
ከጥያቄ/መልስ የተወሰደ። ጥያቄ፤ እንድቀየር ምን ማድረግ እንዳለብኝ እርዳኝ፡ የሱስ እና የአመል ችግሮቼን ለመፍታት እንደምትረዳኝ ተስፋ በማድረግ ይህን ጽፌልሃለሁ፡፡ የተሻለን ሰው ለመሆን እና የሃጥያተኛ ወላፈኔን አና መንገዶቼን ለመለወጥ እየሞከርኩ ነው ግን ችግር አለብኝ ፡፡ እኔ በልቤ ውስጥ አንድ የተወሰነ ኃጢአት መሥራቴን አቆማለሁ ብዮ እወስንና ለተወሰነ ጊዜ አቆማለሁ ሆኖም ግን እንደገና እንዳደርገዋለሁ ፡፡ እውነተኛው ጉዳይ እኔ ማን እንደሆንኩ ጸባየንም መለወጥ አልቻልኩም። አመሰግናለሁ።
#መልስ፤ ይቅርታ ወንድማችን፣ ሕይወትህን በውስጥ እንዴት መለወጥ እንደምትችል አቃራጭ ቀመር ልነግርህ አልችልም፡፡ ህይወትህን ሊቅውየርበት የሚችለው አንድ ነው። ያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ጸባዮ የምትለውን ክርስቶስ ወደ ጸባዩ ይቀይረዋል አመሌ የምትለውን ወደ አመሉ፤ ባህርየ የምትለውን ወደ ክርስቶስ ባህርይ የለውጠዋል። ኢየሱስን ማግኘት ከእኔ ይልቅ በጣም ቀላል ነው የልብህ አምላክ ነውና ከእስትንፋስም ይልቅ ይቀርብሃል፡፡ ፌስቡክ ወይም ቫይበር ሳያስፈልግህ በእምነት ወደ አባት ጸልይ በስውር የሚያይ መንፈሳዊ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። ከእኔ ጋር እንደምታወራው ልክ እሱንም አነጋግረው፡፡ “ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሁሉ እግዚአብሔር መኖሩንና ከልብ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን አለበት።ወደ ዕብራውያን 11፡6” እኔ የምነግርህ ማንኛውም ነገር ቢሆን በክርስቶስ ውስጥ የተማርኩትን ነው፡፡ ሁሉም አካሄድ ከሰው ወደ ሰው ይለያያል መንፈሳዊ አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።፡፡ ውስጥህን ሊለውጥ የሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው ፡፡ እንዴት መለወጥ እንደሚቻል ቀመር ወይም ስሌ መንገር ሞኝነት ነው ፡፡ሁሉ ነገር ከእግዚአብሔር ፈቃድ ይፈልጋል በመንፈሱ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለምና፡፡ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው። ወንድም ቢኒ።