ጥያቄና/መልስ ጳውሎስ “ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ” ሲል ምን ማለቱ ነው? ባሪያ ለምን አለ? ወይስ ልጅነቱ አልበራለትም?


ጥያቄና/መልስ ጳውሎስ “ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ” ሲል ምን ማለቱ ነው? ባሪያ ለምን አለ? ወይስ ልጅነቱ አልበራለትም?
ልጅነት በደንብ አርጎ ገብቶታል የብስለቱ ደረጃ ከፍተኛ መሆኑ የሚያሳይ ነው ። ሰው ወደ ክርስቶስ ባደገ ቁጥር ወደ ትህትና ወደ ቅንነት ማደጉ የታወቀ ነው። ጌታ ቀሊል ቀምበር ብሎ የጠራት ባህርዪ “በልቤ የዋህና ትሁት ነኝ ከእኔ ተማሩ” ለእግዚአብሔር ባሪያ ተገኝቶ ነው ክብር ነው። ጌታ እየሱሰ በብዙ ቦታ ላይ ባሪያ ተብሎ ተጠርተዋል ። የኢሳያስ ትንቢት53፡11 ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሰከማል።

ይሄ እኮ የሪሌሽን ሽፕ እርከን ነው እንጂ ሌላ ነገር አይደለም።እኔ አንድ ሰው ስሆን ለአባቴ ልጅ ነኝ ለወንድሜ ወንድም ለሚስቴ ባል ነኝ ለልጆቼ አባት ነኝ ለወዳጆቼ ጋደኛ ነኝ ። ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ አገልጋይ ወይም ባሪያ ሲባል በራሱ ፈቃድ ሳይሆን በላከው ፈቃድ መኖሩን የሚያሳይ ነው።
ጳውሎስን እንይው
ሮሜ1”1-2 ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ(G, appointed) የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ (G, little) በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።”

፨ሐዋሪያ ሊሆን የተጠራ ሐዋሪ ያ የተላከ ወይም መልክተኛ ማለት ነው:: ይህም ማለት በላኪው ተመርጦ የተጠራና ትእዛዝን የተቀበለ ሲሆን የተቀበለውም ትእዛዝ በራሱ ስልጣንን ይዞ የሚመጣ ነው ይህም ሃላፊነት ያለበት ትዛዙን የሚፈጽም ቧለማል የላከውን እንጂ የራሱን ፈቃድ የማያደርግ እንደራሴ ነው:: የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ እራሱን ባሪያ ብሎ መጥራቱ ምክንያት ህግን ጠንቅቆ የተማረ ሰው ስለ ነበር የህግ ፍጻሜ ወይም ግብ የሆነው በክርስቶስ ዘንድ ያለውን መንፈሳዊ ፍቺ ስለ ሚገነዘብ ነው::

በኛ ዘመን ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ የትምህርት ተቅዋም እንደሆነ ሁሉ በታሪክ መዛግብት ስታስተውሉ በዚያ ዘመንም ገማሊያ ከተባለ በአይሁድ የተከበረ የህግ ትምህርት ቤት አንዱ ወስጥ ተምረዋል:: በመጽሐፍ ቅዱስም ስለዚህ ት/ቤት መስራች ሰው ወጤማታማ የህግ መምህር ዕንደ ነበረ ፍንጭን ይሰጠናል:: “በሐዋ5:32 ነገር ግን በህዝቡ ሁሉ ዘንድ የከበረ የህግ መምህር ገማልያል የሚሉት “ ሲለው እራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ ከዚህ ሰው እግር ስር የአባቶችን ህግ ማለትም የሙሴ ህግን እንደ ተማረ ይናገራል:: “ሐዋ22:3 በገማልያል እግር አጠገብ ያደግኩ: የአባቶችንም ህግ ጠንቅቄ የተመርሁ::” ነኝ ይላል::
መማር መቸም መልካም ነው። ብትማሩ ይበልጥ እ/ርን ትጠቅሙታላቹሁ ጳውሎስ ከነጴጥሮስ ይልቅ የተማረ ስለ ነበር ብዙ ቋንቋም ይናገር ነበርና እ/ር በአይሁድ ላሉ ብቻ ሳይሆን ለአህዛም ጭምር ተጠቀመበት። እ/ር ለነገሩ ሰው ተማረ አልተማረ አላማው በርሱ ላይ ካለ አይገደውም ዋናው ሰውየው ከእ/ር የሰማና የተማረ ይሁን እንጂ የእ/ር ፈቃድ ይፈጸማል። ለነገሩ ሁሉ ከእ/ር የሚሰሙበትና የሚማሩበት ተስፋ እንዳለ እኮ መጽሐፍ በብዙ ቦታ ያስተምራል የእ/ር አላማውና አሰራሩ ጥልቅና ውስብስብ ስለ ሆነ ለማስተዋል ከራሱ ከእ/ር የመጣ መጠነ ሰፊ እገዛ ወሳኝ ነው ውንጂ። “ዮሃ 6:45 ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ ተብሎ በነቢያት ተጽፎአል፤ እንግዲህ ከአብ የሰማ የተማረም ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።”

፨“ህግ ጠንቅቄ የተመርሁ” በዚህም ምክንያት ጳውሎስ የእየሱስ ባሪያ ብሎ እራሱን መጥራቱ አንደኛ እስራኤል ከግብጽ ምድር ከዋጃቸው ቡሃላ በመለኮት ህግ እንዳስረዳቸው ለዋጃቸው ጌታ ብቻ ባሪያዎች እንደሆኑ እንደሚገባ ይገነዘባል:: “ኦሪት ዘሌዋውያን 25:42 ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎቼ ናቸውና እንደ ባሪያዎች አይሸጡ።”
ኦሪት ዘሌዋውያን “25፥55 የእስራኤል ልጆች ለእኔ ባሪያዎች ናቸውና ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎቼ ናቸው እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።” እ/ር ሃይሉን በመግለጥ ዋጋ ከፍሎ ባርነት ካወጣቸው ቡሃላ ለዋጃቸው ጌታ ብቻ ሊያድሩና ሊያገለግሉ የተገባቸው እንደሆነ ከህጉ ያስተውላል:: በዚህም ጳውሎስ የእየሱስ ባሪያ ብሎ እራሱን መጥራቱ ትህትናውን እናስተውላለን:: ሌላው ወደ ጌታው እንደ ተመለሰ የጌታው ወዳጅ ባሪያ አድርጎ እራሱን መቁጠሩ ነው:: ጆሮው ወደ መንፈሳዊ በሩ ኢየሱስ ክርስቶስ ተደግፈዋል:: ጆሮውም የክርስቶስን ፍቅር ሊሰማና ሊያውቅ ተከፍተዋል:: ይህ ህግ የሚገኘው “በዘጸ21:5 “(ነጻ የወጣው )ባሪያውም :ጌታየን ሚስቴን ልጆቼንም እወዳለሁ አርነት አልወጣም ብሎ ቢናገር ጌታው ወደ ፈራጆች ይውሰደው ወደ ደጁም ወደ መቃኑ አቅርቦ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው ለዘላለምም ባሪያው ይሁን” መጽሐፍ “በ1ቆሮ10:11” በቀደሙት ላይ ይህ ሁሉ እንደ ምሳሌ የደረሰባቸው እኛን በዘመን መጨረሻ ያለነውን ሊናገረን እደሆነ ይናገራል:: ጆሮን ወደ በሩ መደገፍና መበሳት መንፈሳዊ አመልካችነቱ የእ/ር ቃልን ለመስማት መከፈቱን ነው:: “በመዝ 40:6-8 መስዋእትንና ቁርባን አልፈለግክም ጆሮቼን ግን ከፈትክ….አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ላደርግ እሻለሁ ህግህም በልቤ ውስጥ አለ::” ፈቃደኛው ባሪያ የእ/ርን ፈቃድ ሊያደርግ ደስ ይለዋል ጆሮው ተከፍተዋልና ለእ/ር መንፈሳዊ ድምጽ ህያው ነው:: ምክንያቱም ህጉ በልቡ ውስጥ ተጽፈዋል እንጂ በውጪ አይደለም:: ይህ ቃል በጌታ እየሱስ ላይም ተፈጽመዋል:: “ዮሃ4:34 የኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግ ነው ስራውንም መፈጸም ነው” ወንድም ቢኒ

ለትህትና ነው ወይ ሀዋሪያው ባሪያ ነኝ ያለው የሚል ወንድማችን ጠይቆ ነበር።
ነፃ ፈቃድን እርሳው። ለትህትና ብቻ ሳይሆን እኔም አንተም የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ከአንድ ባርነት አምልጠው ወደሌላ ባርነት ነው የገባነው ወይም የገቡት ያም በፊት የሀጥያት ባሪያዋች ነበርን አሁን የፅድቅ ባሪያዋች ነን። እርፍ ነው እንግዲህ!
ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ6፡16 ለመታዘዝ ባሪያዎች እንድትሆኑ ራሳችሁን ለምታቀርቡለት፥ ለእርሱ ለምትታዘዙለት ባሪያዎች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? ወይም ለሞት የኃጢአት ባሪያዎች ወይም ለጽድቅ የመታዘዝ ባሪያዎች ናችሁ።

17-18 ነገር ግን አስቀድማችሁ የኃጢአት ባሪያዎች ከሆናችሁ፥ ለተሰጣችሁለት ለትምህርት ዓይነት ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ ከኃጢአትም አርነት ወጥታችሁ ለጽድቅ ስለ ተገዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።
19 ስለ ሥጋችሁ ድካም እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። ብልቶቻችሁ ዓመፃ ሊያደርጉ ለርኵስነትና ለዓመፃ ባሪያዎች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ፥ እንደዚሁ ብልቶቻችሁ ሊቀደሱ ለጽድቅ ባሪያዎች አድርጋችሁ አሁን አቅርቡ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal