
ከውይይት የተጠቀሰ፤ ሰላም ይሁን፤ በመልኩና በአምሳሉ ስለፈጠረው ሰው፤ ሁላችንም እ/ር ፈቅዶ በሰጠንን መረዳት ልንመላለስ የግድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ለአንዳዱ ሰው እያነበበው ለማሰላሰል እንኳ ማቆም የማይችልበት አስደናቂ የመገለጥ ተፋሰሱ ሳይቃረጥ መጽሐፍን ያደንቃል በአንጻሩ ሌላኛው ደግሞ ያንን ጥቅስ ለበርካታ ሰዓታት እያነበበው ከመንፈሳዊ እይታ ወደ ፊደል ሊጠፋ ይችላል ፡፡ በጣም ብዙ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው በተናገሩ ሰዎች መሆኑን በጭራሽ ይዘነጉታል ፣ እናም ተፈጥሮአዊው ለኃጢያት የእምሮው ንቃተ፟ህሊና ያለው ለመንፈሳዊ ነገር ንቁ ሆኖ አባት ለሕዝቡ የሚናገረውን በጭራሽ ሊረዳ አይችልም ፡፡ ተፈጥሮአዊው አእምሮ የእግዚአብሔር የሆኑትን ነገሮች ለመቀበል ችሎታ የለውምና ፣ ነገር ግን ጳውሎስ በዘመኑ ለነበሩ ቅዱሳን” በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ያ አስተሳሰብ፣ በእናንተም ዘንድ ይሁን” ብሏል ፡፡
ይህ ሃሳብ ለብዙ ወገኖች በጣም አወዛጋቢ ገጽታ ሆኖ ይታያል፡፡ በመልኩና በአምሳሉ ስለፈጠረው ሰው ከማውራታችን በፊት የአባትን #ሁለት ቁልፍ መላኮታዊ ልእለ፟ተፈጥሮ ባህርይ ወይም መንፈሳዊ የእ/ር ክብር አልያም መልኩን እና ምስሉን በእ/ር ቃል እውነት ማስተዋልና ማወቅ አለብን። #የመጀመርያው እግዚአብሔር መልኩ እና ምስሉ የማይታይ ባህርይ ማንነት ያለው መንፈስ ነው እንጂ አካል ያለው ወይም ስጋ ወይም ሌላ ሃሳበ-መ፟ሲሂ ቅርጸ-፟ባ፟ህርይ ያለው አይደለም። እ/ርን ልክ እንደ ማንኛውም ቀርጽ ያለው ተመላኪ ጣኦት ይህን ይመስላል ብላችሁ ለእ/ር ቅርጽ ልትሰጡት ከቶ አትችሉም እ/ር የማይታይ መለኮት የሆነ መንፈስ ነውና። በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው አንዱ አስተሳሰብ፣ በእኛ ዘንድ መሆን ካለበት አንዱ የዮሐንስ ወንጌል 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው። የሚለው እውነት ነው። “God [is] spirit (or: Breath), and it is binding (necessary) for the ones continuously worshiping Him to be constantly worshiping with spirit and Truth (in breath [= life] and reality; within the midst of [the] Spirit and [the] Fact).” የሮሜ አንድን ቃል እንዲገባን በዚህ መልክ በቀላል አማርኛ ብናስተውለው። “ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ መንፈስ በመሆኑ የማይታየው የእግዚአብሔር ባሕርይ የዘላለማዊ ኀይሉና መለኮትነቱ፣ ለፍጥረቱ በግልጽ ይታያል፤ ስለዚህ ሰዎች ማመካኛ የላቸውም።እግዚአብሔርን ቢያውቁም እንኳ፣ እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም፤ ምስጋናም አላቀረቡለትም፤ ነገር ግን ሐሳባቸው ፍሬ ቢስ ሆነ፤ የማያስተውል ልባቸው ጨለመ።” እ/ር መንፈስ ስለሆነ አይታይም። የዮሐንስ ወንጌል 1፡18 መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም። የዮሐንስ ወንጌል 5፡37 የአባትን ድምፁን ከቶ አልሰማችሁም፥ መልኩንም አላያችሁም።
የማይታየው ባሕርይው ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡20-21 የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ። እርሱ የማይታየውን አምላክ ባሕሪዎች ትክክለኛ አምሳያ ነው፡፡ For from [the] creation (framing; founding) of [the] ordered system (world) [Now] He is the exact likeness of the unseen God [(qualities; attributes) the visible representation of the invisible] which – both His imperceptible (or: perpetual) power (ability; capacity) and divinity (divine nature; godship) – are habitually seen clearly (held within view by looking down; perceived), being continually comprehended
የእግዚአብሔር ክብር ነገርን መሰወር ብቻ ሳይሆን በባህርዩ መንፈስ በመሆኑ እራሱን የሚሰውር ብሎም በስውር የሚያይና የሚሰማም ነው ተግባሩም በመንፈሳዊ የማይታይ ባህርዩ ምክኛት የሚከውነው በመንፈሱ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም። መጽሐፈ ምሳሌ 25፡2 የእግዚአብሔር ክብር ነገርን መሰወር ነው። የማቴዎስ ወንጌል 6፡3-4 በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 22፡12 መሰወርያውን ጨለማ አደረገ። መጽሐፈ ኢዮብ 37፡9 ከተሰወረ ማደሪያውም። መጽሐፈ ኢዮብ 34፡29 ፊቱንስ ቢሰውር የሚያየው ማን ነው?። የዮሐንስ ወንጌል 14፡17 እርሱ ዓለም የማያየውና የማያውቀው። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡20 ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፡15-16 እርሱ የማይታየው አምላክ አምሳል ነው። የአባትና-የልጅ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ተፈጥሮ አንፃር ምን ማለት ነው? መቼም ቃሉ ህይወትና መንፈስ ብቻ ሳይሆን ጌታችን እንዳለው በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው እንዳለ ከሚቀድሰን የእውነት ቃል አንዱ “እግዚአብሔር መንፈስ ነው” የዮሐንስ ወንጌል 4/24 የሚለው መንፈሳዊ ሃቅ ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ከሆነ በመልኩና በአምሳሉ የተፈጠረው የመጀመርያው ሰው የእ/ርን መልክ ያለምንም ቃል መሸቀጥ የመንፈስ መልክና አምሳል ያለው ነው። ይገባናል ለእ/ር ጠላት ለተፈጥራዊው ስጋዊ አእምሮ ሳይሆን ለመንፈሳዊው ለክርስቶስ አእምሮ የአባትና-የልጅ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ልእለ፟ተፈጥሮ መለኮት ባህርይ አንፃር ምን ማለት እንደሆነ የዘፍጥረቱን አዳም ጨምሮ። አዳም የእግዚአብሔር ልጅ Adam, [son] of God የሉቃስ ወንጌል 3፡38። በአጭር አማርኛ ልጆቹም እሱን ይመስላሉ እንጂ ሌላ አይመስሉም። መቼም ነገር ሳይንዛዛ በአጭር ቃል እንቅጩን እንደጌታ ኢየሱስ ክርስቶ የሚያስቀምጠው የለም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው! ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው! የዮሐንስ ወንጌል 3/6 አለቀ እግዚአብሔር መንፈስ ነው ከመንፈስ እግዚአብሔር የተወለደ መንፈስ ነው! አንዳንዱ ሰው ኢየሱስን ውሸታም ለማድረግ በውሸት የትህትና ጭምብል ተላብሶ የግግምናው ብዛት ከመንፈስ የተወለደ ሥጋ ነው ብሎ ገልብጦ ይረዳዋል ዘፍጥረት ላይ መንፈስ የሆነውን የእ/ርን አምሳልና መልክን ገልብጦ ይረዳዋል።
እግዚአብሔር ዘፍጥረት 1 ላይ ሁሉ እንደ ወገኑ ዘሩ ያዘጋጅ ይብዛ አላለም? በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን፥ ውኃይቱ እንደ ወገኑ ያስገኘቻቸውንም ተንቀሳቃሾቹን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፥ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም አለ፦ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፤ እንዲሁም ሆነ።
ታዲያ ሰው ጋር ሲደርስ እንደ ወገኑ እንደ እግዚአብሔር የማይዘጋጅበት ምን ምክንያት አለ? እግዚአብሔር መንፈስ ነው እንደ ወገኑ በእ/ር መልክ በመንፈስ የተፈጠረ መንፈስ ነው እንዲሁም በአዲስ ኪዳን ከመንፈስ እግዚአብሔር የተወለደም መንፈስ ነው! እነርሱ ከእግዚአብሔር ወገን ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወገን ወይም ከወንድ ፈቃድ ወገን አልተወለዱምና ።የዮሐንስ ወንጌል 1/13
#ሁለተኛው ማወቅ ያለብን “እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡[ አዳምን Adam (male and female) ]ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ።” የሚለው ውስጥ ከትዮሎጅያን የተሰወረው እውነት አለ። ይህን በክርስቶስ መንፈሳዊ አእምሮ ማየት አለብን። የእ/ር መንፈሳዊ ነገር ለተፈጥራዊው አእምሮ የተከደነ የተከለከለ ነውና።።
እንደምናስተውለው ይህ ቃል የእ/ር ሙላተ ክብር የሚያሳይ ቃል ነው። የእግዚአብሔር መልክ፤ አምሳል እና አምሳያ በዚህ ቃል መሰረት እግዚአብሔር የወንድን እና የሴትን ገጽታን በሙላት ያካትታል። ይህ ባይሆን ኖሮ ምድራዊው የእግዚአብሔር አምሳያ ተብሎ የፈጠረው ሰው አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት የያዘ ባለ አንድ ፆታ ብቻ ሆኖ ይፈጥረው ነበረ። ሲፈጥራቸው ግን በአንድ አዳም ውስጥ ሁለት ፆታ በአንድ ላይ ነበር አዳምን የፈጠረው እግዚአብሔር ግን ቡሃላ ለሁለት ከፈላቸው ።
እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በመልኩ? በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ;;
በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ? ግልጽ ነው። Gen 1 verse 27, “And God created man in His own image, in the image of God He created him; male and female He created them.” The #image and #likeness of #God, then, #includes #male and #female #aspects of #God. If this were not so, then the #earthly #image of God would #express just #one #sex, either male or female.
የአባትና-የልጅ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ተፈጥሮ አንፃር ምን ማለት ነው? የሚለው አዲስ አወዛጋቢ ሃሳብ አይደለም ይህ በአራተኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የነበረችው ቤተክርስቲያን የሥላሴ አማኞች እና ንዑስ፟ ተዋናዮች(Subordinationism) መካከል ዋነኛው ጉዳይ ነበረ።
ይህንን ጭብጥ የበለጠ ለማጎልበት ማስተዋል ያለብን ሰው ራሱ ከእግዚአብሔር እንደወጣ እና በሂደቱ ውስጥ የእግዚአብሔር አላማ ሆኖ ከክብሩ ዝቅ እንዲል አጠቃላይ ክፍፍሉ ከእ/ር ክብር ከክርስቶስ ጎድሎ እንደነበረ ልብ ማለት አለብን ፡፡ የዘፍጥረት መጽሐፍ ስለ ሰው አፈጣጠር ሁለት ዘገባዎችን ይሰጣል ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነግረን ፣ ብዙ ነገሮችን በጣም ግልጽ አድርዋል። ከእነዚህም አንዱ በዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ እና ሁለት ውስጥ የተገለጡ ሁለት የተለያዩ የእግዚአብሔር የአፈጣጠር ህይደቶች ወይም ሥራዎች አሉ ሁለቱን የአፈጣጠር ሂደቶች አንድ ናቸው ብለው ለሚያስቡ ቃሉን በጥሞና መከለስ አለባቸው በመጀመርያ በመራፍ 1ቁ26 ላይ እግዚአብሔር (ኤሎሂም)፣ “ሰውን በመልካችን፣ በአምሳላችን #እንሥራ አለ። ከዛም ቁ፤27 ላይ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰውን በራሱ መልክ #ፈጠረው፤በእግዚአብሔር (ኤሎሂም) መልክ #ፈጠረው፤ ምእራፍ2፡7 ላይ ደግሞ የዚህ አፈጣጠር ህይደት ሙላቱ ባለ ሁለት ምእራፍ እንደሆነ እንዲህ ሲል ይትተርክልናል። እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ከምድር ዐፈር ወስዶ ሰውን #አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ።ማስተዋል ያለብን #ፈጠረው[Hebrew፡ בָּרָ֥א bara’ baw-raw’ to create መፍጠር፤ He created ፈጠረ] የሚለው ቃል እና #አበጀው[ Hebrew፡ וַיִּיצֶר֩ yatsar yaw-tsar’ through the squeezing into Shape በመጠምጠጥ ቅርፅ ማስያዝ፤ to mould into a form; especially as a potter ወደ ቅርፅ መቅረጽ; በተለይም እንደ ሸክላ ሠሪ፤ to fashion መልክ አድርጎ መስራት]መንታ ቃላቶች አይደሉም።
ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው[ሁለት ጾታ በአንድ]፡፡ በዘፍ. 1፡26-27 የፍጥረት ሥራዎች የመጀመሪያው ተግባሮት እናስተውላለን፣ እናም “በእግዚአብሔር መልክና አምሳል የተፈጠረው” ስንመለከት የእግዚአብሔር መልክና አምሳል አንድ እ/ር መንፈስ ነው ሁለት ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው እ/ር ድርብ ክብር ያለው ወንድና ሴት ነው። መደምደሚያው እዚህ ጋር ሲፈጥረው መንፈስና ወንድና ሴት ማንነትን የያዘ አንድ ሰው ፈጠረ ቡሃላ ሄዋንን ከጎኑ እስኪያወጣት ማለት ነው፡፡ የመጀመሪያው የፈጠራ ተግባሮት ላይ የፈጠረው መንፈሳዊ ሰው ሲሆን ይህም ሁሉን ቻይ ከሆነው የእግዚአብሔር መንፈሳዊ ማንነት አምጥቶ የራሱን መለኮታዊ ተፈጥሮ ፣ ባህሪው እና ባህርያቱን ተሸክሟል። የእግዚአብሔር አምሳል በሰው ተፈጥሮ ውስጥ የተፈጠረ የእግዚአብሔር ባሕርይ ነው ፡፡
በሰው ላይ የተከናወነው የእግዚአብሔር ሁለተኛው የሚዛመድ ሥራ በዘፍ 2፡7 ውስጥ ይህ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው ሲከናወን እንመለከተዋለን ፡፡ “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ ፡፡” በሌላ አገላለጽ እንዳስተዋልነው መንፈሳዊ ሰው በመጀመሪያ ተፈጥሯል ያም እንደ የእግዚአብሔር መንፈሳዊ ምስል ከዛም አንድ ተጨማሪ ሥራ ይቀረዋል እና ሰው አሁን ከትቢያ ውስጥ ከምድር አፈር የማበጀት ስራ ተበጅቶ ሕያው ነፍስ ይሆን ዘንድ እስትንፋሱን እፍ አለበት ። ይህም በምድራዊ ግዛት መገለጥ የሚያስችለው ማንነት ያዘ። የመጀመርያው የተፈጠረ ሰው ነው The first is the created man። ሁለተኛው የተበጀ ሰው ነው the second the formed man፡፡የመጀመርያው የእግዚአብሔር መንፈሳዊ መልክ የተሸከመ ሰው ነው The first is a spiritual man bearing God’s image፣ ሁለተኛው ሥጋዊ ሰው ነው the second a physical man። ፊተኛው የሰማይን ምስል ወስዳል The first bears the image of the heavenly ፥ ሁለተኛው ደግሞ የምድርን መልክ ይዛል while the second bears the image of the earthly። የመጀመሪያው በእግዚአብሔር መንፈስ ዘንድ የታወቀ ነው ፣ ሁለተኛው ደግሞ ለሥጋዊው ዓለም ይገለጣል ፡፡ የመጀመሪያው በእግዚአብሔር የመንፈስ አንድነት ይኖራል ፣ ሁለተኛው ወደ ሥጋው ዓለም እውነታ ይከፈላል ፡፡ መጽሐፍ አዳም ከንጹህ መንፈስ ወደ ሕያው ነፍስ ሆኗል የሚለው አንድ እውነት ይገልጻል ይህ ሂደት ከንጹህ መንፈስ ወደ ሕያው ነፍስ ዝቅ ወዳለው ዓለም ሕልውና እንደወረደ የሚያሳይ እውነታ ነው።
አዳም መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ ፍሬ ከመብላቱ በፊት አዳም ቀድሞውኑ “እንደወደቀ” በዚሁ እጠቁማለሁ ፡፡ ይህ ምክንያቱም ቀደም ብሎ ስለተከናወነ ዛፉን ለመብላት በቂ ዳካማ ተደርጎ ወርዶ ነበረ። ይህን እውነት ከሚያሳየው ግሩም ጽሑፎች መካከል አንዱ መዝ 8፡4-5 በዚህ ውስጥ እናነባለን- በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው? #ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው፤ የክብርንና የሞገስን ዘውድ አቀዳጀኸው።በዚህ ምንባብ ውስጥ “መላእክት” የሚለው ቃል ከዕብራይስጡ ‘elohiym el-o-heem’ Elohim ኤሎሂም ሲሆን ሁል ጊዜም የእግዚአብሔር የብሉይ ኪዳን ቃል ነው ፡፡ “ከኤሎሂም በትንሹ ወደ ታች ዝቅ አደረከው” ብቻ ሳይሆን ይህ ሐረግ በእብራይስጡ ጽሑፍ “ከኤሎሂም እንዲያጣ(እንዲጎድል) በምክንያት አድርገኸው “You have caused him (man) to lack from Elohim.” ተብሎ በነጻነት ሊተረጎም ይችላል፡፡
በዚህ ሃሳብ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ግንኙነት ያስፈልገናል we need Holy Ghost connection ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በክርስቶስ ውስጥ መርጦናልናል ብቻ ሳይሆን በክርስቶስ ውስጥም አስቀድሞ ፈጥሮናል የሚለውን ማንፀባረቅ ነበረበት። 1ኛ, *በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን ባቻ ሳይሆን መተርጎም ያለበት በክርስቶስ ኢየሱስ “ውስጥ” ተፈጠርን ነው።[created in(within) Christ Jesus ]
‘ምክንያቱም፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀልንን መልካም ሥራ እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ “ውስጥ” የተፈጠርን [created in(within) Christ Jesus ]የእግዚአብሔር ፍጥረቱ ነን። ‘ኤፌሶን 2:10
(Eph 2:10 [KJV])For we are his workmanship, created in Christ Jesus unto good works, which God hath before ordained that we should walk in them.
2ኛ, መተርጎም የነበረበት ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በክርስቶስ መርጦናልናል ሳይሆን መተርጎም የነበረበት *ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በክርስቶስ “ውስጥ” [in(within) Christ] መርጦናልና። He chose us “in” Christ before the foundation of the world”
‘በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በክርስቶስ “ውስጥ” [in(within Him) Christ] መርጦናልና። በፍቅር፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ፣ እንደ በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ወሰነን፤ ‘ኤፌሶን 1:4-5
Eph 1:4 . even as He chose us out (selects, picks us out), within Him. before [the] casting down (a laying of the foundation; a conception) of [the] ordered system (world), [for] us to continuously be set apart (holy) ones and flawless ones (ones without stain; blameless ones) in His sight (presence) [in love; or, putting this phrase at the beginning of vs. 5:]
አባት ምድርን በመሠረተ ጊዜ የእግዚአብሔርም ልጆች ሁሉ እልል ሲሉ፥ እኛ ወዴት እንደነበርን? እናስታውሳልንን ? ከእግዚአብሔርም ልጆች መካከል አንድስ እንካ የሚያስታውስ የለም። የእግዚአብሔር ክብር ክርስቶስ ጎድሎባቸው ከርመዋል ገና ወደ ክብራቸው ወደ ክርስቶስ በማገገም ላይ ናቸውና።
መጽሐፈ ኢዮብ 38: 4 ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ? ታስተውል እንደ ሆንህ ተናገር።5 ብታውቅስ መሠፈሪያዋን የወሰነ፥ በላይዋስ የመለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው? 6-7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ የእግዚአብሔርም ልጆች ሁሉ እልል ሲሉ፥መሠረቶችዋን በምን ላይ ተተክለው ነበር?የማዕዘንዋንስ ድንጋይ ያቆመ ማን ነው?
በተለያዩ ትርጉሞች ለማየት ካስፈለገ ጥቅሶች
(Eph 1:4 [AMP])Even as [in His love] He chose us [actually picked us out for Himself as His own] #in Christ before the foundation of the world, that we should be holy (consecrated and set apart for Him) and blameless in His sight, even above reproach, before Him in love.
(Eph 1:4 [ESV2011])even as he chose us in him before the foundation of the world, that we should be holy and blameless before him. In love
(Eph 1:4 [HCSB])For He chose us in Him, before the foundation of the world, to be holy and blameless in His sight. In love
(Eph 2:10 [ESV2011])For we are his workmanship, created in Christ Jesus for good works, which God prepared beforehand, that we should walk in them.
(Eph 2:10 [HCSB])For we are His creation, created in Christ Jesus for good works, which God prepared ahead of time so that we should walk in them.
for we are (we continually exist being) the result of His work (His creation; the thing He has constructed; what He did; His achievement; His opus; His deed), ones being reduced from a state of disorder and wildness (ones being built, framed, founded, created) “within” Christ Jesus upon good works (deeds) which God made (makes) ready (prepared/prepares) beforehand, to the end that we may walk about (around) within them{JMT] Eph 2:10
(Eph 2:10 [NET])For we are his workmanship, having been created in Christ Jesus for good works that God prepared beforehand so we may do them.
(Eph 2:10 [Webster])For we are his workmanship, created in Christ Jesus to good works, which God hath before ordained that we should walk in them.
(Eph 2:10 [Weymouth])For we are God’s own handiwork, created in Christ Jesus for good works which He has pre-destined us to practise.
(Eph 2:10 [YLT])for of Him we are workmanship, created in Christ Jesus to good works, which God did before prepare, that in them we may walk.
(Eph 2:10 [AMP])For we are God’s [own] handiwork (His workmanship), recreated in Christ Jesus, [born anew] that we may do those good works which God predestined (planned beforehand) for us [taking paths which He prepared ahead of time], that we should walk in them [living the good life which He prearranged and made ready for us to live].
መቼም እ/ር አለ ማለት ሆነ ነው አይዋሽምና። የሁሉም ነገሮች መንስኤ ፣ ምንጭ ፣ እና ምንጭ እሱ እ/ር ነው። ከማይታየው ማንነቱ ወስዶ የሚታየውን ፍጥረትን ሁሉ ፈጠረው ማለት የማይታየው እራሱ እ/ር ነው። የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና ሲል እውነት ነውና። ሁሉ ከእርሱ ወጥተዋል በእርሱ ይኖራል በእርሱ ያበቃል፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 11፡36 ማለትም እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡28 ከዛም የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል። የዮሐንስ ራእይ 10፡7 አዎን ሁሉ ከእርሱ ወጥተዋል በእርሱ ይኖራል በእርሱ ያበቃል። “From Him everything comes, by Him everything exists, and in Him everything ends!” (Rom. 11:36).
If God be the Creator of ALL THINGS, then it must of necessity follow that God is the source of all things. We read the passage quoted above from the Diaglott. “Because OUT of HIM, and THROUGH HIM, and FOR HIM are ALL THINGS, to Him be the glory for the ages. Amen.” All things are out of God , all things are through Him, all things are for Him, and all things are unto Him, ending in Him.
The clearest possible rendering is given by Goodspeed, “For from Him everything comes; through Him everything exists; and in Him everything ends! Glory to Him forever! Amen.”
The Amplified Bible also expresses it beautifully, “For from Him and through Him and to Him are all things. For all things originate with Him and come from Him , all things live through Him, and all things center in and tend to consummate and end in Him. To Him he glory forever! Amen – so be it.”
መንፈስ ለቤተ/ክ የሚናገረውን ከሰማን ለዘመናችንና ለትውልዳችን ድል ነሺዎች ነን። “እ/ር ግን እውቀትና ጥበብን ይሰጣል” “ጥበብን ለጠቢባን እውቀትን ላስተዋዮች” ዳንኤል። ለገዛ ዘመናችንም ልንጠቀምበት የተገባውን ምክርና ጥበብ ማስተዋልም የአምላካችንም እውቀት ቢሆን ከኛ አይሰወርም ከእርሱ የተነሳ እናድጋልን ። ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም ከእ/ር አፍ ተዘጋጅት በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ› የበላ ያድጋልና መንፈሳዊ እንጀራና ውሃ የሆነውን ክርስቶስን እለት እለት እንመገብ። በማስተዋላችንም ፈጣኖች አንሆናለን። ሃሌሉያ! ‹ምክር በሰው ልብ እንደ ጠሊቅ ውሃ ነው አይምሮ ያለው ሰው ግንይቀዳዋል። ምሳ»20/5 ብርታታቸው ከእ/ር የሆነና አማካሪያቸውም በምክሩ ድንቅና ግሩም የሆነው እ/ር የሆነ ምንኛ ብጹአን ወይም ደስተኞች ናቸው? አሜን! ጥበብ በልጆችቃ ፀደቀች [ትክክል ሆነች] አሜን! ወንድም ቢኒ።