ቀጣይ ጥያቄ/መልስ የሲኦል እና የገሃነም የዘላለም ፍርድና እሳት ፍቺ።


 
ቀጣይ ጥያቄ/መልስ Part 1 ሰላም ይሁን፤ ወንድም ቢኒ። በቅድምያ የክርስቶስን ህይወት ብቻ በመግለጥ ላይ ብንፀና ለራሳችንም ለሚሰሙትም መልካም ነው። የስጋ ስራ መግለጥ ቀላል ነውና ማንንም ደግሞ አያንጽምም በተቻለን አቅም በቃሉ ላይ እንቆይ የሃላ ሃላ ሁሉም ጌታ እንዳስረዳው መጠን በደረሰበት ሊመላለስ የግድ ነውና ለዚህም እ/ር ይመስገን። ወደ ቃሉ እንመለስና ለመከራከርያህ መሰረት አርገህ ያቀረብከው ቃል “የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን ለዘልአለም ነው።” የሚለው ቃል እዚህ ጋር የተጠቀመበት አሁንም አስተውል ከግዜ ጋር የተቆራኘ ነው ዘላለም የሚለው ቃል የትርጉም ስህተት ነው እንጂ ቃሉ [ለዘመናት aionios] ነው። በአዲስ ኪዳን ”ዘልአለም Eteernal, Everlasting” የሚለው ቃል ከዋናው የግሪኩ ቅጂ ላይ “aionions” ከሚለው ቃል የተረጎመ ነው የቃሉ ስር ወይም፡ ንብረትነቱ “EION” ነው። ትርጉሙም “ዘመን age” ማለት ነው። ሁለቱ የተለያየ ትርጉም ያላቸው ናቸው ማለት አይደለም ። aion(the noun form) ሰዋሶው ወይም ነባር ስም ሲሆን aionions (the adjective form ቅጽል ነው። ሁለቱ ቃላት ሰዋሶው እና ቅፅል ናቸው። ለምሳሌ ሳምንት ሰዋሰው ሲሆን ሳምንታዊ ደግሞ ተቀፅላው ነው። ልክ እለት፦ እለታዊ, አመት ፦አመታዊ እንደሚባለው መለት ነው። Greek word “aion” (Strongs #165) or its adjective form “aionios” (#166).
በመረዳት ብርሃን ማስተዋል ያለብን ዘመን ማለት ዘልአለም ማለት አይደለም። ቃሉን ደግሞ የተጠቀመበት እንደአንተ አቀራረብ የጨለማ ማንፈሳዊ አካሎች ዘላለማዊ ናቸው ብሎ አይደለም። በተለምዶ ዘላለማዊ የሚባሉት ለምሳሌ ሲኦል፤ ገሃነም፤ ስቃይ፤ ሞት፤ ሰይጣን፤ ትል፤ ፍርድ ወዘተ….. ዘላለማዊ ናቸው ብለህ ለማጽደቅ እንደ ተጠምክበት ሳይሆን እነዚህ ሁሉ በየእሳት ባህር ውስጥ ይጠፋሉና። ማስተዋል ያለብክ ከላይ ቁጥር 16 በደንብ ደመህ አስተውል የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል። የሚለውን ለማሳየት ነው። መርሳት የሌለብን የእ/ር ህይወት በባህርዩ ዘልአለማዊ[የማይበሰብስ incorruptible] ቢሆንም ያ ህይወት የተወጋው ዘልአለማዊ ባልሆነ በጊዜ በተወሰነ ማንነት ላይ ስለሆነ የዘመኑ ህይወት ነው የተሰጠን ። አሁን ያለን በእ/ር ህይወት ልክ ዘልአለማዊ[የማይበሰብስ incorruptible] ቢሆን ኖሮ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር መለወጥ ባላስፈለጋን ነበር። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3/18 እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን። ….2
Part 2 ወንድም ቢኒ። ዘላለማዊ ያልካቸው ሁሉ እ/ር የመሎከት የማጣርያ ባህር፣ “በራእይ 20/4 a lake of divine purifcation አስገብቶ ይደመሣቸዋልና። ካስተዋልን ጅማሬ አላቸው ፍፃሜም አላቸው። ለምሳሌ “የሁለተኛው ሞት ፍቺ፤ በዚህ ቦታ ላይ ሁለተኛው ሞት ማለት የመጀመርያው ሞት እና ሲኦል በእሳት ባህር ውስጥ ሲደመሰሱ ማለት ነው። “በራእይ 20/4 ሞትና ሲኦልም የእሳት ባህር ውስጥ ተጣሉ። ይህም “የእሳት ባህር” [ይህ ሃሳብ ሲተረጎም ለሁለተኛ ጊዜ የተጨመረ ነው።] ሁለተኛው ሞት ነው።” “death and hell were cast into the lake of fire. THIS IS THE SCOND DATH.”k.j.v. ትክክለኛው ትርጉም ለአንባቢያን እንዲገባ መሆን የነበረበት “ሞትና ሲኦልም በእሳት ባህር ውስጥ ተጣሉ። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።” እንደ ምናስተውለው ሞትና ሲኦል ወደ እሳት ባህር ሲጣሉ ሁለተኛው ሞት ይባላል። ይሄ መንፈስ ቅዱስ እራሱ ሲያጽፈው ሁለተኛው ሞት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሰጠው ፍቺ ነው።
አስተውሉ ሁለተኛው ሞት ማለት ሰዎች በማይጠፋው እሳት ለዘልአለም ሲቀቀሉና ሲሰቃዩ ማለት አይደለም። አሊያም እንደ ሚባለው ክርስቶስን ያልተቀበሉ ከሞት ቡሃላ የሚጠብቃቸው ኑሮ አፈ ታሪኩ የዘልአለም ሞትና ስቃይ አይደለም። አሁን አይናችን ተከፍቶ ማየት ችለናል ሁለተኛው ሞት ማለት የአንደኛው ሞትና የሲኦል የሞት ግዛት ሁሉ በእሳት ባህር ውስጥ ተጥለው ሲደመሰሱና ሲጠፉ ማለት ነው ። በህይወት መጽሐፍ ያልተገኘ ሁሉ የመተላለፍና የሃጥያትና የሲኦል ተፈጥሮ ማንነቱ የተናወጣቸው አመል ሁሉ የአመፃ ሚስጥር ሁሉ ወደ የመለኮት የማጣርያ የእሳት ባህር ይጣላሉ።
“እ/ር መንፈስ ነው። ዮሃ 4/24” መንፈሳዊው ነገር ለቁሳዊው አለም ለማስረዳት በአካላዊ ቋንቋ መስሎ ያስረዳናል። የብዙ አማኞች ችግር ይሄ ነው። ለዚህም ነው በመንፈስ መገለጥ እንድንረዳቸው በተምሳሌነት የተጠቀመባቸው ምልክቶች፣ SYMBOLS ቀጥታ ከመተርጎም የመጡ ብዙ ችግሮች የተከሰቱት። መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ መጽሐፍ ነው። አስተውሉት እስቲ “የእሳት ባህር” የሚለውን ቃል እንየው “ባህር ምንድነው?” ስፋትና ጥልቀት ያለው በውሃ የተሞላ ቦታ ነው። ይሄኛው ልዩነቱ በእሳት መሞላቱ ነው። በምልክት ወይም በገላጭ ቋንቋ ጌታ ተጥቅሞ ተናገረው። እስራኤል ቀይ ባህር በጌታ ለሁለት ተከፍሎ መንገድ አድርጎላቸው በውስጡ ባለፉ ግዜ ሐዋርያው በጥምቀት አልመሰለውምን ? 1ኛ ቆሮ 10/2 እነዚህም በመለኮታዊ ማጣርያ በእሳት ባህር የሚያልፉትም እንደዚሁ ነው። ለእ/ር እንዲ ሰለጥኑለት በልምድ ውስጥ ያሳልፋቸዋል።
የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም[ለዘመናት aionios] ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4/16 ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል። 17-18 የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም[ለዘመናት aionios] ነው።
(2Cor 4:18 [YLT]) we not looking to the things seen, but to the things not seen; for the things seen are temporary, but the things not seen are age-during. 166 aionios ahee-o’-nee-os
ሌላው ፍርድን መእ/ር ቃል በሚገባ መረዳት አለብን። የማቴዎስ ወንጌል 25-46 እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ። በግሪኩ ዘላለም ቅጣት፥ “kolasin aionion.” Kolasin “punishment ቅጣት፤, chastening አሳዶ መቅጣት፤ , correction ማረም, to cut-off as in pruning a tree to bare more fruit መቁረጥ ልክ እንድን ዛፍ አብዝቶ እንዲያፈራ እንደ መግረዝ.” “aionions” የሚለው ቃል የተረጎመ ነው የቃሉ ስር ወይም፡ ንብረትነቱ “EION” ነው። ትርጉሙም “ዘመን age” ማለት ነው። ሁለቱ የተለያየ ትርጉም ያላቸው ናቸው ማለት አይደለም ። aion(the noun form) ሰዋሶው ወይም ነባር ስም ሲሆን aionions (the adjective form ቅጽል ነው። ሁለቱ ቃላት ሰዋሶው እና ቅፅል ናቸው። ለምሳሌ ሳምንት ሰዋሰው ሲሆን ሳምንታዊ ደግሞ ተቀፅላው ነው። ልክ እለት፦ እለታዊ, አመት ፦አመታዊ እንደሚባለው መለት ነው። Greek word “aion” (Strongs #165) or its adjective form “aionios” (#166).
እንግዲያው ይህን ካስተዋልን ተብሎ መተርጎም የነበረበት “የማቴዎስ ወንጌል 25-46 እነዚያም ወደ ዘመኑ ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘመኑ ሕይወት ይሄዳሉ።” ወደ ዘመየኑ ቅጣቱና የጊዜው ጉዳይ ስናይ ወደ ቅጣት የሚሄዱትም ለዘላአለም ሊደመሰሱ ወይም ሊሰቃዩ ሳይሆን 1,ኛ”Kolasin “punishment ቅጣት፤(እንዲቀጡ), 2,ኛchastening አሳዶ መቅጣት፤(ይህ ቃል chasteneth በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት እንዴት እንደተጠቀመበት እናስተውል KJV Heb 12/6 For whom the Lord loveth he chasteneth, and scourgeth every son whom he receiveth) , 3,ኛcorrection ማረም (Correctional judgement የሚያርም ፍርድ ነው), 4,ኛto cut-off as in pruning a tree to bare more fruit መቁረጥ ልክ እንድን ዛፍ አብዝቶ እንዲያፈራ እንደ መግረዝ.”
አሁንም እናስተውል ጻድቃን ግን ወደ ዘመኑ ሕይወት ይሄዳሉ። የእ/ር ህይወት በባህርዩ ዘልአለማዊ ቢሆንም ያ ህይወት የተወጋው ዘልአለማዊ ባልሆነ ማንነት ላይ ስለሆነ የዘመኑ ህይወት ተባለ ።
(Matt 25:46Open in Logos Bible Software (if available) [YLT])And these shall go away to punishment age-during, but the righteous to life age-during.’ ወንድም ቢኒ።
  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal