
እኔ ነኝ ! (እግዚአብሔር አንድ አምላክ ነው ወይስ ስላሴ[ሶስት] ? )
ክፍል ሁለት
እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን?
‘የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በእርሱ ይኖራልና፤ ‘ቈላስይስ 2:9
“For in Him dwelleth all the fullness of the Divinity bodily” (Col. 2:9.)
አስተውሉ! በመሎኮት አካል ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ አለ እያለን ሳይሆን ፡ በተቃራኒው ልክ የወይን መጥመቂያ ውስጥ አዲስ የወይን ጠጅ ቲፍ ብሎ እንደሚሞላ በኢየሱስ ክርስቶስ አካል ውስጡ መሎኮት በሙላት ቲፍ ብሎ ታጭቆ ይኖራልና! እያለን ነው። ሃሌሉያ!
‘እናንተም የገዥነትና የሥልጣን ሁሉ ራስ በሆነው በክርስቶስ ሙሉ ሆናችኋል። የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በእርሱ ይኖራልና፤ ‘ቈላስይስ 2:9-10
በዚህ ቃል ውስጥ ሁለት የተገለጡ ሚስጥራትን እናስተውላለን አንደኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ሳይቀር የበላይ ራስ ነው ይለናል ይህ ራስነቱ በፈጠራቸው በተቃራኒ ሃይላት ላይም የበላይነቱን ሉአላዊነቱን የሚያሳይ ነው። [የገዥነትና የሥልጣን ሁሉ ራስ በሆነው በክርስቶስ]
በዚያ አይቋጨውም ሁለተኛው እንድናስተውል የተፃፈልን በቁጥር 10 ላይ ስናስተውል ለኛም ሌላ ዜና አለው። [በዚህ የሁሉ ራስ ፤ጌታ፤ ፈጣሪ፤ በእርሱ መአርግ ሙሉ ሆናችኋል! ye are complete in him!] በቅድሚያ ይህ ክርስቶስ የሁሉ ራስ መሆኑ የታወቀ ይሁን። እርሱ ለአለቅነት፤ ለገዥነትና ለሥልጣናት ሁሉ ሳይቀር ራስ ነው፡፡ ሁሉም ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የጸናው በእርሱ ኅይል ነው። እርሱ ቢለቀው ሁሉ አለቀለት እሱ የሰራው ግን ለዘልአለም ጽኑ ነው።[እግዚአብሔር ያደረገው ሁሉ ለዘላለም እንዲኖር አወቅሁ፤ ሊጨመርበት ወይም ከእርሱ ሊጐድል አይቻልም፤ እግዚአብሔርም በፊቱ ይፈሩ ዘንድ አደረገ።መጽሐፈ መክብብ 3/14]
እርሱ ከሁሉ በፊት ነው፤ ሁሉም ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የጸናው በእርሱ ነው። እርሱ ለነዚህ የጽልመት ሃይላት ሳይቀር ከእግሩ መረገጫ ያደረገ ማለትም ከስልጣኑ ስር ያደረገ የበላይ ራስ ብቻ ሳይሆን በተቃራኒው ከተለመደው ስብከት እውነቱ ባሻገር እሱ ሁሉን በአላማ የፈጠረ ፈጣሬያቸውም ነው። ተረት የሚመስለው ድሮ እንደተነገረን መፈንቅለ መንግስት ካደረገው ከወደቀው መላክ ካር የወደቁ 1/3 ድሮ መላክት የነበሩ ቡሃላ እራሳቸውን ወደ ክፉት ሰራዊት የቀየሩ አይልም። ሁሉን ፈጠራቸው ግን ይላል። “የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል”
እርሱ የማይታየው አምላክን ወደ መታየት ያመጣ የሚታይ አምላክ ፉፁም የምስሉ የመልኩ መገለጥም ነው።
የሃይሉ ታላቅነት ስታስተውሉ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል ደግሞም ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር [በቃ እግዚአብሔር መ-ጀ-መ-ር-ያ ነው! “በ-መ-ጀ-መ-ሪ-ያ-ው ቃል(እግዚአብሔር) ነበረ!” የዮሐንስ ወንጌል 1/1 ፤ “በ-መ-ጀ-መ-ሪ-ያ እግዚአብሔር !” ኦሪት ዘፍጥረት 1:1] ነው ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤17 እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።”
መንፈሳዊው ነገር ልናስተውለው ከምንችለው በላይ ልእለ ተፈጥሮ ነው ታዲያ ጌታ እንዴት ያስረዳን ? መንፈሳዊውን የቃል አለም እነጳውሎስ ሲያዩ ያልተገባ ከማለት በቀር ቋንቋ አጡለት። [ወደ ገነት ተነጠቀ፥ ሰውም ሊናገር የማይገባውን የማይነገረውን ቃል ሰማ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/4 ]
‘እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም[መንፈሴንም(ከአብ[ከመንፈስ] ወጥቼ መጥቻለሁ)] ባወቃችሁት ነበር። ከአሁን ጀምሮ ግን ታውቁታላችሁ፤ አ-ይ-ታ-ች-ሁ-ታ-ል-ም።” ፊልጶስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አብን አሳየንና ይበቃናል” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “አንተ ፊልጶስ! ይህን ያህል ጊዜ ከእናንተ ጋር ስ-ኖ-ር አ-ታ-ው-ቀ-ኝ-ም-ን? እኔን ያየ አብን[መንፈሴንም] አይቶአል፤ እንዴትስ፣ ‘አብን[መንፈስን] አሳየን’ ትላለህ? እኔ በአብ [በመንፈሴ] እንዳለሁ፣ አብም[መንፈሴም] በእኔ እንዳለ አ-ታ-ም-ን-ም-ን? የምነግራችሁ ቃል ከራሴ አይደለም፤ ነገር ግን ሥራውን የሚሠራው በእኔ የሚኖረው አብ[መንፈሴ] ነው። እ-ኔ በ-አ-ብ እ-ን-ዳ-ለሁ አ-ብ-ም[መንፈሴም] በ-እ-ኔ እ-ን-ዳ-ለ ስ-ነ-ግ-ራ-ች-ሁ እ-መ-ኑ-ኝ፤ ሌላው ቢቀር ስለ ድንቅ ሥራዎቹ እንኳ እመኑ። ‘ ዮሐንስ 14:7-11
ግልጽ ቋንቋ የሚገባው ብሩክ ነው። ክርስቶስ እውነት ነው። ሌላ ሊሆን አይችልም።
ምክንያቱም እ/ር[መንፈስ] እውነት ነው ። እርሱም በእ/ር[መንፈስ] ውስጥ ያድራል። እርሱ ሌላ ሊሆን አይችልም እውነት እንጂ፤ ምክንያቱም እ/ር እውነት ነው እርሱም በእ/ር ውስጥ ያድራል፤ እርሱ ሌላ ነገር ሊሆን አይችልም ህይወት እንጂ እ/ር[መንፈስ] ህይወት ነውና እርሱም በእ/ር ውስጥ ያድራል። በውኑ የአባቱ[መንፈሱ] ሁለንተና በልጁ አድሮ የለምን? ጌታ እየሱስ ክርስቶስ የእ/ር ሙሉ ፈቃድ ነው። የራሱን ፈቃድ ሊያደርግ አልመጣም ነገር ግን የላከውና በእርሱ ውስጥ ያደረው የአባቱን ፈቃድ እንጂ። የሰራቸው ድንቆች ሁሉ “ስራውን የሰራው በእኔ ውስጥ ያለው አባቴ [መንፈሴ] ነው” ይላቸው ነበር። “የዮሐንስ ወንጌል 4/24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥” ለዚህም ነው ወጥቼ ወደ መጣሁበት ወደ አባቴ[መንፈሴ] እመለሳለሁ ሲል ወደ መንፈሴ ክብር እመለሳለሁ እያላቸው ነው። የተናገራቸው ታላላቅ የህይወትና የጥበብ ቃላቶችና አባባሎች የአባቱ[የመንፈሱ] ቃሎች ነበሩ። እርሱ እራሱ የእ/ር[መንፈስ] ቃል ነበረ። ብሩኩ እየሱስ ክርስቶስ የእ/ር[መንፈስ] ቃል ሰባኪ ብቻ አልነበረም እራሱ የእ/ር[መንፈስ] ቃል ነበረ እንጂ።
ይህን የዘልአለም የእ/ር ሚስጥር ከሚገልጡልን ቃላቶች አንዱ አስደናቂ ቃል በየሃ1/18 የሚገኜው ነው። “የዮሐንስ ወንጌል 1/18 መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን[መንፈስን] ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ[በመንፈሱ] እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።” የህያው ቃል ትርጉም እንዲህ ያስቀምጠዋል። “እ/ር[መንፈስን] መቼም ቢሆን ያየው ሰው የለም። ነገር ግን ከአብ[ከመንፈስ] ጋር ፍፁም አንድ የሆነው አንድ ልጁ እየሱስ ክርስቶስ መጥቶ ለአለም ገለጠው። ” ይህን ቃል Amplifid Bible“በየትኛውም ጊዜ እ/ርን[መንፈስን] ያየው ሰው በፍፁም የለም። ብቻውን ልዩ የሆነው ልጁ በእቅፉ የነበው እርሱ አወጀው።
እርሱ ገለጠው። ሊታይበት ወደ ሚችለው አወጣው። እርሱ እንዲታወቅ አደረገው።” RHM የተባለው ትርጉም ደግሞ “እርሱ ገለጠው አስተረጎመው” ይላል። እንዲህ ትርጉም ጽህፈት ቤት ሰው የሚሄደው በሚገባው ወይም በተፈለገው ቋንቋ ተተርጉም ነገሩን ለመረዳት ነው። ጌታ እ/ርንም[መንፈስንም] በሚገባን በሰው ቋንቋ ተርጉሞ አሳየን። ሌላ ትርጉም ሙልአት ወዳለው መገለጥ አመጣው ይላል። እንግዲህ እየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ውስጥ የሚኖረው የማይታየው አምላክና አባት ሙሉ መገለጥ ነው። እ/ር በሙልአት እራሱን በልጁ አስቀመጠ ወይም አደረ የማይታይ የዘልአለም ባህርዩን ለሰው ይገልጥ ዘንድ።
‘እርሱ የማይታየው አምላክ አምሳል ነው፤ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለ ሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። ‘ ቈላስይስ 1:15-16 ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል? ታድያ ሁለት ወይስ ሦስት ፈጣሪ አለ? በእርግጥም አንድ ፈጣሪ አለ።
በቡልይ እኔ ፈጣሪነኝ ሲል የነበረው በአዲስ ስለ እየሱስ ክርስቶስ ሲናገር የሁሉ ፈጣሪ ነው ይለዋል እና ስንት ፈጣሪአለ አንድ ሦስትም አይደለም አንድ።
ትንቢተ ኢሳይያስ 44/8 አትፍሩ አትደንግጡም፤ ከጥንቱ ጀምሬ አልነገርኋችሁምን? ወይስ አላሳየኋችሁምን? እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ የለም ማንንም አላውቅም።
‘“ከማሕፀን የሠራህ፣ የተቤዠህም፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሁሉን ነገር የፈጠርሁ፣ ብቻዬን ሰማያትን የዘረጋሁ፣ ምድርን ያንጣለልሁ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ‘ኢሳይያስ 44:24
ትንቢተ ኢሳይያስ 45/22 እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።
የዮሐንስ ራእይ 4/10-11 ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።
*ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ
[ይህን መንፈሳዊ ቅኔን እናስተውል። በኵር? የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ ክርስቶስ ነው።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/4 ። አሃ / የእግዚአብሔር ኃይል ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ጥበብም ክርስቶስ ነው? ታዲያ ጥበብ በኵር ከሆነ መቼ ነው ከእግዚአብሔር በኵር ወይም የመጀመርያ ሆኖ የተወለደው? እኔ ጥበብ፡ እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ፥ በቀድሞ ሥራው መጀመሪያ።ከጥንቱ ከዘላለም ጀምሮ ተሾምሁ ምድር ከመፈጠርዋ አስቀድሞ።ቀላያት ገና ሳይኖሩ እኔ ተወለድሁ፥ የውኃ ምንጮች ገና ሳይፈልቁ።መጽሐፈ ምሳሌ 8] ፤
‘እርሱ አካሉ የሆነችው የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ በሁሉ ነገር የበላይነት ይኖረው ዘንድ እርሱ የመጀመሪያ፣ ከሙታን መካከልም በኵር ነው። እግዚአብሔርም ሙላቱ ሁሉ በእርሱ ይሆን ዘንድ ወዶአልና፤ ‘ቈላስይስ 1:18-19
“ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1/15’እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ወሰናቸው፤ ይኸውም ከብዙ ወንድሞች መካከል እርሱ በኵር እንዲሆን ነው። አስቀድሞ የወሰናቸውን ጠራቸው፤ የጠራቸውን አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውን አከበራቸው። ታዲያ ለዚህ ምን እንመልሳለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፣ ማን ሊቃወመን ይችላል? ‘ሮሜ 8:29-31
-16 እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤17 ‘እርሱ ከሁሉ በፊት ነው፤ ሁሉም ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የጸናው በእርሱ ነው። ‘ቈላስይስ 1:17”
ክርስቶስ ለብዙ ነገር የበላይ ራስም ነው። የአሕዛብም ራስ፤ የሕይወትንም ራስ ፤ የማዕዘን ራስ፤ የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፤ የቤተ ክርስቲያን ራስ፤ የመዳንንም ራስ፤ ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ያመጣ የመዳናችን ራስ፤ የጥበብና የእውቀት ራስ፤ እርሱ የሁሉ ራስ ነው አካሉ የሆነችው የቤተ ክርስቲያን ራስ የመሆኑ ሚስጥር ግን ታላቅ ነው፤ የአንድ አካል ! “ ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5/32” ወደ ሮሜ ሰዎች 12/5 እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6/17 ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/12 አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤ወደ ገላትያ ሰዎች 3/28 አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።ወደ ገላትያ ሰዎች 3/27 ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1/18 እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው።
የራሱ አካል ለሆነችው የቤተክርስቲያን ማለትም የክርስቶስ አካል [በእርሱ ሙሉ ሆናችኋል! ye are complete in him!] ይላታል። ራስ በሆነው በእሱ የመሎኮት ሙልአት ሁሉ በእርሱ ውስጥ ቲፍ ብሎ ተሞልቶዋል ማለት አካል ማለት ከአንገት በላይ ካለው የጭንቅላት የአካል ክፍል ብቻ ሳይሆን ይሄ በንፈሳዊ የክርስቶስ አካል ልጅነት በጥቅሉ ልጆችን ሁሉ የሚጨምር ነው የአካሉ ሙልአት ናችሁና። የጭንቅላት ብቻውን ብታዩ ሙሉ አካል ነው ልትሉ አትችሉም። ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ በውስጣችሁ ተሞልታችኋል። ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል።
ያለመፈንዳታችንም ሚስጥር ነው። የመንፈሱ ሙልአት የማንነቱ መያዣ አርጎ የሰራን እርሱ ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5/ 4 በእውነትም የሚሞተው በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ የማንወድ ስለ ሆነ፥ በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን።5ነገር ግን ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን።
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3/2 ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን። እርፍ እሰይ!!!
ታዲያ ይሄ የእግዚአብሔር ህይወት ምንድ ነው? የእ/ር ህይወት የሁለንተናው ልእለ ተፈጥሮ ማንነቱ ይዞታ ሁሉ ታጭቆ ያለው በማያልቅ ህይወቱ ውስጥ ነው። እ/ር ውስጥ ያለው ሁሉ ነገሩ እና በእ/ር ህይወት እ/ር የሆነውን ሁሉ። ከማስተዋል በላይ የሆነው የሁለንተናው ክብር ተደብቆ ያለው በእ/ር ህይወት ውስጥ ነው። ጥበቡ እውቀቱ ፈቃዱ ኅይሉ ክብሩ ያለው በህይወቱ ውስጥ ነው። እያንዳዱ ነገር ካማይታየው ወደ ሚታየው ከመገለጡ በፊት ምንጩ ህይወቱ ነው።
(John 5:26 [AMP]) For even as the Father has life in Himself and is self-existent, so He has given to the Son to have life in Himself and be self-existent.
ጌታ ሲናገር “መጽሐፍት ሁሉ ስለ እኔ ይናገራሉ” በየትኛውም ቦታ በ እግዚአብሔር ቃል ውስጥ ወደ የትም ብትሄዱ የእየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ሆኖ ታገኙታላችሁ። ዮሐንስ ራዕይ እራሱ ተብሎ መሰየም የነበረበት የየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ነው። Rev 1/1 The Revelation of Jesus Christ….. [Revelation ]602 apokalupsis ap-ok-al’-oop-sis from 601; disclosure:–appearing, coming, lighten, manifestation, be revealed, revelation. see GREEK for 601 ይህ ክርስቶስ ተከድኖ ያለው በልጆቹ ውስጥ ነው። l ልክ ማእድ የያዘ መሶብ አክንባሎውን[ክዳኑን] ብድግ ብታደርጉት የተከደነው ማእድ ሁሉ ወደ እይታ እደሚመጣ ሁሉ ክርስቶስም ከተሸፈነበት መቅደሱ ቀስ በቀስ እየተገለጠ ነው።
ራዕዩ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንደሆነ በመንፈሳዊ ክብሩ የሚያስተምር መጽሐፍ ነው። በሁሉም መንፈሳዊ ክቡራዊነቱ ይገልጠዋል፤ በሙላትነቱ ይገልጣል፤ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ውስጥ በመንፈስ ቅኔ ወርቅና ሰም ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስን ታገኛላችሁ እርሱ ራሱ የእግዚአብሄር ክብር መገለጥ ነውና። የራዕይን መልእክት የሚያነብ ልብ በሚያነበብበት ጊዜ በእያንዳንዱ ገጽ ፊቱን ያያል በእያንዳንዳቸው መስመር ከክርስቶስ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ካላየን የሚታያየው ሁሉ ከንቱ ነው። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደዚህ መጽሐፍ በመቅረብ በክርስቶስ የክብር ባህር መዋኘት እንችላለን።
የእግዚአብሄር ክብር የክርስቶስ መልክ ነው። “ሁሉ ሃጥያትን ሰረተዋል የእ/ር ክብር ጎድላቸዋል” በሃጥያት ምንያት የጎደለብን ብር አልነበረም የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ነው። ሃጥያት የሚለው ጽንሰ ሃሳብ ልንረዳው ይገባል በግሪኩ HARMATIA ሲሆን ይህ እስፖርታዊ ቋንቋ ነው፤ ትርጉሙም ምልክትን መሳት ነው። MISSING THE MARK በአንድ ቀስተኛ ቀስቶ የቀስቱን ፍላጻውን ካሽቀነጠረ ኢላማውን ወይም አላማውን ከሳተ ውድዱሩን የሚያየው ህዝብ ሃማሪቲያ HARMATIA ብሎ በታላቅ ድምጽ ይጮካል። እኛም ኢላማችን የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ስለሳትን ሃማሪቲያ HARMATIA ሆነብን አሁን ግን እ/ር ይመስገን በሃማሪቲያ HARMATIA ያጣነው የጎደለብን የእግዚአብሄር ክብር በክርስቶስ ተመለስን። የእ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን ክ-ብ-ር ኢ-የ-ሱ-ስ ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ነው። የሐዋርያት ሥራ 7/55 መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን ክ-ብ-ር ኢ-የ-ሱ-ስ-ን-ም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፦
ይህ ክርስቶስ አሁን በእኛ ውስጥ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ‘ለእነርሱም እግዚአብሔር የዚህ ምስጢር ክብር ባለጠግነት በአሕዛብ መካከል ምን ያህል እንደሆነ ለማሳወቅ መረጠ፤ እርሱም የክብር ተስፋ የሆነው
በ-እ-ና-ን-ተ ው-ስ-ጥ ያ-ለ-ው ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ነ-ው።
‘ቈላስይስ 1:27
Colssians1/27. To whom God wills (purposed; intends) to make known by intimate experience, what [are] the riches of the glory of this Secret (or: the wealth which has it source in this sacred mystery’s manifestation which calls forth praise) within the multitudes (among the nations; in the Gentiles; among the swarms of ethnic groups), which is (exists being) Christ within you folks, the expectation of the glory (or: Christ, which continuously exists within you [is] the hope of the manifestation which calls forth praise),
*እየሱስ ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው!
ጌታ እየሱስ በምን ስልጣን ነበር የተራራው ስብከት ተብሎ በሚታወቀው በማቲዮስ 5-7 ትምህርቱላይ የፍቺውን ትክክለኛ ትርጉም ሲያርም የነበረው?
ሐዋርያው ጳውሎስ ሲነግረን ስለዚህ በፊት ክርስቶስን በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም፡ ከዚህ ቡሃላ መንፈስ ሆነዋልና። ብሎ ናል ።“ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15/45” “ ጌታ ግን መንፈስ ነው[ Now the Lord is that Spirit:]፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3/17” [2Cor 3/17 Now the Lord is that Spirit: and where the Spirit of the Lord is, there is liberty.]
እየሱስ ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው! ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በስጋ የመጣው ወደ መንፈስ ሊመራን ነው። በመጀመሪያው ቃል እንደ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር እንደነበረ። ቃልም ሥጋ ሆኖ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ እንደመጣ የማያምን ሁሉ ሃሰተኛ መንፈስ ነው የክርስቶስ ተቃዋሚውም መንፈስ ነው፤ ። ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ነው።
“1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4/2 የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥3 ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።”
*እየሱስ ፈጣሪም ነው ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰውም ያህዌ እሱ ነው! ይህንን እውነት ለማስተዋል በቀደሙት ክፍሎች በብዙ አይተነዋል እንዲሁም እያንዳንዱን መጽሐፍት ብትመረምሩ ጌታን በዛ ውስጥ ታገኙታላችሁ። የእብራይስጥ ቋንቋ እራሱ ይህንን እውነት ያረጋግጠዋል። አንድ የእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋ ማንም መረዳቱ የተሰጠውና ቃሉን የሚያጠና ሊቅ ሁሉ ሊያውቀው የተገባ ነው። “የእብራይስጥ ቋንቋ በአብዛኛው የአንድ ቃል ፍቺ ሃብታም ከመሆኑ የተነሳ ከአንድ በላይ ደራርቦ ሃሳብን ሊያሳይ ይችላል። የእብራይስጥ ቋንቋ ቃላት ስእላዊ ገላጭ ያለውና የድምጽ ገላጭም አጣምሮ የያዘ ሊሆንም ይችላል፡፡
ለምሳሌ ሁሉም ፈደሎች ቁጥርም ናቸው ቃላትም ናቸው። ለምሳሌ “alef” የመጀመርያው ፊደል ነው ያው ፊደል የመጀመርያው ቁጥር አንድ ማለትም ነው። “alef” የሚለው ያው ቃል በሬ ማለት ሲሆን ስእላዊ ገላጩም ጥንካሬን፤ ብርታትን [ymbolizes, strength] የሚያመለክት ነው። ሁለተኛው “beth” ቁጥር ሁለት ነው። “beth” የሚለው ቃል እራሱ ቤት ፤ቤተ ሰዎችና ፤ቤተሰቦችን [house or household] ያካተተ ፍቺ አለው።
በእብራይስጥ ቋንቋ ህግ ማለት Torah ነው። በእብራይስጥና ቋንቋ ቶራ[ Torah] ሲፃፍ tav-vav-resh-hey ሆኖ ይፃፋል። ይህ ከተያያዛበት ለየብቻው ቃሉ ሲተረጎም Tav ማለት ምልክት ወይም መስቀል ማለት “a mark or sign” [of the cross] ሲሆን። በዋናው በመጀመርያው ጥናታዊ ያልተበረዘ በእብራይስጥ ቋንቋ “መስቀል” ተብሎ ነበር የተፃፈው። በዘመናይ በእብራይስጥና ቋንቋ ተለይቶ ይገኛን። ይህም የሆነው በባቢሎን 70 አመት ምርኮ ጊዜ የባህል ወረራ ስለደረሰ ከአረሚክ ቋንቋ ጋር ተዳቅሎ ተበረዘ።
ሁለተኛው “vav” የሚለው በግልጽ ትርጉሙ እንደ አገባቡ የተሰቀለው፤በሚስማር
፤የተጠረቀመው፤የተቸከለው “a nail or peg.” ሲሆን ሶስተኛው “resh” የሚለው በግልጽ መሪ ወይም ራስ “a head, or leader.” ማለት ነው። በመጨረሻም “hey” በቃሉ መጨረሻ ሲቀመት ትርጉሙ ከሱ ወይ ከዛ የወጣ የተገኘ ማለት ነው። “what comes from.”
በእብራይስጥና ቋንቋ ህግ ማለትም Torah ከሚለው ቃል ፍቺ እምናስተውለው በመስቀል ላይ ከተሰቀለው መሪ ወይም ራስ የተገኘ “what – comes – from – the – Leader- nailed- to- the – Cross” ማለት ነው ። በሌላ አነጋገር እየሱስ ህግን የሰጠውና በመስቀል ላይ የተሰቀለው መሪ ወይም ራስ እሱ መሆኑን በዚህ ታላቅ ሚስጥር ውስጥ የእ/ር ድንቅ ስራ ይስተዋላል።
ጌታ እየሱስ ከስጋ ወደ መንፈስ ሊመራን ነው የመጣው። “2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡16 … ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።” አዎን አሁን 33 ½ አመት በስጋ ውስጥ ተዎስኖ እደነበረው አይደለም ህይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነዋል:: “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡45 …ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።” ደግሞም ከሰማያት ሁሉ በላይ አልፎ ሁሉን ሞልቶታል በስጋ ተወስኖ ሁሉ መሙላት አይችልም ወደ መንፈስ ክብሩ ተመልሶ እንጂ። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡10 ይህ የወረደው ሁሉን ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ደግሞ ያው ነው።
Eph 4፡10 He that descended is the same also that ascended up far above all heavens, that he might fill all things.)”
ጌታ እየሱስ ከስጋ ወደ መንፈስ ሊመራን ነው የመጣው ሲባል በሙሴ ህግ በስጋ መገረዝ፡ ቅዱስ ቀናትን መጠበቅ ሰንበትን መጠበቅ፡ ወዘተ ብዙ ነገሮች አካላዊ ግዴታዎች ነበሩ። ጌታ በጠበቀ ሁኔታ በመንፈስ ህግ መጣ በማቴ 5፡6፡7 ሲናገር እንደዚህ ሲባል ሰምታችሃል(በሙሴ ህግ ማለት ነው) እኔ ግን እዲህ እላችሃለሁ እያለ ምሳሌን ሰጠ
በሙሴ ማል በክርስቶስ ፈጽመህ አትማል
በሙሴ ጠላትህን ጥላ በከርስቶስ ጠላትህን ውደድ
በሙሴ አትዘሙት በክርስቶስ ወደ ምንጩ ሄዶ በአይንህ አይተህ በልብህ አትመኝ
እያለ ከስጋ ድካም ወደ መንፈስ ብርታት ዘወር እድንል አስተምራል።
እምናወራው ያለው ስለ መንፈሳዊ ነገር እደሆነ እንደ ተሰመረበት ይሁንና ስለ ስምምነት ስናነሳ መንፈሳዊውን ስምምነት በምሳሌ የሚያስስረዱ ሁለት አይነት የጋብቻ ግንኝነቶች እንዳሉ ሳይወሳ መታለፍ የሌለበት ነው።
በገላቲያ4: 22/31-22 አንዱ ከባሪያይቱ አንዱም ከጨዋይቱ የሆኑ ሁለት ልጆች ለአብርሃም እንደ ነበሩት ተጽፎአልና።
23 ነገር ግን የባሪያይቱ ልጅ እንደ ሥጋ ተወልዶአል፥ የጨዋይቱ ግን በተስፋው ቃል ተወልዶአል።
24 ይህም ነገር ምሳሌ ነው፤ እነዚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ኪዳኖች ናቸውና። ከደብረ ሲና የሆነችው አንዲቱ ለባርነት ልጆችን ትወልዳለች፥ እርስዋም አጋር ናት።
25 ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ ሲና ናት፤ አሁንም ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና።
26 ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት የምትኖር ናት እርስዋም እናታችን ናት።
27 አንቺ የማትወልጅ መካን፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፥ እልል በዪና ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአል።
28 እኛም፥ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን።
29 ነገር ግን እንደ ሥጋ የተወለደው እንደ መንፈስ የተወለደውን በዚያን ጊዜ እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው።
30 ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? የባሪያይቱ ልጅ ከጨዋይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት።
31 ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጨዋይቱ ልጆች ነን እንጂ የባሪያይቱ አይደለንም።”
ሐዋሪያው ስለ ሁለት ኪዳኖች በሁለቱ ሚስቶች እንደ ሚመሰሉ ነግሮናል ማለትም አጋርና ሳራ ባሪያይቱና (bondwoman) ነጻ ያልሆነችው ሴትና ጨዋይቱ (freewoman) ነጻይቱ ሴት ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሁለት የተለያዩ የጋብቻ አይነቶች ነበሩ። ሰውየው ባሪያይቱን ካገባ ያላቸው ግንኝነት የጌታና የባሪያ ነው። እዲህ አይነትዋ ሚስትም ያላት መብት ውስን ሲሆን በቤተሰብ ውሳኔ ውስጥ ምንም ድምጽ የላትም። ባልዋ እድሉን ሊያቀርብ ይችላል ነገር ግን እደዛ እዳያደርግ የተወሰነ ነበረ።
ይህ የአጋር አይነት የጋብቻ ግኑነት ነው። እስራኤል ከእ/ር ጋራ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ በጋብቻ በተሳሰሩ ጊዜ ያለውንም ያሳያል። ይሄ የአሮጌው ኪዳን ጋብቻ ነው። በዘፅአት 19/5 እስራኤል ለባልዋ ለመታዘዝ መማል ነበረባት። እስራኤልም የእ/ር አገልጋይ ሚስቱ ሆነች። ይሄ መጥፎ አይደለም በዛው አንጻርም እ/ር ከህዝቡጋር ሙሉ ለሙሉ የሚፈልገው ጋብቻ አይደለም። የተሻለ ህብረትን ይሻልና ለዚህም ነበር በአጀንዳው ውስጥ እስራኤልን ሊፈታት እቅዱን ያስቀመጠው።
“ትንቢተ ኤርምያስ 3፡8 ከዳተኛይቱም እስራኤል ስላመነዘረች ስለዚህ ፈትቻታለሁ የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን እንዳልፈራች እርስዋም ደግሞ ሄዳ እንደ ጋለሞተች አየሁ።
Jer 3፡8 And I saw, when for all the causes whereby backsliding Israel committed adultery I had put her away, and given her a bill of divorce; yet her treacherous sister Judah feared not, but went and played the harlot also.” ከዛም በተሻለ ነገር ላይ የተመሰረተውን አዲሱን ኪዳን አደረገ።
አዲሱ ኪዳን የተመሰለው በነጻይቱ ሴት በሳራ ነው። በአዲሱ ኪዳን የተመሰረተው ጋብቻ መታዘዝ በሚለው ሃሳብ ላይ የተመሰረተ አይዳለም። ሁለት የተጋቡ ወንድና ሴት ከተስማሙ እዲታዘዙ መናገር የሚያስፈልግ አይደለም። አንዳቸው አንዳቸው አንድን ነገር እንዲያርጉ በስልጠን የሚያዙበት ምክንያት የለም ስምምነቱ አለና ። የቤተሰብ ስልጣን የሚገለጠው የስምምነት እጥረት በመካከላቸው ካለ ነው።
በዚህ ምንያት እ/ር ድል ነሺ ካልሆኑበቀር ለማግባት ሃሳቡም የለውም። ድል ነሺነው ከእ/ር ጋር ወይም ከጌታ እየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚስማማው። ድል ነሺ የጌታን አይምሮ ያውቃል አሊያም እንዲያውቀው ይሻል። የእ/ርን ፈቃድ ሲያገኘውም ከፈቃዱ ጋር ተስማምቶ እራሱን ያገኘዋል። አልያም ከፈቃዱ ጋር ፍጹም አንድ እስኪ ሆን መረዳትን ለመቀበል እስከ መጨረሻው ይሻል። በመንፈሳዊ እድገት የመማር ሂደት ወስጥ በእርግጥም ድል ነሺው የእ/ርን ሃሳብ ቶሎ ላያስተውል ይችላል:: እንደ እ/ር አገልጋይ እ/ርን ይታዘዛል። ሙሉ ግንዛቤን ገና ስላላገኘ ፈቃዱን በማድረግ ብቻ ገና አልረካም የእ/ርን አይምሮ እስኪ ያገኘውና ገብቶት በሙሉ ስምምነት እራሱን እስኪ ያገኘው ወደ ፊት ይዘረጋል።
ከእ/ር ጋር አለመስማማት ምክንያቱ የመረዳት እጥረት ነው። መላው አለምን እ/ር እንደሚያየው ብናየው እ/ር የሚያደርገውን ሁሉለምን እደሚያደረገው ያለመስማማት ባልኖረ ነበር። ችግሩ አለም ሁሉ መለኮት ከሚያየው አካያ አናየውም። ይህ አብ አንድን ሰው ወደ ጌታ እንደ ሳበው በጌታ እንደሆነ የሚገኝ ለውጥ አይደለም። በመንፈስ ሲሞላም በነገር ሁሉ ከእ/ር ፈቃድ ጋር ሙሉ ለሙሉ መስማማቱ ወድያው አይመጣም። ከእ/ር ጋር አብሮ መጔዝን ይጠይቃል አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ የእ/ርን ባህርይ አይበዘብዝም አብሮ ጊዜ ማሳለፍን ይጠይቃል ደቀ መዛሙርቱ ሰዎች ከንግግራቸው የተነሳ ከእየሱስ ጋር እደነበሩ ያወቁት ለሰዎስት አመት ተኩል አብረው በመውጣት በመግባት ባህርዩን በከፊል ስለ ተካፈሉ ነው።
መጽሐፈ ኢዮብ 22:21 አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ በዚያም በጎነት ታገኛለህ።
22 ከአፉም ሕጉን ተቀበል፥ በልብህም ቃሉን አኑር፤
23 ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመለስ፥ ብትዋረድም፥ ኃጢአትንም ከድንኳንህ ብታርቅ፥
24 የወርቅን ዕቃ በአፈር ውስጥ፥ የኦፊርንም ወርቅ በጅረት ድንጋይ መካከል ብትጥል፥
25 ሁሉን የሚችል አምላክ ወርቅና የሚብለጨለጭ ብር ይሆንልሃል።
26 የዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፥ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታነሣለህ።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡19 ….የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዎንና አይደለም አልነበረም፥ ነገር ግን በእርሱ አዎን ሆኖአል።
የዮሐንስ ራእይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል። ለእ/ር ፈቃድ አሜን እደሆነ እኛንም አሜን ያድርገን።አሜን። ክፍል ሶስት ጌታ እንደፈቀደ መጠን ይቀጥላል። እወድዳችሃለሁ ተባረኩልኝ። ወንድም ቢኒ።