
Binyam TA
3 hrs ·
ወቅታዊ አጭር ፀሎት፤ የሰማዩ ጻድቅ አባታችን ሆይ ፣ ክብር ለእግዚአብሔር ለአንተ ለአባታችን በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም ሁሉ በጎ ፈቃድ ይሁን። “ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፤ መንፈሴም በውስጤ ትፈልግሃለች። ፍርድህ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ፣ የዓለም ነዋሪዎቹ ሕዝቦች ጽድቅን ይማራሉ። ትንቢተ ኢሳይያስ 26፡9 when thy judgments are in the earth, the inhabitants of the world will learn righteousness.” በኢሳይያስ በኩል በቃልህ ከፍተኛ ውዳሴ ውስጥ አሁን መለኮታዊ ጥበቃህን እንቀበላለን። ከዓለም መሰረት መጣል ጀምሮ በታረደው በበጉ ደም እምነታችንን እናውጃለን። the One having been slaughtered from a casting‑down of [the] ordered arrangement (world) [or: from {the} world’s founding].።
ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለንና። አንድ ሀሳብ ከአንተ ጋር መንደመሆናችንና እንደ አንድ የአንተ ህዝብነትችን የኢየሱስን ደም በግምባራችን ላይ ምልክትን እናደርጋለን ፡፡በጆሮዎቻችንም ላይም የኢየሱስን ደሙን ተግባራዊ እናደርጋለን ፣ ምክንያቱም ቅዱስ ቃልህን ሰምተነዋል እና እውነት እንደሆነ ከአንተ የተነሳ እናምናለንና። ፊርማህንና እና ተፈጥሮህን በግምባሮቻችን ላይ በመንፈስህ መጻፉን ስለቀጠልክ እናመሰግንሃለን።
ከጫንቃችን እኛን ላለመልቀቅ ፈቃደኛ በማይሆኑት ላይ ከመጣው አጥፊ፣ ከማንኛውም ዓይነት መቅሰፍት ሁሉ እና ከአጥፊው አጥማጅ አሁን ሁላችንን በስምህ እንድትጠብቀን እንጠይቃለን የምንጠይቅህ ከክፉው እንድትጠብቀን እንጂ፣ ከዓለም እንድታወጣን አይደለም።፡፡ በምትሠራው ነገር ሁሉ እናከብርሃለን በምድር ላይ ከላከው ፍርዶችህ ጋር ተስማምተን እንቀጥላለን ፣ ምክንያቱም ብርቱ ክንድህ በፍርድ መገለጡ የሰውን ልብ ሁሉ ማቅለጡ እነዚህ ሁሉ በጨለማ ላሉት ጽድቅን ለማስተማር የተቀየሱ አሰራርህ መሆናቸውን እናውቃለን ፡፡ የመንፈስ በኵራት የተቀበላችሁ ልጆች ብለህ ስለጠራሃንና እንዲሁም አንድያ የእግዚአብሔር ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወራሾች እንሆን ዘንድ ስለጠራከን እናመሰግናለን። ወደ በኩር ልጅህ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራከን እግዚአብሔር አባታችን የታመንክ ጻድቅና ቅዱስ አባታችን ሆይ እንወድሃለን። አሜን።
የቅዱሳት መጻሕፍት የተደገፈ ጸሎት፤ “ትንቢተ ኢሳይያስ 26፡20 ሕዝቤ ሆይ፤ ሂድ ወደ ቤትህ ግባ፤ በርህን ከኋላህ ዝጋ፤
ቍጣው እስኪያልፍ ድረስ፣ ለጥቂት ቀን ተሸሸግ።”ወንድም ቢኒ።4You, Demis Nida, Terefe Bekele and 1 other1 Share