እግዚአብሔር የሰዎች ሁሉ አዳኝ ነው


ከውይይት የተጠቀሰ፤ ሰላም ወንድማችን፤ FasilAndarge ፤ እግዚአብሔር #የሰዎች#ሁሉ#አዳኝ ነው! ጥሩ ነው ሥነ- አመንክዮህን በሁለት አስቀምጠከዋል። አሁን ያነሳካቸው ከመሰረታዊ ሃሳቦች አሁንም ከፊል እውነት ናቸውና ችግር የለብኝም እኔም ብሆን ዛሬ ያስታወስከንን እይታዎች ከሞላ ጎደል በቤተ/ክርስቲያን የዛሬ 20 አመታት ገደማ አስተምራቸው ነበር። እንዳልከው ሁሉም ይድናሉ ሲባል የራሱ የሆነ የእ/ር አካሄድ ጌታ አለው። ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና እሳቱ ደግሞ የእ/ር የሚባላ እሳት ባህርዩ ነው ስለዚህ በማንነቱ ሰው ሁሉ ይቀመማል። የሚበላውም በሰው(አዳማዊ ተፈጥሮና ባህርይ) ውስጥ ያለው የአመጻ ሚስጢር ነው። ወደ ዕብራውያን 12፡29 አምላካችን በእውነት የሚባላ እሳት ነውና። Heb 12፡29 For our God is a consuming fire.መቸም ይገባሃል የምናወራው መንፈሳዊ ነገር ነው። ለመንፈሳው ሰው ሁሉ ነገር መንፈሳዊ ነው ለተፈጥራዊ ሰው ሁሉም ነገር ተፈጥራዊ ነው ኢየሱስን አስብ። ፍርድ የለም ሳይሆን እኛ ያልነው ፍርዱ ዘላለማዊ ሳይሆን በጊዜ የተገደበ ነው። እ/ር ፉጡራኑን በእሳት እየቀቀለ ለዘላለም የማሰቃየት አባዜ እየለብትም ፍርዱ ሲገለጥ በአላልማ ነው አላማውም ጽድቅን ለማስተማር ነው። ትንቢተ ኢሳይያስ 26፡9 #ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ #ጽድቅን#ይማራሉና ። የእ/ር የእሳቱ ባህርይ ልንገነዘበው ይገባል። ሚልክ 3/2 ነገር ግን እርሱ[እ/ር] እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ[እ/ር] በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው? 3 እርሱም[እ/ርም] ብርን እንደሚያነጥርና እንደ ሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ። በዚህ ተምሳሌታዊ አነጋገር ፈጣሪ እንደ አንጥረኛ ብቻ ሳይሆን የሚመጣው እንደ አንጥረኛ “እሳትም” ሆኖ ነው የሚመጣው። ደግሞም እንደ ልብስ አጣቢ ብቻ ሳይሆን የሚመጣው እንደ አጣቢ ”ሳሙናም“ ነው የሚመጣው። እንደ ባለተክሎ የሚቀመጠው እሱ ነው! እሳቱም እሱ ነው! አጣቢውም እሱ ነው! ሳሙናውም እሱ ነው!ለመሆኑ በተፈጥራዊው አለም አንጥረኛ ወይም ባለ ተክእሎ ሰው አላማው ምንድ ነው? ብርን በእሳት ሲያነጥረው ብሩን ወይም ወርቁን ድራሹን ለማጥፋት ነውን? አይደለም! ብሩን ለማንጠርና ለሚፈልገው ውበትና ክብር ሊያውለው እንጂ! በቅድሚያ ወርቁን ሊፈትን በእሳት ውስጥ ይከተዋል። ወርቁንም በእሳት ሲፈትን አርቲፊሻል የወርቅ ቅብ ከሆነ የሸፈነው እየተቀረፈ እየወደቀ የውስጥ ክብሩ እየተብለጨለጨ ቢጫ እየሆነ እየባሰበት እየደመቀ እሳቱ ዉበቱን እየገለጠው ይመጣል ዚንኩ ሁሉ[መራራ ማንነት] ከአፈሩ [ምድራዊ ማንነት ሁሉ] ጋር ተፈልቅቀው ይገነጣጠላሉ። ባለ ተክእለውም ሰው በሂደቱ ጊዜ ወርቁ እሳት በዝቶበት እንዳ ይበላሽ ፊቱን አስጠግቶ አይኑን ተክሎ ያየዋል ወርቁ የሰውየውን መልክ ካንፀባረቀ ወርቁ ለሚፈልገው ክብር መድረሱን ያውቃል ያን ጊዜ ብቻ ያወጣዋል። እ/ርም የሰውን ዘር በእሳት ባህር ማንጠሩ ላማጥፋት ሳይሆን መልኩና አምሳሉን በሰው ውስጥ ለማየት ነው። መልኩን ካየ ቡሃላ የእሳት ባህሩ ውስጥ ዳግም ለመክተት አያስፈልገውም። እ/ር ይመስገን። የከበረ ነገር አለህ የአባት ፈቃድ ከሆነ አንድ ነገር ከቃሉ እንዲቀርልህ እፈልጋለሁ። ለምሳሌ ያህል የጌታን ቃል በአጽናኦት ካስተዋልነው የማቴዎስ ወንጌል 25-46 እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ። በግሪኩ ዘላለም ቅጣት፥ “kolasin aionion.” Kolasin “punishment ቅጣት፤, chastening አሳዶ መቅጣት፤ , correction ማረም, to cut-off as in pruning a tree to bare more fruit መቁረጥ ልክ እንድን ዛፍ አብዝቶ እንዲያፈራ እንደ መግረዝ.” “aionions” የሚለው ቃል የተረጎመ ነው የቃሉ ስር ወይም፡ ንብረትነቱ “EION” ነው። ትርጉሙም “ዘመን age” ማለት ነው። ሁለቱ የተለያየ ትርጉም ያላቸው ናቸው ማለት አይደለም ። aion(the noun form) ሰዋሶው ወይም ነባር ስም ሲሆን aionions (the adjective form ቅጽል ነው። ሁለቱ ቃላት ሰዋሶው እና ቅፅል ናቸው። ለምሳሌ ሳምንት ሰዋሰው ሲሆን ሳምንታዊ ደግሞ ተቀፅላው ነው። ልክ እለት፦ እለታዊ, አመት ፦አመታዊ እንደሚባለው መለት ነው። Greek word “aion” (Strongs #165) or its adjective form “aionios” (#166).እንግዲያው ይህን ካስተዋልን ተብሎ መተርጎም የነበረበት “የማቴዎስ ወንጌል 25-46 እነዚያም ወደ ዘመኑ ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘመኑ ሕይወት ይሄዳሉ።” ወደ ዘመየኑ ቅጣቱና የጊዜው ጉዳይ ስናይ ወደ ቅጣት የሚሄዱትም ለዘላአለም ሊደመሰሱ ወይም ሊሰቃዩ ሳይሆን 1,ኛ”Kolasin “punishment ቅጣት፤(እንዲቀጡ), 2,ኛchastening አሳዶ መቅጣት፤(ይህ ቃል chasteneth በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት እንዴት እንደተጠቀመበት እናስተውል KJV Heb 12/6 For whom the Lord loveth he chasteneth, and scourgeth every son whom he receiveth) , 3,ኛcorrection ማረም (Correctional judgement የሚያርም ፍርድ ነው), 4,ኛto cut-off as in pruning a tree to bare more fruit መቁረጥ ልክ እንድን ዛፍ አብዝቶ እንዲያፈራ እንደ መግረዝ.”ጻድቃን ግን ወደ ዘመኑ ሕይወት ይሄዳሉ። የእ/ር ህይወት በባህርዩ ዘልአለማዊ ቢሆንም ያ ህይወት የተወጋው ዘልአለማዊ ባልሆነ ማንነት ላይ ስለሆነ የዘመኑ ህይወት ተባለ ።(Matt 25:46Open in Logos Bible Software (if available) [YLT])And these shall go away to punishment age-during, but the righteous to life age-during.’ ወደ ምፈልገው ሃሳብ ለመምጣት በቅድሚያ የአባታችንን ጠቅላላ ምክሩ በልባችን እንዲቀርልን የእ/ር ቃል የእ/ር የልቡን ትርታ እንደመስማት ነውና ፤ መንፈሳዊው ጻድቅና ቅዱስ አባታችን ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገረውን አንርሳ፥ #ሁሉን ነገር #የሚታደስበት ዘመን እቅዱ ውስጥ እንዳለ መርሳት የለብንም። አንተም እኔም እናውቀዋለን እ/ር አለ ማለት ሆነ ማለት ነው። ይህ አዲስ ትምህርት አይደለም ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ በእምነት አባቶችም ወዘተ…. ሊያደርግ ያለውን እቅድ ይናገር ነበርና። የሐዋርያት ሥራ 3፡21 ፣ በክርስቶስ ያቀደውንም የፈቃዱን ምስጢር እንደ በጎ ሐሳቡ እንድናውቅ አደረገ። [ምንድን ነው ያቀደው?] 10በዘመን ፍጻሜ ይሆን ዘንድ ያለው ሐሳቡ #በሰማይም#በምድርም ያሉትን ነገሮች #ሁሉ ራስ በሆነው #በክርስቶስ#ሥር#ለመጠቅለል ነው። ኤፌሶን 1፡10የእ/ር አባታችን የዘላለም አጀንዳው እቅዱ በክርስቶስ ሊያደርግ ያሳወቀንን ፈቃዱን ስንነጋገር አብዛኛዎቹ ወገኖችና ሰባክያን ዘላለማዊ ሞትና ገሃነም ብሎ ነገር እንደሌለ ያውቃሉ ገሃነም የፍርድ ምሳሌ ነውና ፣ ሞትም ቢሆን እንደ እ/ር ቃል የመጨረሻው ጠላት ሞት እንደሚደመሰስ እንደሚሻር ያውቃሉ፤ ይህ የፈቃዱን ሚስጥር ቢክዱትም በቃሉ እንዳስታወቀን እንዳለ ያውቃሉ። በዘመን ፍፃሜ ሊያደረግ ያለው ሀሳቡም #ሁሉን[የሁሉ ትርጉም ሁሉ ነው] በክርስቶስ ስልጣን ስር ሊጠቀልል እንደወሰነ ያውቃሉ። ወዘተ….. ፅፎልናል።“ኤፌ2/6 አንዳንዶች ደግሞ የጸጋው ዘመን ያበቃልም ይላሉ። ቃሉስ ምን ይላል? በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር ኣስቀመጠን። ይኸውም #በሚመጣው#ዘመን በክርስቶስ ኢየሱስ በቸርነቱ የገለጠልን ወደር የሌለውን የፀጋውን ባለጠግነት #ያሳይ#ዘንድ ነው። ምን ምን አለ? በሚመጣው ዘመን ፤በሚመጣው ዘመን እሺ? …ወደር የሌለውን #የፀጋውን#ባለጠግነት#ያሳይ ዘንድ ፤#በሚመጣው#ዘመን ….በሚመጣው ዘመን በክርስቶስ ኢየሱስ በቸርነቱ የገለጠልን ወደር የሌለውን የፀጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ነው። እልልልልልልልልልልልልልል… በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ወይም በመንፈሳዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር ያስቀመጠን ምክንያት ወደር የሌለውን የፀጋውን ባለጠግነት ፤ ለፍጥረት በተራው በሚመጣው ዘመናት ለፍጥረት ሁሉ ገና ያሳይ ዘንድ ይህን አደረከ።የእንግሊዝኛው ትርጉም ቅደም ተከተሉ ሳይዛባ ተፋሰሱን ጠብቆ እንዲ ያስቀምጠዋል። Eph 2/7…THAT IN THE AGES TO COME HE MIGHT SHOW (greek; exhibit,put on display for all to see) THE EXCEEDING RICHES OF HIS GRACE in his kindness toward us in Christ jesus” የፀጋውም ባለጠግነት በሚመጡት ዘመናት ለፍጥረት ሁሉ ያሳየዋል ያስጎበኘዋል። ይህም የሚገልጠው በእ/ር ልጆች በክብር መገለጥ ጊዜ ነው። አሁን እያዳነ ያለው የመንፈስ በኩራት የሚቀበሉትን ነው። እ/ር አሁን ሁሉን በአንዴ ለማዳን ኣላማው አይደለም። እደዛ ሲሆን ፈቃዱን በቅፅበት ባደረገው ነበር። በሚመጡት ዘመናት የፀጋውን ባለጠግነት ለፍጥረት ሁሉ የሚያሳዩለትን ህዝቦች እየሰበሰበ ነው። ያቆብ ይህን ያስተውል ዘንድ ተሰጥቶት ስለ ነበር እንዲህ ብሎ አወጀ። እ/ር ለሱሙ የሚሆን ወገን ከአህዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጎበኘ ስምኦን ተርከዋል። ከዚህ ቡሀላ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩ ኣህዛብ ሁሉ ጌታን ይፈልጉ ዘንድ እመለሳለሁ.….ከጥንት ጀምሮ ስራው ሁሉ በእ/ር ዘንድ የታወቀ ነው። ሀዋ15/14,17,18” እንደ እውነቱ ከሆነ “የፀጋ ዘመን” ሊያበቃ ነው መባሉ ከእውነት ዘንድ ኣይደለም። ፀጋ ግን ከቀደመው ግዜ ይበልጡኑ በሚመጡት ዘመናት እንደባለጠኘቱ መጠንን አብዝቶ ለፍጥረት ሁሉ ይገለጣል።እንዲያውም ይሄ በቅርቡ ሊዘጋ ያለው ዘመን የቤተ ክርስትያን ዘመን ተብሎ ሊጠራ ይገባል። ፀጋ አያበቃምና። ነገር ግን አሁን ያለው ገፅታና የቤተ/ክ መስተዳድር ያበቃል። በሚመጡት ዘመናት እ/ር ለስሙ የሚጠሩትን አካል ተፈፅሞ ወደ ህዝቦች ሁሉ ወደ ፍጥረት ሁሉ ማዳን ይሻገራል ይንቀሳቀሳልና። ቤተ/ክ {church[ecclesia,በግሪኩ]} ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን “ተጠርተው የወጡ” ማለት ነው።ቤተ/ክ ማለት በቀላሉ በክርስቶስ እየሱስ ያሉት ከአለም ተጠርተው የወጡት አማኞች ማለት ነው እንጂ በዚህ ዘመን የምናየው ትእይንት አይደለም። እስቲ ፀጋ በግዜ የማይወስን መሆኑን እናስተውል። “1ኛጢሞ1/9 ያዳነንና በቅዱሱ አጠራር የጠራን እ/ር ነውና ይህም እንደራሱ ሀሳብና ፀጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ስራችን መጠን አይደለም። ይህም ፀጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት{BEFORE THE WORLD[ages] BEGAN ተሰጠን” የፀጋው ባለጠግነት የተሰጠን ዘመናት[ጊዜያት] ከመጀመራቸው በፊት ነው። ስለዚህ ፀጋ በጊዜ የታሰረ አይደለም። እ/ር ፀጋን ለመግለጥ ሁሉንም ዘመን መጠቀም ይችላል።“ወደ ሮሜ ሰዎች 9/16 እንግዲህ ምሕረት ለወደደ[ግሪክ፡ ለፈቀደ willeth] ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ። Rom 9/16 So then it is not of him that willeth, nor of him that runneth, but of God that sheweth mercy.” እንግዲህ ምሕረት ለወደደ willeth ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚ ምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ። but of God that sheweth mercy.” እንዴ ምንድ ነው ነገሩ እ/ር ከፈቃዳቸው ውጪ ሰዎችን ሊያድን ይችላል? ሊነሳብን ይችላል። መልሱ አይደለም ነው። እንደዛ ማድረግ አያስፈልገውም። ሰው ሁሉ እ/ር እራሱን ሲገልጥለት መቶ በመቶ ፈቃደኛ ይሆናልና። መንፈሳዊ እውርነቱ ሲበራ ወይም የዶንቆሮው ጆሮ ሲከፈት ለሙታንም ህይወትን ሲሰጠው ለከንቱነት የተገዛው ተፈጥራዊው ማንነት ፋንታ መንፈሳዊ አእምሮ ሲሰጠው ሲመለስለት ሁሉ የሰማይ አምላክን ያመሰግናል። እኛ የዳነው “በእምነታችን በኩል በጸጋ ነው” (ኤፌ 2 8), ነገር ግን ከእግዚአብሄር እስካልተሰጠን ድረስ እምነት የእኛ አይደለም. ሮሜ. 12: 4, “እግዚአብሔር ለእያንዳንዱም የእምነትን መጠና አካፈለው ለገሰው” እግዚአብሔር ለእኛ እምነት ከሰጠን በኋላ የእኛ ይሆናል! በጣም ቆንጆና ቀላል ሆኖ ልንረዳው ከምንችለው በላይ ባለመፃፉ ደስ ይላል። ሁሉ የሚድነው በእ/ር የማዳን ሃይል ነው። ሓዋርያው ጳውሎስ ከሃጥያተኞች ሁሉ ዋንኛ የምሆን እኔን የማረው አቅሙን ለማሳየት ምሳሌውን ለማሳየት ነው አላለንምን? ጌታ ፈቃዱን ሳይጠይቅ በታቅ ብርሃን፡ ጳውሎስ ላይ አልወደቀብትምን ታድያ ምንም እንካ ሳኦል[ጳውሎስ] ከሃጥያተኞች ሁሉ ዋንኛ ቢሆንም ጌታን ተቀበል ብሎ ፈቃዱን ጠየቀውን? ትእይንቱን እናስተውል እ/ር እራሱን ሲገልጥለት ሃጥያተኛው ሳኦል[ጳውሎስ] መቶ በመቶ ፈቃደኛ ሆኖ እያለቀሰ “ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ!!!” በቃ ፍጥረትም እዲሁ ነው እ/ር እራሱን ሲገልጥለት መቶ በመቶ ፈቃደኛ ይሆናል። ማወቅ ያለብን የእ/ር ታላቅ አሰራር መካከል “ጌታ ጌታየን ሁሉን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው” ማለትም ከእግሩ ስር የሚያመለክተው ሁሉን ከስልጣኑ ስር እስኪ ያደርግለት ድረስ ማለት ነው የሁሉ ትርጉም ደግሞ ሁሉ ነው።እናስተውል“1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/3 ….በመንፈስ ቅዱስም ሃይል ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ። 1Cor 12/3 ….that no man can say that Jesus is the Lord, but by the Holy Ghost” እናስተውል አሁንም። በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቆናል አሁን ጠላቶቹ የሆኑት አድስዋቸው ከክርስቶስ ስልጣን ስር ሲጠቀለሉ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ሆነው ኢየሱስ ጌታ ነው እያሉ ለበጉ ክብርን ተንበርክከው ይሰጣሉ። “የዮሐንስ ራእይ 5/13 #በሰማይና#በምድርም#ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ #ፍጥረት#ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን[ኢየሱስ ክርስቶስ] ሲሉ ሰማሁ። Rev 5/13 And every creature which is in heaven, and on the earth, and under the earth, and such as are in the sea, and all that are in them, heard I saying, Blessing, and honour, and glory, and power, be unto him that sitteth upon the throne, and unto the Lamb for ever and ever.” እንግዲህ የመጨረሻው ጠላይ ሞት ከነ መውጊያው ከሃጥያት ጭምር ሲደመሰስ እ/ርም እራሱን ለፍጡራኑ ሲገልጥለት መቶ በመቶ ፈቃደኛ ሆኖ እያለቀሰ በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በመንፈስ ቅዱስም ሆነው በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ይላሉ።። አሜን!ጌታን ሳይቀበሉ በድንገት የሚሞቱትስ እነሱም ይድናሉ? እንግዲህ እስካሁን ወንጌልን ከሰማው ያልሰማው ይበዛል 162 ቢልዮን ሰዎች እስካሁን እንደተፈጠሩ ይገመታል ከነዛ ውስጥ ወደ 4 ቢልዮን ሰዎች ክርስቲያን ናቸው ተብለዋል የቀሩት 158 ቢልዮን ህዝቦች ጌታን ሳያውቁ አልፈዋል። በውኑ እ/ር ፍቅር ከሆነ ፍቅር 158 ቢልዮን ህዝቦች ጌታን ሳያውቁ ስለቀሩ ለዘልአለም ያሰቃያቸዋልን? ይህ ከሱ ይራቅ የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን? የእ/ር ፍርድ ለማረም ነው ወይስ ለዘልአለም በእሳት ለማሳቃየት?ኢሳ 29/9 ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩት ጽድቅን ይማራሉና: በእለም ያሉ ሁሉ ጽድቅ ተምረው ታይቶ ይታወቃልን ስለዚህ ይህ ገና የሚፈጸም ትንቢት ነው። when thy judgments are in the earth , the inhabitants of the WORLD will learn righteousness .[uprightness & right standing with GOD.] Isaiah 26/9 አስተዋላቹሁን ፍርዱ በአለም ሲገለጥ ምንን ይማራሉ ይላል? ጽድቅን! ሃሌሉያ!Ps 130፡4 But there is forgiveness with thee, that thou mayest be feared ትፈራ ዘንድ በአንተ ዘንድ ይቅርታ አለ። አሜን።ከላይ ወዳነሳካቸው ሃሳቦች እንመለስና እውነት ነው እምነት ከመስማት ነው መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል ነው። አሁንም ደግሜ እላለሁ ኢየሱስን አስብ ከስጋ ወደ መንፈስ ሊመራን ነው የመጣው ይገባሃል የምናወራው መንፈሳዊ ነገር ነው። ለመንፈሳው ሰው ሁሉ ነገር መንፈሳዊ ነው ለተፈጥራዊ ሰው ሁሉም ነገር ተፈጥራዊ ነው። መንፈሳዊ ማስተዋሉ ፈጣን ለሆነ ግልጽ ነው መንፈሳዊ እውቀት ለአስተዋዮች ካልሆነ ለቸልተኞች የተከለከለ ነውና በማስተዋል እንየው። አንተ ሃጥያትን በሁለት ከፍለከዋል ሆኖም የተያያዙ መሆናቸውን አትርሳ የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው፤ በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ሁለ ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና። ህግ ምንም ቢቃወመንም ወደ ክርስቶስ እንድንመጣ የተነደፈ ነው። “ገላ 3/24 ተመልከት. ህግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣን ሞግዚታችን ነበረ።የዘላለም ሞት ስትል ምን ማለትህ ነው? ሞት ይሻራልና!ሰው የመጀመርያውን የፍርድ ብይን የሰማው በኤደን ነበር። የሰው ዘር ሁሉ ገና በአዳም ወገብ ውስጥ ሳለ አዳም ያለመታዘዙ ሀጥያት ቅጣትና እርማት እንደሚገባው በመለኮት ታምኖበት ብይኑ ተነገረው። “ዘፍ2/17ሞትን ትሞታለሁና” በዚህም ጥቅልል የጅምላ ፍርድ ለመጀመርያ ጊዜ ስጋ ሁሉ በሞት ተነካ። “ 1ኛቆሮ ሁሉ በአዳም እንደሞቱ ከቃሉ እንደምናስተውለው ሁሉ በአዳም እንደሞቱ ይነግረናል።” በሮሜ5/12 ደግሞ፡ ስለዚህ ምክንያት ሀጥያት በአንድ ሰው ወደ አለም ገባ በሀጥያትም ሞት እንደዚሁም ሁሉ ሀጥያትንስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ” ። ጥያቄው ታድያ ሞት ዘልአለማዊ ነውን? ዘልአለም ማለት መጀመርያ የሌለው መጨረሻም የሌለውነው። እንደ መፅሀፍ ቅዱስ ቃል እንመን ከተባለ ሞት ግን ጅማሬ አለው ፍፃሜም አለው።ስለዚህ ሞት ዘልአለማዊ አይደለም።“1ኛ ቆሮ 15/26 የመጨረሻው ጠላት የሚደመሰሰው ሞት ነው በውኑ እዚህ ጋር መንፈስ ቅዱስ ልናስተውለው ከምንችለው በላይ አፅፎልናልን? እንደ ቃሉ ሞት የሚደመሰስ ከሆነ ሞት ዘላለማዊ ነውን? እንደተፃፈው ሞት ፈፅሞ ይደመሰሳልና ዘላለማዊ አይደለም። ሞት ዘላለማዊ ካልሆነ ደግሞ ዘላለማዊ ሞት ብሎ ነገር የለም።በመፅሀፍ ቅዱስ ጥናታችን ሞት የሚደመሰሰው እንዴት ነው? የሚለውን ማስተዋሉ ብዙ ነገሮችን አጥርተን እንድናይ ይረዳናልና ይህን እንመልከት። ሰዎች በመፅሀፍ ቅዱሳቸው እንደ ተፃፈው ማንበብ አለባቸው። መፅሀፍ የሀጥያት ደሞዝ የዘላለም ሞትና ስቃይ ነው አይልም። “የሀጥያት ደሞዝ ግን ሞት ነው።ሮሜ6/23” ይላል። እንደ ብዙዎች ቲዮሎጂ የሀጥያት ደሞዝ የዘላለም ሞትና ስቃይ ከሆነ እየሱስ ክርስቶስ የሀጥያትን እዳ ለመክፈል መስዋእት ኣልሆነም ማለታቸው ነዋ? {እንደነሱ አባባል}። እርሱ ለዘላለም በሲኦል አልተሰቃየምና ማለትም እ/ር የሀጥያት ደሞዝ የዘላለም ስቃይና ሞት መሆን አለበት ካለ ማለት ነው። በዚህ አይነት እየሱስ ምንም አልከፈለም ማለት ነዋ? የዘላለም ስቃይ ከሆነ የሀጥያት ደሞዝ እየሱስ ስለ ሀጥያተኞች በሞተ ጊዜ ለዘላለም መሰቃየት ነበረበት ማለትነዋ። እዳው ሊከፈል የሚችለው በዛ መንገድ ብቻ ነውና። ጌታ እየሱስ ግን በምድር ልብ ውስጥ የቆየው ለሰዎስት ቀን ብቻ ነው። በእርግጥም የሀጥያት ደሞዝ የዘላለም ሞት አይደለም!“የሀጥያት ደሞዝ ሞት ነው! ሞትም ዘላለማዊ አይደለም ይሻራል። የሀጥያት ደሞዝም የዘላለም ስቃይ አይደለም። ነው ቢሉም ስቃይም ቢሆን ከአሁኑ የስጋዊ አይምሮ የአለም ስርአት ጋር በክርስቶስ አይምሮ አዲስ ስርአት ሲተካ የቀድመው ስርአት ሁሉ አብረው ይሻራሉና። “ሞትም ከእንግዲህ አይሆንም ሀዘንም ቢሆን ወይም ጩሀት ወይም ስቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም የቀደመው ስርአት አልፈዋልና ራእ21/4። ጌታ እየሱስ የሀጥያትን ስርየት ለማስገኘት ለአለም ሁሉ ሞተዋልን? ተቀብረዋልን? በሰዎስተኛው ቀንም ከሙታን ተነስተዋልን? መልሱ አዎን የአለሙ ሁሉ አዳኝ እንጂ የጥቂቶች ብቻ አይደለም። መዳን ያስፈለገው በጅምላ አለሙ ሁሉ ነውና።“እርሱ የሀጥያታችን ማስተስረያ ነው። ለሀጥያታችን ብቻ አይደለም ነገር ግን ሉኡለሙ ሁተ ሀጥያት እንጂ” 1ኛየሀ2/2 “እርሱም በእውነት ክርስቶስ የአለም መድህኒት እንደሆነ እናውቃለን” ዮሀ4/42 “ እኔም ሱሉአለም ህይወት የምሰጠው እንጀራ ስጋየ ነው።” ዮሀ6/51 “እ/ር ግን በክርስቶስ ሆኖ አለሙን ከራሱ ጋር እያስታረቀ ነበርና በደላቸውንም አይቆጥርባቸውም ነበር።በእኛም የማስታረቅን ቃል አኖረ” 2ኛቆሮ5/19። አዳምና በአዳም ሁሉ ደሞዛቸውን ተቀብለዋል። እ/ር ሞትን ትሞታለህ” ባለው ጊዜ ይህ የመጀመርያው ፍርድ በአንድ ሰው ላይ ብቻ የደረሰበት ሳይሆን ያ ቅፅበት የሰው ዘሮች ሁሉ ላይ ሞት የወደቀበት ነበር።በሮሜ5/18 “በአንዱ በደል ምክንያት ፍርድ ለኩነኔ ወደ ሰው ሁሉ መጥተዋል። ”ይላል። የሁሉ ትርጉም ሁሉ፤ ፍሬ ሃሳቡ በትኩረት ማወቅ ያለብን ከውድቀቱ ጋር መነሳቱም እኩል መሆኑን ነው። እንዲሁም በአንዱ ፅድቅ ምክንያት ስጦታው ህይወትን ለማፅደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ። አስተዋላችሁን የመጨረሻው {እየሱስ ክርስቶስ) በፅድቁ ሁሉን ማዳን አይችልም ብሎ መወሰን በመጀመርያው {በአዳም] ውድቀት ምክንያት ወደ ሰው ሁሉ ኩነኔ አልመጣም ብሎ መሸምጠጥ እንደ ማለት ነው ። ደህንነት ከውድቀት ጋር እኩል ሀይል አለውና። የመጀመርያው አዳም ሁሉን ይዞ ለመውደቅ ሀይል እንደ ነበረው ሁሉ ሁለተኛው አዳም ክርስቶስም ሁሉን ወደ ራሱ ለመሳብ ሀይሉ አለው። የፈለገ ቢሆን የአዳም ሁሉን የመጣል ሀይል ከእየሱስ ሁሉን ከማዳን ሀይል አይበልጠውም። ነገር ግን “ጠላቶችህ ባንተ ላይ ዋሹብህ” ተብሎ እንደተፃፈ ነው። “ዮሀ12/32 እኔም ከምድር ከፍ ያልኩ እንደ ሆነ ሁሉን ወደኔ እስባለሁ[ግሪክ እጎትታለሁ to drag በሃይል በጡንቻ ኢጽ muscular] ” ለመሆኑ ቃሉ ቢያንስ ያመኑልኝን ብቻ የተወሰኑትን ወደኔ እስባለሁ ይላልን? አይልም! ሁሉን ወደኔ እስባለሁ በሀይል እጎትታለሁ፤ የመለኮት ሃይል ምን ያህል ነው? መልሱ የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ።የማቴዎስ ወንጌል 22፡29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ። ሀሌሉያ! በአንዱ ምክንያት ሁሉ ወደቁ በአንዱ ምክንያት ደግሞ ሁሉ ዳኑ ። ሁሉ በአዳም እንደሞቱ ሁሉ በክርስቶስ ህያዋን ይሆናሉ። ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል። 1ኛቆሮ.15/22” ከላይ እንደተፃፈው አሁን ተራቸው ደርሶ ያልዳኑት እያንዳንዱ በተራቸው መዳናቸው አይቀርም። ማወቅ ያለብን “የሁሉ ነገር መታደስ ዘመን አለ።ሀዋ3/21” “ያም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በእየሱስ ስም በሚበረከኩ ጊዜ ምላስም ሁሉ ለእ/ር አብ ክብር እየሱስ ጌታ እንደሆነ የሚመሰክርበት ጊዜ ነው። ፊል2/10” ታድያ እኮ ሁሉን ነገር እ/ር በሚያድስበት ዘመን “እ/ር ሁሉን በሁሉ ይሆናል ተብሎ እንደተፃፈ አሁን የእ/ርን የዘላለም አጀንዳ እና አሰራሩን ላልተረዳ ሰው በሰማይ በምድር ከምድር በታች ያሉት ሁሉ በዝያን ጊዜ እየሱስ ጌታ ነው! ብለው የሚመሰክሩት ተገደው ይመስለዋል እንጂ በእ/ር መንፈስ ሆነው አይመስለውም። ምክንያቱም የሚምበረከኩት ስቃይ ቅጣት በዝቶባቸው ተሸንፈው በፍርሀት እየተማፀኑ ይመስለዋል እንጂ ከአባት ከአብ ፍጥረቱን ከሚያርመው ፍርዱና ከምህረቱ ባለጥግነት የተነሳ ክብር ለመስጠት አይመስለውም። በደልን ንቆ የሚተው ይከበራልና። “መዝ130/4 ነገር ግን በአንተ እ/ር ዘንድ ይቅርታ አለ ስለዚህም ልትፈራ {ልትከበር)ይገባሀል።አዲሱ መደበኛ ትርጉም። “ther is forgivness with thee{GOD},in order that you may be respected”.ሰው ጌታን ለመቀበል የሚያበቃው ነፃ ፈቃድ አለው እንዴ ? ምክንያቱም ነፃ ፈቃድ ካለው አንድ ሰው የመቀበልም ያለመቀበልም ነፃነት አለው ። ነፃ ፈቃድስ ካለው ቀድሞኑ ምን አዳኝ ያስፈልገዋል? የትኛው ነፃ ፈቃድ ነው? በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ የተወረሰው ነው ነፃ ፈቃድ ? ያንን ሰዋዊ አውሪያዊ ተፈጥሮ [Man’s beastlt nature] ሃይል እየሰጠ[ energize] እያረገ የሚነዳውን ፈቃድ ነው? ነፃ ፈቃድ የሚባልልኝ? ለመንፈሳዊው ነገር ሁሉ በአዳም ሞተዋል ካለ ሙታን በቃ ሙታን ናቸው ። መጽሐፍ ቅዱሳዊም ሆነ ሳይንሳዊ ማስረጃ [Biblical or scientific evidence] ካለ መልካም። እንካንስ ነፃ ፈቃድ ሙታን ፈቃድም ካላቸው ማስረጃ የሚያመጣ ካለ እንየው ሰዎች የእኛ ፁሁፍ ሳይሆን የሚያሰናክላቸው እውነት የሆነው የእ/ር ቃል ነው።እንግዲህ ምሕረት በተረቱ በነፃ ፈቃድ እሱም ካለው ነው ለፈቀደ willeth ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው “ወደ ሮሜ ሰዎች 9/16 እንግዲህ ምሕረት ለወደደ [ለፈቀደ willeth ]ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ።”Rom 9/16 So then it is not of him that willeth, nor of him that runneth, but of God that sheweth mercy.‘“ከጥንት ጀምሮ እኔው ነኝ፤ ከእጄም ማውጣት የሚችል የለም፤ እኔ የምሠራውን ማን ማገድ ይችላል?” ‘ኢሳይያስ 43:13‘ እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰው ሕይወት በራሱ እጅ እንዳልሆነች፣ አካሄዱንም በራሱ አቃንቶ ሊመራ እንደማይችል ዐውቃለሁ። ‘ ኤርምያስ 10:23ወደ ሮሜ ሰዎች 11/32 እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና።[ማነው የዘጋው ሃጥያተኛው ወይስ እራሱ እግዚአብሔር በእርግጥም እግዚአብሔር። እግዚአብሔር በአለማመን የዘጋውን ማን ሊከፍተው ይችላል? እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና። [ሰው ሳይሆን ] እራሱ ሉኡል እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ አቅዶ ሁሉን በአለመታዘዝ ከዘጋው የዘጋውን ከመክፈት ማን ያስቆመዋል? እግዚአብሔር ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሊሰጣቸው ይችላልና።ወደ ሮሜ ሰዎች 8:20 ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም፤[እውነትን ሰማችሁ? በነፃ ፈቃዱ አይደለም ለከንቱነት የተገዛው። ማነው በአላማ ለከንቱነት ያስገዛው? እራሱ እግዚአብሔር]አንተ እንዳልከው “የመጀመሪያው ሀጥያት original sin ከአዳም የተወረሰው ሁለተኛው አይነት ሀጥያት ህግን በመጣስ የሚመጣ የግብር ሀጥያት ነው ያልከው ለማስተማር ለexpository teaching ይጠቅም ይሆናል እንጂ ምንጫቸው አንድ ነው። የመጀመርያው አዳም ለጽድቅና ለእ/ር ሞተ ለሃጥያት ግን ህያው ሆነ የሞተው ለህይወት ግዛት እንጂ ለሃጥያት ግዛት እማ ህያው ሆነዋል አእምሮውም ህይወት የነበረው ሞት ሆነ። የስጋ አይምሮ ሞት ነው፤ የመንፈስ አእምሮ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡6 የመጨረሻው፡አዳም ደግም ለሃጥያት ሞተ ‘በሞተ ጊዜ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኀጢአት ሞቶአል፤ ነገር ግን በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖራል። ‘ሮሜ 6:10 በዚህም ጽድቅን ሁሉ ፈፀመ። የመጀመርያው ሰው ሰውን ሁሉ ሐጢያተኛ አደረገ የሁለተኛው ሰው ሰውን ሁሉ አፀደቀ በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖሩ ዘንድ። “የመጀመርያው ሞት፤ ሁለተኛው ሞት እና የስጋ ሞት” ልዩነቶችን በአግባቡ ለመረዳት የሚቀጥለውን ሙሉ ሃሳብ አስተውለህ አንብብ። ተባክ።‘ሞት በአንድ ሰው በኩል እንደ መጣ፣ የሙታንም ትንሣኤ በአንድ ሰው በኩል ሆኖአልና። ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤ ‘1 ቆሮንቶስ 15:21-22እንዲሁ ደግሞ፦ ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15/45በዚህ ጉዳይ ላይ እ/ር የሚያውቀው ሁለት የሰዎችን ዘር አዳሞችን ብቻ ነው። ሁለቱም የዘር መጀመሪያ ና መጨረሻ ናቸው። የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው፤ ሁለተኛው ሰው ከሰማይ የሆነ ጌታ ነው።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15/47 The first man is of the earth, earthy: the second man is the Lord from heaven. የመጀመሪያው የሰው ልጆችን ወደ ሞት ይዞ ወረደ ሁለተኛው ወደ ህይወት ይዞ አወጣ። አዳም ሁሉን ወደ ሃጥያት ይዞ ለመውደቅ አቅም እንደ ነበረው ሁሉ ክርስቶስ ይበልጡኑ ሁሉን ወደ ጽድቅ ህይወት ይዞ ሊነሳ የበለጠ ሃይል አለው። ‘እኔ ግን ከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሰውን ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ[እጎትታለሁ፤- በሃይልና በጡንቻ drag, forcefully it is muscular ።” ዮሐንስ12:32 ኅይል የእ/ር ነው!ስለዚህ ሁለቱ ሞቶች አይመሳሰሉም ሁለተኛው ሞት የመጀመሪያውን ሞት ስራ ሁሉ ይቀለብሰዋል። በተመሳሳይ የመጨረሻው አዳም የመጀመርያውን አዳም ስራ ይቀለብሰዋል። በብዙ መልኩ ‘ቀጥሎም፣ “እነሆኝ፤ ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ” አለ፤ ሁለተኛውን ለመመሥረት የመጀመሪያውን ሻረ። ‘ዕብራውያን 10:9የመጀመርያው አዳም ለጽድቅና ለእ/ር ሞተ ለሃጥያት ግን ህያው ሆነ የመጨረሻው፡አዳም ደግም ለሃጥያት ሞተ ‘በሞተ ጊዜ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኀጢአት ሞቶአል፤ ነገር ግን በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖራል። ‘ሮሜ 6:10 በዚህም ጽድቅን ሁሉ ፈፀመ። የመጀመርያው ሰው ሰውን ሁሉ ሐጢያተኛ አደረገ የሁለተኛው ሰው ሰውን ሁሉ አፀደቀ በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖሩ ዘንድ።ሁለተኛው ሞት ከሚበሰብሰው ወደ ማይበሰብሰው ሽግግር ነው። ከስጋዊ አእምሮ ወደ መንፈሳዊ አእምሮ ሽግግር ነው። ለውጡ ለአንዱ አለም ሞቶ ለሌላኛው ከፍ ላለው መንፈሳዊ ግዛት ህያው መሆን ነው። ለእ/ር ከሞተው የአዳም ንቃተ ህሊና ለእ/ር ህያው ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ ንቃተ ህሊና መነሳት መነጠቅ ነው። ጌታ እየሱስ በስጋ በምድር እያለ የሰው ልጅ የሚኖረው በሰማይ[መመንፈስ ግዛት] ነው ይላቸው ነበር። የክርስቶስ ንቃተ ህሊና የሚያድረው በሰማይ[በመንፈስ ግዛት] ነው። ሃሌሉያ! የዮሐንስ ወንጌል 3:13 ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው። ልጅነት እንዲህ ነው ሁለት እግሩ በምድር ቆሞ የሰው ልጅ በመንፈስ አሁን ተነጥቆ የሚኖረው በሰማይ[ the One continuously being (constantly existing) within the heaven] ነው ብሎ እርፍ! “And no one has ascended (stepped up) into the heaven, except the One descending (stepping down) from out of the midst of the heaven: the Son of Mankind (the Son of the human; Humanity’s Son; the Son of man) – the One continuously being (constantly existing) within the heaven . John 3:13የኃጢአት “ደሞዝ” ምንድ ነው? ስለ ኃጢአት ስናስብ “ስጦታ” ብሎ ነገር የለምውም ለኃጢአት ያለው “ደሞዝ” ሲሆን ያም “ሞት” ብቻ ነው። በአንዱ አዳም ሁሉ ጋር ደረሰ። ስለዚህ እንደቃሉ የኃጢአት ደሞዝ ምንድን ነው? «ዘላለማዊ ስቃይ በሲኦል?» ወይስ “ሞት?” እነሆ እንደምናነበው “የኃጢአት ዋጋ ወይም ደሞዝ ሞት ነው” በሲኦል ውስጥ ዘላለማዊ የስቃይ ህይወት አይደለም። አንድ ሰው “ዘለአለማዊ ህይወት” የሚያገኘው ከየት ነው? “ከእግዚአብሔር ስጦታ ከሆነው ከጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ” ነው.።ማወቅ ያለብን እ/ር የሰው ልጆችን ማዳን ወይም መዋጀት ያስፈለገው ከሲኦል አድኖ ወደ መንግስተ ሰማያት ለማሻገር አይደለም። በልምድ የሚነገር ካልሆነ በስተቀር የእ/ር ቃል በቀጥታ እደዛ የሚል በተወዳጁ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። የእ/ር ፍርዱና እሳቱ ከራሳቸው ሃጢያትና በውስጣቸው ከሚሰራው የአመጻ ሚስጥር በማንጻት አላቆ ወደ እ/ር መለኮታዊ ተፈጥሮና ባህሪ ለማምጣት ነው የሚገለጠው። “የማቴዎስ ወንጌል 1፡21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን #ከኃጢአታቸው #ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” አስተዋላችሁ ህዝቡ መዳን ያስፈለጋቸው ከአዳማዊ ማንነታቸው ከገዛ #ሃጢያታቸው እንጂ ከሲኦል አይደለም። ማዳኑ ከአዳም ዘር ወደ ክርስቶስ ዘር ነው። ብዙዎች ክርስቶስ እንዲመክን ቢሹም ክርስቶስ ግ ን ዘሩን እያየ ነው ዘሩን ወደፊትም ያያል።“የሐዋርያት ሥራ 3፡26 ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን #ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።” Acts 3፡26 Unto you first God, having raised up his Son Jesus, sent him to bless you, in turning away every one of you from his iniquities. ደግሞም ወደ ቲቶ 2፡14 መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።“ የእንግሊዝኛው ግልጽ መልእክቱን ስለሚያሳይ እንመልከተው “that he might redeem us from all iniquity,and purify #unto #himself” ከቃሉ እንደምናስተውለው የተዋጀነው ከአንድ ማንነት ወደ ሌላ ማንነት ነው። ይህም ከአመጻ ሁሉ from all iniquity, አጥርቶ ወይም አንጽቶ ወደ ራሱ purify unto himself ነው እንጂ። የተዋጀነው ከቦታ ወደ ቦታ የጂኦግራፊ ወይም የካርታ ለውጥ ከሲኦል ወደሆነ ሩቅ ጠፈር ላይ የሚገኝ ገነት የተባለ ቦታ ወይም ፕላኔት ሰፈር ለመቀየር አይደለም። የተዋጀነው አመጻ ከተሞላ ማንነት ወደ ራሱ መልክና አምሳል ለማምጣት ነው። የመንጻሩም ሂደት በእሳቱ በማሳለፍ አመጻውን ሁሉ በመብላት ወደ መልኩ ማምጣት ነው።“በሃጥያታችሁና በበደላችሁ #ሙታን#ነበራችሁ” የሚለው ቃል እውነት ነው? እውነት ከሆነ ሙታን መስማት ይችላሉን? አይችሉም! መንፈሳዊ ሙታን እንካንስ እምነት ሊኖራቸው በቅድሚያ ከሙታን በትንሳኤው ሃይል መነሳት አለባቸው። ከሙታን የሚነሱት በእ/ር ሃይል ብቻ ነው! ከዛም ቅደም ተከተሉ ይቀጥላል። እሱ ብቻውን …ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ ነውና ከዛም የሚሰሙም ጆሮችን የሚሰጥ እ/ር ነው። እንካን እመነት ንሰሃ እንካን ከእ/ር ካልተሰጠህ የለህም። የሐዋርያት ሥራ 11፡18 ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና፦ እንኪያስ እግዚአብሔር #ለአሕዛብ ደግሞ #ለሕይወት የሚሆን #ንስሐን#ሰጣቸው እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ።አንተ ስታስበው ከክርስቶስ ውጭ እያለው ፍጥረታዊ ሰው በበደሉና በሀጥያቱ ከሙታን ከሆነ ከሙታን ዘንድ በፈቃድ አለን? እውቀትስ ስፍሯ አላትን? “ሙታን ግን ምንም አያውቁም” ቃሉ የሚያስተምረን ያንን እውነት ነው።ታዲያ እንዴት ይድናሉ ለምሳሌ በተፈጥራዊው። እንካን ብናይ አልአዛር 4 ቀን በመቃብር የሞተ ሳለ ነፃ ፈቃድ የነበረውን? በፍፁም የውዱ ቃል የትንሳኤው ህይወትን ታጭቆ ቃሉ ሀይል ለብሶ ወደሱ ሲወረወር መጣ መጀመርያ ሙታን የሚነሱት በፈቃዳቸው ሳይሆን በእ/ር በሀይል ብቻ ነውና የመጣው ቃል ህይወትን ሰጠው ልቡና ሳምባውም መስራት ጀመረ በትንሳኤው ና በህይወት በሀይል አቆመው ግንዘቱንም ፍቱለት እና ይሂድ አለው።ታድያ አልአዛር በነፃ በፈቃዱ ህይወትን ለመቀበልም ሆነ ጌታን አልቀበልም ወግድልኝ ለማለት እዚህ ላይ እውቀት ነበረው ድርሻና ሀይል ውይም ፈቃድ የነበረውን? ለመንፈሳዊ ሙታንም እንዲሁ ነው። “ሀይል የእ/ር ነው” ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለ መታዘዝ ከዘጋ ሸክላ ሰሪው ከሸክላው የላቀ ታላቅ መሆኑ በሁሉ ዘንድ ማስተዋል ይሁን።ሸክላው ሸክላ ሰሪውን ለምን እንዲህ አድርገህ ሰራህኝ ብሎ ቢጠይቀው የስቃል እ/ርም በሰማይ ይስቃል እኔም በደስታ በተሰበሰቡት እልፍ አእላፋት ደስተኛ መልአክት ጋር ሆኜ እንደ መንፈሳዊ አባቴ እስቃለሁ። ሀይል የእ/ር ነውና በሰማይና በምድር የተወደደውን ያደርጋል የሚከለክለውም የለምና ።እ/ር ይህንን ሞት ብሎ አይጠራውምና። እኛ ይህንን ሞት ብለን እንጠራዋለን። ይህ ግን ሞት አይደለም። አስተውሉትማ ወገኖቼ ሙውታን ሳላችሁ ህይወትን ሰጣችሁ! ሙውት ሳለሁ በክርስቶስ ህይወትን ሰጥቶኛል። ታዲያ ያ ማለት በሬሳ ሳጥን ውስጥ ታሸጌ ፅልመት በተሞላበት መቃብር ውስጥ ተቀብሬ ነበረ ማለት ነውን? ሞት ማለት አካሌ በሬሳ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ማለት አይደለም። የተቀበልኩትም ህይወት የማይበሰብስ የስጋ አካል አይደለም። አትመለከቱምን? ሰዎች ሞት ብለው የሚጠሩት ሞት አይደለም። ሰዎችም ህይወት ብለው የሚጠሩት ህይወት አይደለም። መንፈስ ቅዱስ ሲገልጥልን ብቻ የነገሮችን እውነተኛ ተፈጥሮ የጠለቀ ሚስጥራቸውን የምንገነዘበው። አንድ ሰው ከሰማይመጣ በእ/ር ፀጋም ለሰው ሁሉ ሞትን ቀመሰ ። ”ነገሮችን ከተፈጥራዊው ሰው አንፃር ብቻ ካየናቸው እውነት እደተሰወረ ይቀመጥብናል በመንፈስ ግን እ/ር ከሚያየው አንፃር ካየናቸው እውነት አርነት ያወጣናል። ሌላ ቃል ደግሞ እንይ። “እየሱስም፥ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታኖችን ተውዋቸው። ሉቃ9/8” ማለቱ በቃሬዛው ውስጥ ያለውንም የተሸከመውንም አንድ ሙታን አላደረጋቸውምን? በርግጥም ከሰው አለም ከውሸትና ከሞት ግዛት ተኩኖሲታዩ ሉይነት አላቸው። ሁለቱም ግን ከእ/ር አለም ከእውነትና ከህይወት ግዛት ተኩኖ ሲታዩ ሙታን ናቸው። የሰው ልጅም እንዲሁ በሀጥያት ምክንያት ከእ/ር ህልውና ከተባረረ ጀምሮ ያለው ኑሮ ሁሉ እንዲሁ ነው። የሚለያዩት በኮፈኑ ውስጥ ያለው የሞት ወይም የመበስበስ ኑሮ የመጨረሻው የእድገት ደረጃ ላይ በመድረሱ ግብአተ መሬቱ ሊፈፀም መድረሱ ነው። በአጭሩ ሞት ሰው ከእ/ር ጋር በመንፈስ የነበረው ህብረት የተለየበት ወይም ከህይወት ግዛት ከተባረረበት ቅፅበት ጀምሮ ያለው ጠቅላላ ሁኔታውና ማንነት ነው ። ለምሳሌ አንድ የፅጌሬዳ እንቡጥ አበባ ከግንዱ ብትቆርጡት ለአይን ሲታይ ያማረና ህያው ነው። ነገር ግን እውነታው የአበባው ዝንጣፊ ህይወትን ከሚሰጠው ከምንጩ ማለትም ከግንዱ ተቆርጦ ተለይተዋል። ከዚህ ቡሀላ ወደ መጠውለግ ፤ወደ መበስበስ ወይም ወደ ሞሞት ቁልቁል እያደገ ነው። እ/ር ያብራላችሁና በሰማይምም በምድርም እ/ር ህይወት የሚለው አንድ ብቻ ነው። እርሱም በክርስቶስ እየሱስ የሚገኘውን ህይወት ነው። ጌታችንና አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ “እኔ ህይወት ነኝ ማለቱ ሌላውን ሁሉ ሞት አያደርገውምን? እኔ እውነት ነኝ ማለቱ ደግሞ ሌላውን ውሸት ያደርገዋል ። እኔ መንገድ ነኝ ማለቱ ደግም ሌላውን ገደል ያደርገዋል። ክብር ሁሉ ለቅዱስ ስሙ ይሁን። * እግዚአብሔር የሰዎች ሁሉ አዳኝ ነው። 1 ጢሞቴዎስ 4:10 * ጌታ ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት ያስወገደ የእግዚአብሔር በግ ነው.(ዮሐንስ 1:29) እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው። አሜን! ወንድም ቢንያም አለማየሁ። RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND.

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal