እግዚአብሔር የሁሉ ፈጣሪና ዳኛ በመሆኑ የባለቤትነት መብቱና እና ኃላፊነቱ። እግዚአብሔር የሁሉ ፈጣሪና ዳኛ በመሆኑ የባለቤትነት መብቱና እና ኃላፊነቱ።


Binyam TA – እግዚአብሔር የሁሉ ፈጣሪና ዳኛ በመሆኑ የባለቤትነት መብቱና እና ኃላፊነቱ። በወንድም ቢኒያም አለማየሁ።የእግዚአብሔር የኃላፊነት ሕጎች ፡፡ሁሉም ነገር ከእ/ር ነውን? የሁሉስ ዳኛ ማነው? ስማ! የዘላለም ፍርድ ስትል የዘመናት ፍርድ ማለትህ ነውን?የእ/ርን ፍርድ ሁለት ገፅታዎችን ማወቅ!ስማ! የዘላለም ሞት ስትል ምን ማለትህ ነው? ሞት ይሻራልና!እንደ መፅሐፍ ቅዱስ ቃል የሁለተኛው ሞትና የእሳት ባህር ፍቺሁሉን ወደኔ እስባለሁ ፤ እያንዳዱም በራሱ ተራ ይሆናል/ማውጫ፥ እ/ር ማለት እግዝያብሄር ማለት ነው።ሁሉም ነገር ከእ/ር ነውን? የሁሉስ ዳኛ ማነው?የእግዚአብሔር የኃላፊነት ሕጎች ፡፡ በቅድሚያ የነፃ ፈቃድ ጥያቄ ሳይሆን የባለቤትነት ጥያቄ ነው። እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረ ፡፡ እግዚአብሔር በመፍጠር የባለቤትነት መብቱ ሁሉም ነገር የምድን ጨምሮ ባለቤት ከሆነ ፣ መርሳት የሌለብን እኛም ከምድር አፈር የተበጀን የተሠራን መንና ፣ እግዚአብሔር የአንተም የኔም የሰው ሁሉ ባለቤት ነው።
የእግዚአብሔር የተጠያቂነት ህጎች የተመሰረቱት በነጻ ምርጫ ወይም በነጻ ፈቃድ Free Will ላይ ሳይሆን በባለቤትነት ነው። እንድናስተውለው በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ ተብሎ እንደተጻፈ ይህንን ለማረጋገጥ ፣ አንዳንድ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ግዴታን እና የባለቤትነትን ህጎች እንመልከት ፡፡ ዘጸአት 21፡ 33-34 እንዲህ ይላል ፡፡“አንድ ሰው ጒድጓድን ከፍቶ ቢተው፣ ወይም ጒድጓድ ቆፍሮ ሳይከድነው ቢቀርና በሬ ወይም አህያ ቢገባበት፣ 34የጒድጓዱ ባለቤት ኪሳራ ይክፈል፤ ለባለቤቱ መክፈል አለበት፤ የሞተውም እንስሳ ለእርሱ ይሆናል።እዚህ ቃል ላይ ያለው ኃላፊነት በንብረት ባለቤትነት ላይ የተመሠረተ ነው ፡፡
አንድ ሰው ጉድጓዱን ቢቆፍረው ለመሸፈን አስፈላጊውን እርምጃ ካልወሰደ በሬው በራሱ “ነፃ ፈቃድ ወይም ምርጫ Free Will” ወይም በራሱ ሞኝነት stupidity ቢወድቅ በእግዚአብሔር ሕግ ተጠያቂው ማነው ይለናል? በእ/ር የፍርድ ብያኔ መሰረት አስተውሉ የድጓዱ ፈጣሪ ና ባለቤቱ ነው ተጠያቂው ፤ ስለሆነም የሞተውን በሬ ለራሱ ይገዛል የድጓዱ ፈጣሪ ባለቤቱ በቀጥታ የሬውን ዋጋ መክፈል አለበት ከዛም “ነፃ ፈቃድ ወይም ምርጫ Free Will” የሚል የነፍስ ጩሆትና ንትርክ ሳይደረድር በህጉ መሰረት የሞተው በሬ የእሱ ይሆናል።
አሁን አስተውሉ በኤደን የአትክልት ስፍራ ውስጥ እግዚአብሔር መልካምና ክፉን የሚያሳውቀውን ዛፍ በመትከል “ጉድጓዱን” ምሶ ቆፍሯል ፡፡ ዲያቢሎስ ይህንን ዛፍ አልተከለውም ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ እራሱ ይህን አደረገው እንጂ ፣ ዛፉንም ባለቤት እግዚአብሔር ነው ፡፡ ይህ ዛፍ አዳምና ሔዋን ወደ ኃጢአት ሊወድቁ የሚችሉበትን አጋጣሚ ሰጠ። ሕጉ እስከሚያውቀው ድረስ ለ“ጉድጓዱ” ተጠያቂ እራሱ እ/ር ነው ፡፡
በተጨማሪም ፣ እግዚአብሔር ይህንን ጉድጓድ አልሸፈነውም ፡፡ ማለትም ሰው እንዳይበላው ከዛፉ ዙሪያ አጥር አላደረገም ማለት ነው ፡፡ ለእነሱ የሰጠው ማስጠንቀቂያ በዘፍ 2፡17 ላይ “ተጠንቀቁ Keep Out.” ከሚለው የማስጠንቀቂያ ማስታወቂያ ከጉድጓድ አጠገብ ምልክት እንዳደረገ ክፍቱን ትቶታል፡፡ ሆኖም አዳምና ሔዋን ምናልባት በጣም ሰነፍ እና ተሞክሮ የሌላቸው naïve & inexperienced በመሆናቸው ታዛዥ ባለመሆናቸው ወደ ታላቁ የግርግር ጥልቁ ጉድጓድ ውስጥ ወደቁ ፡፡
የአዳምን ውድቀት ለመከላከል እግዚአብሔር ጉድጓዱን አልሸፈነውም ብለን ካስተዋልን ዘንዳ፡፡ ሰው ኃጢአት ከመሥራቱ ለመከላከል አስፈላጊ የሆኑትን ቅድመ ጥንቃቄዎች ስላልወሰደ ሰው ወድቀዋል ፡፡ አዳም በዘፍ፡ 1፡26 ላይ በምድር ላይ ከባለቤቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ የድጥረት ቁንጮ እንዲሆን ሥልጣን ስለተሰጠው ፣ እርሱ በእርግጥ ለሥልጣኑ ከፍተኛ ሃላፊነት አለበት፡ ሆኖም ሆኖ ይህ የእሱ ተጠያቂነት በእግዚአብሔርን እይታ ዘንድ አያረጋግጠውም በራሱ ህግ ፣ ይህ የጻድቅ መለኮታዊ የልዕለ፟-ተፈጥሮ ባህሪው ነፀብራቅ ነውና።
ጥያቄው እግዚአብሔር አምላክና አባት ሰው ኃጢአት እንዳይሠራ መከልከል ይችል ነበር? በእርግጥ ይችላል ይህ ሳይታለም የተፈታ ነው እ/ር እ/ር ነውና። እ/ር ጅማራውን ብቻ ሳይሆን የነገር ፍጻሜን የሚያውቅ ነው ያቢሆን ኖሮ አላማው ዛፉን ከመብላቱ በፊት ሰው ኃጢአት እንዳይሠራ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት በዛፉ ዙርያ ባጠረው ነበር። ቅድደም ተከተሉ ግን ወደ ጉድጋዱ ከወደቀ ቡሃላ ቃሉ ሲነግረን “አዳምንም አስወጣው፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ።” በአጭሩ ያ ቢሆን አላማው እሱ በመጀመሪያ ዛፉን መትከል አልነበረበትም ፣ ወይንም ካደረገ አጥርሩን ሳያጥር መተው አልነበረበትም ፡፡
እንደዚያም ሆኖ ፈታኙን መፍጠር እና ወደ አትክልት ስፍራ እንዲገባ መፍቀድ አልነበረበትም በአላማው ግን ከሰው ከመጀመርያው አዳም ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ፈታኝ ነበረ የተቀመጠለት።፡፡ ለመሆኑ ፈታኙ ያለ እግዚአብሔር እውቀት ሾልኮ ነው እንዴ የገባው? ወይስ እግዚአብሔር ለግዜው የደህንነትን ደወሎች አጥፍቶ በሆነ መንገድ ዲያቢሎስ ሸውዶት ያለ እግዚአብሔር እውቀት ወደ የአትክልት ስፍራው ገባን? እግዚአብሔር “ጉዴ ፈላ ተበላሸብኝ” አለ? በውኑ እግዚአብሔር እንደሰው ውስን ማስተዋል ነውን ወይስ አላዋቂ ነውን?
እውነታውና የዜና ብልጭታው እግዚአብሔር መጨረሻውን ከመጀመሪያው ያውቅ ነበር news flash! God knew the end from the beginning ። እሱ በአጋጣሚ ወይም በsurprise አልወሰደውም አስቀድሞ አቅዶበት premeditated pit ነው ጉድጋዱን ያቀናጀው። እሱ ጉድጓዱን ቆፈረና ሳይሸፍን እቅዱን ዘርግቶ ወጣ ፡፡ ዕቅዱም ሰው እንዲወድቅ ጥሪ አቀረበ ፡፡ እንዲሁም አደረገ ፡፡ መዝሙረኛው ዳዊት እንዳለ 90:3 ሰውን ወደ ኅሳር አወረድከው፤ ደግሞም የሰው ልጆች ሆይ፥ ተመለሱ አልከው። You turn man to destruction, And say, “Return, O children of men.” በእግዚአብሔር ዕዳ ተጠያቂነት ሕግጋት መሠረት እርሱ ተጠያቂ ነው ፡፡
ታዲያ እግዚአብሔር ስለዚህ ነገር ምን አደረገ? ሁሉንም ሰዎች ወደ ራሱ ለመሳብ በመስቀል ላይ ከፍ ከፍ ያለውን አንድያ ልጁን ልኮ ነበር ። ስለ ዓለም ሁሉ ኃጢአት ዋጋ ከፍሏል ምክንያቱም በእ/ር ደራሲነት በፍጥረት ተራኪና ተዋናይነት ፍጥረት ሁሉ በአዳም የጉድጋዱ ትእይንታዊ ድራማ ውድቀት እስከ ሞት ድረስ ስለተገደለ ፡፡ የሞተውን በሬ ገዛ። በሬ አሁን የእሱ ነው ፡፡
ይህ ምን ማለት እንደሆነ ያውቃሉ? የወደቀውን ሰው ሁሉ ዋጀው ገዛው ፣ እናም እነሱ አሁን የእሱ ናቸው። ሰው ወድቆ ከእጁ አመለጠን? በአሁኑ ጊዜ የሰው ልጆች ሁሉ የእርሱ ባይመስሉም ፣ ነገር ግን እውነታው እግዚአብሔር እንደፈጠራቸው እና የሱ ስለሆኑም በእራሱ የኃላፊነት ህጎች አማካኝነት ዓለምን ገዝቷል። ይህን ሲያደርግ የራሱን ህግ ሳይጥስ ሕጉን ፍጹም አሟልቷል ፡፡ ለዚህ ነው ጳውሎስ በሮሜ የጻፈው ፡፡ 5፡18 ፡19 ,18ከእንግዲህ በአንድ ሰው መተላለፍ የተነሣ ኵነኔ #በሁሉ #ሰው ላይ እንደ መጣ፣ እንዲሁም በአንዱ የጽድቅ ሥራ #ለሰው #ሁሉ ሕይወትን የሚሰጥ ጽድቅ ተገኘ። 19በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች[ማለትም ሁሉ ሰው] ኀጢአተኞች እንደሆኑ፣ በአንዱ ሰው መታዘዝ ደግሞ ብዙዎች[ማለትም ሁሉ ሰው] ጻድቃን ይሆናሉ።
እንዳስተዋልነው የመጀመርያው የመፅሐፍ ቅዱስ ቃል ጌታ እ/ር የሁሉ ነገር ፈጣሪ እንደሆነ መሰረት በመጣል ይጀምራል። “በመጀመርያ እ/ር ሰማይና ምድርን ፈጠረ ” ዘፍ1/1 ብዙ ሰዎች ይህን ያምናሉ። ምንን እንደ ሚያመለክት የሚገነዘቡት ግን ጥቂቶች ናቸው። ይሄም ማለት እ/ር በፈጣሪነት መብቱ የሁሉ ነገር ባለቤት ነው። የአንድ ነገር ፈጣሪ የፈጠረው ነገር የባለቤትነት ባለ ሙሉ መብት ነው። “አሁንምቃሌን በእውነት ብትሰሙ ምድር ሁሉ የኔ ናትና ዘፀ,19/5 እ/ር እራሱ የባለቤትነት መብቱን በማይሻረው ቃሉ ‘ምድር ሁሉ የኔ ናት ብሎ ሲያውጅ እናስተውላለን። “ከሰማይ ሁሉ በታች ያለው ገንዘቤ ነው። እዮ 41/3” መፅሀፍ ሁሉም ነገር ከእ/ር ነውን? ሁሉንም ነገርስ ለምን አላማ ፈጠረው? የሚለዉን ጥያቄ ከላይ እንዳስተዋልነውና ደግሞም እንደሚከተለው ይገልጠዋል።
“ጌታችንና አምላካችን ሆይ ክብርና ሞገስ ሀይልም ልትቀበል ይገባሀል። አንተ ሁሉን ፈጥርሀልና በፈቃድህም ተፈጥረዋል ሆነዋልም {ይኖራሉም}።ራእ4/11 ፥ “ the art worthy OLord to receive glory & honour & power : for thou hast created all things. & for thy pleasure they are & were crated.”rev, 4/11. እንደ ምናስተውለው ሁሉም ነገር ለእ/ር ደስታ [pleasure] ተፈጥረዋል። “እ/ር ሁሉን ለእርሱ ለራሱ ፈጠረ። ምሳ16/4 ” ብርሀንን ሰራሁ ጨለማንም ፈጠርኩ ደህንነትን እሰራለሁ ክፋትንም እፈጥራለሁ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚያብሄር እኔ ነኝ” ኢሳ45/7 አስተዋላችሁን ብርሀንን፤ ጨለማን፤ ደህንነትንም፤ ክፋትንም እነዚህን ያደረኩኝ እኔ ነኝ ሲል ሀላፊነቱን እ/ር እራሱ ወስደዋል።
መቸም ከእ/ር በላይ አቃለሁ ማለት ላሳር ነው። ከተፃፈ ተፃፈ ነው ። “የሚታዩትና የማይታዩት ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ስልጣናት በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና” ቆላ1/17 እነዚህ ጥቅሶች እ/ር የሁሉ ነገር ፈጣሪ እንደሆነ ያውጃሉ። ደግሞም ከሱ ውጪም የተፈጠረ ወይም ያለ ፈቃዱ የሚኖር እንደ ሌለ ያስረዱናል። እ/ር አባትና አምላክ የፉጥራኑ ሁሉ ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን ደግሞም የሁሉ ፉጡሯኑ ሀላፊነት ያለበት የሁሉም የበላይ ዳኛ ነው። “የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅንነት አይፈርድምን” ዘፍ18/25 የሁሉ ዳኛ ወደ ሆነው ወደ እ/ር ደርሳችሀል እብ12/23 ከቃሉ እንደ ምናስተውለው የሁሉ ማለት እንደ አገባቡ የመላው፤ የጠቅላላው፤ ሁሉን የሚያካትት፤ ሁሉን የሚያቅፍ ፤ ሁሉን የሚሸበልል ማለት ነው። ሁሉን የሚችል አምላክ ከአይምሯችን በላይ ነው። በሀይልና በፍርድ ታላቅ ነው።
ፅድቁም ብዙ ነው። ማንንም አይጨቁንም። ስለዚህ ሰዎች ይፈሩታል። በልባቸው አስተዋዮች እንደሆኑ የሚያስቡትን አይመለከትም። እዮ37/23“በምድር የሚኖሩ ሁሉ እንደ ምናምን ይቆጠራሉ። በሰማይ ሰራዊት በምድርም በሚኖሩት መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል። እጁን የሚከለክላት ወይም ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም።ስራው ሁሉ እውነት መንገዱም ሁሉ ፍርድ ነውና። በትእቢት የሚሄዱትንም ያዋርድ ዘንድ ይችላል።”ዳን4/35/37 all whose works are truth, & his ways judgments አስተዋላችሁን ስራው ሁሉ እውነት መንገዱ ሁሉ ደግሞ ፍርድ ነው። ሀሌሉያ!እ/ር ፍጥረቱን ለማረምና ለማቅናት ብሎም ፅድቅን ለማስተማር የሚጠቀምበት አንዱ ፍርዱ ነው። የእ/ር ፍርድ ወደ ሚለው ሀሳብ ስንመጣ መፅሀፍ ቅዱስ የሚናገረውን እንጂ ሀይማኖት ና ሰው ሰራሽ ባህል አልያም በሀይማኖት ጣብያ ወይም መስመር የሚሰበከውን ግን የሰውን ለሰው የእ/ርን ለእ/ር የምናስረክብበት ጊዜ ነው። በብዙ ሀይማኖታዊ እይታ የእ/ር ፍርድ ሲነሳ ፍርዱ ለዘላለም ጥፋትና ስቃይ የሚዳርግ ብቻ ተደርጎ ይነገራል። ይህም ፍርሀትና ዘግናኝ አመለካከት የሚሰጥ ሆኖ ይስተዋላል።
እንደ እ/ር ቃል ከሆነ ግን የእ/ር ፍርድ ሲገለጥ ለበጎ ለሰው ልጆች ሁሉ ጥቅምና ለማረም ለማቅናት ለመልካም ፍፃሜም እንደ ሆነና እንደ ቃሉ ፍርዱ ሲገለጥ በደስታ ልንፈነጥዝ እንደሚገባን አምናለሁ። “መዝ96/10 በህዝብ መሀከል እ/ር ነገሰ በሉ እንዳይናወጥ እርሱ አለምን አጠናው። ህዝብንም በቅንነት ይፈርዳል ። ሰማያት ደስ ይበላቸው ምድርም ሀሴት ታድርግ ። ባህርና ሞላዋ ይናወጡ በረሀና በእርስዋ ያሉ ሀሴት ያድርጉ ። የዱር ዛፎች ሁሉ በዝያን ጊዜ በእ/ር ፊት ደስ ይበላቸው ። ይመጣልና በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና እርሱም አለምን በፅድቅ አህዛብንም በቅንነት ይፈርዳል ።” ከዚህ ከወርቅ ይልቅ ከነጠረው ፍቺውም ከሚያበራ የእ/ር ቃል እንደ ምናስተውለው የእ/ር የፍርድ ጊዜ ተፈጥሮውን ስናየው የደስታና የሀሴት ጊዜ ደግሞም የበረከት ጊዜ እንደሆነ እናስተውላለን። ምክንያቱም እ/ር ፍርዱን የሚገልጠው የሰው ልጆችን ለመጉዳት በበቀልም ለዘላለም ለማጥፋት ወይም ለመረምሰስ ወይም በዘላለም እሳት ለመጥበስ ሳይሆን ሳይሆን የሚጠቀምበት ፍጥረቱን ለማረም፤ ለማቅናት፤ ለማደስ፤ ፅድቅን ለማስተማር፤ ሆኖ በቃሉ ተፅፎ ይስተዋላል። ኢሳ 26/9 ፍርድህን በምድር ባደረክ ጊዜ በአለም የሚኖሩ ፅድቅን ይማራሉ።” whan thy judgments are in the earth the inhabitants of the WORLD will learnrighteousness.[uprightness & right standing with GOD.) isaiah 26/9 አስተዋላችሁን ፍርዱ ሲገለጥ በአለም የሚኖሩ ምንን ይማራሉ ይላል? ፅድቅን ይማራሉ። ሀሌሉያ! ሰውን ፅድቅ ለማስተማር የእ/ርን ፍርድ የሚጠይቅ ከሆነ ዘንዳ ለዘመናት በቲዮሎጂያን ስለ እር ፍርድ የተሰጡትን ትምህርቶች እንደ ገና በእ/ር ቃል መፈተን አለባቸው። በዚህም የእ/ርን ፍርድ ከፍቅሩ ጋር እኩል እናከብረዋለን።ስማ! የዘላለም ፍርድ ስትል የዘመናት ፍርድ ማለትህ ነውን?የዘላለም ፍርድ, eternal judgment ወይም ፍፃሜ-አልባ ቅጣት, endess punishment ብሎ ነገር መፅሀፍ ቅዱስ አያስተምርም። የፍርድን ተፈጥሮ ከማስተዋላችን በፊት ዘመን እና ዘላለም የሚሉ ሁለት ቁልፍ ቃላቶች ልዩ ነታቸውንና ተናጋሪው መንፈስ የሆነው እ/ር ከተናገራቸው አካያ ማስተዋሉ እጅግ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘነው በትኩረት በቅድሚያ እነሱን ማየቱ ጠቃሚ ሆኖ አግኝተነዋል። “የዘላለም ፍርድ ቅጣት እውነት እንደሆነ ለማረጋገጥ ከመፅሀፍ ቅዱስ የሚጠቀሱት ቃላቶች ፡፡ ‘ዘላለም” የሚለው ቃል ከዋናው ቅጂ ሲተረጎም የእንግሊዝኛውም የአማርኛውም ላይ ከተፈጠረው የትርጉም ስህተት የተገኘ ፅንሰ ሀሳብ ነው። “መፅሀፍትንና የእ/ር ሀይል ካወቅን አንስትም” በሚለው ፁሁፋችን እንደገለፅነው የትርጉም ስራዎች እንደ ፍፁም ስራ እንዳንደገፍባቸው ታሪካዊ አመጣጣቸውን
በማስተዋል መቃኘታችን ለዚህና ለሌሎች ሀሳቦች እንደ መንደርደርያ እንዲጠቅመን ነው። በአዲስ ኪዳን “ዘላለምeternal,everlasting“ የሚለው ቃል ከዋናው የግሪኩ ቅጂ ላይ “aionions“ ከሚለው ቃል የተተሮጎመ ሲሆን የቃሉ ስር ወይም ንብረትነቱ “AON“ ነው። ትርጉሙም “ዘመን age’ ማለት ነው። ሁለቱ የተለያየ ትርጉም ያላቸው ቃላት ናቸው ማለት አይደለም። aion[the noun formሰዋሰው ወይም ነባር ስም ] ሲሆን aionions [the adjective form, ቅፅል] ነው። ሁለቱ ቃላት ሰዋሰው እና ቅፅል ናቸው። ለምሳሌ ሳምንትሰዋሶው ሲሆን ሳምንታዊ ደግሞ ተቀፅላው ነው። ልክ እለት እለታዊ፤ አመት, አመታዊ እንደ ሚባለው ማለት ነው። “በመረዳት ብርሀን ማስተዋል ያለብን ዘመን ማለት ዘላለም ማለት አይደለም። ብዙ ጊዜዎችና ብዙ ወቅቶች አሉ። ነገር ግን አንድ ዘላለም ብቻ አለ። ዘልአለም ጅማሬ የለውም። ዘላለም ፍፃሜም ቢሆን የለውም።ነገር ግን ጊዜ፤ ዘመን፤ ወቅቶች ሁሉም ጅማሬ አላቸው ደግሞም ፍፃሜም አላቸው። ጊዜ ሲያበቃ ዘላለም ይጀምራል የሚለው አባባል ፈፅሞ ስህተት ነው። ምክንያቱም ዘላለም ጅማሬ የለውም የሚያበቃም አይደለም።
ዘላለም ጌዜ ሲጀምርም የመጣ አይደለም። ዘመናት በዘላለም ውስጥ የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው ልክ ሴኮንድ በደቂቃ ውስጥ ቦታ እንዳለው ደቂቃም በአመት ውስጥ የራሱየሆነ ቦታ እንዳለው። አመታት ያልቃሉ ዘላለም ግን አያበቃም። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ግልፅ እይታ ይኖረን ዘንድ እጅግ ጠቃሚ ነው። ዘመን የሚመደበው በጊዜ ውስጥ ሲሆን ዘላለም ግን ጊዜ አልባነው።“በመፅሀፍ ቅዱስ ጥናታችን ውስጥ ስለ ዘመን የተነገሩትና ስለ ዘላለም የተነገሩትን ለይተን ማስተዋሉ የእ/ርን ጠቅላላ ምክሩ እናስተውል ዘንድ እጅግ ይጠቅመናል። የተጠቀሰ። በጣም የሚያሳዝነው አብዛኛዎቹ የእንግሊዝኛም ሆነ የአማርኛ ትርጎሞች በብዙ የሚመሰገኑበት ቢኖርም “ዘመንን በተመለከተ ሲተሮጉሙ ግን ግድየለሽ ሆነው ”ዘላለም እያሉ በመተርጎማቸው በእ/ርህዝብ ላይ ትልቅ ግራ መጋባትን አስከትለዋል።
ይህም ብዙ ትውልዶችን ለአያሌ ዘመናት የተዛባ መረዳት ውስጥ ቆልፎ አስቀምጥዋቸዋል። ለመጥቀስ ያህል የአማርኛ ትርጉሞችም ላይም ሆነ የእንግሊዝኛ ትርጉሙ “King James Version“ ላይ እንዲሁም በዚህ መፅሀፍ ተፅኖ ስር የተተሮጎሙ ሁሉ ላይ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ስለ ሚሳደብ ሰው የተናገረውን ቃል እንዲህ ያስቀምጡታል። “ማር3/29 መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ሀጢያት እዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም።” ከዚህም የተሳሳተ ትርጓሜ ምክንያት የተፀነሰ የተሳሳተ አስተሳሰብም ተወልደዋል። ‘ለዘላለም ይቅር የማይባል ሀጥያት አለ ብለን ድምዳሜ ላይ እንድንደርስ አድርጎን ነበር።
ነገር ግን የቃሉን ትክክለኛ ፍቺ እንዲያቀብል አርገው ከተሮጎሙት ከጥቂት የእንግሊዝኛ ትርጉሞች መካከል “Emphatic Diaglott“ የተባለው ትርጉም ትክክለኛውን ትርጎም እንዲህ ያስቀምጠዋል። “Whoever may blasphemy the Holy Spirit has no forgiveness to the age, but is exposed to aionian[age lasting] judgment. Mark 3/29” መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ለዘመኑ ይቅር አይባልም። ነገር ግን ለዘመኑ ፍርድ ይጋለጣል።” እንደምናስተውለው ይቅር የማይባለው ለፍርዱ የሚጋለጠው ለዘመኑ ነው እንጂ ለዘላለም አይደለም።
በማቲዮስ12/32 እንዲህ ተብሎ ተተርጉሞዋል “በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ አለም ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም” አለም የሚለው ቃል ከግሪኩaion ማለትም ‘ዘመን ago ተብሎ መተርጎም ከነበረበት ቃል የመጣ ነው። ቃሉ መተርጎም የነበረበት “በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ ዘመንም ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም።” ነው ። ጌታ እየሱስ የተወለደው በህግ ዘመን ስለ ነበር በዚህ ዘመንም ቢሆን ማለቱ የህግን ዘመን ለማሳየት ሲሆን በሚመጣውም ዘመን ቢሆን ሲል ደግሞ አሁን እኛ ያለንበት የፀጋው ዘመን ማለቱ ነው።
የሚቀጥለውን እውነታ ካስተዋልን ስለ ዘመን በተመለከተ ያለን የእይታ ችግር ያጠራልናል። በግሪኩ aion{ሰዋሶው,noun}በግልፅ “ዘመን ወይም ያልተወሰነ ክፍለ ጊዜ ነው , an age or an indefinite period of time, Young’s Concordance” “እንግዲህ እራሳችሁ በሚያስተውለው አይምሯቹሁ አመዛዝኑት። ይሀው አንዱ ቃል “በኪንግ ጀምስ ቨርዥን የተለያየ ትርጉም ተሰጥቶ ተርጉሞታል። የአማርኛችንም ትርጉሞችም በብዛት ፈለጉን ተከ ትለውታል። age {2}ጊዜ,beginning of the World {2}ጊዜ ,course{1}ጊዜ World {32}ጊዜ, eternal {42}ጊዜ, World began{1}, forever{27}, for evermore{2}, ever{1} while the world standeth{1} for ever & ever{20} for evermore{2} never{7} world without end{1} everlasting{25} for ever{1} ጊዜ አንዱ ቃል ፍቺው ብዙ ዘርፍ ታክሎበትና ተራብቶ ተተርጉመዋል።
እንግዲህ ለበለጠ ግንዛቤ ባላችሁ ኮንኮርዳንስ መፅሀፍ እራሳችሁ አጥኑት። ይሄ ሁሉ ቃል የተረጎመው ከዋናው ቅጂ በግሪኩaion ከሚለው አንድ ቃል ሲሆን በእንሊዝኛው age በአማርኛው ዘመን ተብሎ መተርጎም ነበረበት። ከዘመን ጋር የተያያዘ የእ/ር ቃል ሁሉ በጊዜ ሲናገር የተወሰነ ገደብ እንዳለው መርሳት የለብንም። ዘመን ጅማሬ እንዳለው ሁሉ ፍፃሜም አለውና። ዘላለም ግን ጊዜ አልባ ነው። ዘላለም የማያልቅዜ ተብሎም አይገለፅም። የጊዜ ንጥረ ነገር ,lement በዘላለም ውስጥ የለምና። ምናልባት ለብዙ አንባቢዎች መደነቅን ሊያመጣባችሁ ይችላል መፅሀፍ ቅዱስ ከፀሀይ በታች ያለ ነገር ሁሉ በጊዜ ገደብ ውስጥ እንደተቆለፈ ነው የሚያስተምረን። የጊዜ ንጥረ ነገር የሌለው የዘላለም ግዛት የሚባለው ከፀሀይም በላይ በሰማያት {በእ/ር ማደርያ በመንፈሳዊው ግዛት ነው። ከፀሀይ በታችላለ ነገር ሁሉ ግን “ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው ።መክ3/1” ። ፈጣሪ ከፉጥራኑ ጋር ባለው ህብት በተመለከተ ዘላለም, eternal, ከሚለው ቃል ጋር የሚስተካከል ቃል አያስተምረንም። ሁሉም እ/ር ከስጋ ለባሽ ጋር ያለው ጉዳይ ከአላማው አንፃር በዘመናት፤ በየዘመን ሙላት፤ በዘመን ፍፃሜ፤ በጊዜዎች፤
በዎቅቶች የተካተቱ በተቀጠረላቸው ጊዜ ውስጥ የሚፈፀሙ ናቸው። ክርስቶስ ለአባት ፍፁም የሆነን ሰማይና ምድር በሚያስረክብበት ጊዜ ነው ጊዜ ህልውናው የሚነሳው። በዚያን ጊዜ ፀሐይ በቀን ላይ ትሰለጥን ዘንድ አያስፈልጋትም። ጨረቃም ብትሆን በለሊት። ጌታ እ/ር እራሱ ብርሀን ይሆንላቸዋልና። ቀንና ሌሊት ያን ጊዜ አይኖሩምና ጊዜም ህልውና የለውም።ያ ነው የዘላለም ግዛት ማለት። በዛ መንፈሳዊ ግዛት ጊዜ ብቻ ሳይሆን የማይኖረው ነገር ግን ከጊዜ ጋር የሚዛመዱ ሁሉ ይጠፋሉ። መከራ፤ ለቅሶ፤ እምባ፤ መርገም፤ ሲኦል፤ ፍርድ፤ የመጨረሻው ጠላት የሚጠፋው ሞት፤ የእሳት ባህር ወዘተ. የቀድሞው ስርአት ሩጫቸውንና የተፈጠሩበትን አላማ ተፈፅሞ
ወደ ማይመለሱበት ያልፋሉና ከህልውና ይጠፋሉ።ሰማያትና ምድር ሁሉ በክርስቶስ ታድሶ ሁሉን አዲስ አድርጎ ወደ ራሱ ይጠቀለላል።ሁሉንም ወደ ራሱ አስታርቆ እንደ ሚያድሰው ይህን የፈቃዱን ምስጢር እንድናውቅ አድርጎናል። “ሁሉ ከእርሱ ወጥተዋል ሁሉ በእርሱ ፈቃድ ይኖራል ሁሉም ወደ እርሱ ይመለሳል በእርሱም ያበቃል።” በዛም ግዛት “እ/ር ሁሉን በሁሉ ይሆናል” የተባለው ቃል ያንጊዜ ፍፃሜን ያገኛል። አሜን! ”የተጠቀሰ።ለተጨማሪ ግንዛቤ “እ/ር ሁሉን ነገር የሚያድስበት ዘመን በወንድም ቢንያም የተፃፈውን ያንብቡ)
የእ/ርን ፍርድ ሁለት ገፅታዎችን ማወቅ!አንድ ወንድም ፍርድን እንዲህ ሲሉ ባስቀመጡት ልጀምር “የእ/ር ፍርድ በተመለከተ ስናነሳ በሰዎች ዘንድ የተለመደው ባህላዊው ግንዛቤ በእ/ር ቃል ሲመዘን ሚዛኑን ያልጠበቀ የተበላሸ ሆኖ ይስተዋላል። ከጥቂቶች በቀር በብዙ ሰዎች ዘንድ ስለፍርድ ያለው የተዛባ አመለካከት ያለ እውቀት የሚነገር ሰፊ መንፈሳዊ የመሀይምነት ውቂያኖስ ሆኖ ይስተዋላል። በመፅሀፍ ስናስተል የእ/ር ፍርድ ተገልጠዋል እየተገለጠም ነው ደግሞም ይገለጣል። ፍርድ የሚለው ቃል ከሮጌው ኪዳን በአብዛኛው ከሂብሩ ቃል MISHPAI ከሚለው የተተሮጎመ ሲሆን ትርጉሙም ብይን a verdict” ማለት ነው። ይህም ብይን በውስጡ ባለ ሁለት ዘርፍ ፍንጣቂ ቃላቶችን የታቀፈ ነው። የሚወደድና የማይወደድ, favorable or unfavorable ሲሆን እንደ ብይኑ አይነት ይለያል።
ከአንዱ የሁሉ ዳኛ ታላቁ እ/ር ዘንድ ብይኑ ወይ የሚኮንን ሆኖ ለመከራ ይዳርጋል አሊያም ያለኩነኔ ነፃ የሚያወጣ ሆኖ ሊገለጥ ይችላል። አብዛኛውም ሰው ስለ እ/ር ፍርድ ሲያስቡ የሚኮንነውን የእ/ርን የግራ ፍርድ እንጂ ነፃ የሚያወጣውን የቀኙን ፍርድ አይታያቸውም። በዚህም ምክንያት ከብዙዎች ማስተዋል የተሰወረው በፍርዱ የማይስተው የፃድቁ አ/ር ፍርድ መገለጡ ሰዎችን ለዘላለም ለማሰቃየትና በእሳት ባህር ለዘላለም ለመቀቀል እንደሆነ አርገው ያስባሉ።`የተጠቀሰው ተፈጸመ።
እንደ እ/ር ቃል ፍርዱ መገለጡ ለምን እንደሆነ ስናስተውል ግን ለከንቱነት የተገዙቱን ፍጡራኑን ለጥቅማቸው ከቅድስናው እንዲካፈሉ ይፈርድባቸዋል። “እነሆ እ/ር የገሰፀው ምስጉን ነው።እዮ5/17”ተብሎ እንደተፃፈ ፉጡራኑ ምስጉን ይሆኑ ዘንድ ለመገሰፅ፤ ለማረም፤ ይቅር ለማለት፤ ለማደስ፤ ፅድቅንም ለአለም ሁሉ ለማስተማር ነው ፍርዱ የሚገለጠው ብየ አምናለሁ። ነብዩ ኢሳያስ ይህን ስላስተዋለ በትንቢት መንፈስ ይህን የሚቀድስ የቃሉን እውነት በመንፈስ ተናገረ። የእ/ር የፍርዱ አላማም ፍችው ይሄ ነው። “ኢሳ26/9 ፍርድህ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ የአለም ህዝቦች ፅድቅን ይማራሉ። ”{አዲሱ መደበኛው ትርጉም} ታዲያ ቃሉ የእ/ር ፍርድ ወደ አለም በመጣ ጊዜ የአለም ህዝቦች ይጠፋሉ ይላልን? በእርግጥም አይልም! ነገር ግን የፍርዱ አላማው የአለም ህዝቦችን ፅድቅን ለማስተማር ነው። ይላል!
ሀሌሉያ። ደግሞም ምሳር{መጥረቢያ በዛፎች ስር መቀመጡ” ዛፉን ፈፅሞ ለማጥፋት አይደለም መልካም እንዲያበቅል ጉቶውን በመተው ነው እንጂ። ለማጥፋት ከታሰበ ዛፉን ከግንዱ ሳይሆን ከስሩ ይነቅሉታልና። አንድ ብርቅየ ወንድም እንደፃፉት “የሰዎች ሁሉ “ አጠቃላይ የፍርድ ቀን”ተብሎ የሚነገረው ፈፅሞ ከእ/ር ቃል ያልሆነ የአጋንንት ትምህርት እና ፍልስፍና ነው። በአንድ ጊዜ በአንድ ወቅት ፍጥረት ሁሉ በመለኮት ፍርድ ስር ፍርዳቸውን ይቀበላሉ የሚለው ስእል ከእ/ር ቃል ጋር ተፃራሪ ነው። በዳግም የክርስቶስ ምፅአት ጊዜ በታላቁ ነጭ ዙፋን ለፍርድ ይቀመጣል። ከዝያም ሀጢያተኞች ሁሉ በፊቱ ይቀርባሉ። እንዲፈረድባቸውም ከፊቱ ይወድቃሉ።
የተፈጥሮ ሀይላት ይታወካሉመሬት ይንቀጠ ቀጣል መቃብሮች እየተከፈቱአለቶች እየተሰነጣጠቁተራሮች እየወደቁ, ኩዋክብት ከሰማይ እየወደቁ ሀጥያተኞች ሁሉ ከጥልቁ ለፍርድ ተሰብስበው አንድ በአንድ ሀጥያታቸው ለፍርድ ይቀርባል። {ያውም እኮ እንደነሱ አባባል ወደ ነጩ ዙፋን የሚመጡት ምህረት ወደ ሌለው ወደ ዘላለም የእሳት ባህር እየተቀሉ ሊኖሩ መመለሳቸው ላይቀርላቸው ነው።] መቼም ፍርዱ የጠቅላላ የጅምላ ፍርድ ነው ብለው የለ። በዚህ አይነት ፃድቃን አይቀርላቸውም እነሱም ደግሞ ከገነት ወይም ከሰማያት ተመልሰው ይመጣሉ።
{በርግጥም ብዙዎች ፃድቃን ምናልባት ተፈርዶባቸው ወደ ሲእል እንዳ ይወርዱ እየሰጉ ነው የሚመጡት)ከዛ ፃድቃኑ ወደ ሰማያት ይመለሱና ትልልቅ ቤት ይሸለማሉ ደግሞም በወርቅ መንገድ ላይ ነጭ ቢጃማ ለብሰው ዘንባባ እያውለበለቡ ለዘላለም ምንም ሳይሰሩ እዛ ሊኖሩ አርገው ያስባሉ። ሳላመነታ ይሄ አይነቱ አስተሳሰብ አረመኔ ነው እላለሁ። ይህ አይነቱ አስተሳሰብ የመጣው መንፈስ መንፈሳዊውን ነገር ለቁሳዊው አለም ለማስረዳት ደግሞም በመንፈስ መገለጥ እንድን ረዳቸው በተምሳሌነት የተጠቀመባቸው ጥቂት ምልክቶች SYMBOLS ቀጥታ ከመተርጎም የመጣ ነው።”፡፡ የተጠቀሰው ተፈፀመ።”
መፅሀፍ ቅዱስ መንፈሳዊ መፅሀፍ ነው። ለተፈጥራዊው አይምሮ የሚሰጠው ግንዛቤ በጣም ጥቂትና ውስን ነው። ይህ የእ/ር መፅሀፍ ለግድየለሽ አንባቢዎች ሚስጥሩን አይገልጥም። የመፅሀፍ ቅዱስ ምሳሌዎች ቀድሞ ጊዜ እንደ ተነገረን ቀላል አይምሮ ላላቸው ቶሎ እንዲገባቸው የተሰጡም አይደሉም። ለተቃራኒው አላማ እንጂ። ታስታውሱ እንደሆነ ጌታ እየሱስ ለህዝቡ በምሳሌ ይናገራቸው በነበረ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ “ለምን በምሳሌ ትናገራቸዋለህ? ብለው ጠየቁት። መልሱም ማቴ 13/10 ለእናተ የመንግስተ ሰማያት ሚስጥር ማወቅ ተሰጥታችሀል ለነሱ ግን አልተሰጣቸውም። ደግሞም”በሉቃ8/10 ለሌሎች ግን እያዩ እንዳያዩ እየሰሙም እንዳያስተውሉ በምሳሌ ነው።
እንደዚሁም “በማቴ 13/15.በአይናቸው እንዳያዩ በጆራቸው እንዳይሰሙ በልባቸውም እንዳያስተውሉ.” ከጌታ ቃል እንደምታስተውሉት ምሳሌዎች የተሰጡት ሚስጥሩን ለሁሉ ለመግለጥ ሳይሆን በተቃራኒው ከብዝዎች ሚስጥርን ለመደበቅ እንዲያስተውሉ ለተመደቡት ደግሞ በመንፈስ ወደ መንፈሳቸው ሚስጥሩን እንዲያስተውሉ ለመግለጥ ነው። መፅሀፍ ብዙ ብዙ ፍርዶችን ይናገራል። የአጠቃላይ የጅምላ ፍርድ ተደርጎ መታሰቡ የተፈጥራዊው አይምሮ የማስተዋል ውስንነትነው ። እ/ር መቸም ታላቅ ነው። የእ/ርን ፍርድ በመንፈስ ቅዱስ መረዳት ካስተዋልነው ብዙ ገፅታና ረድፍ አለው ። እንደየ አገባቡም መገለጡ ይለያያል።
በተፈጥራዊው መረዳት ብቻ ግን አንድ የጅምላ ፍርድ ብቻ ሊመስለን ይችላል። ብናስተውለው ግን እያንዳዱ የእ/ር ፍርድ ከእ/ር አላማ አካያ ስርአቱን የጠበቀ ባለ ብዙ ገፅታ ባለ ብዙ ሂደት ሆኖ እናገኘዋለን። አንድ ነገር ማስተዋል ያለብን እንደ ሀዋርያው ጴጥሮስ አባባል የፍርድ ቀን ብሎ ሲናገር አጭር ጊዜ ወይም የሀያ አራት ሰአት ጊዜ ማለቱ አይደለም። ይህ ረጅም ጊዜ ነው። ቢያንስ ሺህ አመታቾች ከዝያም በላይ። 2ኛጴጥ 3/7-8 እናተ ግን ወዳጆች ሆይ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ አመት ሺህ አመትም እንደ አንድ ቀን እንደሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ ከዚህ የፍርድ ቀኑ ረጅም ክፍለ ጊዜ እንደሆነ እናስተውላለን። ይህ ሀሳብ በራይ 20/4 ይደግፈዋል። “ዙፋኖችንም አየሁ በእነሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው። …ከክርስቶስ ጋርም ሺህ አመት ኖሩና ነገሱ።”
ይህ የፍርዱ ቀን ከፃድቃን ጋር ሆኖ ጌታ የሚፈርድበት እንደሆነ ያሳየናል።1ኛ ቆሮ6/2 “ቅዱሳን በአለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? “ድል ለነሳው በዙፋኑ ላይ ከኔ ጋር ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ ራይ3/21” “ዳን7/27 መንግስት ግዛትም ከሰማይ ሁሉ በታች ያሉ መንግስታት ታላቅነት ለልኡሉ ቁዱሳን ይሰጣል። መንግስቱ የዘላለም መንግስት ነው። ግዛቶች ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለታልም የነገሩም ፍፃሜ እስከዚህ ድረስ ነው። እኔም ዳንኤል በሀሳቤ እጅግ ተቸገርኩ ፊቴም ተለወጠብኝ ዳሩ ግን ነገሩን በልቤ ጠበቁት።” ዳንኤል በራእዩ በሀሳቡ የተቸገረውና ፊቱም የተለወጠበት ለምንድነው ይላል? ፍርድ ወይም ዳኝነት ለሉኡሉ ቅድሳን እንደ ተሰጠ ባየ ጊዜ ነበር። ጌታ በቅዱሳን ልጆቹ ውስጥ ሆኖ በመገለጥ የሚሰራውን ዳኝነትና የሁሉ ነገር መታደስ ገልጦ ለማሳየት ጊዜና ሁኔታዎች ስለ ማይፈቅዱልን እራሳችንን ሰብሰብ አርገን ወደ ሚቀጥለው ሀሳብ እንገባለን።
ስማ! የዘላለም ሞት ስትል ምን ማለትህ ነው? ሞት ይሻራልና!ሰው የመጀመርያውን የፍርድ ብይን የሰማው በኤደን ነበር። የሰው ዘር ሁሉ ገና በአዳም ወገብ ውስጥ ሳለ አዳም ያለመታዘዙ ሀጥያት ቅጣትና እርማት እንደሚገባው በመለኮት ታምኖበት ብይኑ ተነገረው። “ዘፍ2/17ሞትን ትሞታለሁና” በዚህም ጥቅልል የጅምላ ፍርድ ለመጀመርያ ጊዜ ስጋ ሁሉ በሞት ተነካ። “ 1ኛቆሮ ሁሉ በአዳም እንደሞቱ ከቃሉ እንደምናስተውለው ሁሉ በአዳም እንደሞቱ ይነግረናል።” በሮሜ5/12 ደግሞ፡ ስለዚህ ምክንያት ሀጥያት በአንድ ሰው ወደ አለም ገባ በሀጥያትም ሞት እንደዚሁም ሁሉ ሀጥያትንስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ” ። ጥያቄው ታድያ ሞት ዘልአለማዊ ነውን? ዘልአለም ማለት መጀመርያ የሌለው መጨረሻም የሌለውነው። እንደ መፅሀፍ ቅዱስ ቃል እንመን ከተባለ ሞት ግን ጅማሬ አለው ፍፃሜም አለው።
ስለዚህ ሞት ዘልአለማዊ አይደለም።“1ኛ ቆሮ 15/26 የመጨረሻው ጠላት የሚደመሰሰው ሞት ነው በውኑ እዚህ ጋር መንፈስ ቅዱስ ልናስተውለው ከምንችለው በላይ አፅፎልናልን? እንደ ቃሉ ሞት የሚደመሰስ ከሆነ ሞት ዘላለማዊ ነውን? እንደተፃፈው ሞት ፈፅሞ ይደመሰሳልና ዘላለማዊ አይደለም። ሞት ዘላለማዊ ካልሆነ ደግሞ ዘላለማዊ ሞት ብሎ ነገር የለም።በመፅሀፍ ቅዱስ ጥናታችን ሞት የሚደመሰሰው እንዴት ነው? የሚለውን ማስተዋሉ ብዙ ነገሮችን አጥርተን እንድናይ ይረዳናልና ይህን እንመልከት። ሰዎች በመፅሀፍ ቅዱሳቸው እንደ ተፃፈው ማንበብ አለባቸው። መፅሀፍ የሀጥያት ደሞዝ የዘላለም ሞትና ስቃይ ነው አይልም። “የሀጥያት ደሞዝ ግን ሞት ነው።
ሮሜ6/23” ይላል። እንደ ብዙዎች ቲዮሎጂ የሀጥያት ደሞዝ የዘላለም ሞትና ስቃይ ከሆነ እየሱስ ክርስቶስ የሀጥያትን እዳ ለመክፈል መስዋእት ኣልሆነም ማለታቸው ነዋ? {እንደነሱ አባባል}። እርሱ ለዘላለም በሲኦል አልተሰቃየምና ማለትም እ/ር የሀጥያት ደሞዝ የዘላለም ስቃይና ሞት መሆን አለበት ካለ ማለት ነው። በዚህ አይነት እየሱስ ምንም አልከፈለም ማለት ነዋ? የዘላለም ስቃይ ከሆነ የሀጥያት ደሞዝ እየሱስ ስለ ሀጥያተኞች በሞተ ጊዜ ለዘላለም መሰቃየት ነበረበት ማለትነዋ። እዳው ሊከፈል የሚችለው በዛ መንገድ ብቻ ነውና። ጌታ እየሱስ ግን በምድር ልብ ውስጥ የቆየው ለሰዎስት ቀን ብቻ ነው። በእርግጥም የሀጥያት ደሞዝ የዘላለም ሞት አይደለም!
“የሀጥያት ደሞዝ ሞት ነው! ሞትም ዘላለማዊ አይደለም ይሻራል። የሀጥያት ደሞዝም የዘላለም ስቃይ አይደለም። ነው ቢሉም ስቃይም ቢሆን ከአሁኑ የስጋዊ አይምሮ የአለም ስርአት ጋር በክርስቶስ አይምሮ አዲስ ስርአት ሲተካ የቀድመው ስርአት ሁሉ አብረው ይሻራሉና። “ሞትም ከእንግዲህ አይሆንም ሀዘንም ቢሆን ወይም ጩሀት ወይም ስቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም የቀደመው ስርአት አልፈዋልና ራእ21/4። ጌታ እየሱስ የሀጥያትን ስርየት ለማስገኘት ለአለም ሁሉ ሞተዋልን? ተቀብረዋልን? በሰዎስተኛው ቀንም ከሙታን ተነስተዋልን? መልሱ አዎን የአለሙ ሁሉ አዳኝ እንጂ የጥቂቶች ብቻ አይደለም። መዳን ያስፈለገው በጅምላ አለሙ ሁሉ ነውና።
“እርሱ የሀጥያታችን ማስተስረያ ነው። ለሀጥያታችን ብቻ አይደለም ነገር ግን ሉኡለሙ ሁተ ሀጥያት እንጂ” 1ኛየሀ2/2 “እርሱም በእውነት ክርስቶስ የአለም መድህኒት እንደሆነ እናውቃለን” ዮሀ4/42 “ እኔም ሱሉአለም ህይወት የምሰጠው እንጀራ ስጋየ ነው።” ዮሀ6/51 “እ/ር ግን በክርስቶስ ሆኖ አለሙን ከራሱ ጋር እያስታረቀ ነበርና በደላቸውንም አይቆጥርባቸውም ነበር።በእኛም የማስታረቅን ቃል አኖረ” 2ኛቆሮ5/19። አዳምና በአዳም ሁሉ ደሞዛቸውን ተቀብለዋል። እ/ር ሞትን ትሞታለህ” ባለው ጊዜ ይህ የመጀመርያው ፍርድ በአንድ ሰው ላይ ብቻ የደረሰበት ሳይሆን ያ ቅፅበት የሰው ዘሮች ሁሉ ላይ ሞት የወደቀበት ነበር።
ያ ቅፅበት የሰው ልጅ ከህይወት ግዛት ከኤደን ወደ ሞት ግዛት የተባረረበት ቀን ነበር። “አንዱ ለሁሉ ከሞተ እንግዲያውስ ሁሉም ሞተዋል። ”{2ኛቆሮ5/14} የዚያን ቅፅበት ነበር በሀጥያት ምክንያት የሰው ልጅ ሁሉ ከእ/ር ክብር የጎደለው ። ያለ ክርስቶስ ያለ የህይወት ብርሀን ወደዚህ ሞት ወደ ተባለው ኑሮ የገባው። ሞት የሚለው ቃል ለሞት የተገዛው የሰው አካል ወደ መቃብር ሲሄድ ካለው ፍቺ ባሻገር ነው። ያም ማለት የሰው ዘር ከክርስቶስ ውጭ ያለው ጠቅላላ ሁኔታውና ኑሮው በእ/ር አመለካከት ዘንድ ሞት ማለት ያ ነው።አንድ ወንድም በተቀባ ብእራቸው የፃፉትን ላካፍላችሁ “ ከሞት ወደ ህይወት ተሻገርን” ይሄ ከሆነ ዘንዳ መንፈሳችን በመንፈሱ ተቀስቅሶ ህያዋን ሆነናል። ጳውሎስ ወደ አስደናቂ እውነት ይመራናል። ብዝዎች አማኞች ከማየት የወደቁበት የተመረጡ የእ/ር ፃድቃን ጭምር። “2ኛ ጢሞ9/9-10 እኛ ስላደረግነው አንዳች ነገር ሳይሆን ከእቅዱና ከፀጋው የተነሳ ያዳነን ወደ ቅዱስ ህይወትም የጠራን እርሱ ነው። ይህም ፀጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ እየሱስ ተሰጠን። አሁን ግን ሞትን ደምስሶ በወንጌል አማካይነት ህይወትንና ኢመዋቲነትን ወደ ብርሀን ባወጣው (ባመጣው) በመድሀኒታችን በክርስቶስ እየሱስ መምጣት ተገልጠዋል።” የእ/ር ቃል እውነት ነው። ውሸት አይደለም። ሰዎች ውሸታሞች ናቸው ። እ/ር እውነት ነው።
እ/ርም “ክርስቶስ ሞትን ደመሰሰ ሲል እኛ ትንሽየ የአፈር ትሎች ብናምነው ይሻለናል። እ/ርን ተሳስተሀል በማለት ውሸታም ማለትን እናቁም። የማያምን ቢኖር እ/ርን ውሸታም ያደርገዋልና 1ኛዮሀ 5/10” ኦ ኣንብቡት አንቡቡትና በማይነገር ደስታ ፈንዱቁ በክብርም ሙልአት ሀሴት አድርጉ ሉኡሉንም ከፍ ካለው በላይ በውዳሴ ከፍ አድርጉት። ለሰላሳ ሰዎስ አመት ከግማሽ በሞት ግዛት በተመላለሰበትጊዜ ሞትን ደምስሶና ሽሮ በከበረው ታላቁ ትንሳኤው ውስጥ ያን የትንሳኤ ህይወትን ወደኛ አመጣው። በሚያስደንቅ ሆኔታ ይሄ ቃል እውነት ነው ። ሙታን ሆነን ሳለን…ማማማ ዋሉ ከክርስቶስ ጋር አስነሳን በክርስቶስ እየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።ኤፌ/5-6 እንግዲህ አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ይጠይቃል። ሞትን ከሻረው ለምን ሰዎች መሞት ቀጠሉ? መልሱ በእርግጥም ሰዎች መሞት አልቀጠሉም። ኦህ! አስከሬናቸው ወደ መቃብር መሄድ እንደቀጠለ እናውቃለን። ይህንንም ሞት ብለን እንጠራዋለን። ሞት አይደለም እሱ።
እ/ር ይህንን ሞት ብሎ አይጠራውምና። እኛ ይህንን ሞት ብለን እንጠራዋለን። ይህ ግን ሞት አይደለም። አስተውሉትማ ወገኖቼ ሙውታን ሳላችሁ ህይወትን ሰጣችሁ! ሙውት ሳለሁ በክርስቶስ ህይወትን ሰጥቶኛል። ታዲያ ያ ማለት በሬሳ ሳጥን ውስጥ ታሸጌ ፅልመት በተሞላበት መቃብር ውስጥ ተቀብሬ ነበረ ማለት ነውን? ሞት ማለት አካሌ በሬሳ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ማለት አይደለም። የተቀበልኩትም ህይወት የማይበሰብስ የስጋ አካል አይደለም። አትመለከቱምን? ሰዎች ሞት ብለው የሚጠሩት ሞት አይደለም። ሰዎችም ህይወት ብለው የሚጠሩት ህይወት አይደለም። መንፈስ ቅዱስ ሲገልጥልን ብቻ የነገሮችን እውነተኛ ተፈጥሮ የጠለቀ ሚስጥራቸውን የምንገነዘበው። አንድ ሰው ከሰማይመጣ በእ/ር ፀጋም ለሰው ሁሉ ሞትን ቀመሰ ። ”የተጠቀሰው ተፈፀመ።
ነገሮችን ከተፈጥራዊው ሰው አንፃር ብቻ ካየናቸው እውነት እደተሰወረ ይቀመጥብናል በመንፈስ ግን እ/ር ከሚያየው አንፃር ካየናቸው እውነት አርነት ያወጣናል። ሌላ ቃል ደግሞ እንይ። “እየሱስም፥ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታኖችን ተውዋቸው። ሉቃ9/8” ማለቱ በቃሬዛው ውስጥ ያለውንም የተሸከመውንም አንድ ሙታን አላደረጋቸውምን? በርግጥም ከሰው አለም ከውሸትና ከሞት ግዛት ተኩኖሲታዩ ሉይነት አላቸው። ሁለቱም ግን ከእ/ር አለም ከእውነትና ከህይወት ግዛት ተኩኖ ሲታዩ ሙታንናቸው። የሰው ልጅም እንዲሁ በሀጥያት ምክንያት ከእ/ር ህልውና ከተባረረ ጀምሮ ያለው ኑሮ ሁሉ እንዲሁ ነው። የሚለያዩት በኮፈኑ ውስጥ ያለው የሞት ወይም የመበስበስ ኑሮ የመጨረሻው የእድገት ደረጃ ላይ በመድረሱ ግብአተ መሬቱ ሊፈፀም መድረሱ ነው። በአጭሩ ሞት ሰው ከእ/ር ጋር በመንፈስ የነበረው ህብረት የተለየበት ወይም ከህይወት ግዛት ከተባረረበት ቅፅበት ጀምሮ ያለው ጠቅላላ ሁኔታውና ማንነት ነው ። ለምሳሌ አንድ የፅጌሬዳ እንቡጥ አበባ ከግንዱ ብትቆርጡት ለአይን ሲታይ ያማረና ህያው ነው። ነገር ግን እውነታው የአበባው ዝንጣፊ ህይወትን ከሚሰጠው ከምንጩ ማለትም ከግንዱ ተቆርጦ ተለይተዋል። ከዚህ ቡሀላ ወደ መጠውለግ ፤ወደ መበስበስ ወይም ወደ ሞሞት ቁልቁል እያደገ ነው። እ/ር ያብራላችሁና በሰማይምም በምድርም እ/ር ህይወት የሚለው አንድ ብቻ ነው። እርሱም በክርስቶስ እየሱስ የሚገኘውን ህይወት ነው። ጌታችንና አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ “እኔ ህይወት ነኝ ማለቱ ሌላውን ሁሉ ሞት አያደርገውምን? እኔ እውነት ነኝ ማለቱ ደግሞ ሌላውን ውሸት ያደርገዋል ። እኔ መንገድ ነኝ ማለቱ ደግም ሌላውን ገደል ያደርገዋል።“በመጀመርያ ቃል ነበር። ቃልም ከእ/ር ጋር ነበር። ቃልም እ/ር ነበር። በእርሱም ህይወት ነበረች። ይህች-ም ህይውት የሰ-ው ብርሀን ነብረች። ዮሀ1/1-4 “ምስክርነቱም ይሄ ነው። እ/ር የዘላለም ህይወትን ሰጠን።ይህም ህይወት ያለው በልጁ ነው። ልጁ ያለው ህይወት አለው ልጁ የሌለው ህይወት የለውም” 1ኛዮሀ5/11-12 “ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ።
ማንም ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል። ይህም እንጀራ ለአለም ህይወት የምሰጠው ስጋዬ {ቃልም ስጋ ሆነ}ነው። የሀ6/51።” ሰው ሲወድቅ የወረደው ወይም የተባረረው መፅሀፍ ሞት አልያም እንቅልፍ ብሎ ወደ ሚጠራው ግዛት ነው። ያ ቅፅበት ሰው ልክ እንደ እየሱስ ከአባት ጋር በመንፈሱ በውስጡ ከእ/ር ጋር በመንፈስ የነበረው ህብረትና የተሳሰረ ርክክብ የመግዛት ህይወት የተቋረጠበት ነው። አዳም ሲሞት ያጣው ህይወትን ነበር የተቀበለውም የሀጥያት ደሞዝ የሆነውን ሞትን ነበር።የእ/ር ቁጣ ሀጥያትን በመቃወም ተገልጠዋል። ያም በሰው ዘር ሁሉ ላይ ደርሰዋል። “የሀጥያት ደሞዝ ሞት ነው ሰው ከዛ ቡሀላ ለእ/ር ህይወት የሞተ ለክርስቶስ የሞተበመንፈስ ሀይል ከመግዛት የተባረረ ለእውነት የሞተ, ለንፅህና የሞተ, ለፅድቅ የሞተ, ሆነ። ከአዳም ጀምሮ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ እስከ ተገለጠበት ቅፅበት ድረስ ሁሉ ሰው “ በበደላቸውና በሀጥያታቸው የሞቱ ነበሩ።
የመጀመርያው ህይወት ያለው በዚህ ምድር ወይም ፕላኔት የተመላለሰው እየሱስ ብቻ ነው። “እኔ ከአብ የተነሳ ህያው ነኝ የሚበላኝም {የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ ከኔ የተነሳ ህያው ይሆናል” “ትንሳኤና ህይወት እኔ ነኝ” “ ልጁ ያለው ህይወት አለው ልጁ የሌለው ህይወት የለውም። የእ/ር ቁጣ ግን በእርሱ ይኖራል።” “ስለስጋ ማሰብ ሞት ነው” ሀዋርያው ሞት የሚለውን ሲገነዘበው በድጋሚ እንግዲህ አለ “እኔ ምንኛ ጎስቃላ ሰው ነኝ! ከዚህ ለሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?” ሮሜ7/24 ታድያ ሀዋርያው በዝያን ግዜ ይህን ሲፅፍ በሬሳ ሳጥን ውስጥ ነበረ ማለት ነውን? አይደለም በህይወት ነበር።
እ/ር ሞት ብሎ የሚጠራው ገብቶት ግን ፃፈልን። እንግዲህ ሞት በአጠቃላይ ጠላት እንደሆነ ነገር ግን ሞት ዘላለማዊ እንዳልሆነ ሞትም እደሚጠፋ መፅሀፍ ያስተምረናል። ናሙናውንም እየሱስ ሞትን ደምስሶ በተግባር አሳይተዋል። “ታላቅ ድምፅ ከሰማይ ሆነ። የእ/ር ድንካን በሰዎች መካከል ሆነ። ከእነሱም ጋራ ያድራል። እነሱም ህዝቡ ይሆናሉ። እ/ርም እርሱ ራሱ ከነሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል። እንባዎችንም ሁሉ ከአይናቸው ያብሳል። ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም።ሀዘንም ቢሆን ወይም ጩሀት ወይም ስቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም። የቀደመው ስርአት አልፈዋልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።”ራእይ21/3-4.። ሀሌሉያ!እንደ መፅሐፍ ቅዱስ ቃል የሁለተኛው ሞትና የእሳት ባህር ፍቺስለዚህ ሀሳብ በሰዎች ዘንድ ካለው ሰፊ ግራ የተጋባና የተዛባ አመለካከት የተነሳ ስለ እሳት ባህርሳጠና ሲኦል ዘላለማዊ ነውን? [ is hell eternal or will GODS plan fail ?]________________________________________PAGE 18 OF 25________________________________________
ገፅ 18 የሁሉ ፈጣሪና ዳኛ እ/ር ! በወንድም ቢንያም Rev-charles pridgeon ከነቨበር ወር 1920 እትም መፅሀፋቸው። የእሳት ባህርን በተመለከተ ከገለጡት እጅግ ከሚያስደንቀውየመረዳት ብርሀን የተሞላበት የሊቅ{የስኮላር ስራቸው ለተሻለ ግንዛቤ ለብዙ አስተዋዮች እንደታገዙበት ሁሉ እኔም ከተረዳሁበት መሀከል ለአንባቢያን ጥቅም ልጠቅስ እወዳለሁ የእሳት ባህርና ዲኑ[BHIMSTONEየሚያመለክቱት እሳቱ ከዲኑ ጋር ሲነድ ነው። ዲንbrimstoneወይም ድኝsulphur የሚገልፀው የእሳቱን ባህርይ ነው።የግሪኩ ቃል THEION ሲተረጎም ዲን, brimstoneተብሎ የተተረጎመው ሲሆን ያው የግሪኩ ቃል እራሱ THEIONመለኮት ማለት ነው። በጥንታዊያን ግሪኮች መሀከል ድኝ sulphur የተቀደሰ ነበረ። እናም ለማጠን፤ለማንፃት፤ ለማጥራት ለአምላካቸው ያውሉት ነበር። ለዚህም አላማ ያጥኑ ነበር። homersliad[16:228] አንድ ሰው በእሳትና በዲን ዋንጫውን እያፀዳ እንደሆነ ሊናገር ይችላል።
THEO ከሚለው ቃል የተሳበው ግስ{ግስ ማለት፥ የቋንቋ አረባብ የዘርና ነባር መሰረት ቃል ማለት ነው}THEOO ሲሆን ማለትም ማወደስ መለኮትን መስራት, ለአምላክነት መለየት ማለት ነው ።{liddel &Scott Greek English Lexicon,1897 Edition.} ተመልከት።ለማንኛውም ግሪካዊ ወይም በግሪክ ቋንቋ ለሰለጠነ የእሳት ባህርና ዲን ሆኖ መረዳት የነበረባቸው የመለኮት የማጣርያ ባህር alake of divinepurification ነበር። ፍርድ የሚለው ሀሳብ መከልከል የለበትም። በጥንታዊ ግሪክ ቋንቋ መለኮታዊማጣርያና ለመለኮትነት ማዋል የሚለው ነው ፍቺው። በተራው አገላለፅ ይህ መሰረታዊ የቃሉ ትርጉም ገንጥለው አውጥተውታል። ምንም ነገር ግን የዘላለም ስቃይን አዛምደውታል። “የተጠቀሰው ተፈፀመ። በነገራችን ላይ THEION
________________________________________PAGE 19 OF 25________________________________________
የሚለው ቃል የተሳበው theo ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን እ/ርመለኮት) GOD እየተባለ በአብዛኛውገፅ 19 የሁሉ ፈጣሪና ዳኛ እ/ር ! በወንድም ቢንያም የተተረጎመው ቃል ነው። ቲዮሎጂ {Theologi, is the study ofGOD] የስነመለኮት ጥናት ወይም ስለ እ/ር ማጥናት ከዚህ ሀሳብ የተገኘ ነው። የእ/ርን አሰራርና አደራረጉን ለማወቅ አንድ ሰው ቃሉን እያጠና መንፈስም መረዳትን እያበዛለት ሲመጣ የቃሉን መንፈሳዊ አመልካች ማስተዋል ሲጀምር በመፅሀፉ ፀሀፊ በእ/ር የዘላለም ቅዱስ ልእለ ተፈጥሮ ውበትና እንዲሁም በታላቅ ጥበቡ፤ በፍቅሩ ብልፅግና ይነደፋል ። እ/ርንም ውድድድ ያደርገዋል። በእ/ር ዘንድያለው ፍርድ ለማቃናት እንደሆነ ማስተዋል ይጀምራልና። ሰዎች ለመከራ ይቀጣሉ። እ/ር ግን በፍርዱ ያፀዳል ያቀናል።
የግሪኩ ቃል የጠራ ወይም የነፃpur በዚህ ዘመን እንግሊዝኛ ማፅዳት ወይም ማጣራት, ንፁህ ማድረግ, PURGE & PURIFYለሚሉት ቃላት ስር ወይም ምንጭ ነው። የእ/ር እሳትም የሚያደርገው ያንኑ ነው። የእ/ርን ባህርይናተፈጥሮ ያስይዛል። በዛሬው ጥናታችን በጥቂቱ የእሳቱን ባህርይ በመፅሀፍ ቅዱስ የእውነት ቃል እናጠናለን።ይህን እሳት እየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ለኩሶታል። በእሳት የሚያጠምቅ ሆኖም መጥተዋል። ለሚከተሉት ሁሉ እንደ እሳት መምጣቱን ቀጥለዋል። ገናም ለፉጡራኑ ሁሉ ይመጣል። አሜን ጌታ ሆይማራናታ አብዝተህ ቶሎ ምጣ።የሁለተኛው ሞት ፍቺሁለተኛው ሞት ማለት የመጀመርያው ሞት እና ሲኦል በእሳት ባህር ውስጥሲደመሰሱ ማለት ነው። “ራእ20/14 ሞትና ሲኦልም የእሳት ባህር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባህር{ይህ ቃል ሲተሮጎም ለሁለተኛ ጊዜ የተጨመረ ነው}ሁለተኛው ሞት ነው።” “ death & hellwere cast into the lake of fire. THIS IS THE SECOND
________________________________________PAGE 20 OF 25________________________________________
DEATH.“ KJV,ትክክለኛው ትርጉም ለአንባቢያን እንዲገባ መሆን የነበረበት “ሞትና ሲኦልም በእሳት ባህር ውስጥ ተጣሉ። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው። ”እንደ ምናስተውለው ሞትና ሲኦል ወደ እሳት ባህር ሲጣሉ ሁለተኛው ሞት ይባላል። ይሄ መንፈስ ቅዱስ እራሱ ሲያፅፈው ሁለተኛው ሞት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሰጠውገፅ 20 የሁሉ ፈጣሪና ዳኛ እ/ር ! በወንድም ቢንያም ፍቺ ነው። አስተውሉ ሁለተኛው ሞት ማለት ሰዎች በማይጠፋው እሳት ለዘላለም ሲቀቀሉ ማለት አይደለም። አልያም እንደሚባለው ክርስቶስን ያልተቀበሉ ከሞት ቡሀላ የሚጠብቃቸው ኑሮ አፈ ታሪኩ የዘላለም ሞት ማለትም አይደለም።
የዘላለም ፍርድ ማለትም አይደለም። አሁን አይናችን ተከፍቶ ማየት እንችላለን ሁለተኛው ሞት ማለት የአንደኛው ሞትና የሲኦል{የሞት ግዛት) በእሳት ባህር ውስጥ ተጥለው ሲደመሰሱና ሲጠፉ ነው። በሂይወት መፅሀፍ ያልተገኙት ሁሉ የመተላለፍና የሀጥያት የሲኦልተፈጥሮ ማንነቱ የተጠናወታቸው አመል ሁሉ የአመፃ ሚስጥር ሁሉ ወደ የመለኮት የማጣርያ የእሳትባህር ይጣላሉ።“እ/ር መንፈስ ነው። ዮሀ4/24“ መንፈሳዊውን ነገር ለቁሳዊው አለም ለማስረዳት በአካላዊ ቋንቋ መስሎ ያስረዳናል። የብዙ አማኞች ችግር ይሄ ነው። ለዚህም ነው በመንፈስ መገለጥ እንድንረዳቸው በተምሳሌነት የተጠቀመባቸው ምልክቶች, SYMBOLSቀጥታ ከመተርጎም የመጡ ብዙ ችግሮች የተከሰቱት። መፅሀፍ ቅዱስ መንፈሳዊ መፅሀፍ ነውና። አስተውሉት እስቲ “የእሳት ባህር” የሚለውን ቃል እንየው “ባህር ምንድነው? ስፋትና ጥልቀት ያለው በወሀ የተሞላ ቦታ ነው። ይሄኛው ልዩነቱ በእሳት መሞላቱ ነው። በምልክት ወይም በገላጭ ስእላዊ ቋንቋጌታ ተጠቅሞ ተናገረው ። እስራኤል ቀይ ባህር በጌታ ለሁለት ተከፍሎ መንገድ አድርጎላቸው በውስጡ ባለፉ ጊዜ ሀዋርያው በጥምቀት አልመሰለውምን? 1ኛቆሮ10/2 እነዚህም በመለኮታዊ ማጣርያ በእሳ
________________________________________PAGE 21 OF 25________________________________________
ት ባህር የሚያልፉት እንደዚሁ ነው። ለእ/ር እንዲነጡለትና እንዲነጥሩለት በልምድ ውስጥ ያሳልፋቸዋል።የእ/ር በእሳት የመፈተኑ ባህሪና አላማውን ስናይ “…ወደ እሳት አመጣለሁ እንደ ብር አነጥራቸዋለሁ።እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ። እነሱም ስሜን ይጠራሉ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔም ህዝቤ ናቸው እላለሁ። እነሱም እ/ር አምላካችን ነው ይላሉ። እንደምናስተውለው እንደ ወርቅ በእሳት
ገፅ 21 የሁሉ ፈጣሪና ዳኛ እ/ር ! በወንድም ቢንያም ከተፈተኑና ከነጠሩ ቡሀላ በመጨረሻ እ/ር “ህዝቤ ናቸው ዘካ 13/9 ለማለት አላፈረባቸውም እነሱምበመንፃታቸው “ እ/ር አምላካችን ነው” ሲያስብላቸው ይታያል እንጂ ሲጠፉ አይታይም። ወርቁ እሳቱ ውስጥ የመግባቱ አላማ ወርቁን ወደ ተፈለገው ውበትና ቅርፅ መልክና አምሳል በባለ ተክሎው ሰውወደ ታየለት የክብሩ ደረጃ ለማስያዝ ነው እንጅ ወርቁን ለማጥፋት አይደለም በእሳት ውስጥ የሚከተተው።{ለምሳሌማትዮ23/15 ከእናተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የጋህነም ልጆች ስለምታደርጉ…የሚናገረው ስለ የከፋ ማንነት ወይም ስለየከፋ ተፈጥሮና ባህርይ ነው።“ ..ስንዴውን መልካሙን ዘር በጎተራ ይከተዋልና ገለባውን የአመፃን ሚስጥር ግን በማይጠፋው እሳት ያቃጥለዋል።} ያም የሞት የሲኦል የሀጥያት መጨረሻቸው ነው።እ/ር ሞትን በእሳት ባህር ይደመስሰዋልና። ሲኦልንም እራሱ በእሳት ባህር ጥሎ ያቃጥለዋል።
የአመፃን ሚስጥርና ሀጥያትን በእሳት ባህር ውስጥ ይበላዋልና። በእ/ር መንግስት እርሱ ሁሉን በሁሉ ሲሆንሀጥያት የለም ሀጥያተኛም የለም ሞት የለም ሲኦል የለም። እነዚህ ሁሉ የጨለማው ግዛት ሀይላት ናቸው። እ/ር ሁሉን በሁሉ ሲሆን እ/ር ብርሀን ነው በሱ ዘንድ ጨለማ የለምና ሁሉን በብርሀን ማንነቱይሞላዋል። ብርሀን ለጨለማ እሳቱ ነውና ይበላዋል።________________________________________PAGE 22 OF 25________________________________________
ለምሳሌ በአንድ በለጨለማ ክፍል ስትደርሱ መብራቱን ታበራላችሁ እንበል። ጨለማውም በቅፅበትከህልውና ይጠፋል እንጂ በዚህ ክፍል ውስጥ የቀድሞ ንጉስ ነበርኩና አልሄድም ብሎ መከራከር አይጀምርም ወይም አምፆ በክፍሉ ውስጥ ቅሪቱን የጨለማ ቁራጭ አይተውም። የብርሀን ህግ የበላይ ነውና ክፍሉ በብርሀን ይሞላል ጨለማም ይበላል። እንዲሁ ሰማይና ምድርም በብርሀን አምላክ እርይሞላል። መቸም እ/ር ሰውን በእሳት ባህር እደማያጠፋው የታወቀ ነው። በየትም ቦታ የእ/ር ቃል እንደዛ አይልም። ያ ተፃራሪ አባባል ነው። ሰውን ማምለጫ በሌለው የዘላለም ሞት ውስጥ ፈጥረህ በመክተት ሞትን እንዴት ትደመስሳለህ? የእ/ር መለኮታዊ እሳት ሰዎች ይነጥሩበታል ወይምገፅ 22 የሁሉ ፈጣሪና ዳኛ እ/ር ! በወንድም ቢንያም
ይቀመሙበታል እንጂ አይጠፉበትም። “ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና”ማር9/49 በእሳት ባህር ውስጥየሚደመሰው የገዛቸውም ሞት ሀጥያትና ሲኦል ነው ። የሚጠፋው የመጨረሻው ጠላት ሞት ነው።1ኛቆሮ15/26 የእሳት ባህር ማለት የሞትና የሲኦል መደምሰሻው ነው። በሰው ታላቅ ጥበብ ተብሎ ከሚታወቀው ይልቅ የእ/ር ሞኝነት የሚመስለው ጥበቡ ይበልጣል። “እርሱ እ/ር) እንደ አንጥረኛ እሳት ወይም እንደ ልብስ አጣቢ ሳሙና ነውና። ብርን እንደ ሚያነጥርና እንደሚያ ነፃ ሰው ይቀመጣል …አንፅቶ እንደ ወርቅና እንደብር ያጠራቸዋል። ሚልክ 3/2-3” በዚህ ምሳሌ ፈጣሪ እንደ አንጥረኛና እንደ ልብስ አጣቢ እንደሚቀመጥ ተቀምጠዋል።
ለመሆኑ በተፈጥራዊ አለም አንጥረኛ የተግባሩ አላማው ምንድን ነው? ብርን በእሳት ሲያነጥረው ብሩንድራሹን ለማጥፋት ነውን? አይደለም! ብሩን ለማንጠርና ለሚፈልገው ውበትና ክብር ሊያውለው እንጂ! የልብስ አጣቢና ተግባሩስ ምንድነው? “…ይዞ ወደረጅም ተራራ አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠልብሱም አንፀባረቀ አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ። ማር9/2” ከዚህ ቃል እንደምናስተውለው በምድር ላይ የአጣቢ ተግባሩ ልብስን ማንጣት ነው እንጅ ልብሱን ማጥፋት አይደለም። እ/ር የዘላለም አላማው ከመጀመርያውም “በመልካችንና በአምሳላችን ሰውን እንስራ ዘፍ1/26” አንድም ሰው ሳይቀር “በመልኩና በአምሳሉ” ወዳለው ክብር ለማምጣት እስከ ሆ
________________________________________PAGE 23 OF 25________________________________________
ነ ድረስ እያንዳንዱን ሰው በእሳቱ አሳልፎ መቀመሙ አይቀርም። ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማል’ማር9/49 ተብሎ ተፅፈዋልና።ለመሆኑ ብርን ወይም ወርቅን ለማንጠር የሚቀመጥ በተክእሎት የተካነ ሰው ምን እንደሚያደርግ ታውቃላችሁን? በቅድሚያ ወርቁን እሳት ውስጥ ይፈትነዋል። ወርቁም በእሳት ሲፈተን አርቲፊሻል የወርቅ ቅብ ከሆነ ወድያው ይከስላል። ወርቅ ከሆነ ደግሞ የሸፈነው እየተቀረፈ እየወደቀ የውስጥ ክብሩእየተብለጨለጨ ቢጫ እየሆነ ወርቅነቱ እየባሰበት እየደመቀ እየደመቀ እሳቱ ውበቱንገፅ 23 የሁሉ ፈጣሪና ዳኛ እ/ር ! በወንድም ቢንያም
እየገለጠው ይመጣል። ባለ ተክእሎው ሰው በሂደቱ ጊዜ ወርቁ እሳት በዝቶበት እንዳይበላሽ ፊቱን አስጠግቶ አይኑን ተክሎ በተጠንቀቅ ይጠባበቃል። ወርቁ ተፈላጊው የጥራት ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያውቀው የሰውየው መልክ በወርቁ ውስጥ ተንፀባርቆ ሲያይ ብቻ ነው። በመጨረሻም ወርቁ መልኩንአንፀባርቀዋልና ወድያው ከእሳት ያወጣዋል። አሁን የክብር እቃ ሆነዋል ይላል። እ/ር የሰውን ዘር በእሳት ባህር ማንጠሩ ለማጥፋት ሳይሆን መልኩንና አምሳሉን በሰው ውስጥ ለማየት ነው። መልኩን ካየቡሀላም የእሳት ባህሩ ውስጥ ዳግም ለመክተት አያስፈልገውም። አቤቱ እንደሱ ያለ በፍርዱና በምህረቱ በጥበቡ በማስተዋሉ ባለጠጋ ማንም የለምና እ/ር ክብር የተገባው አምላክ ነው። አሜን! ሀሌሉያእንወድሀለን ጌታ ሆይ! አሁንም አሜን ይሁን!
ሁሉን ወደኔ እስባለሁ ! ፤ እያንዳዱም በራሱ ተራ ይሆናል !በሮሜ5/18 “በአንዱ በደል ምክንያት ፍርድ ለኩነኔ ወደ ሰው ሁሉ መጥተዋል። ”ይላል። ማወቅ ያለብን ግን ከውድቀቱ ጋር መነሳቱም እኩል መሆኑን ነው። እንዲሁም በአንዱ ፅድቅ ምክንያት ስጦታው ህይወትን ለማፅደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ። አስተዋላችሁን የመጨረሻው {እየሱስ ክርስቶስ)በፅድቁ ሁሉን ማዳን አይችልም ብሎ መወሰን በመጀመርያው {በአዳም] ውድቀት ምክንያት ወደ ሰ________________________________________PAGE 24 OF 25________________________________________
ው ሁሉ ኩነኔ አልመጣም እንደ ማለት ነው ። ደህንነት ከውድቀት ጋር እኩል ሀይል አለውና። የመጀመርያው አዳም ሁሉን ይዞ ለመውደቅ ሀይል እንደ ነበረው ሁሉ ሁለተኛው አዳም ክርስቶስም ሁሉንወደ ራሱ ለመሳብ ሀይሉ አለው። የፈለገ ቢሆን የአዳም ሁሉን የመጣል ሀይል ከእየሱስ ሁሉን ከማዳን ሀይል አይበልጠውም። ነገር ግን “ጠላቶችህ ባንተ ላይ ዋሹብህ” ተብሎ እንደተፃፈ ነው። “ዮሀ12/32 እኔም ከምድር ከፍ ያልኩ እንደ ሆነ ሁሉን ወደኔ እስባለሁ” ለመሆኑገፅ 24 የሁሉ ፈጣሪና ዳኛ እ/ር ! በወንድም ቢንያም
ቃሉ ቢያንስ ያመኑልኝን ብቻ የተወሰኑትን ወደኔ እስባለሁ ይላልን? አይልም! ሁሉን ወደኔ እስባለሁ ይላል እንጂ። ሀሌሉያ! በአንዱ ምክንያት ሁሉ ወደቁ በአንዱ ምክንያት ደግሞ ሁሉ ዳኑ ።ሁሉ በአዳም እንደሞቱ ሁሉ በክርስቶስ ህያዋን ይሆናሉ።ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል። 1ኛቆሮ.15/22” ከላይ እንደተፃፈው አሁን ተራቸው ደርሶ ያልዳኑት እያንዳንዱ በተራቸው መዳናቸው አይቀርም። ማወቅ ያለብን “የሁሉ ነገር መታደስ ዘመን አለ።ሀዋ3/21”“ያም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በእየሱስ ስም በሚበረከኩ ጊዜ ምላስም ሁሉለእ/ር አብ ክብር እየሱስ ጌታ እንደሆነ የሚመሰክርበት ጊዜ ነው። ፊል2/10” ታድያ እኮ ሁሉን ነገርእ/ር በሚያድስበት ዘመን “እ/ር ሁሉን በሁሉ ይሆናል ተብሎ እንደተፃፈ አሁን የእ/ርን የዘላለም አጀንዳ እና አሰራሩን ላልተረዳ ሰው በሰማይ በምድር ከምድር በታች ያሉት ሁሉ
በዝያን ጊዜ እየሱስጌታ ነው! ብለው የሚመሰክሩት ተገደው ይመስለዋል እንጂ በእ/ር መንፈስ ሆነው አይመስለውም። ምክንያቱም የሚምበረከኩት ስቃይ ቅጣት በዝቶባቸው ተሸንፈው በፍርሀት እየተማፀኑ ይመስለዋል እንጂ ከአባት ከአብ} ፍጥረቱን ከሚያርመው ፍርዱና ከምህረቱ ባለጥግነት የተነሳ ክብር ለመስጠት አይመስለውም። በደልን ንቆ የሚተው ይከበራልና። “መዝ130/4 ነገር ግን በአንተ እ/ር ዘንድ ይቅርታአለ ስለዚህም ልትፈራ {ልትከበር)ይገባሀል።አዲሱ መደበኛ ትርጉም። “ther is forgivness withthee{GOD},in order that you may be respected”.________________________________________PAGE 25 OF 25________________________________________
ማወቅ ያለብን “1ኛ ቆሮ,12/3 በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር እየሱስ ጌታ ነው! ሊል አንድ እንካ እንዳይችል አስታውቃችሀለሁ።” አስተውሉ እንግዲህ በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር አንድስ እንካ እየሱስ ጌታ እደሆነ ክብርን መስጠት የማይችል ከሆነ አሁን ጠላቶቹ የሆኑት ሁሉ በዝያን ጊዜ ሲታደሱእየሱስ ጌታ ነው! የሚሉት በመንፈስ ቅዱስ ሆነው ነው። ሀሌሉያ! ባለ ራእዩ ዮሀንስ አረ በአውነት ግዛት አንድ የሰማሁት ነገር አለ። ይላል እሱምራእ5/13 በሰማይና በምድርም ከምድርምገፅ 25 የሁሉ ፈጣሪና ዳኛ እ/ር ! በወንድም ቢንያም
በታችም በባህርም ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ያለው ፍጥረት ሁሉ፥ በረከትና ክብር ምስጋናም ሀይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለበጉ ይሁን ሲሉ ሰማሁ።“አስተዋላችሁንሞት ዘላለማዊ አይደለም ሞት ሲደመሰስ ፍጥረት ሁሉ፥ በመንፈስ ቅዱስ ሆኖ ለአብ ክብር እየሱስ ጌታ ነው! ይላል ። ሀሌሉያ! እየሱስ ክርስቶስ ትላንት ዛሬም ነገም ጌታ ነው! አሜን! ተፈፀመ! ገፅ26 የሁሉ ፈጣሪና ዳኛ እ/ር ! በወንድም ቢንያም

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal