እራሳችን ከበሰሉ ክርስቲያኖች ወይስ ከቀናተኛ ክርስቲያን እንመድባለን?


Binyam TA

February 26, 2018 ·

ጥያቄና/መልስ እራሳችን ከበሰሉ ክርስቲያኖች ወይስ ከቀናተኛ ክርስቲያን እንመድባለን?
ወንድሜ “ሃሳቡን አንስተውምና ” ቆም ብለህ እስቲ እየው። ሰውን የሚያይ ይሰበራል እግዚአብሔርን የሚያ ይጠገናል። “ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13/11”
አንድ ቀናተኛ ክርስቲያን ከበሰሉ ክርስቲያን ጋር አንድ አይደለም። ቀናዒነት ብዙውን ጊዜ አክራሪ ነው። ቀናተኛ ስለ አንድ ሁኔታ እና ስለ እግዚአብሔር ቃል በከፊል ግንዛቤ ያለው ስለሆነ የስጋ ስራ እንደመሆኑ እ/ርን የሚያገለግል እየመሰለው ክርስቶስ ዋጋ የከፈለላቸውን ዎንድሞችን ሳይቀር ያሳድዳል ይህም ከንቱነው። በመንገዱ ላይ የሚቆምና ሃሳቡን የማይደግፈውን ሰው አጥፍቶ ለመሞትም ዝግጁ ነው። ግቡን ለመምታት ሁሉን ለመግደል ዝግጁ ነው። በጌታና በእውነት ላይ በቆራጥነትና ጠንካራ አቋም ይዞ ማመን ጥሩ ነገር ነው። ነገር ግን ከመብሰል ውጭ ከሆነ አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ቀናተኛ ክርስቲያኖች ከመንፈሳዊ ብስለት ጋር በሚመሳሰል መልኩ ከበፊቱ የበለጠ ጉዳት ያመጣሉ። ሰዎችን በክርስቶስ አይንና ችሎታ የማየት ብቃታቸው ደካማ ስለሆነ ለሌሎች ክርስቶስ በራራበት መራራት ይቅር በተባሉበት ይቅርታ በተወደዱበት መወደድ እንዳይመላለሱ ያለመብሰል ከፊል መንፈሳዊ እውርነት ሆኖባቸው በብርሃን አለሁ ይላሉ ግን በክርስቶስ ያለ ወንድማቸውን በአመለካከት ልይነት ብቻ ይጠላሉ ። ፍቅር የሆነውን እ/ር ከመግለጥ ይልቅ በውስጣቸው ያለውን ቅዱስ መንፈስ ያሳዝናሉ ወንድማቸውን በመጥላትጠላ እስከ አሁን በጨለማ እንዳሉም አያስተውሉም።
ሌላው ቢቀር ክርስቶስ የሞተለትን ወንድምህን ውደድ የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና። “ በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ። 10 ወንድሙንም የሚወድ በብርሃን ይኖራል ማሰናከያም የለበትም፤ 11 ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2/9”
“የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3/10”
መርሳት የሌለብህ “ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፦ ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/3”
“በራሱ ርኵስ የሆነ ነገር እንደ ሌለ በጌታ በኢየሱስ ሆኜ አውቄአለሁ ተረድቼአለሁም፤ ነገር ግን ምንም ርኵስ እንዲሆን ለሚቆጥር ለእርሱ ርኵስ ነው።ወደ ሮሜ ሰዎች 14/14”
“ለአንተ ያለህ እምነት በእግዚአብሔር ፊት ለራስህ ይሁንልህ። ፈትኖ መልካም እንዲሆን በሚቈጥረው ነገር በራሱ ላይ የማይፈርድ ብፁዕ ነው።ወደ ሮሜ ሰዎች 14/22”
ወንድሜ መጀመርያ ሁሉ የእግዚአብሔር መሆኑን አስተውል ከዛ እግዚአብሔር የወደደውን ውደድ እንጂ ሸክም በራስህ ላይ አትጫን ከፍቅር በቀር ሌላ እዳ አይኑርብህ። ከዛ ያልበሰለ የቡድን ክርስትና ያከትማል።
“ጳውሎስ ቢሆን አጵሎስም ቢሆን ኬፋም ቢሆን ዓለምም ቢሆን ሕይወትም ቢሆን ሞትም ቢሆን ያለውም ቢሆን የሚመጣውም ቢሆን፥23 ሁሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3/22”

ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል። ጥል ክርክርን ታስነሣለች፤ ፍቅር ግን ኃጢአትን ሁሉ ትከድናለች።
ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ሰነፍ ብትሆን ለራስህ ከስንፍና ጥበብ እንደሚበልጥ ሁሉ ከጥላቻም ፍቅር ይበልጣል። እንደጌታ አፍቃሪ ብትሆን ለራስህ መልካም ነው። እኛስ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ሊለየን እንደማይችል ተረድተናል። በመረዳት ውስጥ ሃይል አለ። “የአምላክህን ማስተዋል ታገኛለህ”
“ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ሊለየን ይችላል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?። 36 ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። 37 በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። 38 ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ 39 ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።ወደ ሮሜ ሰዎች 8”

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal