ክፍል 3 ። የአካል መነጠቅ(rapture) ውሸት ነው!


ክፍል 3 ። የአካል መነጠቅ(rapture) ውሸት ነው!
የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ! ክፍል 3
የመነጠቁ( RAPTURE) ጥያቄ እንደ ሚጥሚጣ ሰዎችን ከሚለበልብ አንዱ ተቀዳሚ ሃሳብ
ነው:: ቁጥራቸው የማይታወቅ አያሌ ጻድቃን በዚህ ሃሳብ ተመስጠው በውስጣቸው የሚያሰላስሉትና ብሎም በመናገር ግማሹ በስጋትና በፍርሃት
ግማሹ በጉግት ግማሹ ስራው ያውጣው ብለው የሚጠባበቁት ነው። ይህ ሃሳብ ሲነሳ “መነጠቁ መቼ ይከሰት ይሆን?” “በኔ የህይወት ዘመን
ይሆንን?” ከምወዳቸው መካከል ሁሉ ሲነጠቅ የሚቀር ይኖር ይሆንን? በታላቁ መከራ በማለፍስ ይሰቃዩቡኝ ይሆንን? የባሰ አያምጣና
እኔ እራሴ ሳልነጠቅ እቀር ይሆንን? አይኔ እያየ መለከቱ ሲነፋ የታደሉት ወደ ደመናው ተወንጭፈው መጭ ሲሉ ዋይ ዋይታው እድል ፈንታየ
ይሆንን? እነዚህና የመሰሉ ከፍ ያለ በእ/ር ቃል ላይ የሚነሱ የስጋዊው አይምሮ ሃሳቦች ብዙ ናቸው።
 
አይናችን ሲከፍተውና ከቃሉም ታአምራትን ማየት ስንጀምር ግን አንዱ የእ/ር ቃል እውነት
ሲበራልን አንድ ሺ ወሸት ቢኖር እንኳ ሁሉን ያፈርሰዋል:: የም የሚሆንበት ምክንያት
የእ/ር ሰአት ሲደርስ ብቻ ነው ፍጹም የሆነውን እውቀት ምናውቅና ማለት ስለሆነ ነው:: ከጊዜው በፊት ሁሉን አናውቀውም የእውነት
መንፈስ ግን ወደ እውነት ሁሉ በመራን ቁጥር ማወቃችን ያድጋል። “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 82 ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው
ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤ 3 ማንም ግን እግዚአብሔርን ቢወድ እርሱ በእርሱ ዘንድ የታወቀ ነው።” “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ
ሰዎች 13፡8 እውቀትም ቢሆን ይሻራል። 9 ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፥ …ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው ይሻራል።”
ክርስቶስ የመጣው ወደ መንፈስ ሊመራን ነው። Thev Lord Jesus during his dimamic ministry, he contunesly attempted to turn the perspective, minds and hearts of the disciples to spiritual things, and graduate them from constant expectation of external and natural happenings. But in last resurrection appearance of Jesus before His ascension thy didnt get it, this is what thy say funy funy … yet No cange of view external and natural happenings he corecte them the view will fixed ones thy received the Holy Ghost Acts 1: 6. So then these folks, coming together, indeed kept on asking Him, one after another saying, “Lord (or: Master), are You in this time progressively moving the kingdom away from where it has been put down (or: off its established position and away from the current situation and condition) and now restoring the sovereignty (or: reign) to (or: in; for) Israel?” ለተፈጥራዊው ሰው ሁሉም ነገር ተፈጥራዊ ነው ለመንፈሳዊው ሰው ሁሉም ነገር መንፈሳዊነው። በጌታ ትልቁ ችግር የሰዎች መንፈሳዊ እይታ በምድራዊው ስበት የተወሰነ ሆኖ ስለከረመባቸው እይታቸውን ወደ ሰማይ ወደ መንፈሳዊው መንጠቅ ነበር።
 
መቸም ይሄ ቀላል አርስት አይደለም የብዙ አማኞች ተስፋቸው የተሰራበት ቀመር መነጠቅ
በመሆኑና የእምነታቸውም መጠለያ ድንኳን በመሆኑ ገና ይህን ሃሳብ
ስታነሱ ዘለው እንደ ጴጥሮስ ጆሮ ይቆርጣሉ። ደግነቱ ጆሮን የሰራው ያስተውላል ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ! የእ/ር አሰራር ነውና
ጽዋውን ከሰው እደሆነ ቆጥረህ ልትደፋው አታስብ ብሎ የሚገሰጸውን ገስጾ ጆሮውንም መልሶ ያበጀዋል። ስለዚህ በጴጥሮስና በመሰለቹ
ቂም አይያዝም የጌታ ናቸውና እንዳውም ጌታ ፍጡራኑን ሁሉ ይወዳልና ሁሉን ካልወደድን ከየት ኛው ዛፍ እየበላን እዳለን ማስተዋል
አለብን የሂይወት ዛፍና መልካሙንና ኩፉውን ከሚያሳውቀው ዛፍ አለና። ስለዚህ ሃሳብ ጌታ ሲፈቅድ በሰፊው እናየዋለን።
 
ከላይ እንግዲህ የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ! በሚለው ተከታታይ 2 ክፍሎች በመሃከለኛ
ሃሳብ በኖኅ ዘመን እንደ ነበረ! ካለ በዛ ዘመን የተነጠቁት በሚለው ሃሳብ ስር የጥፋት ውሃው ከመምጣቱ በፊት እነማን ነበሩ ሲበሉና
ሲጠጡ የነበሩት? ሃጥአን ነበሩ። በጥፋት ውሃውስ በኖህ ዘመን የተወሰዱት እነማን ነበሩ? ሃጥአን ነበሩ:: በኖህ ዘመንስ በሃዘን
እያለቀሱ ጥርሳቸውን ያፋጩት እነማን ነበሩ? ሃጥአን ነበሩ:: ታዲያ የጥፋት ውሃው ሲመጣ እ/ር የታደጋቸውና በምድር ላይ የቀሩት
እነማን ነበሩ? አዎን ጻድቃን ነበሩ:: በሚል አይተን ነበረ ።
 
አሁን ደግሞ ጌታ በክብር ስለ መምጣቱ የሚያሳየውና የታወቀው የመጽሐፍ ክፍል ጥቂት
ክፍሎችን እ/ር እንደ ረዳን መጠን አብረን እናየለን::
 
፨ “1ኛወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፡15 በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤
16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
17 ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል(Greek: apantesis ) ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።”
 
፨ ሐዋሪያው በቁጥር 15 ላይ ግልጽ እንዳ ደረገው የትእይንቱ ቅደም ተከተል ስርአት
ላይ አተኩሮ እንደጻፈው እናየዋለን፡፡ ተቀዳሚ ነጥቡም የመጀመርያን ክስተት የሚሆነው የሙታን ትንሳኤ እንደሆነ በማሳየት ይጀምራል።
“እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን (የሞቱትን) አንቀድምም” እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ
ያንቀላፉቱን (የሞቱትን) እስኪነሱ እንቆያለን እነሱ አንቀድምም ከተነሱ ቡሃላ ቁጥር 17 ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር
አንድ ላይ እደሆነ የምንቀበለው እያያዘ ያስረዳናል። ሐዋሪያው በሁለቱ ክስተቶች ያለው ክፍተት ስለ ጊዜ ምንም የነገረን ነገር የለም
ከዚያም ከሚል አያያዥ ቃል ከመጠቀሙ በቀር ያም ቀጥሎ የሚለውን ሃሳብ ያዘለ ነው።
 
፨ በነገራችን ላይ በቁጥር 16 ሙታን እዲነሱ መለከት የሚነፋው የትንሳኤው መልአክ
ሚካኤል (HEBREW who (is) like God እ/ርን የሚመስለው) እደሆነ በዳንኤል 12፡1-3 ግልጽ ያደርግልናል። እ/ርን የሚመስለው እየሱስ ክርስቶስ ነው።
 
ወደ ሐዋሪያው መልክትእንመለሰና 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፡15 ጌታን በአየር ላይ እንደ ምንቀበለው ነግሮናል። ይህ ሁሉ መንፈሳዊ ትእይንት ነው።
ምንቀበለው የሚለው የግሪኩ ቃል Greek: apantesis አፓንቴስስ ማለት ወዳጅን
ከውጭ በመቀበል አጅቦ ወደ ቤት መመለስ ማለት ነው። a (friendly) encounter:–meet or (to
meet and return with as an escort) ይህ አታንቴስስ የሚለው የግሪኩ
ቃል በአዲስ ኪዳን 4 ጊዜ ተጠቅሞበታል:፡
ሙሽራው ስለ መጣ ደናግሎቹ ወጥተው እንዲቀበሉት የተነገራቸው ቦታ ። በየማቴዎስ ወንጌል 25፡1 በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን
ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።2 ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ። 3 ሰነፎቹ መብራታቸውን
ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤ 4 ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ። 5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ
እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። 6 እኩል ሌሊትም ሲሆን። እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት (Greek: apantesis አታንቴስስ
) ዘንድውጡ የሚል ውካታ ሆነ።
 
አምስቱ ሰነፎች ደናግል ነበሩ ለኩራዛቸው በቂ ዘይት ስሌላቸው ሊገዙ ሄዱ። ገዝተውም
ሁሉም ሙሽራውን ይጠቡቅበት ወደ ነበረው ቤት ተመለሱ ። ለሰርጉ ስለ ዘገዩ በሩ ተዘግቶ ነበር። ልባም ደናግሎች ደግሞ ሙሽራውን
 
ይጠባበቁት ከነበሩበት ወደ ደጅ ወጥተው ሆ እያሉ ተቀብለውት አጅበውትም ማለት ነው ወደ
ቤት ይዘውት ተመለሱ ደጁም ተዘጋ :፡
 
በሌላ አነጋገር ሙሽራው ልባም ደናግሎችን ነጥቆ ወደ መንግስተ ሰማይ ይዞ ለመሄድ
አልመጣም። ነገር ግን ልባም ደናግሎች ሙሽራውን ይጠባበቁት ወደ ከነበሩበት
ወደ ደጅ ወጥተው በአክብሮት ተቀብለውት አጅበውትም ወደ ቤት ተያይዘው ተመለሱ ደጁም ተዘጋ :፡ ስለዚህ ተቀበሉት በGreek:
apantesis አፓንቴስስማለት ወዳጅን ከውጭ በመቀበል አጅቦ ወደ ቤት መመለስ ማለት ነው። ይህ ቃል የተጠቀሰበት
ሌላ ቦታ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም እስረኛ ሆኖ ሲወሰድ በሐዋርያት ሥራ 28፡15 ከዚያም ወንድሞች ስለ እኛ ሰምተው እስከ አፍዩስ ፋሩስና ሦስት ማደሪያ እስከ
ሚባለው ሊቀበሉን(Greek: apantesis አታንቴስስ ) ወጡ፥ ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ ልቡም ተጽናና።
 
ታሪኩ ግልጽ ነው ። አማኞቹ ጳውሎስን ተቀብለው አጅበውት ወደ መጡበት ወደ
ሮም ተያይዘው ተመለሱ እንጂ ተቀብለውት እስረኛው ወደ መጣበት ወደ እየሩሳሌም አልሄዱም።ስለዚህ ጳውሎስ በአየር ላይ እንቀበለዋለን ሲል በአየር
ላይ ተቀብለነው በዛው ወደ ሰማያት ይዞን ይወስደናል ማለቱ ሳይሆን ወደ ምድር ሊገዛ ሲመለስ በአየር ላይ ተነጥቀን እንቀበለውና
አጅበነው ሆ እያል ወደ ምድር አብረነው ልንገዛ ሁላችን እንመለሳለን ።ማለቱነው። እንግዲህ ትንቢታዊ መልእክት ያለው የ10 ደናግል
ስእላዊ መልኩ ይህን ነው የሚመስለው።
 
ብዙዎች የሚነጠቁት ጌታን ተቀብለው አጅበውት ለመመለስ ሳይሆን ከታላቁ መከራ ለማምለጥ ወደ ሰማያት ሊወስዳቸው አድርገው ይረዱታል። ለዚህ ማስረጃቸውም “የዮሐንስ ራእይ 7፡14 እኔም። ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁት። አለኝም። እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።”
እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ እንጂ ያመለጡ አይልም። እንዳውም በመከራ ውስጥ ያልፈ ዘንድ የተገባቸው ናቸው ። እንዳውም ጌታ በማቴ24 ሲናገር ከዚያች ወራትም
ከመከራ በኋላ ነው ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻውከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ። የሚለው።
 
በማቴ24፡29 ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ …የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤
 
31 መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።
 
ሌላው ግራ የሚያጋባ አስተምህሮ ደግሞ የአህዛብ ክርስቲያኖች መከራውን ያመልጣሉ የአይሁድ
ክርስቲያኖች ግን በምድር በመከራው ጊዜ ያልፋሉ የሚለው ነው ። ለንጥቀት አስተማሪዎች ይህን ሃሳብ አስታከው ማቴ24፡29᎒1 ለአይሁድ
ራእይ7፡14 አይሁድ ላልሆኑት አማኞች ያቀቡሉታል። ከእይታቸው አይሁድ
ማለት አይሁድና እስራኤል ናቸው የሚለውን የያዘ ነው። እውነቱ ግን እሱ አይደለም። አይሁድ ማነው? የሚለው ጥያቄ በአዲስ ኪዳን
ቤተ ክርስቲያን ነች የይሁዳ ነገድነትን በክርስቶስ በቀጣይነት የተቀበለችው::
 
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:28-29 እንግዲህ ይህ መነጠቅ በተመለከተ የኖኅ ዘመን
እንደ ነበረ ይሆናል ያለውንና ጌታን በአየር ላይ እንቀበለዋለን የሚሉትን በዋንኛነት ሌሎችም አካቶ ማለት ነው ያቀረብነው በዚሁ ይጠናቀቃል
 
ብዙ የጠለቀ መንፈሳው ፍቺና መልእክት እዳዘለው ቢገባን ጠቅላላ ስእሉን ለማስተዋል በቂ ነው ብለን ስላሰብን በዚህ እንፈጽማለን። እ/ር አብዝቶ ይባርካችሁ።
 
በልቤ ሰሞኑን ሲመላለስ የነበረውን ቃል ላካፍላችሁና ልጨርስ “የሐዋርያት ሥራ 17፡25 እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም።….
በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖርማለን።” “ሰቆቃው ኤርምያስ 4፡20 ..በጥላው በሕይወት እንኖራለን ያልነው በእግዚአብሔር የተቀባ
የሕይወታችን እስትንፋስ፥ በጕድጓዳቸው ተያዘ።” የሕይወትን እስትንፋስ ለሁሉም የሚሰጠውና እራሱም የሕይወታችን እስትንፋስ፥ የሆነው በእግዚአብሔር
የተቀባው በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖርማለን ተብሎ የተጻፈለት ጌታ የዘላለም ህይወት ማለት እ/ርን ማወቅ ማለት
ነውና እርሱን ማወቅ ይብዛልን።የዮሐንስ ወንጌል 17፡3 እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። አሜን! August 5, 2011 Brother Binyam T. Alemayehu
CATEGORIESBROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU WRITINGS, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=1689847354434549&id=100002279031400
  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal