
የባቢሎን ሚስጢር አቧራውን ማራገፍ ፡ በወንድም ቢኒያም አለማየሁ። 4/22/020 እ.አ.አ. ጠያቂ ወንድም Demis Nida የባቢሎን ሚስጢር ተፈጥራዊውን አስታኮ እስከ መንፈሳዊ ብዙ ስር ሰደዋል። ሚስጢረ ሃሳቡ ጥልቅ ቢሆንም ጌታ በአሁኑ ጊዚያት ፈቃዱን መግለጡን በቀጠለበት በዚያ ወደ እውነት እንዲራመዱ ለተጠሩ በከፊል ሊጠቅሙ የሚችሉ ጥቂቶች ሊታዩ የሚገባቸው አንካር ሃሳቦችን ማስታወሱ እይታችንን ሊያሰፉና መንደርደርያ ሊሆኑ ስለሚችሉ ለልጆች በጉዳዩ ለማኮብኮብ ያህል የሚረዱ ፍሬ ሃሳቦችን በጥቂቱ ማንሳቱ ጠቃሚ ነው ብየ አስባለሁ። ዞሮ ውሎ ይህ መንፈሳዊ አመልካች ነውና ከባቢሎን ሚስጢር ጋር የተያያዙ የመሰረቱ መነሻ ሃሳቦችን ሰፊ ሃሳብ እንደ መሆኑ ተፈጥራዊው የነገሩ ጽንሰ ሃሳብ ጅማሮም አብሮ ማየቱ መንፈሳዊ ፍቺውን ለማየት ያግዘናል። መልካም ነገር እንዲቀርልን በወንድም ደምስ ከተጠየቀው ጋር የተያያዘ ከሆነው ቃል ብንጀምር መልካም ነው። የጋለሞታይቱን ማንነት ምልክት “በግምባሯም ላይ እንዲህ የሚል የምስጢር ስም ተጽፎ ነበር፤ ታላቂቱ ባቢሎን፣ የአመንዝሮችና የምድር ርኵሰቶች እናት። ሴቲቱንም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ተደነቅሁ። ከዮሐንስ ራእይ 17:5” Rev 17፡5 And upon her forehead, a name having been written: “A MYSTERY (A SECRET; a matter to the knowledge of which initiation is necessary) ‑‑ BABYLON the GREAT: The Mother of the Prostitutes and of The Abominations (Detestable Things) of The Land (earth). And I saw the woman, being continuously drunk from out of the blood of the set‑apart (holy) ones and from out of the blood of the witnesses of Jesus, and seeing her I wondered (marveled) a great wonder (or: I wondered, [It is] a great marvel!).ከዚያም ከሰማይ ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ከዚያም ከሰማይ ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ ሕዝቤ ሆይ፤ በኀጢአቷ እንዳትተባበሩ፣ ከመቅሠፍቷም እንዳትካፈሉ፣ #ከእርሷ#ውጡ፤ ራእይ 18፡4 And I heard another voice from heaven, saying, #Come#out of her, my people፣ that ye be not partakers of her sins, and that ye receive not of her plagues” በሕይወታችን ውስጥ የዘዴዋ የሲስተምዋ ምርኮኞች ሆነን የነበርንባት ከተማ በመንፈሳዊ መጠርያዋ እንደ ባህሪዋ በሚመጥን በማአርግዋ ስም ‘ባቢሎን’ ተብላ ትጠራለች! የጌታን ጥሪውን ሰምተን በጸጋው አቅም አግኝተን ለአባት ምላሽ ሰጥተን ከባቢሎን ከዘየዋ ምርኮ በሃይሉ ከእሷ መውጣት ሆኖልናል። ከጸረ ጌታ ከከተማ ሲወጣ ደግሞ የተለመደው ትእዛዝ አለ የእግራችሁን ትቢያ አራግፋችሁ ውጡ። ስንቶቻችን አፈሩዋን አራግፈናል? የነበረንበትን የተጸኖ አቧራ እና ውጤት ከላያችን አንስተናልን? አቧራ ስለ የሥጋ ዘየና አሰራር መዋቅር ወይም ስለ ሥጋዊ አስተሳሰብ እና አመክንዮ የሚናገር ሲሆን ሁላችንም በረቀቀ ኩናቴዋ በአስተሳሰባችን ላይ በቀላሉ ከቃሉ ጋር ተበርዞ በሁላችን ላይ ባቢሎን በእጇ በነበራት የተቀላቀለ ተፈጥራዊም እና መንፈሳዊ ስልጣን ተጠቅማ በጌታ አይን የሚያስጸይፍ የመንፈሳዊ የዝሙቷ ርኵሰት የሞላበትን የወርቅ ጽዋ ያለውን ስላጠጣችን ለአብዛኛው ሰው ከስካሩ ነቅቶ እውነትን የለመለየት አቅሙ እምብዛም አስቸጋሪ በሆኑ መንገዶችዋን የመለየት መንፈስ ጌታ ሲያስችለን ብቻ የሚቻል መሆኑ ግልጽ ነው። አባታችን እግዚአብሔር ወደ እውነት በመንፈሱ እንደመራን መጠን በጉ ወደሄደበት ልንሄድ የግድ ነው።በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና እንደ በኩር ወንድማችን እንደምሳሊያችን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስን ይሰማ እንደነበር ልንሰማ ይገባል ውስጣችንም ሲመስክርልንም ፈቃዱ ወለል ብሎ እንዲታይ አደረጋል፡፡ በዚህም ሁሉም የአቧራን ቅሪቶች ቅንጣቶች አደራረግዋን ናፍቆትዋ መአዛዋን ሳይቀር ከእግራችን ከአካሄዳችን ማራቅ አለብን። ዕርፍ ጨብጦ ወደ ኋላ የሚመለከት ሰው ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለምና ወደ ባቢሎን ስራት የመመለስ ማንኛውም ሀሳብ ወዚያች ወደተደራጀው ሰው ሰራሽ የሃይማኖት ከተማና ስርዓትዋ እንደገና አስቀያሚ ጭንቅላትዋን ተጠቅማ እንድትጨፍርብን መመለስ በጭራሽ የማይታሰብ ነው። ለተፈጥራዊ ጸረ ክርስቶስ ከተማ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ለምትመስለዋ ከተማም የሚራገፈው ያው ነው “ከተማውን ለቃችሁ ስትሄዱ፣ ምስክር እንዲሆንባቸው የእግራችሁን ትቢያ አራግፋችሁ ውጡ። የሉቃስ ወንጌል 9፡5”ይህን ረቂቅ የባቢሎን ውስብስብ ሰርአት እውነተኛ እና የሐሰት ብርዝ ያዝውለ በመሆኑ በሁሉቱ መካከል ልዩነቱን እንለይ ዘንድ መለኮታዊ መገለጥ የመንፈስ ቅዱስ ብርሃን እንዲያበራልን የግድ ነው።በዘየዋ እውነት ከስህተት ጋር ተጣምሮ ስላለ ለባቢሎን ምርኮኞችዋ ሁሉም ግራ ነገር ሆኗል ፣ ከለበሰችው የስያሜዋ ካባ የተነሳ የቤተ-ክርስቲያን ክብር ይዛ የሃይማኖት ዘየዋ ምን ያህል ፀረ-ክርስቶስ እንደሆነ እንኳን ለብዙዎች መለየት አይችሉም ወይም አወዛጋቢ ሆናባቸዋለች። በናምሩድ ተጸንሶ የተጀመረው የባቢሎን እራስን ከፍ የማድረግ መንግሥት ምን ያህል ሰፊ ርቀት ተጉዞ መንፈሳዊ እስኪመስል ከፍ ማለቱ በግልፅ ማየት የሚችሉት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመንፈስ “የተነሱ initiated” ልጆች ብቻ ናቸው ፡፡ይባስ ብሎ በተጨማሪም ባቢሎን ለዘመናት ሆነ በዚህ ዘመን ባቢሎን በሦስት የተለያዩ መንገዶች ስርዋ ተንሰራፍቶ ይታያልና ነገሩ እብዙ የዋሃን ቀላል አልሆነም። የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል ተብሎ እንደተጻፈ ማስተዋል ይገባናል።ባቢሎን ዛሬ ዛሬ የሃይማኖታዊ ፣ የፖለቲካ እና የምጣኔ ሀብት ረቂቅ ትስስር አላት፣ ግን ሁሉም የአለም ጥበቦች በተመሳሳይ የፀረ-ክርስቶስ መንፈሰ ሥር የሚተገበሩ የአንዲት እናት ልጆች ናቸው ፡፡ ሁሉም የአለም ሃይማኖቶች የባቢሎን ሚስጢር ይሰራባቸዋል ለምሳሌ ያህል ኦርቶዶክነትም orthodox ይሁን እስልምና Islam፤ ሂንዱዝም Hinduism፤ አረማዊነት paganism፤ የቻይና ባህላዊ ሃይማኖት Chinese traditional religion፤ ቡዲዝም Buddhism፤ አፍሪካዊ ባህላዊ እና ዳያፊሮኒክ African traditional and Diasporic፤ ካቶሊካዊነት Catholicism፤ ቢሆን ወይም ሴት ልጆዋም ፕሮቴስታንትም Protestant ቢሆኑ የባቢሎን ሃይማኖታዊ ክፍልን ይናገራሉ ፡፡ ብሎም በተለያዩ መንገዶች የተገለጠት የሁሉንም የምድር መንግስታት አገዛዝ ቢሆኑ ክፋዮችዋ ናቸው። እነሱም በእርግጥ ኢኮኖሚያዊውን ግዛት አፈፍ አድርገውታል። ሦስቱም በባቢሎን መንፈስ በጣም የተሳሰሩ ናቸው ገንዘብ ፣ ፖለቲካ ፣ ሃይማኖት ሁሉም በአንድ እጅ ተያይዘው በሰው ላይ ገነው ይሄዳሉ ፡፡ ይህ ለማየ ሩቅ መሄድ አያስፈልገንም ሌላው ቀርቶ በእኛ ዘመን የባቢሎን ነገስታት ትንንሽ የየራሳቸውን መንግስታት በቤተ ክርስቲያን ስም መስርተው ምርኮኞቻቸውን ሲበዘብዙ ይታያል ሊሎችም በባቢሎን ሌላ ገጽታ በሚገኙ መስቀለኛ መንገዶች ላይ አነስተኛ ማኅበረሰብ ጨምሮ ቤተክርስቲያን ተጸኖ ውስጥም ውጭም በግልጽ ቅርጫፍዋ ይታያል ፡፡እሷ በራሷ መልክ እና አምልሳ ልጆችን የምትወልድ እንዲሁም “የጋለሞታዎች እናት ” ተብላም የተጠራች መንፈሳዊ ጋለሞታ ናት ። እሷም “የምድር ርኩሰት ” እናት ነች ። ርኩሰት abomination በዕብራይስጣዊ የሚያሳየው የጣኦትን an idol ነው ፣ ስለዚህ ይህች መንፈሳዊ ጋለሞታ በምድር ላይ የጣኦት አምልኮዎች ሁሉ እናት ንደሆነች ይመስላታል። ስለዚህ ጋለሞታይቷ የምታፈራቸው ልጆችዋም በሁሉም በምልክት የገለፃቸው መንገዶቻቸው ሁሉ ወደ ጣኦት አምልኮ የሚታለሉ seductive ይመሰላሉ።ወቅቱ በአባት መንፈስ የክርስቶስ አካል የባቢሎን (ግራ መጋባት) እና የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ትክክለኛ ግንዛቤ ሊኖራት የሚገባበት ጊዜ ነው። የአባትም ጥሪን ለመስማት ጊዜው አሁን ነው… ሕዝቤ ሆይ፤ በኀጢአቷ እንዳትተባበሩ፣ ከመቅሠፍቷም እንዳትካፈሉ፣ ከእርሷ ውጡ (ራዕይ 18 4) COME OUT OF HER, MY PEOPLE ( Revelation 18:4 )!!!! ከባቢሎን ቤተ-ክርስቲያን ውዥንብር ከስጋ ድካም ወደ መንፈስ ብርታት ወደ ሰማይ አባታችን የእውነት መገለጥ ዘወር እንበልና እንውጣ!የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ The spirit of antichrist እናት ባቢሎን የህብረተሰባችንን ሁሉንም አካባቢዎች አጥለቅልቋለች። በሃይማኖታችን ፣ በኢኮኖሚያችን እና በፖለቲካችን ውስጥ መንፈሱ እየሰራ ይገኛል ፡፡ መንፈሱ…… ለእኔ ለኔ፣ ለስሜቴ እና ለፖሊቲካዊ አጀንዳዬ ስም ማዘጋጀት እፈልጋለሁ ይላል፡፡ ለታይታ የአምልኮና የሃይማኖታዊ መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ለጥቅማቸው ክደዋል። ልጅ ከሆንክ ከእነዚህ መንገድ ራቅ ነው በዘዴም በግልጽም ለገዛ ጥፋታቸው የእግዚአብሔርን ልጅ እንደ ገና ይሰቅሉታል፤ ያዋርዱታልምና።ይህ የባቢሎን መንፈስ የጀመረበት የዘፍጥረት መጽሐፍ ድረስ ተመልሰን ብንከተለው ምንጩ ሊገኝ ይችላል ፡፡ በዘፍጥረት 11፡9 መሠረት የከለዳውያን ዋና ከተማ የሆነችው “ባቢሎን Babylon” የሚለው ቃል ትርጓሜ ግራ መጋባት confusion ወይም መደናገር ማለት ነው፡፡ confusion ፤ to confound ዘፍጥረት 11 4-9 ስለ ናምሩድ ፣ ስለ መንግሥቱ ይናገራልእና የባቢሎን ግንብ በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ጥቅም ላይ የዋለው “ባቤል Babel” የሚለው ይህ ቃል ማለት ግራ መጋባት (በመደባለቅ፤ ወይም መደናገር ) confusion by mixing ፡፡ “ባቢሎን Babylon” የሚለው ቃል “ባቤል Babel” ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ተመሳሳይ ነው ፡፡ በዘፍጥረት ምዕራፍ 11 ቁጥር 4 እና 9 የተነገሩት ሰዎች ከተማ ወደ ላይ የሚደርሱ ከተማ እና ግንብ ለመገንባት ፈልገው ነበር ፡፡ ለራሳችን ታላቅ ስም እንስራ ሲሉ ጀመሩት ጌታ ግን ግዑዝ ግንብ የመገንባት ዕቅዶቻቸውን አቆመ ፣ የሰው ልጅ ግን የባቢሎን መንፈስ በልቡ ውስጥ ይዞ ወደፊት መመረሽን ቀጥሏል።እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩና እንደ ምሳሌው ፈጥሮ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ ብሎ ከመጀመርያው ቢፈጥረውም ሰው ገዢነቱ ቀርቶ ሰው በሰው ወደ መገዛት ሚስጥር መታየት የጀመረው በጥንት በባቢሎን መስራች ነው። በዘየ ሰዎችን የመግዛትና የመበዝበዝ የባቢሎን ሚስጢር የጀመረው በሃያሉ በናምሮድ ዘመን ነው። ከመፅሀፍ ቅዱስ ውጭ ሁለተኛ ማስረጃ ብናይ እንካን የያሻር መጽሐፍ The Book of Jasher ተብሎ ወደሚጠራው የጥንት ታሪካዊ ምንጭ ከተመለከትን ፣ አንድ ጥሩ መልስ እናገኛለን ፡፡ የያሻር መጽሐፍ መፅሀፍ ቅዱስ የመሰከረለት የእውነት የታመነ መጽሃፍ ነው። “በመጽሐፈ ኢያሱ 10፡13 ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ #በያሻር#መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም።” እና “በ2ኛ ሳሙ. 1፡18 የይሁዳንም ልጆች ያስተምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ፥ ይህ #በያሻር#መጽሐፍ ተጽፎአል።” በእርግጥም የተመሰከረለት መጽሓፍ ነው፡፡ በሮማው ጀነራል ታይተስ በ70 እ.አ.አ. ኢየሩሳሌም ከጠፋች በኋላ ይህ መጽሐፍ ጠፍቶ ነበር ቡላም በ1613 በአንድ በረቢ rabbi’s ጽ/ቤት ውስጥ አንድ የድሮ ግልባጭ እስኪገኝ ድረስ ይህ መጽሐፍ ደብዙ የለም ነበር ፡፡ የያሸር መጽሃፍ 13:14፤ 27: 2 ወዘተ..ላይ መጽሐፉ ናምሩድን በብዙ ቦታ “ዓመፀኛው the rebel” ብሎ ይጠራዋል ባህርዩም ማመጽ የተሞላበት ህይወት ነበር፡፡ አመጸኛ ሰው ሃፍረት የለውምና እግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ይገዛ ዘንድ የሾመውን ሰውን የሙያህል ክቡር ፍጥረት በተቃራኒው ተገዢ አርጎ ሰውን ሰው መግዛት የጀመረው በዚህ የባቢሎንና የሌሎች ታላላቅ ከተማዎች መስራች ሰው ነበር። “የኖኅ ልጅ የካም ልጅ ኩሽ በዚያ ዘመን በዕድሜው አርጅቶ ሚስትን አገባ። ወንድ ልጅም ወለደች ፤ ስሙንም ናምሩድ ብለው ጠሩት ፤ በዚያን ጊዜ የሰው ልጁ በአምላክ እግዚአብሔር ላይ ማመፅ ጀመረ ፤ ሕፃኑም አደገ ፤ አባቱም ወደደው እርሱ በጣም የእርጅናው ልጅ ነበርና እጅግ እጅግ ደስ አለው ፡፡ከያሸር መጽሃፍ” “8ኩሽ የናምሩድ አባት ነበረ፤ ናምሩድም በምድር ላይ ኀያል ሰው እየሆነ ሄደ። 9በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ብርቱ አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ አዳኝ” ይባል ነበር። 10የግዛቱም የመጀመሪያ ከተሞች፦ ባቢሎን፣ ኦሬክ፣ አርካድና ካልኔ ናቸው፤ እነዚህ በሰናዖር ምድር ነበሩ። 11ከዚያም ምድር ወደ አሦር ወጥቶ ነነዌን፣ ረሆቦትን፣ ካለህን 12እንዲሁም በነነዌና በካለህ መካከል ሬስን ቈረቈረ፤ ታላቁንም ከተማ መሠረተ። ዘፍ 10፡8”በአጭሩ ናምሩድ ኃያል ሆነ ፤ ኃያል ፣ ዝነኛ ፣ በሰዎች ጉዳዮች ውስጥ አምባገነን መሪ ሆኖ ተነሳ። እርሱ የመጀመሪያው የሰው መንግሥት ለማደራጀት ተልሞ ያሳካ ሃያል እንደነበር ይነግሯል ፡፡ በአማርኛውም በእንግሊዝኛውም በጌታ ፊት ኃያል አዳኝ እንደነበር ተብሎ ተገልጸዋል ፡፡ የዕብራይስጡ ቃል ግን ተጨማሪ እይታ ይሰጠናል “ፊት” በብዙ የተለያዩ የሃሳብ ገላጭ መተግበሪያዎች ውስጥ ጥቅም ላይ ውላል ፣ ለምሳሌ በጥሬው “ተቃራኒ against” ማለት ነው። ናምሩድ እራሱን ከፍ አድርጎ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን በእግዚአብሔር ፊት እራሱን ተክቶ በተቃውሞ ሰዎችን ለመግዛት እግዚአብሔርን ተቃርኖ በሰዎች ላይ ሰልጥኖ ተንሰራፋ ፡፡ የስሙ የናምሩድ ትርጉሙ እራሱ የአመጻ ባህርዩን ይናገራል ወደ ላይ እንነሳ ወይም ደግሞ እናምፅ ማለት ነው። አንድ የአይሁድ ኢንሳይክሎፒዲያ ጸሐፊ ናምሩድ ማለት “ሕዝቡን ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ እንዲያምፁ ያደረገው” ማለት ነው ብሎ ጽፈውታል። በዛሬው ጊዜና ዘመን ያሉ በርካታ አረማዊ paganistic አምልኮና ልማዶች የተጻፉበት ዘመን ምንጫቸው የናምሩድ ዘመን እንደሆነ የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ።ሁሉም በእግዚአብሔር ላይ በመቃወም የተነሱና ጸረ ANTI እግዚአብሔር ይዘት ያላቸው ናቸው ፡፡ከላይ እንደጀመርነው በምንጩ ስናየው ደግሞ በመጀመርያው የፍጥረት ስርአት ሰዎች ፈጣሪያቸውን እግዚአብሔርን እየመረመሩ ያገኙት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ በመልኩ እና በምሳሌ ፈጠረ፥ እግዚአብሔር በመልኩ እና በምሳሌ መንፈስ ነው ዮሃ 4፡24 ይህ ሰው በዚህ ምድር በስጋ ውስጥ ቆይታውም በተፈጥራዊው አለም ህያው ሆኖ ይመላለስ ዘንድ መንፈስ፤ ነፍስም ሥጋም ያካተተ ሆኖ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖርበት ስፍራ ዳርቻ መደበሎት ተባዛ። ሰዎች ቢባዙም ከአንድ ወገን ነበሩና ለሁሉም አንድ ቋንቋ ነበራቸው። በናምሮድ መሪነት እርስ በርሳቸውም ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው ተባባሉ። እግዚአብሔርም ከአንዱ ከአዳም የፈጠራቸው ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። ለሁሉም ሰዎች አንድ ቋንቋ ሳሉ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው ሲል እግዚአብሔርም በሰው ላይ ድንገተኛ ግራ መጋባት የተገበረበት ቅጽበት በባቢሎን ነበረ። በጌታ ቀመርም በሰው ሁሉ ግራ መጋባትም ሆነ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ ደባለቀው አንዱ በእሳት የተኵሰው ጡብ አቀብልለኝ ሲለው ጭቃ ይሰጠው ጀመረ ተደናግረውም መግባባትና ስራውን መቀጠ አልቻሉም እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ። ስለዚህም ስምዋ “ባቢሎን Babylon”[ ትርጓሜውም፤ ግራ መጋባት confusion ወይም መደናገር ማለት ነው፡፡ confusion ፤ to confound] ተባለ፥ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል። ኦሪት ዘፍጥረት 11፡1-9 በተጨማሪም በመጽሐፈ ኢያሱ 10፡13 እና በ2ኛ ሳሙ. 1፡18 የተመሰከረለት የነገስታት ጥንታዊ የታሪክ መጽሃፍ እንዲህ ያስቀምጠዋል “በያሻር መጽሐፍ 11 ላይ የኩሽ ልጅ ናምሩድ ግን በሰናአር ምድር ገና ነበረ ፤ በእርሱም ላይ ነገሠ በዚያ ተቀመጠ ፤ በሰናአር ምድርም ከተማዎችን ሠራ። የገነባቸው የአራቱ ከተሞች ስም እነዚህ ናቸው ፤ ስማቸውም በህንፃው ግንባታ ላይ ካጋጠሟቸው ክስተቶች በኋላ እንደ የባህርያቸው ሰይሞ ጠራቸው፡፡ የፊተኛውንም ባቢሎን ብሎ ጠራው። ጌታ እንዳይግባቡ የመላው ምድር ቋንቋውን ድንግርግር አድርጎ ደባልቆታልና የሁለተኛውንም ስም ኢራች ብሎ ጠራው ፤ ምክንያቱም ከዚያ የተነሳ እግዚአብሔር በታትኗቸዋልና ፡፡ እኛ የምንመለከተው እይታ የዓለም ተቋዋአማዊ መዋቅሮች ክፍል አመልካችነቱን ብቻ አይደለም በእርግጥ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ መሆኑ ግልታጽ ነው ሆኖም ልታአስቡት የሚገባው አንድ መንፈሳዊ ሰው መንፈሳዊውን ትቶ ተፈጥራዊ ገጽታው ላይ ብቻ እየሮጠ ከተላተመ የተላተመበትን ሲያሽ የመንፈሳዊው እውነታ ዘንድ ይተላለፋል። ማለትም የፊደል እይታ ፀሃፊው literalist እይታው በፍጹም ትክክል ሆኖ የሚሰራው ሰውየው በእይታው የህግ ቃልን ወይም ህጉን ቃልያዊ ውክልና የሚያከብር ሲሆን ችግር የለውም። መንፈሳዊውን ያሳይ ዘንድ በተምሳሌት ፤ በምልክት፤ በምሳሌ የየተጻፈውን ጽሑፍን በጥሬው የሚተረጉም ሰው ግን ከመንፈሳዊ አመልካችነቱ ጋር ይተላለፋል። በዛም እይታ የሙጭኝ ለሚል የአለም ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ ፣ ወይም ሃይማኖታዊ ሁካታ ጋር ይረጋል በጠቅላላው ምንጩን ስናስብ ሊፃፍ የሚችል አንድ ቃል አለ እንዲህ ዓይነቱን ግራ መጋባት የሚመጣው የመልካም እና የክፉው ፍሬ ተቀላቢ ነው መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ እየቀጠፈ ልሚኖር ሞትን ትሞታለህና እንደተባለ ዛሬም ያው ነው ስጋዊ አእምሮ መያዝ ሞት ነውና የሚያዘጋጀው ያንን ብቻ ነው ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡6 ። “Now the mind of the flesh [which is sense and reason without the Holy Spirit] is death [death that comprises all the miseries arising from sin, both here and hereafter]. But the mind of the [Holy] Spirit is life and [soul] peace [both now and forever]. (Rom 8:6 [AMP])”“For the thinking (mind-set; way of thinking; disposition; understanding and inclination; the minding; the opinion; the thought) of the flesh [is] death, yet the thinking (mind-set; disposition; thought and way of thinking) of the spirit (or: the Spirit) [is] Life and Peace, JMT” ስለዚህ ግራ መጋባቱ የበዛው እይታው ዘንድ እውነት ከስህተት ጋር በመበረዙ ነው።በተጨማሪም ባቢሎን በእግዚአብሔር ፊት የሚቃወሙትን ሃይላት ሁሉ አካል የለበሱትንም ያልለበሱትንም ዘየዎች ትወክላለች ፣ ምክንያቱም ባቢሎን በባህርይዋ ፀረ-ክርስቶስ ናት። “ፀረ” ማለት በተቃራኒው ወይም በምትኩ ልሁን ባይ ናት፡፡ የእያንዳንዱ ገጽታ ለእግዚአብሔር ወይም ለአሰራሩ ከሥነ ምግባር ውጭ የሆነ ጥላቻን ያሳያል። በእርግጥም ይህ እግዚአብሔርን የሚቃወም እና ራሱን በተቃራኒው ወይም በምትኩ ከፍ የሚያደርግ” ስርዓታዊ የሆነ ከሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ የሰው ማንነትም የእርሱ አካል ነው። 2ኛ ተሰሎንቄ 2: 4 በእርግጥ አልፎ አልፎም ይሁን ቡዙውን ግዜ ውጫዊ ተቃውሞ ሊኖር ይችላል የውጫዊ ፍሬ ምንጩ ግን ውስጣዊ ነው ። ምንም እንኳን ባቢሎናዊነት በባህርይዩ ፀረ-ክርስቶስ ቢሆንም ማስታወስ ያለብን ባቢሎን እንደቀድሞ አሁንም በእግዚአብሄር ሉዓላዊ እጅ ውስጥ ነች። እውነትን ከማወቅ አንጻር እንጂ ሁሉንም እርሱ እንደሚቆጣጠረው መርሳት የለብንም። ሃይል የአባታችን ነው የሰማይ አባታችን ከሁሉ ይበልጣል!!! “መጻሕፍት አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 15፡4” የባቢሎን ሚስጥር መንፈሳዊውን ነገር እንዴት ተንብዮ እንደሚያሳየን ስንመለከት ባቢሎን በሙስናዋ ሁሉ እንኳን በእግዚአብሔር ዓላማ የጎኑየሽ እቃ ሆና ጥቅም ላይ ውላለች በእግዚአብሔር በራሱ እጅ ውስጥም ሆና ምድርን ሁሉ ያሰከረች የወርቅ ጽዋ ነች ፡፡ “ትንቢተ ኤርምያስ 51፡7 ባቢሎን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ምድርን ሁሉ ያሰከረች የወርቅ ጽዋ ነበረች፥ አሕዛብም ከጠጅዋ ጠጥተዋል ስለዚህ አሕዛብ አብደዋል።” የተመደበላት ዓላማዋን በተፈጸመች ጊዜ ግን እግዚአብሔር ፍጻሜዋን እንደወሰነ ይታያል፡፡ እንዳየነው ለዘመናይቱ ከተማም ለትንቢቱ የተረጋገጠ ትንቢታዊ ቃል ነው ፡፡በዮሐንስ ራእይ 17፡2 የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ ብሎ ተናገረኝ።” ይለናል።በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ምንዝርነት ደጋግሞ የሚያሳየው ጣኦት ማምለክን ያመለክታል፡፡ ይልቁንም ወደ መንፈሳዊው ስንመጣ ከጥንትም ፈጣሪያችን ና ቤዛችንን ከማምለክ እና ከማገልገል ወደ “ሌሎች አማልክትን” መኮብለልንና ማምለክ እና ማገልገል ለሌላ ማደርን የሚያሳይ ነው። ጌታ እንዳለው ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አንችልም። በአሁኑም ዘመን ቢሆን ሩጫው የዓለምን መንፈስ ስርዓት ስፍራውን እንዲወርስ የማስቀመጥ ጥረት ነው ጌታ ግን ያንንም አልፎ ለበጎ ይጠቀምበታል። የዘመናዩ ስርዓቱም ቢሆን የሥጋ ምኞቶችን ሁሉ አልሞ ያስባል መንገድም ያቀናል እንዲሁም አገልግሏል እያገለገለም ነው። በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት። ”(1 ዮሐ. 2 16) ጌታ እንዳለውም ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤ ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል። ባቢሎን የሃይማኖታዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ራእዮች አንድ ማህበር ነው። ባህርዩ በሦስት የተለያዩ መንገዶች ተገልፀዋል ፣ ግን ሁሉም በተመሳሳይ መንፈስ የሚነዱ የፀረ-ክርስትና መንፈስ ስር እና ሦስቱም በጣም የተሳሰሩ ናቸው። እንደ አንድ ሰው ድርጅቶች ወይም በጣም ብዙ አምባገነናዊ አገዛዞች ውስብስብ የአለም መዋቅር ቢሆን ሁሉም የተሰማሩት የሁከትና ግራ መጋባት መንፈስ ስር ልክ እንደ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ባህርይ አምሳልነት አላቸው ፡፡ እውነት ነው የባቢሎን ከተማ በአንድ ወቅት እውን ከተማ ነበረች። አሁን ማወቅ ያለብን በአንድ ሰው የተገነባ ጸረ ክርስቶስ ከተማ ናት ያ ሰውም #አዳም ነው። “ባቢሎን” ሥጋዊነትን፣ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ የሰውን ጥረት እና ሀሳቦችን እንዲሁም ሥጋዊ አእምሮን የአለም ጸረ ክርስቶስ ስራትንም ወዘተ…ይወክላል። ይህም አሁን በማይታዘዙት ልጆች ላይ ስለሚሠራው የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስም ይናገራል ኤፌ. 2 1 ፣ 2)። እንደ ተፈጥራዊ ሰው ባቢሎን የምትባል ጥንታዊት ምድራዊ ከተማ ብቻ በማሰብ በምናባችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ መሄዳችንን ማቆም አለብን ፡፡ እንደዚሁም በዘልማድ እንደሚባለው “ተቃዋሚው Antichrist” ተብሎ የሚነገረውን የአንድ ሰው በአለም ላይ መነሳት በምናባችን ማሰብም ማቆም አለብን ፡፡ የጠቢብ ዓይኖች በራሱ ላይ ናቸውና እውነታው ወደ ራስዎ ይመልከቱ ነው The wise man’s eyes are in his head the truth is LOOK TO YOURSELVES 2 ኛ ዮሐንስ 1:8 !!! እግዚአብሔር ይብዛልን። ወንድም ቢኒ። ይህ ባቢሎን የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን የተጠቀሰባቸው ቦታዎች ማቴ 1:11 ፣ ማቴ 1:12 ፣ ማቴ 1:17 ፣ ሐዋ 7:43 1 Pe 5:13 ራዕ 14:8 ፣ ራዕ 16:19 ፣ ራዕ 17:5 ፣ ራዕ 18:2 ፣ ራዕ 18:10 ፣ ራዕ 18:21