ክጥያቄና መልስ የተወሰደ። ወንድም ቢንያም ለወንድም አስመሮም ክፍል 2የበጎችን ና ፍየሎች ተምሳሌት
በመጨረሻው በመምጣቱ የተነገረ ነው ያልከው?ከዛ ቡሃላስ ሌላ ዘመን ወይም እንደ አንተ እይታ ሌላ ዘልአለም አለው ወይ ነው ? ጥያቄህ, ልጠይቅህ እስቲ በ 90 A.D. ከጌታ ትንሳኤ ከ56 አመት ከስድስት ወር ገደማ ቡሃላ አሁን የመጨረሻው ሰአት ነው። ተብሎ ተጽፎ ነበር ከዛ ቡሃላ ሌላ ዘመን ነበረን? ወይም እንደ አንተ እይታ ሌላ ዘልአለም ነው የጀመረው?አዎን ሌላ ዘመን ወይም ዘመኖች እንጂ ሌላ ዘልአለም አልጀመረም እነሆ ቀጠሎማ ከ2000 ሺ ዘመናት ቡሃላም ቢሆን እ/ር የሰጠውን ቃሉን አሁንም የሚያወሩት ብዙ ሰራዊቶቹ ናቸው። በነገራችን ላይ ሌላ ዜና አለኝ የዘመን ፍፃሜ እንጂ የአለም ፍፃሜ የለም። በእርግጥ የመጨረሻው ጠላት ሞት ሲደመሰስ የቀደመው ሥርዓት ሁሉ ያልፋል። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2፥18 ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።
“ትንቢተ ዳንኤል 12/2 “Olam” ነው የሚለው አይሰራም ብለሃል በደፈናው እንደዛ አይባልም ማስረጃ ካለህ ማቅረብ ማንም ሲናገር እንደ እ/ር ቃል ይናገር እንደሚል አልዘነጋሃውምና። መቸም ለፈጣን ጆሮ ግማሽ ቃል ይበቃዋልና እርግጠኛ የሆነ ሌላ ልጨምርልህ ወደ ዕብራውያን 1/8 ስለ ልጁ ግን፦ አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። Heb 1/8 But unto the Son he saith, Thy throne, O God, is for ever and ever: a sceptre of righteousness is the sceptre of thy kingdom. የዕብራውያን ፀሃፊ የጠቀሰው ከመዝሙር45:6 ነው። መዝሙረ ዳዊት 45/6 አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘላለም “Olam” ነው፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። አስተውል የተጠቀመውን ቃል “Olam” አሁን የዕብራውያን ፀሃፊ ያንኑ ቃል የጠቀሰውን ሲጠቀም “EION” ተጠቅመዋል ወደ ዕብራውያን 1/8 እና መዝሙረ ዳዊት 45/6 አነፃጽጽረው አሁን በእርግጠኝነት “Olam” በእብራይጥና “EION” በግሪክ እኩል የሆነ ትርጉም አላቸው።
(Heb 1:8 [YLT])and unto the Son: ‘Thy throne, O God, is to the age of the age; a sceptre of righteousness is the sceptre of thy reign;
(Heb 1:8 Jonathan Mitchell’s New Testament Translation 8. Yet to the Son, “Your throne, O God, [is] into the age of the age, and the scepter of straightness, [is] a scepter of Your [p46, Aleph & B read: His] kingdom.
“ትንቢተ ዳንኤል 12/2 በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም“Olam” ጕስቍልና” ይሄ ፍፃሜ የሌለው የዘልአለም ቅጣትን ለማሳየት የተነገረ አልነበረም እ/ር የሚቀጣው ሰዎች እስኪ ታረሙና ንስሃን እስኪ ሰጣቸው ድረስ ነው። “Olam” ተብሎ መተርጎም የነበረበት “indefinitely ላልታወቀ ጊዜ” ወይም “age-lasting እድሜ ልክ.” ነበር። በጥንቃቄ በዚህ መልክ ቢተረጎም ኖሮ ብዙ አወዛጋቢ ሃሳቦችን ባጠራ ነበር።
ብራዘር, በሁለት ቃላት ፍቺ ተሰናከልክን? ከዚያም በላይ ጠብቅ። ከእውቀት ከፍለህ አውቀሃልና ተዘጋጅ ገና ከሚወድህ እ/ር ዘንድ ፍጹም የሆነ እውቀት ሲመጣ የቀድሞው እውቀትህ ሊሻር የግድ ነው። “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13/8 … እውቀትም ቢሆን ይሻራል። 9 ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፥ …. 10 ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው ይሻራል።” መቸም የዘመን ፍፃሜ እንጂ የአለም ፍፃሜ የለም። ስል በጆንያ ሙሉ ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላል ይህን በትንሹ እንየውና እ/ር ቢረዳን ወደ ጥያቄው እንሄዳለን።
በቅድምያ አይከብድህም ወይ ላልከው ጥያቄ, እንግዲህ አይከብደኝም ብራዘር, ቀንበሬ የዋህነትና የልብ ትህትና የተባለው ልዝብ ነው, ስለዚህ ሸክሜም ቀሊል ነው። ከጌታየ የተነሳ ብፁዕ ወይም (ደስተኛ) ነኝ ። የማቴዎስ ወንጌል 11/29 ። ከኔ ወድያ አዋቂ የለም እኔን እመኑኝ አላልኩም። አንተ አልክ! የሚታመን እግዚአብሄር ቃል እያለ ይህን ምን አመጣው? ነገር ግን እ/ር እንኴን በኔ የእ/ር ልጅ ከቃል የተውለድኩ ቀርቶ የነብዩን እብድት ይመልስ ዘንድ በአህያም ተናግረዋል። “2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2/16 ነገር ግን ስለ መተላለፉ ተዘለፈ፤ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩን እብድነት አገደ።” አምላክህ ወደኔ ያቀረበውን ለመናገር ግን ስጋና ደምን አላማክርም እርሱ ብቻ ወደ እውነት ሁሉ ይምራኝ እንጂ ከተሳሳትኩም የሚታረም ልብ አለኝ። መጽሐፍትንና የእ/ር ቃል ካወቅን አንስትምና። ደግሞም አምላኩን የሚያውቅ ህዝብ እየበረታ ይሄዳልና። እኔም በወንጌል አላፍርም የእ/ር ሃይል ለማዳን ነው እንጂ ለማጥፋት አይደለም። የቀደሙት የምድር ሃያላና ሊቃውንት የእ/ር ናቸው እ/ር አምላክም ለክብሩ ተጠቀመባቸው መርሳት የሌለብን ግን እነሱም እንደኛ ሰው ነበሩ። አሁንም ይሰራል። የያዕቆብ መልእክት 5/17 ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥።
በቅድምያ የዘመን ፍፃሜ እንጂ የአለም ፍፃሜ የለም። ማለቴ ከእውነት ነው! በክርስቶስ ወንድሜ እንደመሆንህ እልሃለሁ ጊዜ ውሰድና በትኩረት የእ/ርን ቃል እራስህ አጥና ከዛም እኔም ሆነ ሌላ ሰው በሚናገረው አትሰናከልም። የአለም ፍፃሜ ከሚለው ላይ “aion” ከሆነ የትርጉሙ ምንጭ የዘመን ፍፃሜ ብለህ ተረዳው የአለም ፍፃሜ ቢሆን ኖሮ የፀሐፊው መልእክት በ”aion ዘመን” ፈንታ “kosmos አለም” በተጠቀመ ነበርና። “ይሄ የእየሱስ ክርስቶስ ዲክሽነሪ ነው። ኪኪኪ ”
ለምሳሌ ይህን ክፍል ብታጠናው ሁለቱም ቃላት በልዮኡነት ተጠቅሞባቸው ታገኛቸዋለህ (KJV Matt 13:38 And the field is the world [አለም kosmos]; and as for the good seed, these are the sons of the kingdom; and the tares are the sons of the evil one; 39 and the enemy who sowed them is the devil, and the harvest is the end of the age [ዘመን aion]; and the reapers are angels. 40 “Therefore just as the tares are gathered up and burned with fire, so shall it be at the end of the age [ዘመን aion]..
Strong’s Concordance
kosmos: order, the world
Original Word: κόσμος, ου, ὁ
Part of Speech: Noun, Masculine
Transliteration: kosmos
Phonetic Spelling: (kos’-mos)
Short Definition: the world, universe
Definition: the world, universe; worldly affairs; the inhabitants of the world; adornment.
HELPS Word-studies
2889 kósmos (literally, “something ordered”) – properly, an “ordered system” (like the universe, creation); the world.
[The English term “cosmetic” is derived from 2889 /kósmos, i.e. the order(“ensemble”) used of treating the face as a whole.]
ባለፈው እንደ አነሳሁት እግዚያብሄር ያሳይህ አንዱ ዘመን “aion” የሚለው ቃል ወደ ስንት ተበታትኖ እንደ ተተረጎመ age ዘመን 2 ጊዜ, beginning of the World የአለም ጅማሬ{2} ጊዜ, for ever and ever ከዘላለም እስከ ዘላለም,(8) course{1}ጊዜ World አለም{32} ጊዜ eternal ዘላለማዊ {42}ጊዜ, world began የአለም ጅማሬ{1}ጊዜ forever ዘልአለም {27}, for evermore ከዘልአለም ላይ{2}, እነዚህ ሁሉ ዘመን ወይም እንደ አገባቡ ዘመን፤ ለዘመናት፤ ለዘመኑ፤ ለዘመናትም፤ ለዘመነ ዘመናት፤ ከዘመናት ወዘተ… ተብሎ በቀላሉ በዚህ መልክ መተርጎም ነበረበት።
በአዲስ ኪዳን ”ዘልአለም Eteernal, Everlasting” የሚለው ቃል ከዋናው የግሪኩ ቅጂ ላይ “aionions” ከሚለው ቃል የተረጎመ ነው የቃሉ ስር ወይም፡ ንብረትነቱ “EION” ነው። ትርጉሙም “ዘመን age” ማለት ነው። ሁለቱ የተለያየ ትርጉም ያላቸው ናቸው ማለት አይደለም ። aion(the noun form) ሰዋሶው ወይም ነባር ስም ሲሆን aionions (the adjective form ቅጽል ነው። ሁለቱ ቃላት ሰዋሶው እና ቅፅል ናቸው። ለምሳሌ ሳምንት ሰዋሰው ሲሆን ሳምንታዊ ደግሞ ተቀፅላው ነው። ልክ እለት፦ እለታዊ, አመት ፦አመታዊ እንደሚባለው መለት ነው። Greek word “aion” (Strongs #165) or its adjective form “aionios” (#166).
እንደ አንድ አንድ ሃሰተኛ ነብያት ትንቢት የአለም ፍፃሜ በዚህና በዛ ዘመን ወይ ቀን ሲል እኛ ካመንአቸው መንፈሳዊ ሚስኪን ነን። እስቲ ይህን እናስተውል። ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ ብለዋል። “ኦሪት ዘጸአት 20/6 ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።” ሺህ ትውልድ ? መቸም እ/ር ተናገረ ማለት ሆነ ማለት እንደሆነ እናውቃለን። ቃሉ ከአፉ ወጣ ማለት ሳይፈፀም በከንቱ ወደሱ እደማይመለስም እንገነዘባለን። ቀመሩን አስተውሉ ስቲ, ሺህ ትውልድ ? የአንዱን ትውልድ የእድሜ ጣራ በአማካይ በትንሹ 50 አመት ይሁን ብንል እንኴን, ብራዘሮች እና ሲስተሮች, አለም ባይፈፀምም እንደነ ደምስሰው እይታ ብናስበውና ፍፃሜው ቢያንስ ገና 50ሺ አመት ይቀረዋል ያስቃል… ጌታውን የሚጠብቅ አያፍርምና ቢያንስ 50ሺ አመት ብቻ ጠብቁ ኪኪኪ…።
በዚህ አጋጣሚ አንድ መንፈሳዊ ቀልድ ትዝ አለኝ አንዱ ነው አሉ እ/ር ይገለጥለትና ይነጋገራሉ ወጣቱ ጠየቀ ጌታ ሆይ አንድ ሺ አመት በአንተ ዘንድ እንደ ምን ያህል ነው? አለው ጌታም እንደ አንድ ቀን ነው ልጄ እንዳውም እንደ አንድ ሴኮንድ ነው አለው። ልጁም ይገርማል አለና, አንድ ሚሊዮን ብርስ በአንተ ዘንድ እንደ ስንት ነው? አለው። ጌታም እንደ አንድ ሳንቲም ነው ልጄ አለው። ልጁም ቀበል አድርጎ አንድ ሳንቲም ስጠኝ ጌታየ አለው። ጌታም መልሶ አንድ ሴኮንድ ጠብቀኝ ልጄ አለው ይባላል።
ወደ ቁምነገሩ እንመለስና ብራዘር ዘመናትን በልጁ ለአላማ እንደ ፈጠረው ታውቃለህ? መቸም የአማርኛው ትርጉምን ሳይቀር ቃል በቃል ትርጉሞችን የሚያርም ትውልድ እ/ር ማስነሳቱ የማይቀር ነው ብየ አስባለሁ።ሌላው ቀርቶ KJV ብዙ ጊዜ መታረሙን ታውቃለህ? “የተጠቀሰ Since the first King James Bible rolled off the press in 1611 to the King James Bible you buy off the shelf today, there have been – are you ready – there have been a grand total of 421 word changes! That’s it!” አማርኛውም ከ5 ጊዜ በላይ ታርመዋል ትርጉም ስለሆነ እርማት ያለ ነገር ነው። የማይነካካው ዋናው ቅጂ ብቻ ነውና። ለምሳሌ በአማርኛው “ዓለማትን በፈጠረበት” ይለዋል መሆን የነበረበት “ዘመናትን በፈጠረበት” ነበር እንዳንረሳ ሁሉን የፈጠረም እርሱ ነውና። “ወደ ዕብራውያን 1/2 ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤” ትክክል ከተረጎሙት መካከል ግን
(Heb 1:2 [YLT]) in these last days did speak to us in a Son, whom He appointed heir of all things, through whom also He did make the ages;
(Heb 1:2 [Weymouth]) has at the end of these days spoken to us through a Son, who is the pre-destined Lord of the universe, and through whom He made the Ages.
(Heb 1:2 Jonathan Mitchell’s New Testament Translation). upon the last of these days spoke to us in a Son whom He placed [as; to be] Heir of all [ – being both masc. & neut., this could also read: One who receives all men as an allotment; or: heir of all things; One who received everything as his allotted inheritance] through Whom He also made (formed; constructed) the ages (eons).
የበጎችን ና ፍየሎች ተምሳሌት
እንደ ሚመስለው ጌታ እየሱስ ስለ ተናገረው ስለዚህ ድንቅ ምሳሌ ተደጋግሞ በተለያየ መልኩ በብዙ ወገኖች ፍቺው ቢነገርም የተነገረው ጋር የተላለፉ ብዙ ወገኖች ያሉ ይመስላል በትንሹ ቢረዳ ቀለል ባለ መልኩ ለማቅረብ እሞክራለሁ።
የማቴዎስ ወንጌል 25-41 በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
(መተርጎም የነበረበት) የማቴዎስ ወንጌል 25-41 በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘመኑ እሳት ከእኔ ሂዱ። “ይሄ የእየሱስ ክርስቶስ ዲክሽነሪ ነው። ”
(Matt 25:41 [YLT])
Then shall he say also to those on the left hand, Go ye from me, the cursed, to the fire, the age-during, that hath been prepared for the Devil and his messengers;
(Matt 25:41 [Weymouth])
“Then will He say to those at His left, “‘Begone from me, with the curse resting upon you, into the Fire of the Ages, which has been prepared for the Devil and his angels.
Matthew 25:41. Jonathan Mitchell New Testament “At that point, He will also say to those at the places on [His] left, ‘[You] folks having been brought under the curse, continue proceeding on your way, away from Me, into the eonian fire (the fire pertaining to and having its source in the Age; the age-lasting fire; the fire having the quality and characteristics of the Age) – the one having been prepared and made ready for the person who thrusts [something] through [folks] (the adversary; the devil) and for his agents (messengers).
በቀደም እንዳየነው የማቴዎስ ወንጌል 25/31 የሚያወራው ጌታን እንደ ግል አዳኝ አድርጎ ግለሰቡ መቀበሉ ወይም ስላለመቀበሉ የተነገረ አይደለም የሚያወራው ስለ አህዛብ መለየት ነው እነሱ ጌታ እየሱስን እንዴት እዳስተናገዱት ነው ያም ማለት ለጌታ ወንድሞች በጎ ያደረጉና ያላደረጉትን እየለየ ነው ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ወደ ፍርድ የመጡት ጌታን ስላልተቀበሉ አይደለም ። ይህን ከደህንነት ጋር ምንም አያገናኘውም። “40 ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።” ከዚህ ከሚቀጥለው ቃላት ውስጥ ጌታን እንደግል አዳኝህ አልተቀበልክም የሚል አለ?የለም እርሱ ወንድሞች ብሎ ሊጠራ የማያፍርባቸውን አሁንም እንደሚታየው መልካምን ስራ ስላልሰሩና ስለሰሩ ህዝቦች እያወራ ነው። 34 ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። 35 ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ 36 ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። 37 ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ? 38 እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ? 39 ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን? 40 ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል። 41 በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ። 42 ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥ 43 ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና። 44 እነርሱ ደግሞ ይመልሱና፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል። 45 ያን ጊዜ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።
የማቴዎስ ወንጌል 25-46 እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ። በግሪኩ ዘላለም ቅጣት፥ “kolasin aionion.” Kolasin “punishment ቅጣት፤, chastening አሳዶ መቅጣት፤ , correction ማረም, to cut-off as in pruning a tree to bare more fruit መቁረጥ ልክ እንድን ዛፍ አብዝቶ እንዲያፈራ እንደ መግረዝ.” “aionions” የሚለው ቃል የተረጎመ ነው የቃሉ ስር ወይም፡ ንብረትነቱ “EION” ነው። ትርጉሙም “ዘመን age” ማለት ነው። ሁለቱ የተለያየ ትርጉም ያላቸው ናቸው ማለት አይደለም ። aion(the noun form) ሰዋሶው ወይም ነባር ስም ሲሆን aionions (the adjective form ቅጽል ነው። ሁለቱ ቃላት ሰዋሶው እና ቅፅል ናቸው። ለምሳሌ ሳምንት ሰዋሰው ሲሆን ሳምንታዊ ደግሞ ተቀፅላው ነው። ልክ እለት፦ እለታዊ, አመት ፦አመታዊ እንደሚባለው መለት ነው። Greek word “aion” (Strongs #165) or its adjective form “aionios” (#166).
እንግዲያው ይህን ካስተዋልን ተብሎ መተርጎም የነበረበት “የማቴዎስ ወንጌል 25-46 እነዚያም ወደ ዘመኑ ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘመኑ ሕይወት ይሄዳሉ።” ወደ ዘመየኑ ቅጣቱና የጊዜው ጉዳይ ስናይ ወደ ቅጣት የሚሄዱትም ለዘላአለም ሊደመሰሱ ወይም ሊሰቃዩ ሳይሆን 1,ኛ”Kolasin “punishment ቅጣት፤(እንዲቀጡ), 2,ኛchastening አሳዶ መቅጣት፤(ይህ ቃል chasteneth በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት እንዴት እንደተጠቀመበት እናስተውል KJV Heb 12/6 For whom the Lord loveth he chasteneth, and scourgeth every son whom he receiveth) , 3,ኛcorrection ማረም (Correctional judgement የሚያርም ፍርድ ነው), 4,ኛto cut-off as in pruning a tree to bare more fruit መቁረጥ ልክ እንድን ዛፍ አብዝቶ እንዲያፈራ እንደ መግረዝ.”
ጻድቃን ግን ወደ ዘመኑ ሕይወት ይሄዳሉ። የእ/ር ህይወት በባህርዩ ዘልአለማዊ ቢሆንም ያ ህይወት የተወጋው ዘልአለማዊ ባልሆነ ማንነት ላይ ስለሆነ የዘመኑ ህይወት ተባለ ።
(Matt 25:46 [YLT])And these shall go away to punishment age-during, but the righteous to life age-during.’
7/25/2017 ወንድም ቢንያም ለወንድም አስመሮም ክፍል 2
BROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU WRITINGS, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING