
ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች[ትክክል ሆና ተገኘች} ጌታ በጥበብብ በማይመላለሱ የብርሃን ልጆች ተናዶ የተናገረው ቃል ሁሌ ይደንቀኛል። “#የዚህ #ዓለም[aion ዘመን] ልጆች #ለትውልዳቸው #ከብርሃን #ልጆች ይልቅ #ልባሞች ናቸውና።” እኛ የብርሃን ልጆች ብርሃን ነን ለትውልዳችን መብለጥ ልህቀት ማሳየት እዳለብን አባት በቁጣ ምክር አንድ ቃል ይነግረናል። ይህ እንደሚቻል ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑን የጥላው ዘመን እስራኤል 12 ነገድ ቢሆኑም ይህ ሁሉ ህዝብ የሚገባውን ያደርግ ዘንድ #ዘመኑን #የሚያውቁ #ጥበበኞች ሰዎች #የይሳኮር #ልጆች #አለቆች ቁጥራቸው ሁለት መቶ ብቻ ቢሆንም ህዝብ ሁሉ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ይታዘዙአቸው ነበር። ተመልከቱ እንካን የይሳኮር ልጆች ጠቢቡ ሰለሞን ከክርስቶስ ጥበብት ተገምሶ ተስጦት ነው። በውስጣቹሁ ክርስቶስ አድሮ እናንተማ እንዴት? ከመቅደሳቹ የሚበልጥ ከዚህ አለ ብቻ ሳይሆን ወይም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ ብቻ ሳይሆን እውስጣቹሁ ሆኖ ክርስቶስ እንዲህ ይላል ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፡27
የሉቃስ ወንጌል 16፡8 ጌታውም ዓመፀኛውን መጋቢ በልባምነት ስላደረገ አመሰገነው #የዚህ #ዓለም[aion ዘመን] ልጆች #ለትውልዳቸው #ከብርሃን #ልጆች ይልቅ #ልባሞች ናቸውና።
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 12፡32 እስራኤልም የሚገባውን ያደርግ ዘንድ #ዘመኑን #የሚያውቁ #ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ይታዘዙአቸው ነበር። ወንድም ቢኒ።