If we walk in the light በብርሃን ብንመላለስ


If we walk in the light በብርሃን ብንመላለስ

ወንድም ቢንያም ክፍል አንድ

በአሮጌው ሰማይ መረዳት ብዙ ሰዎች የሚቀደሱት የእ/ር ፍርድና ሲኦልን በፍራት ነው። ልክ ሲኦልንና የዘላለም ስቃይ ከፊታቸው በእ/ር ቃል ስታነሱት በቅድስና የሚመላለሱበትን ህይወት ቀይረው ይላላጣሉ። እ/ርን የምንከተለው በፍቅር ስለምንወደው እንጂ የእ/ር ፍርድና ሲኦልን የዘላለም ስቃይን በፍራት መሆን የለበትም። እውነት ነው እ/ር ፍቅር ነው መርሳት የሌለብን ግን እ/ር የሚባላ እሳት መሆኑንም ነው። የው የእ/ር ፍቅር ለእናንተው ጥቅም ሊቀድሳቹሁ እሳት ሆኖ ሊቀምማቹሁ በህይወታቹ ልትለማመዱት ትችላላቹሁና።

መቼም የየሰዉየብስለት እርከን ይለያያል እንጂ ሌላ ከፍ ያለ ሰማይ ገብቻለሁ ብሎ ያለቅድስና መመላለስ የአዳም ትራፊ ነው እንጂ የክርስቶስ ባህርይ አይደለም እየሱስ ክርስቶስ አሮጌው ሰዌ አስቸገረኝ አባቴን አልታዘዝኩም ብሎ ተናግሮ አያውቅም።  “1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:7 ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።”   “If we walk in the light, as He is in the light, we have fellowship one with another, and the blood of Jesus Christ His Son cleanseth us from all sin.” (1 John 1:7 [Open in Logos Bible Software (if available)] )”  [Walk in the light በብርሃን ብንመላለስ] መቼም ያለ ጥርጥር እርሱ ብርሃናችን ሲሆን ነው የመንፈሳዊ እድገታችን ሂደት እውን የሚሆነው:: የሚያስችል እርሱ ብቻ ነውና:: ከእርሱ ውጪ ምንም ልናደርግ አንችልምና።

“ የዮሐንስ ወንጌል 1፡4 በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።”

“KJV John 1፡4 In him was life; and the life was the light of men.”

“መጽሐፈ ኢዮብ 32:8 ነገር ግን በሰው ውስጥ መንፈስ አለ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ማስተዋልን ይሰጠዋል። Job 32፡8 But there is a spirit in man: and the inspiration of the Almighty giveth them understanding.” “ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን” መቼም የተወሰኑ ጊዜያት ላይ በሰዎች ብርሃን  የተመላለስንባቸው ጊዜያት ነበሩ። በሰው ጥበብም ሃሳብም ፍልስፍናም አመለካከትም ፈለጎችን ተከትለን ልንራመድ ስንሞክር ወደ ጨለማና ግራ መጋባት ሲመራን ነበር። ጌታን የሚተካ ማንም የለም። ስናስበው ነብዩ እንዲህ ብሎ ማወጁ የሚያስደንቅ ነገር አልነበረም። ትንቢተ “ኢሳይያስ 50፡11 እነሆ፥ እሳት የምታነድዱ የእሳትንም ወላፈን የምትታጠቁ ሁላችሁ፥ በእሳታችሁ ነበልባል ባነደዳችሁትም ወላፈን ሂዱ ይህ ከእጄ ይሆንባችኋል በኀዘን ትተኛላችሁ።”

“KJV Isa 50፡11 Behold, all ye that kindle a fire, that compass yourselves about with sparks: walk in the light of your fire, and in the sparks that ye have kindled. This shall ye have of mine hand; ye shall lie down in sorrow” ይሃውላቹ እንግዲህ ሰው በለኮሰውና በጀመረው ብርሃን ለመላለስ መሞከር ሃዘንን እንደ ሚያዘጋጅ ቃሉ ስተምረናል። በጌታ በራሱ በመንገዳችን ላይ በሚያበራልን የብርሃን ጸዳል መመላለስ ግን እንዴት የከበረና ድንቅ ነገር ነው። “መጽሐፈ ምሳሌ 4፡18 የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል።

KJV Prov 4፡18 But the path of the just is as the shining light, that shineth more and more unto the perfect day.”

“1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1፡5 ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት። እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።

KJV1John 1፡5 This then is the message which we have heard of him, and declare unto you, that God is light, and in him is no darkness at all.” እግዚአብሔር የብርሃን ምንጭ ነው የብርሃናትም ሁሉ አባት ነው። እርሱ የሁሉ በጎ ነገር ምንጭ ነው። ጥበብ፤ ቅድስና፤ ንጽህና ወዘተ… በእርሱ ዘንድ ነው በርሱ ዘንድ ጨለማ የለም ክፉም የለም። ጨላማና ክፉን ግን በአላማ ሊፈጥር ይችላል።

በትንቢተ ኢሳይያስ 45፡7 ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ እነነዚህንሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። አዎን ሁሉን መፍጠሩን እ/ር ሃላፊነቱን ወስደዋል:: እርስ በራሳቸው የሚቃረኑትም ጭምር ማለትነው። ለማሰብ ያህል መራራና ጣፋጭ፤ ሃዘንና ደስታ፤ ድሃና ባለጠጋ፤ ጨለማና ብርሃን፤ መልካምና ክፉ፤ ህግና ጸጋ፤ ተፈጥራዊ ነገሮች ና መንፈሳዊ ነገሮች፤ ሞትና ህይወት፤ እስራትና ነጻነት፤ አዎን ሁሉን መፍጠሩን እ/ር ሃላፊነቱን ወስደዋል:: የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው? ከሚገልጥልን በቀር ማስተዋል አይቻልም መንፈሳዊው ነገር ከሰው ማስተዋል በላይ ግዙፉ ነውና። ቢሞከርም ከውቂያኖስ ይልቅ ጠሊቅ ከሆነው ምክሩ በማንኪያ ጨልፈን እደመረዳት ያህል ነው። ወንድም ቢኒ

ክፍል ሁለት

ከፈጠራቸው እንውጣና ወደ ማንነቱ ስንመጣ “እግዚአብሔር ብርሃን ነው” አይናችን ተከፍቶም ከቃሉ ታእምራቱን በእርሱ ልናይ ይገባናል። “ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንደሆነ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን” ማለትም በእርሱ ፈቃድ ጥበብ ቅድስና ብንመላለስ ህብረት ለእያንዳንዳችን አለን። በእርሱ የዘልአለም ብርሃን መኖር ማለት ጨለማ በእኛ ላይ የመግዛት ስልጣን የለውም ማለት ነው። የማይቃረጥና የማይሰበር ህብርት የሚመጣው በእርሱ ብርሃን መመላለሳችንን የለማቃራት ከቀጠልን ብቻ ነው።ያመኑትን ምን አላቸው?  [በቃሌ ያለማቋረጥ ብትኖሩ If ye continue in my word]

የዮሐንስ ወንጌል 8/31 ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ። እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤

31 Then said Jesus to those Jews which believed on him, If ye continue in my word, then are ye my disciples indeed;

32 እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።

32 And ye shall know the truth, and the truth shall make you free.”

ከእ/ር ጋር የማያቃርጥ እብረት እንዲኖረን ምኞታችን እንናገራለን እርሱም የጠበቀ እብረት ይፈልጋል ለዛም ጠርቶናል።

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡9 ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።

KJV 1Cor 1፡9 God is faithful, by whom ye were called unto the fellowship of his Son Jesus Christ our Lord. ነገር ግን

“ትንቢተ አሞጽ 3፡3 በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ በአንድነት ይሄዳሉን?

KJV Amos 3፡3 Can two walk together, except they be agreed?”

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡14 …ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?

KJV 2Cor 6፡14: for what fellowship hath righteousness with unrighteousness? and what communion hath light with darkness?”

“የዮሐንስ ወንጌል 12፡36 የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃኑ እመኑ አላቸው። ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ሄደና ተሰወረባቸው[ወደ መንፈስነት ተቀየረ]።

KJV John 12፡36 While ye have light, believe in the light, that ye may be the children of light.” በሙልአት ማደሪያችን እኪሆን በብርሃኑ ልናምን ይገባናል። አዎን ከብርሃኑ ጋር አንድ እስክንሆን ድረስ ብርሃን ከውርሳችን ክፍል አንዱ ነውና ።

“1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡17 ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው።

KJV 1Cor 6፡17 But he that is joined unto the Lord is one spirit.” አሜን!

ትንቢተ ኢሳይያስ 60

1 ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ።

1 Arise, shine; for thy light is come, and the glory of the Lord is risen upon thee.

2 እነሆ፥ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል

2 For, behold, the darkness shall cover the earth, and gross darkness the people: but the Lord shall arise upon thee, and his glory shall be seen upon thee.

3 አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ።

3 And the Gentiles shall come to thy light, and kings to the brightness of thy rising.

“ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንደሆነ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን” አሜን! ተፈፀመ። ወንድም ቢኒ

 

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal