
ጥያቄ/መልስ የተወሰደ። #ጥያቄ፡ አሁን አሁን ላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ውስጥ የሚያስቸግረኝ አንድ ቃል አለ ፣ እናም የገባህ ነገር ካለ በእሱ ቃል ላይ ማብራራት የሚያስችል ብርሃን ቢኖርህ በጌታ ይገርመኛል ፡፡ ይህን የሚረብሸኝ ቃል ክርስቶስ አሳልፎ የሚሰጠውን ይሁዳን እንዳለው በጣም እርግጠኛ ነኝ፡፡ “የሰው ልጅ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈው ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ለዚያ ሰው ሳይወለድ ቢቀር ይሻለው ነበር።” ትክክለኛውን የቃላት አፃፃፍን እያሰብኩ እንደሆንኩ እርግጠኛ አይደለሁም ፣ ግን በእነዚህ መስመሮች ላይ ለዚያ ሰው ሳይወለድ ቢቀር ይሻለው ነበር ያለው ከራሴ ጋር አያይዤ በጣም እኮነንበታለሁ፡፡ ክርስቶስ ይህን ማለቱ ምን ማለቱ ነው። ተባረክ።
#መልስ ከቢኒ፡ ሰላም ለአንተ ይሁን። በቅድሚያ መዘንጋት የሌለብህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡1 ባነሳከው ሃሳብ ላይ የቀድሞ ትርጉም ይሁን አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእንግሊዝኛ የባለስልጣኑ ኪንግ ጀምስ ትርጉም ተብሎ የሚታወቀው ጭምር ገልብጠው ተርጉመውታል። በዚህ ጥቅስ ላይ ትክክለኛ ትርጉም አይደለም የተቀመጠው፡፡ መነበብ ያለበት: “ስለ እሱ [ጌታ ኢየሱስ ማለት ነው] ተብሎ እንደተጻፈው የሰው ልጅ በእርግጥ ይሄዳል ፤ ነገር ግን የሰው ልጅ [አሁንም ጌታ ኢየሱስ ማለት ነው] አልፎ በተሰጠበት በዚያ ሰው (እርሱም ሰው ይሁዳ) ነው! ያ ሰው [ይሁዳ] ባልተወለደ ለእርሱ [ለጌታ ኢየሱስ ፣ ያ ሰው ፣ ይሁዳ ሳይሆን] መልካም ነበር! ”(ማቴ. 26 24 ፣ ኮንኮርዳንስ መጽሐፍ ቅዱስ አዲስ ኪዳን)”
The Son of Man is indeed going away, according as it is written concerning Him [Jesus], yet who to that man [that man is Judas] through whom the Son of Man [Jesus] is being given up! Ideal were it for Him [JESUS, not ‘that man, Judas’] if that man [Judas] were not born!” (Matt. 26:24, Concordant Literal New Testament)
ሌላ አማራጭ ትርጉም
JMT “”On the one hand, the Son of the Man

(= Adam’s son; = the representative human; = the eschatological messianic figure) is progressively leading the way under (or: is now going away) – just as (correspondingly as) it has been written about and concerning Him. Yet tragic will be the fate for THAT MAN through whom the Son of the Man is in the process of being turned over. It was continuing being beautiful for Him [i.e., for the Son of the Man] (or: It was being ideal to Him; It was existing fine for Him) – if THAT MAN was not brought to birth (or: had [just] not been born)!” ወንድም ቢኒ።