
እ/ር ለምን ተቃራኒ ሃይላትን ፈጠረ? ወንድም ቢኒ።
የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው? ከሚገልጥልን በቀር ማስተዋል አይቻልም መንፈሳዊው ነገር ከሰው ማስተዋል በላይ ግዙፉ ነውና። ቢሞከርም ከውቂያኖስ ይልቅ ጠሊቅ ከሆነው ምክሩ በማንኪያ ጨልፈን እደመረዳት ያህል ነው። ስለ ተቃራኒ ሃይላት ስናስብ መገንዘብ ያለብን ከሚቋቋመን ተቃራኒ ነገር የምንማረው ነገር አለ። ለዚያም ነው እ/ር ተቃራኒ ሃይላትን የፈጠረው። በትንቢተ ኢሳይያስ 45፡7 ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ እነነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። አዎን ሁሉን መፍጠሩን እ/ር ሃላፊነቱን ወስደዋል:: እራስ በራሳቸው የሚቃረኑትም ጭምር ማለት ነው። ለማሰብ ያህል መራራና ጣፋጭ፤ ሃዘንና ደስታ፤ ድሃና ባለጠጋ፤ ጨለማና ብርሃን፤ መልካምና ክፉ፤ ህግና ጸጋ፤ ተፈጥራዊ ነገሮች ና መንፈሳዊ ነገሮች፤ ሞትና ህይወት፤ እስራትና ነጻነት፤ ለምን ብሎ እ/ር እንደዚህ በጥብቅ የሚቃረኑ ሃይላትን ፈጠረ?
አዎን ማየት ያለብን እ/ር መንገዱን ሊያስተምረን ተቃራኒ ሃይሎችን መፍጠር ነበረበት። መልካምን እንዴት እንረዳው ነበረ ክፉ ባይኖር ኖሮ? የእ/ርን ረቂቅ ጥበቡን በመጠኑም ቢሆን ልንገነዘበው ይገባል። ፉጡራኑን ወደ ብስለት ለማምጣት በምን እደሚያሳልፈን ስናስተውል ይደንቃል:: ተፈጥሮውና ባህርዩ በሰው ውስጥ ይገለጥ ዘንድ የሚጠቀመው ተቃራኒ ሃይላትን ነው:: “መዝሙረ ዳዊት 119፡71 ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።” መጽሐፈ ኢዮብ 36፡15 …. በመከራም ጆሮአቸውን ይገልጣል። Job 36፡15 He… openeth their ears in oppression.
አንድ ሰው በእብራዊን ቋንቋ የጌታን ድምጽ ሰማሁ ካለ ፈጽሞ ሰምቶ ፈጽሞ መታዘዙን የሚያሳይ ነው። ሰምቶ ካልታዘዘም ፈጽሞ አልሰማም። በመገለጥ እንዲሰማም በሌላ ሂደት ያልፋል። “በመከራ ጆራቸውን ይከፍታል። እዮብ36፡15 በእብራይስጥ መከራ የሚለው ውጥረት ይለዋል። አንዳንድ ጊዜ ለምን ይሄ ሁሉ ውጥረት በመንገዳችን እንደ ሚያልፍ እንደነቃለን። እንደ ዛም ሆኖ ነገር ሁሉ ተያይዘው ለበጎ እንዲደረግ እንረዳለን። በብዙ መከራ ማለፋችንም ለብዙ አላማ እንደሆነ እናውቃለን። ከዛ ውስጥ አንዱ ጆራችን እዲከፈት ነው። ጳውሎስ የደቀ መዛምርቱን ልብ በማበረታታትና በእምነታቸወ ጸንተው እንዲሩ በመምከር “ወደ እ/ር መንግስት ለመግባት በብዙመከራ (ግሪክ፦ pressure, እደአገባቡ ቃሉ ሲተረጎም ውጥረት ግፊት መገፋፋት ተጽኧኖ የሚያመጣ ውጥረት )ማለፍ አለብን “” ሐዋ14፡22 ይህም ውጥረት ከአሮጌው አውጥቶ ወደ አዲሱ ተጭኖ ያስገባናል። እ/ር አምላክ ጥበበኛ ነው። አንዱን ውጥረት ከአንድ ነገር ለማውጣትና በተመሳሳይ ሰአትም የስጋን ፈቃድ ሰብሮ የመንፈስን ድምጽ ወደ መስማት ግዛት ያመጣናል።
አብዛኛውን ጊዜ እ/ር በሂወታችን አንድ ነገር እዲያደረግ እንፀልያለን ስራውን ይጀምራል ከዛም እርሱን በቃወም እንዋጋዋለን እርሱ ግን ለጸሎታችን መልስ እየሰራ ነው ለምን ግን? አዎን ይህን የምናደርገው መንገዱን ስለ ማንረዳ ነው:: እኛን ለማስተማር የሚጠቀምባቸውን ተቃራኒ ሃይላት አናስተውለውም አይገቡንንም። እ/ር የፍቅር ሰው እድትሆኑ ከጠየቃችሁት ለጥላቻ ያጋልጣችሃል። ይህን የሚያደርገውም ጥላቻንና ፍቅርን አይታችሁ ምን እደሆኑ እንድታውቁና ምንን እንደሚያዘጋጁ እድትረዱ ነው። ይህንንም ወይ በሂወታቹሁ ወይ በሌላ ሰው ህይወት ሊሆን ይችላል። ይሄ ለምሳሌ ያህል ነው እንጂ ይህን የሚረጋግጡ ብዙ ነጥቦችም አሉ። እናተም የምትገነዘቡትም ብዙ ይኖራል። በእግዚአብሄር አሰራር ውስጥ የሚጠቀምባችውን ተቃራኒ ሃይላት ካላስተዋልን ለመማር እንቸገራለን። እራሳችንን በፊቱ ዝቅ አድርገን ለመንገዶቹ የነቃ ህሊና ይኑረን። ወደ መለኩና አምሳሉ ሊያመጣን ሊሞርደን ተቃራኒ ሃይላት እደሚጠቀም መገንዘባችን ውስጥ ሃይል አለው። ምን አይነት ታላቅና በጥበብ ሁሉ የተሞላ አምላክና አባት ነው ያለን? ጌታ በማርቆስ ወንጌል 9፡49 ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፥ ሲል እውነቱን ነገሮናል እውነት የሆነውን አስቡ ተብለናልና እውነት የሆነውን እናስብ። ወደ ዕብራውያን 5፡8 ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ እኛ ከሱ አንበልጥምና መታዘዝን እንማር ዘንድ በሚያሳልፈን መንገድ ሁሉ ፈቃድህ ይሁን እንጂ ፈቃዳችን አይሁን ማለት እንችል ዘንድ የእ/ር ጸጋ ይርዳን። ሰላም ይሁን። አሜን! July 14, 2011 Brother Binyam T. Alemayehu Wongel Radio