
ጥያቄና/መልስ። ውድ ወንድም። በሚደረገው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና ጹሁፎች ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ማስተዋልን እየሰጠን እንደሆነ ፣አስተውያለሁ ተባረኩ። ምን ያህል እንደተባረኩሁ ልነግራችሁ ፈለግሁ ፡፡ ምንም እንካን ሁላችሁም የእግዚአብሔር ልጆች በተለያየ የአለም ክፍል ብትኖሩም ከታላላቆች የተሰወረ የእግዚያብሄር ፈቃድና መንፈሳዊ ምግቡ እና የመንፈስ አንድነቱና ህብረትቱ አስደናቂ ነው! ለሁላችሁም ብዙ ፍቅር ከጌታ ይሰማኛል ፡፡
የዛሬው ጥያቄዮ። በኦሪት ዘኍልቍ መጽሐፍ ምዕራፍ 22 እስከ 24 ፣ የበለዓም እና የባላቅ ታሪክ ፣ በለዓም ማንን ይወክላል ብዬ ከበፊት ሁሌም እገረመዋለሁ ፡፡ በምዕራፍ 24 /2 ላይ በለዓምም ዓይኑን አንሥቶ እስራኤል በየነገዱ ተቀምጦ አየ፤ #የእግዚአብሔርም #መንፈስ #በላዩ #መጣ።ቁ. 3 ላይ”… .. ዓይኖቹ የተከፈቱለት ሰው እንዲህ ይላል” የእግዚያብሔር መንፈስ ወድቆበት መንፈሳዊ አይኖቹ ተከፍቶ ማን ይወድቃል? የጌታ ፍቅር ፣ ሰላምና ፀጋ ከሂላችን ጋር ይሁን።
መልስ። ውድ የጌታ ልጅ፤ ስለ መልካም ቃል እ/ር ይክበር።
በለዓም የሚያመለክተው የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ጌታ ተጠንቀቁ ያለን በጠቅላላው ዓለማዊ ንዋይና ንብረቶችን የሚቃሙጡ ለጭንብል የእግዚአብሔርን ከፊል እውነቶች በማስተማር እያደናገሩ በአለማዊ ፍላጎት የታሰሩትን ሁሉንም ነቢያት ይወክላል ፡፡ ለዚህም ነው በአዲስ ኪዳን ውስጥ ተጠንቀቁ እያለ ስለ በለዓም መንፈስ ብዙ ጊዜ ማስጠንቀቂያ የተሰጠን ፡፡ የበለዓም ትምህርት የራሳቸውን ኪስ ቲፍ ብሎ እንዲሞላ አካውንታቸውን በማያያዝ ለሁለት ጌቶች ለመገዛት ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ ለመገዛት ለሚፋለጡ የእግዚአብሔርንም ህዝብ ወደ ጣኦት አምልኮ እና መንፈሳዊ ዝሙት በዘየ የሚመሩ ናቸው፡፡ ይህ ሁሉ ከጥቅማቸው ጋር የተያያዘ አካሄድ ነው። ይህንን አካሄድ መጽሐፍ “የነቢያት እብደት” ይለዋል።2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:16
ማወቅ ያለብን በለዓም የተወሰኑትን የእግዚአብሔር እውነቶች በማወቁ ልዩ ነብይ ነው ብለን ማሰብ አይገባንም። ነገር ግን ለትርፍ ሐሰትን ለማስተማር መርጠዋል እውነትን ግዛ እንጂ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም የሚለውን የጌታ መርህን ትተዋል።፡ ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል ሰው አባባል ሁሌም ይገርመኛል ፣
“የአይሁድ #አለቃ A RULER ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ፈሪሳዊ ሰው ነበረ ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጣ እርሱም“ ረቢ፤ መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ #እናውቃለን [WE ALL KNOW [that is, ‘we ALL RULERS of the Jews,’ K-N-O-W!] አለው። ዮሐ. 3 1-2
እናም በእርግጠኝነት በዚህ ዘመንም የዛሬዋ የታላቂቱ ከተማ፥ የብርቱይቱ ከተማ የቸርች ገዥዎች ፣ የእግዚአብሔር ቃል እውነት ምን እንደሚያስተምር እንደ ኒቆዲሞስ ያውቃሉ። እግዚአብሔር ሁሉን ነገር የሚያድስበት ዘመን እንዳለ ያውቃሉ፣ ዘላለማዊ ሞትና ገሃነም ብሎ ነገር እንደሌለ ያውቃሉ፣ የመጨረሻው ጠላት ሞት እንደሚሻር ያውቃሉ፤ የፈቃዱን ሚስጥር ቢክዱትም እንዳስታወቀን ያውቃሉ። በዘመን ፍፃሜ ሊያደረግ ያለው ሀሳቡም ሁሉን በክርስቶስ ስልጣን ስር ሊጠቀልል እንደወሰነ ያውቃሉ። ወዘተ….. ፅፎልናል።“ኤፌ2/6 በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር ኣስቀመጠን። ይኸውም #በሚመጣው #ዘመን በክርስቶስ ኢየሱስ በቸርነቱ የገለጠልን ወደር የሌለውን የፀጋውን ባለጠግነት #ያሳይ #ዘንድ ነው። ምን ምን አለ? በሚመጣው ዘመን ፤በሚመጣው ዘመን እሺ? …ወደር የሌለውን #የፀጋውን #ባለጠግነት #ያሳይ ዘንድ ፤#በሚመጣው #ዘመን ….በሚመጣው ዘመን በክርስቶስ ኢየሱስ በቸርነቱ የገለጠልን ወደር የሌለውን የፀጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ነው። እልልልልልልልልልልልልልል… በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ወይም በመንፈሳዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር ያስቀመጠን ምክኛት ወደር የሌለውን የፀጋውን ባለጠግነት ፤ ለፍጥረት በተራው በሚመጣው ዘመናት ለፍጥረት ሁሉ ገና ያሳይ ዘንድ ይህን አደረከ።
የእንግሊዝኛው ትርጉም ቅደም ተከተሉ ሳይዛባ እንዲ ያስቀምጠዋል። Eph 2/7…THAT IN THE AGES TO COME HE MIGHT SHOW (greek; exhibit,put on display for all to see) THE EXCEEDING RICHES OF HIS GRACE in his kindness toward us in Christ jesus” የፀጋውም ባለጠግነት በሚመጡት ዘመናት ለፍጥረት ሁሉ ያሳየዋል ያስጎበኘዋል። ይህም የሚገልጠው በእ/ር ልጆች በክብር መገለጥ ጊዜ ነው። አሁን እያዳነ ያለው የመንፈስ በኩራት የሚቀበሉትን ነው። እ/ር አሁን ሁሉን በአንዴ ለማዳን ኣላማው አይደለም። እደዛ ሲሆን ፈቃዱን በቅፅበት ባደረገው ነበር። በሚመጡት ዘመናት የፀጋውን ባለጠግነት ለፍጥረት ሁሉ የሚያሳዩለትን ህዝቦች እየሰበሰበ ነው። ያቆብ ይህን ያስተውል ዘንድ ተሰጥቶት ስለ ነበር እንዲህ ብሎ አወጀ። እ/ር ለሱሙ የሚሆን ወገን ከአህዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጎበኘ ስምኦን ተርከዋል። ከዚህ ቡሀላ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩ ኣህዛብ ሁሉ ጌታን ይፈልጉ ዘንድ እመለሳለሁ.….ከጥንት ጀምሮ ስራው ሁሉ በእ/ር ዘንድ የታወቀ ነው። ሀዋ15/14,17,18” እንደ እውነቱ ከሆነ “የፀጋ ዘመን” ሊያበቃ ነው መባሉ ከእውነት ዘንድ ኣይደለም። ፀጋ ግን ከቀደመው ግዜ ይበልጡኑ በሚመጡት ዘመናት እንደባለጠኘቱ መጠንን አብዝቶ ለፍጥረት ሁሉ ይገለጣል።
እንዲያውም ይሄ በቅርቡ ሊዘጋ ያለው ዘመን የቤተ ክርስትያን ዘመን ተብሎ ሊጠራ ይገባል። ፀጋ አያበቃምና። ነገር ግን አሁን ያለው ገፅታና የቤተ/ክ መስተዳድር ያበቃል። በሚመጡት ዘመናት እ/ር ለስሙ የሚጠሩትን አካል ተፈፅሞ ወደ ህዝቦች ሁሉ ወደ ፍጥረት ሁሉ ማዳን ይሻገራል ይንቀሳቀሳልና። ቤተ/ክ {church[ecclesia,በግሪኩ]} ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን “ተጠርተው የወጡ” ማለት ነው።ቤተ/ክ ማለት በቀላሉ በክርስቶስ እየሱስ ያሉት ከአለም ተጠርተው የወጡት አማኞች ማለት ነው እንጂ በዚህ ዘመን የምናየው ትእይንት አይደለም። እስቲ ፀጋ በግዜ የማይወስን መሆኑን እናስተውል። “1ኛጢሞ1/9 ያዳነንና በቅዱሱ አጠራር የጠራን እ/ር ነውና ይህም እንደራሱ ሀሳብና ፀጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ስራችን መጠን አይደለም። ይህም ፀጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት{BEFORE THE WORLD[ages] BEGAN ተሰጠን” የፀጋው ባለጠግነት የተሰጠን ዘመናት[ጊዜያት] ከመጀመራቸው በፊት ነው። ስለዚህ ፀጋ በጊዜ የታሰረ አይደለም። እ/ር ፀጋን ለመግለጥ ሁሉንም ዘመን መጠቀም ይችላል።
የበላም መንገድ አያዋጣም ተመለሱ። አንድ ሰው ሁለት ጌቶችን ማገልገል አይችልም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል፤ ወይም አንዱን አክብሮ ሌላውን ይንቃል። እግዚአብሔርንና ገንዘብን በአንድነት ማገልገል አይቻልም።
እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው። አሜን! ወንድም ቢንያም አለማየሁ። RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND.