የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ


ከውይይት የተጠቀሰ፤ Yabez Gezu እና Tesfaye Gemechu በዚህ አጋጣሚ ብንወያይበት አይከፋም። ከላይ ያለው ሃሳብ በሚገባ ለመገንዘብ ራእይ መንፈሳዊ መጽሐፍ መሆኑን በቅድሚያ ማስተዋል ይኖርብናል። ስለ ራእይ በጥልቀት ቢጻፍ አመታት አይበቃውም ትንሽየ ፍንጭ ለመጠቆም የፈለግኩት መንፈሳዊ ሚስጥራዊ አመልካችነቱን ፍንጭ ለመጠቆም ነው እንጂ ሙሉውን ትንተና ለማቅረብ አይደለም። በአብዛኛው መንፈሳዊ መረዳት እንደ ቱባ ክር ነው ጫፉን ከያዛችሁት ዝም ብሎ ይተረተራል ካልያዛችሁት ጫፉን ፍለጋ ቱባውን በማሽከርከር ጊዜ መግደል ነውና የእዚአብሔር መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ ይምራን እላለሁ። በአጠቃላይ መጽሓፍ ቅዱስ በታሪክና በትንቢት የተሞላ ብቻ ሳይሆን ብዙ መንፈሳዊ ገጽታ ጠቃሚ ገጸ ባህርያት ጭምር ባላቸው ትእይንቶች የተሞላ ነው። ምሳሌዎቹ ተፈጥራዊውን ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊውን እውነታ እንረዳ ዘንድ የአላፊ ግዜ ፤ የወቅቱ ሁኔታ ፤ ደግሞም የወደፊቱን የሚያመለክቱ ትንቢታዊም ሊሆኑ ይችላሉ። ጌታ እየሱስ በስጋ ወራቱም ሆነ ወደ ቀድሞው የመንፈስ ክብሩ ከተመለሰ ቡሃላ በአብዛኛው ምሳሌያዊ ወይም ምልክታዊ ዘየ የተሞላ መልክት ነው ያስተማረን። በስጋ ወራቱ ካለው ስንጀምር ለመጥቀስ ያክል ትምህርቶቹ ቃሉ ሁሉ ቋንቋው symbolic ምሳሌያዊ ወይም ምልክታዊ ነበረ። የአማርኛችን ትርጉም በከፊል ደብቆታል እንጂ ጌታ በመልክተኛው በምልክቶች ነው ለአገልጋዩ ዮሐንስ የነገረው [ለባሪያው አገልጋዩ ዮሐንስ #በምልክቶች አመልክቷል የዮሐንስ ራእይ 1፡1 He indicated by #signs (#symbols) to (in; for) His bond‑servant John JMT] በየዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ በእምነታችን ደራሲ በክርስቶስ የሆነው ይከው ነው። የራእይ መጽሃፉን ሲጀምር እራሱ የመጽሐፉን ሙሉ መልእክት ቅልብጭ አድርጎ አስቀምጦታል። አሁንም እናስተውል የአማርኛ ትርጉም “ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ #አመለከተ” ሲል በከፊል ቀጥተኛ ትርጉሙን እንዳያቀብል ደብቆታል እንጂ ሲጀምር መተርጎም የነበረበት ቀጥተኛ ፍቺው ከላይ እንደጠቀስነው ነው። የመጽሐፉ አረስት እራሱ ተመሳሳይ የትርጉ ዝንፈት አክልዋል። ለየሐንስ የተሰጠው መንፈሳዊ ራእይ ቢሆንም የዮሐንስ ራእይ ይልቅ “The Unveiling of Jesus Christ ” “የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ” ተብሎ ቢሰየም በቀላሉ ለመገንዘብ ይደራ ነበር ጌታ ግን ወዶ በአላማ በዚህ መልኩ እንዲተረጎም ፈቅዶ ቢሆን ማን ያውቃል። በአጭሩ ሙሉ ስሙ መሆን የነበረበት “የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ተብሎ ነበር።፤ An unveiling of Jesus Christ.” Revelation 1:1 [jmt] The Revelation of Jesus Christ [kjv]” ይህ ሐረግ ሁሉንም ይነግረናልና። መጽሐፉ በአጭሩ ለአንድ ዓላማ ነው የተጻፈው እሱም በቅዱሳኑ ውስጥ በመንፈስ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሸፈነበት የስጋ መጋረጃ የክብሩን የመገለጥን ረቂቃዊ መንፈሳዊ ሚስጥራዊ መንፈሳዊ ሂደቱን ለመግለጥ ለማሳየት ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ ተጓዳኝ አጀቦች ሁሉ በሱ ታላቅ ክብርና ብርሃን ቦግ ብሎ መብራት ምክንያት ተጋልጠው እሱ ሲከብር እነሱ ለእይታ ተጋልጠው በብርሃን ይዋጣሉ። የጨለማ ህልውና በብርሃን ህልውና ይዋጣልና ።
በቀላል ቋንቋ የቀሩት የዚህ የእግዚአብሔር ብርሃን የክርስቶስ መገለጥ በራሱ ብዙ ገመናቸውን ያጋለጣቸው ትእይንቶች ናቸው። ልክ ማታ ውሃ ጠምቶህ/ሽ ወደ ወጥ ቤት ትሄድና መብራቱን ስታበራ በረሮው ይሁን ሌላው ነገር ሁሉ ግልጥ ብሎ ሲተራመስ እንደሚታይ በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ፤ የቀሩት ሁሉ ወደ መታየት መጥተው ሲተራመሱ ይስተዋላል ። በምስል በምልክት ያፃፋቸው ሁሉ የመንፈሳዊ ነገሮች እውነታ ገፀ-ባህርይ አመልካች ወካይ ምልክቶች እና አመልካቾች ናቸው። እያንዳንዱ ዋይታ፤ እያንዳንዱ ነጎድጓድ፤መቅረዞች ፤ ፈረሶች ፤ አንበጣ፤ ፤ አራዊት ፤ ወፎች ፤ እንስሳት ፤ አርማጌዶን ፤ እባብ፤ ዘንደዎች፤ ራሶች፤ ፤ ቀንዶች ፤ ጥርስ ፤ ጅራታቸው ፤ ዓይኖች ፤ አእዋፎች፤፤ ክንፎች ፤ ጸጉር፤ እግር ፤ እጅ ፤ በግምባራቸው ፤ ዕጣን ፤መጻሕፍት ፤የወርቅ ፤ ማኅተሞች ፤ ደፍተው ፤ ስሞች ፤ ከተሞች ፤ በአሕዛብ ፤ ነገሥታት ፤ ልሳኖች ፤የኒቆላውያንን፤ አንቲጳስ ፤ በለዓም ፤ ባቢሎን፤ ሰዶምና ፤ ግብጽ ፤ ኤልዛቤል ፤ መጽሐፍ ሕይወት ፤ የሕይወት ዛፍ ፤ የሕይወት ውኃ ፤ ሰዓታት ፤ ቀናት ፤ ወራት ፤ ወቅቶች ፤ የብረት በትር ፤ ማጭዱን ፤ ቀስት ፤ ሰይፎች ፤ ያጭዳል ፤ የመከር ፤ የሣር ፤ ዛፎች ፤ ዙፋኖች ፤ ልብስ ፤ ምስሎች ፤ ድንቅ ፤ ምልክቶች ፤ ቁጥሮች ፤ ጽዋዎች ፤ መለከት ፤ነፋሳት ፤ ወንዞች ፤ ሀይቆች ፤ ባህሮች ፤ ውኃ ፤ ደመና ፤ ጎርፍ ፤ ተራሮች ፤ ደሴቶች ፤ መብረቅና ፤ ድምፆች ፤ ያንጎደጉዳል ፤ነውጦች ፤ በረዶ ፤ ዘንዶ፤ ፤ ዘፈኖች ፤ የወይን መጭመቂያ ፤ ወይን ጠጅ ፤ ሚዛን ፤ ስንዴ ፤ ገብስ ፤ ዘይት ፤ የዓይን ሽፋሽፍት፤ ጠጠሮች ፤ መና ፤ ጉንጉን ፤ የዘንባባ ዝንጣፊ ፤ የጋለሞታዎችና ፤ ጋለሞቶች ፤ ዝሙት ፤ ቁልፎች ፤ በሮች ፤ ቤተ መቅደሶች ፤ ምኵራቦች ፤ አዕማድ [ምሶሶ]፤ ሀብታም ፤ ድሃ፤ ዕውር ፤ እርቃናቸውን ፤ትኩስ ፤ቀዝቃዛ ፤ ለብ፤ ደም፤ እሳት ፤ ዲን[ሰልፈር] ፤ እሳትና ፤ ጭስ ፤ ፀሐይ ፤ ጨረቃ ፤ ከዋክብት፤ እንስሶች፤ ምስሎች,፤ምልክቶች፤ ባቢሎን፤ዘንዶ፤ወዘተ… ከብርሃኑ መከሰት የተነሳ በምልክት መንፈሳዊውን ሚስጥር ወክለው የተጋለጡ የነገሮች ገፀ-ባህርይ አመልካች ወካይ ምልክቶች እና አመልካቾች ናቸው። ። በአጭሩ በክብር መገለጡ የኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ የመከራዎች ወይም የክርስቶስ ተቃዋሚያን ሃይላት መገለጥ ለማሳየት አይደለም። እነሱ የጎንዮሽ ትእይንት ናቸው እንጂ ዋናው የእግዚአብሔር ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ነው። ሃይል የአንዱ የእግዚአብሔር ነውና። እርሱ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት የሚኖር ጌታችንና አምላካችን ሁሉን ፈጥረዋልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም የእርሱ ነው። የዮሐንስ ራእይ 4፡10-11
የማቴዎስ ወንጌል 13፡34-35 ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ #በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም፦ #በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ #የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም። ይህንንም በነብዩ ዳዊት ላይ ሆኖ መንፈስ በመዝሙር 77/2 ላይ አስቀድሞ ተናግሮት ነበረ። እንደ ምናስተውሉት ትንቢቱ ፍፃሜ ያገኘው ጌታ ያለ #ምሳሌ ስላስተማረ ነው።
ባለፈው እንደጠቀስኩት በጥቂቱ ለመድገም ያክል ከ 41 በላይ #ምሳሌዎችን ተናግረዋል የዘልአለም ስቃይ ሰባኪዎች ግን ነጥለው እውነተኛ ታሪክ ነው የሚሉት የሃብታሙ ሰውና አልአዛር የበጎችና ፍየሎች ወዘተ…. ያስፈራራሉ የሚልዋቸውን ምሳሌዎችን ነው። እውነታው ግን ጌታ ከተናገራቸው ምሳሌዎች ለማስታወስ ያህል። ከእንቅብ በታች ያለ መብራት፤ የሰናፍጭ ቅንጣት፤ ልባምና ሰነፍ አናፂዎች፤ በአረጀ ልብስ ላይ አዲስ እራፊ፤ በአረጀ አቅማዳ ላይ አዲስ ወይን፤ ዘሪና የመሬት አይነቶች፤ የተሸሸገ እርሾ ፤ በባህር ላይ የተጣለ መረብ፤ የጠፋ በግ፤ምህረት የማያደርግ ባርያ፤ አስሩ ቆነጃጅት፤ በጎችና ፍየሎች፤ ደጉ ሳምራዊ፤ የጠፋ ድሪም፤ ወዘተ…… ዶክትሪናቸውን ለማጽደቅ ሁሉም የዘልአለም ስቃይ ሰባኪዎች ነጥለው እውነተኛ ታሪክ ነው ብለው የሙጭኝ ይላሉ።
እውነታው ግን ጌታ ከ 41 በላይ ምሳሌዎችን ተናግረዋል አንዳቸውም በእውን የተፈፅሙ የተከሰቱ ታሪኮች አልነበሩም። ተምሳሌትን ምሳሌነቱን ትተን ወደ እውነተኛ ታሪክ ስንከረብተው ወይም ስንገለብጠው ተምሳሌነቱ ይጠፋል።
ሁላችንም እንደምናውቀው ምሳሌ ወይም ተምሳሌት የሚነገረው በጥሬው ካለው ትርጉሙ ውጪ ሌላ ነገርን የሚወክል ቃል ወይም ሃረግ ነው። ለምሳሌ አንበሳ የጀግና ምሳሌ ነው፤ በግ/እርግብ የየዋህነት የንጽህና ምሳሌ ነው።
በተፃራሪው ታሪክ ማለት ደግሞ ባለፉት ዘመናት እውን የነበሩ ክስተቶች ትውፊት፤ የሚዘገብ ክንዋኔ፤ ለምሳሌ ቀድሞ የነበረ ወግ፤ ጀብድ፤ ጀግንነት፤ የሃገር ኩራት፤ ወዘተ….ማንኛውም የሚያኮራ ይሁን አሳፋሪ ክስተት ሁሉ በዘመኑ ባለ ትውልድ እንደ “ነበረ” የሚታሰብና የሚነገር የሚዘገብ የአላፊ ጊዜ “ክስተት” ታሪክ ይባላል።
ጌታ እየሱስ በየትኛውም ቦታ ለፈሪሳውያን ይሁን ለህዝቡ ሲያስተምር ያለ ምሳሌ ሲያስተምር አታዩም። ምሳሌዎቹ ግን ብዙ ገፅታ ሊያሳዩ ይችላሉ። የአላፊ ግዜ ፤ የወቅቱ ሁኔታ ፤ ደግሞም የወደፊቱን የሚያመለክቱ ትንቢታዊ ሊሆኑ ይችላሉ። አንድ ነገር ሲመስል ወይም እንደ ሌላ ነገር ሲያስቀምጠው ዘይቤያዊ አነጋገር፣ ተለዋጭ መልክት የሚያመላክት ነው። ለምሳሌ ከእ/ር ቃል ለመጥቀስ ያክል
ዘይቤያዊ አነጋገር፣ ተለዋጭ – “ሕይወት ሁሉ ሣር ነው” ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤ 1ኛ ጴጥ 1:24 ስለሆነም እንደምናስተውለው የዚህ መልክት ተምሳሌት ነው እንጂ ቃል በቃል ሊወሰድ አይችልም። It IS a metaphor and CANNOT be literal.
ምሳሌ – ” እርሱም፦ ያለ ጥርጥር ይህን ምሳሌ፦ “ባለ መድኃኒት[ሃኪም] ሆይ፥ ራስህን ፈውስ፤ “ሉቃስ 4:23)
ምሳሌያዊ ፤ ይህም ነገር #ምሳሌ ነው፤ እነዚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ኪዳኖች ናቸውና። (ገላ 4 22-28)
እንደ ራዕይ (ሰማይም ተከፍቶ በአራት ማዕዘን የተያዘ ታላቅ ሸማ የሚመስል ዕቃ ወደ ምድር ሲወርድ አየ ሐዋ 10 /11-16)
ምልክት (ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ #ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። ማቴ 12 ፡39)
ዓይነቶች – (በአዳም እና በክርስቶስ እንደሚያመሳሰል ሮሜ 5 /12-21)
እንደ ጥላ (ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና። ዕብ 10: 1)
የሚመስሉ – ( እንግዲህ በሰማያት ያሉትን የሚመስለው ነገር በዚህ ሊነጻ እንጂ በሰማያት ያሉቱ ራሳቸው ከእርሱ ይልቅ በሚበልጥ መስዋዕት ሊነጹ የግድ ነበረ። ዕብ 9:23)
የዮሐንስ ራእይ 1፡10 በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ። የጌታ ቀን በውስጡ ብዙ ጥልቀትን ያካተተ ቢሆንም አይነተኛ ነገሩ በመንፈስ ከመሆን ጋር የተያያዘ ነው። በጌታ ቀን መሆን ማለት በመንፈስ ውስጥ መሆን ነው። የዮሐንስ ራእይ 1፡10 በጌታ ቀን በመንፈስ ውስጥ ነበርሁ። KJV Rev 1፡10 I was in the Spirit on the Lord’s day AMP 10: I was in the Spirit [rapt in His power] on the Lord’s Day (Rev 1:10 [Weymouth]) In the Spirit I found myself present on the day of the Lord, ወዘተ….. ወንድም ቢኒ።

  • Binyam TA የውይይት ሊንክ https://www.facebook.com/sola.scriptura.94064/posts/132934464946524Edit or delete this
  • Active NowTesfaye Gemechu Thank you for the detailed information. I have seen them, it is a good introductory material on the book Revelation and a kind of summary using the imagery and symbols of the book, yet I have to say that I am not in agreement with a total spiritualaisation of the book, except it’s own lead towards symbolic interpretation. In relation to the initial post and my comment on it, I was not saying that the serpent nor the dragon are literal. As I said there these are names which expresses it’s craftiness and cruelty. Symbolic, figurative expressions are common in every day communication, clues in the context will lead to that. You know a lot on the point, yet if you want discussion make them short, pointed and even questions that will engage the participant, now you lecture and I reflect, this is not discussion. Any way thank you. I really appreciate you for sending your detailed perspective and view on the book of Revelation. Blessings1Delete or hide this
  • Binyam TA Dear Tesfaye Gemechu thank you and good point by the way. As you know we all have to take the bible seriously. Study, rightly dividing the word of truth and strive to teach and practice love, acceptance, and forgiveness that takes serious time. Even th…See MoreEdit or delete thiskingdombiblestudies.orgKindgdom Bible Studies Savior of the World Series Part 1Kindgdom Bible Studies Savior of the World Series Part 1
  • Active NowTesfaye Gemechu Blessings again. ተሳክቶልህ ቶሎ እንድትፅፍ አሁን እፀልይልሀለሁ። I hope you will succesed soon. አንተው “በዚህ አጋጣሚ ብንወያይበት አይከፋም” ብለህ ስለፃፍህ ነው ስለመወያየት እንዲህ እንዲያ ቢሆን ያልኩህ። የጠቀስካቸውን ፅሁፎች ላያቸው እሞክራለሁ። ከመጽሐፉ Apocalyptic ባህሪ የተነሳ የተለያየ አተያይና አተረጉዋጎም እንዳለ ሳትረዳ አትቀርምና በገባህ ልክ መንፈሳዊ ሕይወትህን በማነፅና ሌሎችንም በመጥቀም አገልግልበት ግን መጽሐፍ ቅዱስ የራዕይ መጽሐፍ ብቻ እንደሆነ ያክል በሱ ብቻ አትወሰድ ሌላ አተያይ ላላቸው ያለህን ፍቅርና አክብሮት አትጣል ያንተን አፈታት ብቸኛው አርገህ አታስብ። ፀጋ፣ ምህረትና ፍቅር ይብዛልህ።2Delete or hide this
  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal