አይደለንም። ለምን? ምክንያቱም ስለ እኛ ጌታ ኢየሱስ ዕዳችንን ስለከፈለልን እና ህጉ ስለረካ ነው። እንግዲህ ፍሬ ሃሳቡ ምንድር ነው? ኢየሱስ ዕዳችንን ለመክፈል አቅም ኖሮት ቢከፍልንን በኃጢአት እንቀጥላለን? በጭራሽ! ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላይደለን ኃጢአትን እንሥራን? እ/ር ያርቀው አያድርገው እና! ክርስቲያኖች፤ የእ/ር ልጆች ጸጋ የኃጢአት መንጃ ፈቃድ አለመሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል። ጸጋ የኃጢአት ዕዳ የተከፈለለት አንድ ሰው ሁኔታ ብቻ ነው። ስለዚህ ሕጉ በአሁን ጊዜ በእርሱ ላይ የነበረው እዳ የተከፈለለት በመሆኑ ጸጋ እንዳይከሰት ከለላ ሆኖታል። የኃጢአት ትርጉም አልተለወጠም ኃጥያት ማለት ህግን መተላለፍ ነው። እግዚአብሔር አምላክም የሃጥያት ትርጉም ሰው እንዲቀይር ስልጣንን አልሰጠውም። ሕጉን ለማጥናት ጊዜ ብንወስድ እግዚአብሔር የኃጢአትን ትርጉምና እውቀት ሊሰጠን የእርሱን ህግ ሰጥቶናል። አንድ ጊዜ ሕጉን ስናውቅና ስንቀበል ሕሊናችን ማስተዋል ይችላል የእግዚአብሄርን ህግ በአግባቡ በግል ሕይወት እንዴት እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል አቅልሎታል ፍቅር የህግ የነብያት ሁሉ ፍፃሜ ነው። በፍቅር የሚኖር ክፉን አያደርግምና ህኝ ሁሉ ፈጽመዋል። በአሮጌው ኪዳን ለዕብራውያን ህግ በድንጋይ በጽላት ላይ የተፃፈ በውጪ የተፃፈ ነበር። በአዲሱ ኪዳን ግን እንዲህ ይላል። ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው በስጋ በጽላት ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ። “ወደ ዕብራውያን 10/15-16 መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፤ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ ብሎ ከተናገረ በኋላ፥” በክርስቶስ ያለ ፍቅር የህግ ፍፃሜ ነው።
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4/16 እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3/9 ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ #ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ #ከእግዚአብሔርም #ተወልዶአልና #ኃጢአትን[ sin is the transgression of the law ኃጥያት ህግን መተላለፍ ነው።] #ሊያደርግ አይችልም። ወንድም ቢኒ።
እምነትህን ከሥራ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ። ምን ማለት ነው?
ድል ለሚነሳው የሐዋርያው ጳውሎስ እና የሐዋርያው ያዕቆብ መልእክት በአካሄዱ ድርሻ አላቸውን ወይስ ስማዳን ነው የሚያወራው?
መንፈስ የሚናገረውን የሚሰማ ድል ነሺ የእ/ር ልጅ እንደሆነ ጌታ እየሱስ ነግሮናል። በውስጡ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን መንፈሳዊ ጆሮ ከላይ የተሰጠውና የሚሰማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ ከነ ሽልማቱ ነግሮናል። በክርስቶስ አእምሮ መመላለስ ማለት አባትን መስማትና በፈቃዱ መመላለስ ነው። ልጅነት በእግዚአብሔር መንፈስ ከመመራት ውጭ የለምና። እምነት በተፈጥሮው የሰው ምርት አይደለም። የእምነትን መጠን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነውና። እምነት የሚመነጨው ከእግዚያብሔር አፍ ተዘጋጅቶ በሚወጣ ቃል ሁሉ ነውና። ያንን የእ/ር ቃል ወይም ድምጽ ከመስማት እምነት በእኛ ህያው ይሆናል። የእግዚአብሔርን ቃል ወይም ድምፅ አለመስማት ከእምነት ነገር መጥፋትን ያመጣል። እምነትን የባቢሎን ነገስታት ስላሰቃዩት ብቻ አንዳንዳንድ የእ/ር ልጆች ተጋጭቶባቸው እምነትን ገለል ሊያረጉ ይሻሉ። “1ኛጢሞ1፡19 እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና፤” ልጆች በእምነት ማለትም ቃሉን በመስማት ይኖራሉና ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ወይም ልጅነት ምሪት ከእምነት[ቃሉን በመስማት] ወደ እምነት[ቃሉን በመስማት] በእርሱ በእግዚአብሔር ይገለጣልና።
ወደ ሮሜ ሰዎች 1/17 ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።
አሁን ወደ ሐዋርያው ጳውሎስ እና የሐዋርያው ያዕቆብ መልእክት እንግባ ‘ነገር ግን አንድ ሰው “አንተ እምነት አለህ፤ እኔ ሥራ አለኝ” ይላል። እምነትህን ከሥራ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ። ‘ያዕቆብ 2:18
ያዕቆብ 2:18 የአንድ ተግባራዊ ግልጦት የውስጥ ስሜት ነፀብራቆች ናቸው። የእርስዎ እርምጃዎች ከልብዎ ስውር ሃሳብ የተዘጋጁ ፍሬዎች ናቸው። በእውነት እግዚአብሔር መንፈሳዊውን ግዛት ለማስተዋል ለመስማት ለማየት ዓይን እና ጆሮ ሰጥቶን ከሆነ ያ በእርስዎ ድርጊት ውስጥ ግልጽ ይሆናል በፍሬዎም ይታያል።
ምክንያቱም ልጅነት ለመታዘዝ ከመናፍስት አባት የወጣ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ የሆነ በመንፈስ የሚመራ በመንፈስ የተሞላ በመንፈስ የሚመላለስ ነውና። የራሱን ሳይሆን የአባቱን ፈቃድ በመፈፀምም የአባቱና የልጅ ደስታ ፍፁም ይሆናል። “1, * መስማት” እና “2, * መታዘዝን” ስናስተውል ከዕብራይስጥ ቃል * ሽማዕ shema የመጡ ተመሳሳይ ወይም መንታ ትርጉም ከያዘ ቃል የተገኙ ናቸው፡ የአንድ ቃል ሁለት ፍቺ ናቸው።
ከእግዚአብሔር በእውነት የሚሰማ ጆሮ የተሰጦት ከሆነ ያለጥርጥር ከዚያ ቡሃላ ድምፁን መስማታችሁ በመታዘዛችሁም ውስጥ ይንጸባረቃሉ። አምላክ ድል ነሺ overcomer ልትሆኑ የጠራችሁ ከሆነ፡ በድል ነሺ ተግባራዊ ህይወት ይመላለሱ ይገለጡ። አንድ ድል ነሺ overcomer ነኝ ብሎ ሚናገር ሰው አይደለም ነገር ግን ድርጊቶቹ ለአንድን ሰው ስያሜውን ያመጡታል። ያዕቆብ 2:18 የእሱን ቃላት መርህ ነው ያንጸባረቀው።
ድል ነሺ እኮ በቀላሉ በማስተዋሉ ፈጣን የሆነ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን መንፈሳዊ ጆሮ ያለው ና የስማ ሰምቶም የታዘዘ ነው።
የዮሐንስ ራእይ2፥7 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።
2፥11 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል የነሣው በሁለተኛው ሞት አይጐዳም።
2፥17 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፥ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፥ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።
2፥29 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።
3፥6 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።
ጌታ ሰዎች ሁሉ ላይ የበረከት መልእክት አስተላልፏል በረከቱም “1, * ለሚሰሙና” በተግባር 2 * ለሚታዘዙለት) ሁሉ ላይ ነው። በዕብራይስጥ ቋንቋ ውስጥ, idiom ቃል ይህ የዕብራይስጥ ፈሊጥ ነው። በዕብራይስጥ ቋንቋ ውስጥ, shemameans የቃሉ ፍቺ ድርብ ነው መስማት እና መታዘዝ ነው።
ዘዳግም 6.4 ስማ [* ሽማዕ] እስራኤል ሆይ! ጌታ አምላካችን ነው, አንድ ጌታ ነው! የቃሉ ትእዛዝ የሚጀምረው ስማ/ታዘዝ በማለት ነው።
አንድ ሰው እንግዲህ የሉኡሉን ቃል ሰምቶ የማይታዘዝ ከሆነ ታዲያ እንዴት ብሎ ቃሉን ሰምተዋል ሊባል ይችላል? አንድ ሰው ደግሞ ካልታዘዘ በስተቀር በዕብራይስጥ ፈሊጥ ውስጥ ማንም ገና ሰውየው በእውነት አልሰማም። ይህ ጽንሰ-ሐሳብ ደግሞ ለያዕቆብ ‘ትምህርት መሠረት ነው። እሱም * በያዕቆብ 1:22 ላይ እንዲህ ይላል * 22 ‘ቃሉ የሚናገረውን አድርጉ እንጂ ሰሚዎች ብቻ ሆናችሁ ራሳችሁን አታታልሉ። ‘
እምነት ከመስማት ነው መስማትም ከእግዚአብሔር ድምጽ ወይም ቃል ነው። እናም እግዚአብሔርን መስማትህ የተረጋገጠ የሚሆነው ሰምተህ ከታዘዝክ ነው። ነብዩ ዮናስ እስኪ ሰማ እስከ ሲኦል መውረድ ነበረበት። አንዳድ ሰው በመገለጥ ስለ ማይሰማ መንፈስ ቅዱስ ወደ ተግባር ትምህርት ቤት ያስገባውና በተግሳጽ ጆሮውን የከፈተዋል። “ትንቢተ ዮናስ 2/3 በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ እርሱም ሰማኝ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ፥ ቃሌንም አዳመጥህ።”
አንድ ሰው በእብራዊን ቋንቋ የጌታን ድምጽ ሰማሁ ካለ ፈጽሞ ሰምቶ ፈጽሞ መታዘዙን የሚያሳይ ነው። ሰምቶ ካልታዘዘም ፈጽሞ አልሰማም። በመገለጥ እንዲሰማም በሌላ በተግባር ሂደት ያልፋል። “በመከራ ጆራቸውን ይከፍታል። እዮብ36፡15 በእብራይስጥ መከራ የሚለው ውጥረት ይለዋል። አንዳንድ ጊዜ ለምን ይሄ ሁሉ ውጥረት በመንገዳችን እንደ ሚያልፍ እንደነቃለን።
እንደ ዛም ሆኖ ነገር ሁሉ ተያይዘው ለበጎ እንዲደረግ እንረዳለን። በብዙ መከራ ማለፋችንም ለብዙ አላማ እንደሆነ እናውቃለን። ከዛ ውስጥ አንዱ ጆራችን እዲከፈት ነው። ጳውሎስ የደቀ መዛምርቱን ልብ በማበረታታትና በእምነታቸወ ጸንተው እንዲሩ በመምከር “ወደ እ/ር መንግስት ለመግባት በብዙ መከራ (ግሪክ፦ pressure, እንደ አገባቡ ቃሉ ሲተረጎም ውጥረት ግፊት መገፋፋት ተጽኧኖ የሚያመጣ ውጥረት )ማለፍ አለብን “”
ሐዋ14፡22 ይህም ውጥረት ከአሮጌው አውጥቶ ወደ አዲሱ ተጭኖ ያስገባናል። እ/ር አምላክ ጥበበኛ ነው። አንዱን ውጥረት ከአንድ ነገር ለማውጣትና በተመሳሳይ ሰአትም የስጋን ፈቃድ ሰብሮ የመንፈስን ድምጽ ወደ መስማት ግዛት ያመጣናል።” ከስጋ ድካምም ወደ መንፈስ ብርታት ዘወር እንላለን።
እንደተነጋገር ነው እምነት ከመስማት ነው መስማትም ከእግዚአብሔር ድምጽ ወይም ቃል ነው። እናም እግዚአብሔር መስማትህ የተረጋገጠ የሚሆነው ሰምተህ ከታዘዝክ ነው። በዚህም መሰረት ያዕቆብን እንስማው እስቲ
‘ነገር ግን አንድ ሰው “አንተ እምነት አለህ፤ እኔ ሥራ አለኝ” ይላል። እምነትህን ከሥራ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ። ‘ያዕቆብ 2:18
* የጳውሎስ እና ያዕቆብ መልክቶች በተመለከተ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንዳንድ ውዝግቦች አሉ። ማስተዋል ያለብን ጳውሎስ እኛ በሥራ ሳይሆን በእምነት የጸደቅን መሆናቸውን ለማሳየት የአብርሃም ምሳሌ ተጠቅማል ።
ሮሜ.4:1-4 *. ያዕቆብ እምነታችንን በሥራ የሚረጋገጥ መሆኑን ለማሳየት የአብርሃም ተመሳሳይ ሰው ምሳሌ ይጠቀማል። አንዳንዶች ጳውሎስና ያዕቆብ እርስ በርሳቸው እንደ ሚጋጩ ይናገራሉ ብሎም አንዳንድ ክርስቲያኖች ከአንዱ ለመወገን ጎራ ይለያሉ ።
* ያዕቆብ 2.21-24 ሌሎች ደግሞ ጳውሎስ በእምነት ብቻ ለጸደቁ ሰዎች አይሁዳውያን ላልሆኑ ነው መልክቱ ሲሉ
ሌሎቹ ደግሞ ያዕቆብ በጻፈው ደብዳቤ በሆነ መንገድ በሥራ ለጸደቁ የአይሁድ ሰዎች መጻፉ ነበር ይላሉ።
* የጌታ ቃል ሲነግረን እምነት በፍቅር የሚሰራ ነው ይለናል። እምነት ፍቅር ከሌለው እግር የሌለው ሽባ ይሆናል እምነትን የሚያሰራው፡ሃይል ፍቅር ነው። ፍቅር ታዛዥ ነው። እምነት መስራቱ በሥራ የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል እምነት ዱዳ አይደለም ይናገራል “አመንኩ ስለዚህም ተናገርኩ”። በእብራዊያን 11 ያሉ የእምነት ግዙፎችን አስተውሉ ሁሉ እምነታቸውን በስራ ገልጠዋል።
‘አቤል ከቃየል ይልቅ የበለጠ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ። እግዚአብሔር ስለ ስጦታው በተናገረለት ጊዜ፣ እርሱ በእምነት ጻድቅ እንደሆነ ተመሰከረለት፤ ቢሞትም እንኳ እስከ አሁን በእምነቱ ይናገራል። ‘ዕብራውያን 11:4
‘ሄኖክ ሞትን እንዳያይ ከዚህ ዓለም በእምነት ተወሰደ፤ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም፤ ከመወሰዱም በፊት እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና።
ደግሞም ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሁሉ እግዚአብሔር መኖሩንና ከልብ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን አለበት። ‘ ዕብራውያን 11:4-5
‘ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ፣ እግዚአብሔርን ፈርቶ ቤተ ሰዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት ሠራ፤ በእምነቱ ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ። ‘ ዕብራውያን 11:7
‘አብርሃም ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም፣ እሺ ብሎ ሄደ። በባዕድ አገር እንዳለ መጻተኛ በተስፋዪቱ ምድር በእምነት ተቀመጠ፤ የተስፋውን ቃል አብረውት እንደሚወርሱት እንደ ይስሐቅና እንደ ያዕቆብ በድንኳን ኖረ፤ ምክንያቱም መሠረት ያላትን፣ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠባበቅ ነበር። አብርሃም ምንም እንኳ ዕድሜው ቢገፋም፣ ሣራም #11፥11 ወይም ሣራ … አብርሃምም … ስለቈጠረች ሦስት ወር ሸሸጉት፤ የንጉሡንም ዐዋጅ አልፈሩም። ራሷ መካን ብትሆንም፣ ተስፋን የሰጠውን ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረ #11፥11 ወይም ሣራ … አብርሃምም … ስለቈጠረች ሦስት ወር ሸሸጉት፤ የንጉሡንም ዐዋጅ አልፈሩም። በእምነት የልጅ አባት ለመሆን በቃ። ስለዚህ እንደ ሞተ ሰው ከሚቈጠር ከዚህ ከአንድ ሰው፣ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ተቈጥሮ የማያልቅ ዘር ተገኘ። ‘ዕብራውያን 11:8-12
እናም ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው የያቆብ ነጥብ ። ማጠቃለያ እምነት የሚረጋገጠው በታዛዥነት ነው። ታዛዥነት ከሌለ ምንም መስማት የለም እና መስማት ከሌለ ምንም ዓይነት እውነተኛ እምነት የለም። ጳውሎስ * ሮሜ:14.23 ላይ እንዲህ ይላል ‘ በእምነት ያልተደረገ ሁሉ ኀጢአት ነውና።” ወንድም ቢኒ። By Brother Binyam T. Alemayehu