የእግዚአብሔርን  ሉዓላዊነት በነገር ሁሉ ላይ ማየት መቻል ለልጆች ከፍ ያለ የብስለት እርከን ነው።


የእግዚአብሔርን  ሉዓላዊነት በነገር ሁሉ ላይ ማየት መቻል ለልጆች ከፍ ያለ የብስለት እርከን ነው። ወንድም ቢኒ።

Brother Binyam T. Alemayehu 8/11/2018

“የእግዚአብሔር  ሉዓላዊነት ስንል በቀላሉ የእግዚአብሔርን በሁሉነገር የበላይነት አለው ለማለት ነው። ሁሉ ከእርሱ በእርሱ ለእርሱ መሆኑን የበላይ መሆኑን መገንዘብንም ጨምሮ ማለት ነው። ወይም የእርሱን ንግሥና እና ራስነት የበላይነት በነገር ሁሉ ላይ ማየት መቻል ማለት ነው። ማለትም በጥሬ ትርጉሙ” እግዚአብሔር  ልእለ ሁሉ ነው “ማለት ነው። እግዚአብሔር ወሰን የሌለው ልእለ ተፈጥሮ ሃያል ነው።

የያዕቆብምን ህይወት ብንመለከት ያዕቆብም የእ/ር ለእልና የገባው በ98 አመቱ ገደማ ነው። ያዕቆብም አስጨናቂዎቹ ዔሳውና ላባ እንካን የእ/ር እጅ እንዳለበት በነሱ ውስጥ እ/ርን ማየት የቻለው በሃለኛ ዘመነቹ ነበር። ማንነቱ ከተቀየረ ቡሃል አስጨናቂውን ዔሳውን ሲያይ በሱ ውስጥ እ/ርን ማየት ተችሎት ነበርና አስጨናቂዎቹ ዔሳውና ሲነግረው “የእግዚአብሔርን ፊት እንደሚያይ ፊትህን አይቼአለሁና፥I have seen thy face, as though I had seen the face of God” አለ። ኦሪት ዘፍጥረት 33/10 ያዕቆብም አለ፦ የእግዚአብሔርን ፊት እንደሚያይ ፊትህን አይቼአለሁና፥ በቸርነትም ተቀብለኸኛልና።

ዔሳው በጡንቻው ሲኖር: ያዕቆብም በጥበብ ይኖር ነበር ይሁን እንጂ ጠቢብ ሰው ጥበቡን ለመልካም ሆነ ለክፉ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ያዕቆብ ዔሳውንና አባቱን ጨምሮ እንዲያታልል ጥበቡን አጣሞ ተጠቅሞበት ነበር። በዚህም ምክንያት በማሰናከል ስራው ተሰዶ ከቤተሰቦቹ ተለያይቶ በሶርያ አገር ከአጎቱ ላባ ጋር መኖር ነበረበት። እሱ ከሱ በባሰ አታላይ ላይ እ/ር ጥሎት አጎቱ እያምታታው 20 ዓመታት ከሱጋር አሳልፏል። ላባ ትንሽ ብልሹነት ያለው ባህሪ ነበረው። የያዕቆብን ደሞዝ አሥር ጊዜ ቀይሮቷል ( ዘፍ 31 :7 ). ይሁን እንጂ አሁንም አጎቱን ልእለብልጠት ተጠቅሞ በመብለጥ በአጎቱ ሜዳና ወጪ ሀብታም ለመሆን ቻለ። በመጨረሻም ያዕቆብ ወደ ከነዓን (ወደ ፍልስጤም) ወደ አባቱ ቤት ተመለሰ።

ወደ ቄው ሲመለስ በያቦቅ ወንዝ በኩል ቆመ። ዔሳው ከ 400 ቀስተኞች ሰዎች ጋር እርሱን ለመገናኘት እየመጣ መሆኑን ሰማ ደነገጠ በእርግጥ ፈራም እና በዚያ ምሽት ለመጸለይ ወጣ ቃሉ እንዲህ ይላል :

‘ያዕቆብ ግን ብቻውን እዚያው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስኪነጋ ድረስ ሲታገለው አደረ። ያም ሰው ያዕቆብን ታግሎ ማሸነፍ እንዳቃተው በተረዳ ጊዜ፣ የጭኑን ሹልዳ ነካው፤ በግብ ግቡም የያዕቆብ ጭን ከመጋጠሚያው ላይ ተናጋ። በዚያን ጊዜ ሰውየው፣ “እንግዲህ መንጋቱ ስለ ሆነ ልቀቀኝና ልሂድ” አለው። ያዕቆብም፣ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው። ሰውየውም፣ “ስምህ ማን ነው?” አለው። እርሱም፣ “ያዕቆብ ነው” አለ። ሰውየውም፣ “ከእግዚአብሔርም (ኤሎሂም) ፣ ከሰዎችም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና ከእንግዲህ ስምህ እስራኤል እንጂ፣ ያዕቆብ አይባልም” አለው። ‘ዘፍጥረት 32:24-28

ያዕቆብ የሚለው ስም ቃል በቃል ሲተረጎም “ተረከዝ ያዥ” “a heel-catcher,” ማለት ሲሆን ያምማለት አሰናካይ፤ ጠላፊ ወይም አታላይ ማለት ነው.። እስራኤል ማለት “እግዚአብሔር ይገዛል ወይም የሚገዛው” “God rules, God commands.”ማለት ነው። አንዳንዶች እንደሚመስላቸውና እንደሚጠቁሙት እስራኤል ማለት “ከእግዚአብሔር ጋር ሆኖ መግዛት” “ruling with God,”ማለት ነው ይላሉ። ሽንገላውም “ከእግዚአብሔርም (ኤሎሂም) ፣ ከሰዎችም ጋር ታግሎ አሸንፈዋል የሚለውን ለማጉላት ሲሆን እውነታው ግን ማንም ከእግዚአብሔር የበለጠ ኃይል የለውም እናም የአዲሱ ስም ትርጉም በግልጽ እንደሚያሳየው ያዕቆብ ያሸነፈው በመሸነፍ መሆኑ ተሰውሮባቸዋል። ያዕቆብ ይህንን የጨዋታውን ውድቀት በማሸነፍ የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት ከተረዳ በኋላ አዲስ ስም ሰጠው ።

” እስራኤል = ‘”እግዚአብሔር ይገዛል ወይም የሚገዛው ፤ ማለት ነው ። የዕብራይስጥ ስሞች ውስጥ ወደ አርባ የሆኑ ስሞች የተቆራኙት ‘ኤል’ ወይም ‘ያህ ‘El’ ወይም ‘Jah’ በስተመጨረሻቸው ካለ የበላይ አድራጊው እግዚአብሔር መሆኑን የሚያሳይ ነው። ለምሳሌ ዳኒኤል cp. Dani -el, ‘ኤል’ የሚለው አድራጊው እ/ር መሆኑን የሚያሳይ ነው። እግዚአብሔር ይፈርዳል God judges.” ስለዚህም ነው.። እስራኤል Isra – el ‘ኤል’ የሚያሳየው የእ/ር አድራጊ መሆኑን ነው “እግዚአብሔር ይገዛዋል ወይም የሚገዛው” “God rules.”ማለት ነው።

 

ያቆብ በመለው ስም ና ተፈጥሮ ሳይለወጥ በፊት [“ተረከዝ ያዥ” “a heel-catcher,” ማለት ሲሆን ያምማለት አሰናካይ፤ ጠላፊ ወይም አታላይ ማለት ነው.።] በብዙታግሎ ተሳክቷል ለ ቡክርና መብቱ ተሟግቷል እና ተሳክቶለት ነበር (25 29-34)። ከሱ በባሰ ጨላጫ ከባርነት ለመውጣት ከላባ ጋር ተሟግቷል እና ተሳክቶለት ነበር (27). በዚህም ‘ከሰው’ ጋር ተሟግቷል እናም ተሳካለት ማለት ነው። አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ይሟገጣል- እናም አልተሳካለትም። ምክንያቱም ሌባውና አሰናካይ ማንነቱን ተወስዶበት የለወጠው ነገር አለ አሁን ያቆብ ሳይሆን የሚያዘው እ/ር ነው። ስም በመጽሓፍ ቅዱስ የሚያሳየው ተፈጥሮንና ባህርይን ነውና። [እስራኤል ማለት “እግዚአብሔር ይገዛል ወይም የሚገዛው” “God rules, God commands.”ማለት ነው። ] ስለዚህም ከዚህ የምንማረው የገባው የተባለ የእ/ር ልጅ ማለትም ወደ ክርስቶስ አእምሮ እየተጠጋ ነው ወይም እየበሰለ ነው በተባለ ቁጥር በእግዚአብሄር ላይ ጥገኝነቱ ጨምረዋል እኔነቱ እየጠፋ ጌታ እየደመቀ ነው ማለት ነው።

ያቆብ ህይወት ትምህርቱ ቢቀርልን ለእያንዳዳችን በጣም አስፈላጊ የሆነውን እናስተውላለን ጌታ ልክ እንደ ያዕቆብ በባህሪያችን ላይ ለውጥ በማድረጉ እኛ እስራኤላዊ ነን እስራኤል Isra – el ‘ኤል’ የሚያሳየው በሂወታችን የእ/ር ገዢነት ፤ አድራጊ መሆኑን ነው። “እግዚአብሔር ይገዛዋል ወይም የሚገዛው” “God rules.”ማለት ነው።. እኛ ሁላችንም ልንማረው የምንችለው ያዕቆብ የተማረው ትምህርት ነው። ከእግዚአብሔር የበለጠ ኃያል ሰው መሆናችንን የምናስተምረው ትምህርት ከንቱ ነው። በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት ላይ እምነት ሊኖረን የሚገባን እና ከሥጋ አማካኝነት በትንሽ በትንሽ ድጋፍ ለእ/ር ብናደርግለት የገባውን ቃልኪዳን ለማስፈፀም ይችላል ብለን እግዚአብሔርንም ሌሎችን መዋሸት ወይም ማጭበርበር አያስፈልገንም። ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች የሚሠራው የሚያስበው ያዕቆብነት ብቻ እንጂ እስራኤል አይደለም። የእ/ር እስራኤል በእ/ር ሉአላዊነው ታምኖ የማንንም ተረከዝ አያሰናክልም።

ስለዚህ፡ ያዕቆብ እስራኤል ሆኖ እንዳልተወለድ አይተናል። እስራኤል ሆኖ የተቀየረው በብዙ ተግባራዊ ትምህርት ቤት እ/ር አሳልፎት በኃላ በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት ከገባው ቡሃላ ነበር ለውጥ የመጣው። ስለዚህ፡ “እስራኤል” የሚለው ቃል የትውልድ ሃረግ genealogy አይደለም። ነገር ግን የባህርይ ለውጥ ህያው ምስክርነት ነው። ከጊዜ በኋላ የያዕቆብ ዝርያዎች “እስራኤላዊያን” ተብለው የተቆጠሩት እንደገና በባህርይ ለውጥ እስራኤል ተብሎ ድጋሚ ከተሰየመው ሰው ዘር መሆናቸውን ለማሳየት ነው።

ይህ የመጀመሪያው ቁልፍ ነገር የስያሜው ትርጉም ከተረዳን እስራኤላዊ ማነው ብለን ስናጠና በቀላሉ ይገባናል።

ወደ ሮሜ ሰዎች 2:28 በግልጥ አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ አይደለምና፥ በግልጥ በሥጋ የሚደረግ መገረዝም መገረዝ አይደለምና፤29 ዳሩ ግን በስውር አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ ነው፥ መገረዝም በመንፈስ የሚደረግ የልብ መገረዝ ነው እንጂ በመጽሐፍ አይደለም፤ የእርሱ ምስጋና ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም

*ወደ ሮሜ ሰዎች 9:6 ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የተሻረ አይደለም። እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና፤ የአብርሃምም ዘር ስለሆኑ ሁላቸው ልጆች አይደሉም፥7 ነገር ግን፦ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል ተባለ።

8 ይህም፥ የተስፋ ቃል ልጆች ዘር ሆነው ይቆጠራሉ እንጂ እነዚህ የሥጋ ልጆች የሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም ማለት ነው።26 እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም በተባለላቸውም ስፍራ በዚያ የሕያው እግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉ ይላል።

በቅድሚያ እነዚህ የ-ሥ-ጋ  ል-ጆ-ች  የ-ሆ-ኑ የእ-ግ-አ-ብ-ሔ-ር  ል-ጆ-ች  አ-ይ-ደ-ሉ-ም :። ተስፋው በክርስቶስ ላለ ብቻ ነው። በክርስቶስ እስኪሆኑ ድረስ በስጋ አይሁዳዊ የሆኑ አይሁዳዊ አይደሉም በስጋ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉም ይህ መንፈሳዊ እስራኤላዊነት አይመለከታቸውም። አሁን ያሉበት ተፈጥሮ ጌታ እንዳላቸው። በክርስቶስ ካልሆኑ የማን ልጆች እንደሆኑ ይታወቃል። በክርስቶስ እንዳልሆነ እንደማንም ሰው በባህርይ የአባታቸው የዲያቢሎስ ልጆች ናቸው። የእፉኝት ልጆች። የዮሐንስ ወንጌል 8/41 እናንተ የአባታችሁን ሥራ ታደርጋላችሁ አላቸው። 42 ኢየሱስም አላቸው፦ እግዚአብሔርስ አባታችሁ ከሆነ በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፤ እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁምና። 44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ። ማወቅ ያለብን ግን በእ/ር አጀንዳ ውስጥ እንደ ሰው ሁሉ በክርስቶስ ሁሉ ይድናሉ።  ወደ ሮሜ ሰዎች 9:6 ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የተሻረ አይደለም። እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና፤ የአብርሃምም ዘር ስለሆኑ ሁላቸው ልጆች አይደሉም 8 ይህም፥ የተስፋ ቃል ልጆች ዘር ሆነው ይቆጠራሉ እንጂ እነዚህ የሥጋ ልጆች የሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም ማለት ነው

 

አሁን እናስተውል በአሮጌው ኪዳን ቃል የነበረው እ/ር ስጋ ከመልበሱ በፊት ጌታ በነብዩ በኩል ከእስራኤልና ከይሁዳ ጋር ያለው ቃል ኪዳን የጋብቻ ቃል ኪዳን እንደሆነ አስጠንቅቆ ተናግረዋል። በአሮጌው ኪዳን የነበረው ጋብቻ ከባሪያይቱ እንጂ ከጨዋይቱ ጋር እንዳላሆነ ቃሉ ይነግረናል። በገላትያ 4 እነዚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ኪዳኖች ናቸውና። ከደብረ ሲና የሆነችው አንዲቱ ለባርነት ልጆችን ትወልዳለች፥ እርስዋም አጋር ናት።25 ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ ሲና ናት፤ አሁንም ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና። ባሪያ በመሆንዋም ለባልዋ መታዘዝ ግዴታዋ ነው።[እየሱስ ቃል የነበረው እ/ር ስጋ ከመልበሱ በፊት በነበረው ቅርጽ]የሰጣት ተስፋ አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ የሚል በሁኔታዎች የተደገፈ ቃል ኪዳን ነበረ። ኦሪት ዘጸአት 19/5 አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤6 እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ። ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው።

ይህ የአጋር አይነት የጋብቻ ግኑነት ነው። እስራኤል ከእ/ር ጋራ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ በጋብቻ በተሳሰሩ ጊዜ ያለውንም ያሳያል። ይሄ የአሮጌው ኪዳን ጋብቻ ነው። በዘፅአት 19/5 እስራኤል ለባልዋ ለመታዘዝ መማል ነበረባት። እስራኤልም የእ/ር አገልጋይ ሚስቱ ሆነች። ይሄ መጥፎ አይደለም በዛው አንጻርም እ/ር ከህዝቡጋር ሙሉ ለሙሉ የሚፈልገው ጋብቻ አይደለም። የተሻለ ህብረትን ይሻልና ለዚህም ነበር በአጀንዳው ውስጥ እስራኤልን ሊፈታት እቅዱን ያስቀመጠው።

እስራኤል ለብዙ ክፍለዘመን ታማኝ ሳትሆን ዘማዊሆና አስቸግራው ጌታ በመጨረሻ የፍቺ ወረቀትዋን ሰጣት

“ትንቢተ ኤርምያስ 3፡8 ከዳተኛይቱም እስራኤል ስላመነዘረች ስለዚህ ፈትቻታለሁ የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን እንዳልፈራች እርስዋም ደግሞ ሄዳ እንደ ጋለሞተች አየሁ።

Jer 3፡8 And I saw, when for all the causes whereby backsliding Israel committed adultery I had put her away, and given her a bill of divorce; yet her treacherous sister Judah feared not, but went and played the harlot also.” ከዛም በተሻለ ነገር ላይ የተመሰረተውን አዲሱን ኪዳን አደረገ።

ጌታ እስራኤልን አግብቷት ባይሆን ኖሮ ፈፍቺ ወረቀት መስጠት ባላስፈለገው ነበር። ይህን ሲያደርግ እራሱ የሰጠውን የጋብቻ ህግ እያከበረ ነበር፡

‘አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባ በኋላ፣ አሳፋሪ ነገር አግኝቶባት ባይደሰትባት፣ የፍቺ ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ይስደዳት። ከቤቱ ከወጣች በኋላ ሌላ ባል ብታገባ፣ ሁለተኛ ባሏም እንደዚሁ ጠልቷት የፍቺ ወረቀት በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ቢሰዳት ወይም ቢሞት፣ ከዚያ በኋላ የፈታት የመጀመሪያ ባሏ፣ የረከሰች በመሆኗ እንደ ገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት አስጸያፊ ነው። አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኀጢአት አታምጣ። ‘ዘዳግም 24:1-4

ይህ ህግ ትንቢታዊ እንደ ነበር እ/ር ከህዝቦች ጋር እንዴት እንደሚሰራም በእስራኤል ጋብቻ ላይ ያሳየናል።

እምናወራው ያለው ስለ መንፈሳዊ ነገር እደሆነ እንደ ተሰመረበት ይሁንና መንፈሳዊውን ጋብቻ በምሳሌ የሚያስስረዱ ሁለት አይነት የጋብቻ ግንኝነቶች እንዳሉ ሳይወሳ መታለፍ የሌለበት ነው።

በገላቲያ4: 22/31-22 አንዱ ከባሪያይቱ አንዱም ከጨዋይቱ የሆኑ ሁለት ልጆች ለአብርሃም እንደ ነበሩት ተጽፎአልና።

23 ነገር ግን የባሪያይቱ ልጅ እንደ ሥጋ ተወልዶአል፥ የጨዋይቱ ግን በተስፋው ቃል ተወልዶአል።

24 ይህም ነገር ምሳሌ ነው፤ እነዚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ኪዳኖች ናቸውና። ከደብረ ሲና የሆነችው አንዲቱ ለባርነት ልጆችን ትወልዳለች፥ እርስዋም አጋር ናት።

25 ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ ሲና ናት፤ አሁንም ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና።

26 ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት የምትኖር ናት እርስዋም እናታችን ናት።

27 አንቺ የማትወልጅ መካን፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፥ እልል በዪና ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአል።

28 እኛም፥ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን።

29 ነገር ግን እንደ ሥጋ የተወለደው እንደ መንፈስ የተወለደውን በዚያን ጊዜ እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው።

30 ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? የባሪያይቱ ልጅ ከጨዋይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት።

31 ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጨዋይቱ ልጆች ነን እንጂ የባሪያይቱ አይደለንም።”

 

ሐዋሪያው ስለ ሁለት ኪዳኖች በሁለቱ ሚስቶች እንደ ሚመሰሉ ነግሮናል ማለትም አጋርና ሳራ ባሪያይቱና (bondwoman) ነጻ ያልሆነችው ሴትና ጨዋይቱ (freewoman) ነጻይቱ ሴት ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሁለት የተለያዩ የጋብቻ አይነቶች ነበሩ። ሰውየው ባሪያይቱን ካገባ ያላቸው ግንኝነት የጌታና የባሪያ ነው። እዲህ አይነትዋ ሚስትም ያላት መብት ውስን ሲሆን በቤተሰብ ውሳኔ ውስጥ ምንም ድምጽ የላትም። ባልዋ እድሉን ሊያቀርብ ይችላል ነገር ግን እደዛ እዳያደርግ የተወሰነ ነበረ።

ይህ የአጋር አይነት የጋብቻ ግኑነት ነው። እስራኤል ከእ/ር ጋራ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ በጋብቻ በተሳሰሩ ጊዜ ያለውንም ያሳያል። ይሄ የአሮጌው ኪዳን ጋብቻ ነው። በዘፅአት 19/5 እስራኤል ለባልዋ ለመታዘዝ መማል ነበረባት። እስራኤልም የእ/ር አገልጋይ ሚስቱ ሆነች። ይሄ መጥፎ አይደለም በዛው አንጻርም እ/ር ከህዝቡጋር ሙሉ ለሙሉ የሚፈልገው ጋብቻ አይደለም። የተሻለ ህብረትን ይሻልና ለዚህም ነበር በአጀንዳው ውስጥ እስራኤልን ሊፈታት እቅዱን ያስቀመጠው።

“ትንቢተ ኤርምያስ 3፡8 ከዳተኛይቱም እስራኤል ስላመነዘረች ስለዚህ ፈትቻታለሁ የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን እንዳልፈራች እርስዋም ደግሞ ሄዳ እንደ ጋለሞተች አየሁ።

Jer 3፡8 And I saw, when for all the causes whereby backsliding Israel committed adultery I had put her away, and given her a bill of divorce; yet her treacherous sister Judah feared not, but went and played the harlot also.” ከዛም በተሻለ ነገር ላይ የተመሰረተውን አዲሱን ኪዳን አደረገ።

አዲሱ ኪዳን የተመሰለው በነጻይቱ ሴት በሳራ ነው። በአዲሱ ኪዳን የተመሰረተው ጋብቻ መታዘዝ በሚለው ሃሳብ ላይ የተመሰረተ አይዳለም። ሁለት የተጋቡ ወንድና ሴት ከተስማሙ እዲታዘዙ መናገር የሚያስፈልግ አይደለም። አንዳቸው አንዳቸው አንድን ነገር እንዲያርጉ በስልጠን የሚያዙበት ምክንያት የለም ስምምነቱ አለና ። የቤተሰብ ስልጣን የሚገለጠው የስምምነት እጥረት በመካከላቸው ካለ ነው።

በዚህ ምንያት እ/ር ድል ነሺ ካልሆኑበቀር ለማግባት ሃሳቡም የለውም። ድል ነሺነው ከእ/ር ጋር ወይም ከጌታ እየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚስማማው። ድል ነሺ የጌታን አይምሮ ያውቃል አሊያም እንዲያውቀው ይሻል። የእ/ርን ፈቃድ ሲያገኘውም ከፈቃዱ ጋር ተስማምቶ እራሱን ያገኘዋል። አልያም ከፈቃዱ ጋር ፍጹም አንድ እስኪ ሆን መረዳትን ለመቀበል እስከ መጨረሻው ይሻል። በመንፈሳዊ እድገት የመማር ሂደት ወስጥ በእርግጥም ድል ነሺው የእ/ርን ሃሳብ ቶሎ ላያስተውል ይችላል:: እንደ እ/ር አገልጋይ እ/ርን ይታዘዛል። ሙሉ ግንዛቤን ገና ስላላገኘ ፈቃዱን በማድረግ ብቻ ገና አልረካም የእ/ርን አይምሮ እስኪ ያገኘውና ገብቶት በሙሉ ስምምነት እራሱን እስኪ ያገኘው ወደ ፊት ይዘረጋል።

ከእ/ር ጋር አለመስማማት ምክንያቱ የመረዳት እጥረት ነው። መላው አለምን እ/ር እንደሚያየው ብናየው እ/ር የሚያደርገውን ሁሉ ለምን እደሚያደረገው ያለመስማማት ባልኖረ ነበር። ችግሩ አለም ሁሉ መለኮት ከሚያየው አካያ አናየውም። ይህ አብ አንድን ሰው ወደ ጌታ እንደ ሳበው በጌታ እንደሆነ የሚገኝ ለውጥ አይደለም። በመንፈስ ሲሞላም በነገር ሁሉ ከእ/ር ፈቃድ ጋር ሙሉ ለሙሉ መስማማቱ ወድያው አይመጣም። ከእ/ር ጋር አብሮ መጔዝን ይጠይቃል አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ የእ/ርን ባህርይ አይበዘብዝም አብሮ ጊዜ ማሳለፍን ይጠይቃል ደቀ መዛሙርቱ ሰዎች ከንግግራቸው የተነሳ ከእየሱስ ጋር እደነበሩ ያወቁት ለሰዎስት አመት ተኩል አብረው በመውጣት በመግባት ባህርዩን በከፊል ስለ ተካፈሉ ነው። ወንድም ቢኒ። Brother Binyam T. Alemayehu 8/11/2018

 

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal