በንጥቀት ላይ ተጨማሪ ከምላሽ የተወሰደ።


በንጥቀት ላይ ተጨማሪ ከምላሽ የተወሰደ። ከወንድም ቢኒ። ወንድማችን እንደ ብዙ ወገኖች በዛው መጭ ማለትን ላይ ነው የናፈቀውና ያተኮረው ያላስተዋለው ግን አንድ ነገር አለ። እንዳው በሱ አካሄድ ይሁን ብለን ብናየው እንኳ በአየር ተቀብለን እንመለሳለን እንጂ በዛው መጭ እንላለን እያለ እንዳልሆነ ወንድማችን አላስተዋለውም። ቃሉን አስተውሉ “በአየር ለመቀበል” “1ኛወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፡/17 ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል(Greek: apantesis ) ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።”
ወንድማችን “አየር” ላይ የምትለው መልህቅ አርጎ ይዝዋታል ያላስተዋለው ግን ለመቀበል(Greek: apantesis ) እስቲ ከቃሉ እናስተውል። ወደ ሐዋሪያው መልክት እንመለሰና 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፡ ጌታን በአየር ላይ እንደ ምንቀበለው ነግሮናል። ይህ ሁሉ መንፈሳዊ ትእይንት ነው ሆኖም እንደሱ አካላዊ ወይም ተፈጥራዊ እይታ ቢሆን እንኳ ንጥቀቱ አየር ላይ የምንቀበለውን እንጂ ተቀብለን በዛው እንሄዳለን አይልም። የግሪኩ ቃል መቀበል Greek: apantesis አፓንቴስስ ማለት ወዳጅን ከውጭ በመቀበል አጅቦ ወደ ቤት መመለስ ማለት ነው። a (friendly) encounter:–meet or (to meet and return with as an escort) ይህ አታንቴስስ የሚለው የግሪኩ ቃል በአዲስ ኪዳን 4 ጊዜ ተጠቅሞበታል:፡ ሙሽራው ስለ መጣ ደናግሎቹ ወጥተው እንዲቀበሉት የተነገራቸው ቦታ ። በየማቴዎስ ወንጌል 25፡1 በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።2 ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ። 3 ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤ 4 ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ። 5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። 6 እኩል ሌሊትም ሲሆን። እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት (Greek: apantesis አታንቴስስ) ዘንድውጡ የሚል ውካታ ሆነ።
፨ በነገራችን ላይ በቁጥር 16 ሙታን እዲነሱ መለከት የሚነፋው የትንሳኤው መልአክ ሚካኤል (HEBREW who (is) like God እ/ርን የሚመስለው) እደሆነ በዳንኤል 12፡1-3 ግልጽ ያደርግልናል። እ/ርን የሚመስለው መንፈስ የሆነው በመንፈስ ያለማቋረጥ እየመጣልን ያለው ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ነው። አምስቱ ሰነፎች ደናግል ነበሩ ለኩራዛቸው በቂ ዘይት ስሌላቸው ሊገዙ ሄዱ። ገዝተውም ሁሉም ሙሽራውን ይጠቡቅበት ወደ ነበረው ቤት ተመለሱ ። ለሰርጉ ስለ ዘገዩ በሩ ተዘግቶ ነበር። ልባም ደናግሎች ደግሞ ሙሽራውን ይጠባበቁት ከነበሩበት ወደ ደጅ ወጥተው ሆ እያሉ ተቀብለውት አጅበውትም ማለት ነው ወደ ቤት ይዘውት ተመለሱ ደጁም ተዘጋ :፡
በሌላ አነጋገር ሙሽራው ልባም ደናግሎችን ነጥቆ ወደ መንግስተ ሰማይ ይዞ ለመሄድ አልመጣም። ነገር ግን ልባም ደናግሎች ሙሽራውን ይጠባበቁት ወደ ከነበሩበት ወደ ደጅ ወጥተው በአክብሮት ተቀብለውት አጅበውትም ወደ ቤት ተያይዘው ተመለሱ ደጁም ተዘጋ :፡ ስለዚህ ተቀበሉት በGreek: apantesis አፓንቴስስማለት ወዳጅን ከውጭ በመቀበል አጅቦ ወደ ቤት መመለስ ማለት ነው። ይህ ቃል የተጠቀሰበት ሌላ ቦታ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም እስረኛ ሆኖ ሲወሰድ በሐዋርያት ሥራ 28፡15 ከዚያም ወንድሞች ስለ እኛ ሰምተው እስከ አፍዩስ ፋሩስና ሦስት ማደሪያ እስከ ሚባለው ሊቀበሉን(Greek: apantesis አታንቴስስ ) ወጡ፥ ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ ልቡም ተጽናና።
ታሪኩ ግልጽ ነው ። አማኞቹ ጳውሎስን ተቀብለው አጅበውት ወደ መጡበት ወደ ሮም ተያይዘው ተመለሱ እንጂ ተቀብለውት እስረኛው ወደ መጣበት ወደ እየሩሳሌም አልሄዱም። በመንፈሳዊነቱም ሆነ በአካላዊነት እንረዳው ጳውሎስ በአየር ላይ እንቀበለዋለን ሲል በአየር ላይ ተቀብለነው በዛው ወደ ሰማያት ይዞን ይወስደናል ማለቱ ሳይሆን አሁንም በመንፈሳዊነቱም ሆነ በአካላዊነት እንረዳው ሊገዛ ሲመለስ በአየር ላይ ተነጥቀን እንቀበለውና አጅበነው ሆ እያል ወደ ምድር አብረነው ልንገዛ ሁላችን እንመለሳለን ።ማለቱነው። እንግዲህ ትንቢታዊ መልእክት ያለው የ10 ደናግል ስእላዊ መልኩ ይህን ነው የሚመስለው።
ብዙዎች የሚነጠቁት ጌታን ተቀብለው አጅበውት ለመመለስ ሳይሆን ከታላቁ መከራ ለማምለጥ ወደ ሰማያት እንደሮኬት ተፈትልከው ሲወስዳቸው ከመከራ ሲያመልጡ በምናባቸው እየሳሉ ይረዱታል። ለዚህ ማስረጃቸውም “የዮሐንስ ራእይ 7፡14 እኔም። ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁት። አለኝም። እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።” አስተውሉ እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ እንጂ ያመለጡ አይልም። እንዳውም በመከራ ውስጥ ያልፉ ዘንድ የተገባቸው ናቸው ። እንዳውም ጌታ በማቴ24 ሲናገር ከዚያች ወራትም
ከመከራ በኋላ ነው ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ ያለው።
በአካል ንጥቀት ከሆነና መጭ ብለን ሁልጊዜም በሰማይ ላይ ለመቆየት ከሄድንና ካልተመለስን በምድር ላይ ለመግዛት ከላይ እንደተፃፈው ለእኛ የሚሆን መንገድ አይኖርም በምድር ያሉቱን አሕዛብ ፈጽሞ በጽድቅ በእግዚአብሔር ልጆች ክብር ላይገዙ ተሻረ ማለት ነው። የክርስቶስ ሙሽራም መቼም ቢሆን የእግዚአብሔርን ክብር ለመገለጥ ከሰማይ[ከመንፈስ ግዛት] ስትወርድ አትታይም። You misunderstand Bro. Jesus Christ is the very Glory of God, The manifestation of God’s glory is no more in Lord Jesus glorified one person body or HIS FLESH, but rather OUR FLESH we are his body NOW he is the head of the corporate body. Also, if you still think heaven is a piece of real estate “out there” in space somewhere, rather than within your own thinking [within your heart and mind – i.e. – a state of being], then your road to enlightenment has reached an impasse which requires a total paradigm shift in your thinking. GOD IS LOVE! Bro. Bini.
  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal